ጄነራል ታደሰ ወረደ እና ሌሎች የቀድሞ የሕወሃት መኮንኖች ከእስር መለቀቃቸውን ምንጮች አስታወቁ። በአሁኑ ጊዜ መኮንኖቹ በሀገር መከላከያ ሰራዊት እጅ የሚገኙ ሲሆን፣ በደህና ሁኔታ ላይ መሆናቸውም ታውቋል።
እነዚህ መኮንኖች በህወሓት ከታሰሩበት ከመቀሌ ወደ ሰሜን ድንበር ተወስደው እንደነበር ይታወሳል። ይህም ለኤርትራ መንግሥት ይሰጣሉ የሚል ትልቅ ስጋት ፈጥሮ እንደነበር አይዘነጋም።
ጄነራል ታደሰ ወረደ በፌዴራሉ መንግሥት የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት ሆነው ዳግም መመረጣቸውን ተከትሎ፣ የህወሃት አመራሮች በሃይል ከሥልጣናቸው በማውረድ ለአጭር ጊዜም ቢሆን የራሳቸውን አስተዳደር መሥርተው እንደነበር ይታወቃል፡፡
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
