በዕውቋ ድምፃዊት ዘሪቱ ከበደ ተፅፎ የተዘጋጀው “ቀሚስ የለበስኩለት” የተሰኘ ፊልም በሚቀጥለው ሳምንት እሁድ በአፍሪካ ህብረት አዳራሽና በአዲስ አበባ ሲኒማ ቤቶች ይመረቃል፡፡ የድራማ ዘውግ ባለው የ1፡40 ደቂቃ ፊልም ላይ፤ ድምፃዊቷ ዘሪቱ ከበደ፣ የንግድ ም/ቤት ፕሬዚዳንቷ ሙሉ ሰለሞን፣ የጃኖ ባንዱ ድምፃዊ ዲበኩሉ ታፈሰ፣ ሙዚቀኛው ሄኖክ መሐሪ፣ ይስሃቅ ዘለቀና ሌሎችም እንደተወኑበት ታውቋል፡፡ ፊልሙን ሰርቶ ለማጠናቀቅ ሁለት ዓመት የፈጀ ሲሆን ቀረፃውን “የሳቢሳ ፊልሞች” እንዳከናወነው ለማወቅ ተችሏል፡፡
Published in
ኪነ-ጥበባዊ ዜና