የአቶ ካሣዬ ተክለአረጋይ ቤተሰቦች የተለያየ ቅፅ ኢንሳይክሎፒዲያ፣ የወንጀለኛ መቅጫ፣ የተጠቃለሉ ሕጐች፣ የሕግ መጽሔቶችና ጠቅላላ ዕውቀትን ጨምሮ 60 ያህል መፃሕፍትን ለዕውቀትና ትጋት አሰፋ ጎሳዬ የሕዝብ ቤተ-መፃሕፍት ሰሞኑን አበረከቱ፡፡
የሕግ ባለሙያ የነበሩት አቶ ካሣዬ ተክለአረጋይ በሕይወት ሳሉ ሲጠቀሙባቸው የነበሩ መፃሕፍትን ለቤተመፃሕፍቱ ያበረከቱት ልጃቸው አቶ ሰለሞን ካሣዬ ናቸው፡፡ የአቶ ሰለሞን ካሣዬ ባለቤት ወ/ሮ ምህረት ጌታቸው በወቅቱ እንደተናገሩት፤ “መጻህፍቱን እንድንሰጣቸው የጠየቁ ግለሰቦች የነበሩ ቢሆንም መፃሕፍቱ የበለጠ ከአንባቢያን ጋር ሊገናኙ የሚችሉት በቤተ-መፃሕፍት ውስጥ ቢቀመጡ ነው በሚል እምነት አበርክተንላችኋል” ብለዋል፡፡
Published in
ኪነ-ጥበባዊ ዜና