Monday, 06 April 2015 09:35

ደደቢት 3 ንፁህ ጎሎች ይፈልጋል

Written by  ግሩም ሠይፉ
Rate this item
(0 votes)

በአፍሪካ ክለቦች ኮንፌዴሬሽን ካፕ ዘንድሮ ለ4ኛ ጊዜ የሚሳተፈው የደደቢት እግር ኳስ ክለብ ወደ ሁለተኛ ዙር ለመግባት በወሳኝ የመልስ ጨዋታ ባህርዳር ስታድዬም ላይ የናይጄርያውን ዋሪ ዎልቭስ ያስተናግዳል፡፡ ሁለቱ ክለቦች ከ2 ሳምንት በፊት  በናይጄሪያ ዋሪስ ታውንስ ሺፕ ስታዲየም ባደረጉት ጨዋታ ዋሪ ዎልቭስ  2ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፉ ይታወሳል፡፡  በመልሱ ጨዋታ ደደቢት ተጋጣሚውን በሜዳው ጥሎ ለማለፍ በሶስት ንፁህ ጎሎች ማሸነፍ ይጠበቅበታል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ዋሪ ዎልቭስ  ለመልሱ ጨዋታ ወደ ኢትዮጵያ ለሚያደርገው ጉዞ በቂ ፋይናንስ  ባለማግኘቱ ፎርፌ  ለመስጠት አቅማምቶ እንደነበር በሳምንቱ መግቢያ ላይ ተዘግቦ ነበር፡፡ ይሁንና በሳምንቱ አጋማሽ ላይ ክለቡ የገባበት አጣብቂኝ በመንግስት ድጋፍ እንደተቀየረና ትናንት አዲስ አበባ በመግባት ለመልሱ ጨዋታ እንደሚደርስ ከናይጄርያ የወጡ ዘገባዎች ገልጸዋል፡፡

Read 1267 times