Saturday, 07 December 2013 12:34

“የአርበኛው ልጅ” ፊልም ነገ ይመረቃል

Written by  መልካሙ ተክሌ
Rate this item
(2 votes)

አንተነህ ኃይሌ ጽፎ ያዘጋጀውና በትሩዝ ፊልም ፕሮዳክሽን ተሰርቶ በውዳሴ ፊልም ፕሮዳክሽን የቀረበው “የአርበኛው ልጅ” የአክሽን ኮሜዲ ፊልም ነገ ይመረቃል፡፡ “ከጀግና ቤት መጠለል ጀግና አያስብልም” የሚል መሪ ቃል ይዞ በተሰራው ፊልም፤ ካሳሁን ፍስሐ (ማንዴላ)፣ ሞዴል የትምወርቅ ጉበርዣ፣ ጌታቸው ታደሰ፣ ሰለሞን ተካ፣ አበበ ፍሬው እና ሌሎችም ተውነዋል፡፡ ፊልሙ ነገ ከ8-12 ሰአት የሚመረቀው በአዲስ አበባ፣ አዳማ፣ ዱከም፣ ደብረዘይት እና ሰበታ ከተሞች በሚገኙ ሲኒማ ቤቶች ነው፡፡

Read 1786 times