ለመጀመርያው የጎልደን ኮላር ሽልማት በ”ዘ አርቲስት” ፊልም ላይ ያለችው ‹ሃውጊ› የተባለች ድንክ ውሻና በማርቲን ስኮርሲስ ፊልም ‹ሁጎ› ላይ ያለው ሶሎግ ውሻ ‹ብላኪ› ዋና ተፎካካሪዎች ሆነዋል፡፡ በሆሊውድ በሚሊዮን ዶላር የሚሰላ ገቢ ያላቸው በርካታ የውሾች ዝርያዎች መኖራቸውን የሚያትተው ዎልስትሪት፤ ይሁንና ውሾቹ ከእንስሳነት ባህርያቸው ይልቅ ሰዋዊ ስብእና እንዲተውኑ እየተደረጉ ጫና ውስጥ እንደሚገቡ ዘግቧል፡፡ ውሾች ከተወኑባቸው የቅርብ ጊዜ ፊልሞች “ቢግነርስ” እና “ያንግ አደልት” ይጠቀሳሉ፡፡