“ጥሪ አይቀበልም” በአዲስ አበባ ዮፍታሔ፣ እምቢልታና ሴባስቶፖል ሲኒማዎች እንዲሁም በደብረዘይትና በናዝሬት በነገው እለት የሚመረቅ ሲሆን በዋነኛነት ከቀኑ 8 ሰዓት በሲኒማ ዮፍታሔ እንደሚመረቅ ለማወቅ ተችሏል፡፡ እስኩፒ ፊልም ፕሮዳክሽን ከሆቢላንድ ፒክቸርስ ጋር ተባብሮ በማዘጋጀት ያቀረበው “የማልተኛው” ድራማቲክ ኮሜዲ ፊልም ዛሬ ከቀኑ 8፡30 በአዲስ አበባ ትያትርና ባህል አዳራሽ ያስመርቃል፡፡ ያሬድ ተስፋዬ ጽፎ ባዘጋጀው የ96 ደቂቃ የቤተሰብ ፊልም ላይ እነ ችሮታው ከልካይ፣ ወንድወሰን አውራሪስ፣ ሕይወት ግርማ፣ ትዕግስት ረጋሳ፣ ቢኒያም እሸቱ (ጀቤሳ) ይተውኑበታል፡፡