Saturday, 17 October 2015 11:34

“Under The Shade of Gashe” ለንባብ በቃ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(3 votes)

      በቀድሞው ፕሬዚዳንት ክቡር ዶ/ር ግርማ ወ/ ጊዮርጊስ የህይወት ታሪክ ላይ የሚያጠነጥነው “Under The Shade of Gashe” የተሰኘ መፅሐፍ ባለፈው ሳምንት ተመርቆ ለንባብ በቅቷል፡፡ መጽሐፉ ኪባኩመር ኬ.ፒ በተባሉ ህንዳዊ ምሁር በእንግሊዝኛ
ቋንቋ የተፃፈ ሲሆን የፕሬዚዳንቱን የህይወት ታሪክ ከውልደት አሁን እስከሚገኙበት እንዲሁም የተቀዳጇቸውን ስኬቶች እንደሚዳስስ፣የአሳታሚው የማይክሮ ቢዝነስ ኮሌጅ ፕሬዚደንት አቶ አበራ ጥላሁን ተናግረዋል፡፡ ኮሌጁ መረጃ በማሰባሰብና በጥናትና ምርምር
አባላት በመታገዝ፣የፕሬዚዳንት ግርማን መፅሃፍ አዘጋጅቶ ለማሳተም መቻሉን የገለጹት የኮሌጁ ፕሬዚዳንት፤መረጃ ማሰባሰቡ ብቻ ሁለት አመት እንደፈጀ ጠቁመዋል፡፡ መፅሃፉ በእንግሊዝኛ የተፃፈበትን ምክንያት ሲያስረዱም፤ ክቡር ግርማ የሰሩት ስራ፣ ያለፉበት መልካም አስተዳደግና ለአገራቸው ያበረከቱት አስተዋፅኦ ከፍተኛ በመሆኑ ማንኛውም ዜጋ አንብቦ እንዲማርበት በማሰብ
ነው ብለዋል፡፡ 198 ገጾች ያሉት መፅሃፉ፤ወደ አማርኛ እየተተረጐመ መሆኑን የኮሌጁ ፕሬዚዳንት ጠቁመው፣ ወደ ኦሮምኛ ለመተርጐም ፕሮፖዛል ያቀረቡ አካላት እንዳሉም ገልፀዋል፡፡ መጽሐፉ በ250 ብር ለገበያ መቅረቡም ታውቋል፡፡

Read 2414 times