Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 31 December 2011 12:10

“እፎይ” ፊልም ዛሬ ማታ ይመረቃል

Written by 
Rate this item
(0 votes)

በወይዘሪት የትናየት ባህሩ ተፅፎ የተዘጋጀው “እፎይ” አስቂኝ የፍቅር ፊልም ዛሬ ማታ በዓለም ሲኒማ እንዲሁም ነገ በሌሎች የአዲስ አበባ ሲኒማ ቤቶች፣ ለገና (የልደት በዓል) ደግሞ በድሬዳዋ እና ሌሎች ከተሞች ይመረቃል፡፡ አዳዲስ ወጣት ተዋንያን በተለይ ቤተልሄም ከፍያለው፣ጴጥሮስ ከበደና አበበ ማሞ በዋናነት በሚተውኑበት በዚህ ፊልም ከተሳተፉ ታዋቂ አርቲስቶች መካከል ሸዋፈራሁ ደሳለኝ፣ ወለላ አሰፋ፣ ዘነቡ ገሠሠ እና ሰላም ይሁን አሥራት ይገኙበታል፡፡ የ100 ደቂቃ ርዝመት ያለው “እፎይ” ፊልም ከምረቃው በኋላ ለሕዝብ እይታ እንደሚቀርብ ታውቋል፡፡ የፊልሙ ደራሲና አዘጋጅ ወ/ሪት የትናየት ባህሩ ለአዲስ አድማስ ስለ ፊልሙ ዝግጅት ስትናገር፤ “ታሪኩ ሰፋ ስለሚልና የቀረፃ ቦታ አስቸጋሪ ስለነበር ከፊተኛው ፊልሜ የበለጠ ከብዶኛል” ብላለች፡፡ የትናየት ከዚህ ቀደም በአድማስ አድቨርታይዚንግ ስቱዲዮ የተሰራ “አልደወለም” የተሰኘ ፊልም ማቅረቧ ይታወሳል፡፡

 

 

Read 2164 times Last modified on Saturday, 31 December 2011 12:12