Saturday, 10 October 2015 16:01

የጠ/ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ አዲሱ ካቢኔ

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(9 votes)

  ሃገሪቱን ለ5 አመት የሚመራ መንግስት ሰሞኑን ተመስርቷል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው የተሠየሙት አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝም የካቢኔ አባላትን መርጠው ሹመታቸውን በፓርላማው አስፀድቀዋል፡፡
በዘንድሮው የመንግስት ምስረታ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች የመዋቅር ሽግሽግ በስፋት ተከናውኗል፡፡ 12 ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች የመዋቅር ማሻሻያ ተደርጐባቸው፤ ግማሾቹ ሁለት ቦታ እንዲከፈሉ ሲደረግ፣ በአዲስ መልክ የተቋቋሙም አሉ፡፡ እነዚህ  አዳዲስ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች  የሚከተሉት ናቸው፡-
የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ሚኒስቴር - ወ/ሮ ዘነቡ ታደሰ (ብአዴን)
የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር - አቶ ሬድዋን ሁሴን (ደኢህዴን)
የእርሻና የተፈጥሮ ሃብት ልማት ሚኒስቴር - አቶ ተፈራ ደርበው (ብአዴን)
የእንስሳትና የአሳ ሃብት ልማት ሚኒስቴር - አቶ ስለሺ ጌታሁን (ኦህዴድ)
የማዕድን ነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ሚኒስቴር  አቶ ቶሎሣ ሻጊ (ኦህዴድ)
የውሃ መስኖና ኤሌክትሪክ ሚኒስቴር - አቶ ሞቱማ መቃሣ (ኦህዴድ)
የገንዘብ እና የኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር - አቶ አብዱላዚዝ መሃሙድ (ኦህዴድ)
የፌደራልና አርብቶ አደር ልማት ጉዳዮች ሚኒስቴር - አቶ ካሣ ተክለብርሃን (ብአዴን)
የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስቴር - አቶ መኩሪያ ሃይሌ (ደኢህዴን)
የኮንስትራክሽን ሚኒስቴር - ዶ/ር አምባቸው መኮንን (ብአዴን)
የመንግስት የልማት ድርጅቶች ሚኒስቴር - ወ/ሮ ደሚቱ ሃምቢሣ (ኦህዴድ)
የአካባቢ ደን ልማት እና አየር ንብረት ለውጥ ሚኒስቴር - ዶ/ር ሽፈራው ተ/ማርያም (ደኢህዴን)
ባሉበት አወቃቀርና ስያሜ የቀጠሉ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች  
የንግድ ሚኒስቴር - አቶ ያዕቆብ ያላ (ደኢህዴን)
ሣይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር - አቶ አብይ አህመድ (ኦህዴድ)
የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር - ኢንጂነር አይሻ መሃመድ ሙሳ (አብዴፓ)
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር - ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም (ህወኃት)
የመከላከያ ሚኒስቴር - አቶ ሲራጅ ፈጌሣ (ደኢህዴን)
የፍትህ ሚኒስቴር - አቶ ጌታቸው አምባዬ (ብአዴን)
የትራንስፖርት ሚኒስቴር - አቶ ወርቅነህ ገበየሁ (ኦህዴድ)
የትምህርት ሚኒስቴር - አቶ ሽፈራው ሽጉጤ (ደኢህአዴን)
የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር - አቶ አብዱልፈታ አብዱላሂ (ኢሶህዴፓ)
የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር - አቶ አህመድ አብተው (ብአዴን)
የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር - ዶ/ር ከሰተብርሃን አድማሱ (ደኢህዴን)
በነዚህ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ከአቶ ያዕቆብ እና ኢንጂነር አይሻ በቀር ሁሉም በነበሩበት  የሚኒስትር አመራርነት ቀጥለዋል፡፡
በሚኒስትር ማዕረግ የሚመራቸውን መስሪያ ቤቶች ይዘው የካቢኔ አባል እንዲሆኑ የተሾሙ
የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ሃላፊ - አቶ ጌታቸው ረዳ (ህወኃት)
የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር - አቶ በከር ሻሌ (ኦህዴድ)
የፕላኒንግ ኮሚሽን ሃላፊ - ዶ/ር ይናገር ደሴ (ብአዴን)
በፓርላማ የመንግስት ዋና ተጠሪ - አቶ አስመላሽ ወ/ስላሴ (ህወኃት)
በመንግስት አወቃቀሩ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን፤ የማህበራዊ ዘርፍ ክላስተር አስተባባሪ ሆነው ይሠራሉ ተብሏል፡፡
ሌሎች በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ ሚኒስትር መስሪያ ቤቶችን እንዲመሩ የተሾሙ፡-
ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ህወኃት) በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ፣ የኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪ እና የመገናኛ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስትር
ወ/ሮ አስቴር ማሞ (ኦህዴድ) በምክትል ጠ/ሚኒስትር ማዕረግ፣ የመልካም አስተዳደር ክላስተር አስተባባሪና የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ሚኒስትር
በዚህ የካቢኔ አወቃቀር መሠረት ከብአዴን 8፣ ከኦህዴድ 9፣ ከደኢህዴን 7፣ ከህወኃት 4 እንዲሁም ከአጋር ፓርቲዎች ኢሶዴፓ 1፣ ከአብዴፓ 1 ተወክለውበታል፡፡
በተጨማሪም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለ7 የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት የአማካሪ ሚኒስትርነትና የካቢኔ ጉዳይ ሚኒስትርነት ሹመት ሰጥተዋል፡፡ በዚህ መሠረት፡-
የቀድሞው የንግድ ሚኒስትር አቶ ከበደ ጫኔ - የጠቅላይ ሚኒስትሩ የህዝብ ግንኙነት አማካሪ ሚኒስትር
አቶ በዙ ዋቅቤካ - የጠቅላይ ሚኒስትሩ የህዝብ አደረጃጀት ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር
ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል - የጠ/ሚሩ የማህበራዊ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር
አቶ ሱፊያን አህመድ - የጠ/ሚሩ የፊስካል ፖሊሲ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር
አቶ መኮንን ማንያዘዋል - የጠ/ሚሩ የአለም አቀፍ ንግድ ግንኙነት ድርድር ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር
አቶ በለጠ ታፈረ - የጠ/ሚሩ የተፋሰሶችና የአየር ንብረት ለውጥ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር
አቶ አለማየሁ ተገኑ - የጠ/ሚሩ የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል፡፡  

Read 7424 times