ዶ/ር ይርጉ ገ/ሕይወት የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር ፕሬዝደንት እንደገለጹት የጤና ባለሙያዎች የነበራቸውን እውቀት በተወሰነ የጊዜ እርቀት የሚያዳብሩበት፣ የየእለት ተግባራቸውን በሚመለከት ልምድ የሚለዋወጡበት ፣አዳዲስ የተደረሰባቸውን ግኝቶች የሚያ ውቁበት መድረክ መዘጋጀቱ ለወደፊት የተሻለ አሰራር ይረዳል፡፡ በስብሰባው ላይ በመጀመሪያው ቀን የተሳተፉት ኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች ፡-
የእናቶችን ጤና ማሻሻል እንዴት ይቻላል?
ለውጦች ሲመጡ እንዴት መገመት ይቻላል?
በቡድን ስራን መስራት ምን ይጠይቃል? ምን ያህልስ ይጠቅማል? የሚለውን ለመመልከት የሚያስችላቸውን መረጃ አግኝተዋል፡፡
በሁለተኛው ቀን በተደረገው ስብሰባ በዚሁ ፕሮጀክት ውስጥ ከአፍሪካ የመጡትን ባለሙያዎች ጨምሮ ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ የተሰሩትን ስራዎች መፈተሸ የተቻለበት ውይይት ተካሂዶአል፡፡ ይኼውም ለመውለድ እና ተያያዥ ለሆኑ ሌሎች ሕክምናዎች ወደሆ ስፒታል የመጡ እናቶች ሞተው ከሆነ የሞቱት በምን ምክንያት ነው የሚለውን እና ከሞት ተርፈውም ከሆነ የተረፉት ምን ስለተሰራ ነወ የሚለውን በመመልከት ለቀጣዩ ምን ቢደረግ ይሻላል የሚለውን ልምድ ለመለዋወጥ ያስቻለ ስብሰባ ነበር፡፡ ይህንን እንደጤና ተቋም ፣እንደ ጤና ባለሙያ እና ህብተረሰቡስ ጭምር ምን ቢያሟላ የእናቶቹን ሞት ቁጥር መቀነስ ይቻላል የሚለውንም ተሰብሳቢዎቹ የተወያዩበት እና በቋሚነት እንዴት ወደ ጤና አገልግሎቱ ሊካተት ይችላል የሚለውን የተመለከቱበት ነበር፡፡
ከአፍሪካ የመጡት ተሰብሳዎች ከቡርኪናፋሶ ፣ከካሜሩን ፣ከኡጋንዳ ፣ከሞዛምቢክ እና ከናይጄሪያ ናቸው ፡፡ እነዚህ አገራት FIGO በሚሰጠው ድጋፍ የእናቶችን ሞት ምክንያት ለማወቅ ፕሮጀክት ነድፈወ የሚንቀሳቀሱ ሲሆን ወደኢትዮጵያ የመጡበት ምክንያትም ድጋፍ እንደሚያደርገው የአለም አቀፉ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር FIGO እይታ ኢትዮጵያ የተሻለ ስራ እየሰራች ስለሆነች ልምድ እንዲቀስሙ ለማድረግ ነው፡፡ በዚህም መሰረት ከናይጄሪያ የመጡት ተሰብሳቢዎች ወደ ቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ኮሌጅ ሆስፒታል በመሄድ የእናቶች ጤንነትን በሚመለከት የሚደረገውን አመዘጋገብ እና ሞትን ለመቀነስ በሚደረገው ጥረት ያለ ውን አሰራር በመመልከት አድንቀው ትልቅ ልምድ እንዳገኙ ገልጸዋል፡፡
የልምድ ልውውጡን ለማድረግ የተጠሩት ተሰብሳቢዎች በጋራ በመሆን በአሰራራቸው የገጠማቸውን ችግር እና ለመፍትሔውም ያላቸውን ሀሳብ ሰንዝረዋል፡፡ ከኡጋንዳ ፣ከናይጄሪያ፣ ሞዛምቢክ እና ኢትዮጵያ የተውጣጡ ተሰብሳቢዎች እንደጠቆሙት
የእናቶችን ሞት ሁኔታ ለመቀነስና ምክንያቶቹንም ለይቶ ለማወቅ እንደ አንድ ችግር የሚቆጠረው የባለሙያ ወይንም የሰራተኛ ኃይል እጥረት መሆኑ፣
የእናቶችን ሞት በሚመለከት ችግሩ ከምን እንደሚመነጭ ለማሳወቅ ከተለያዩ የጤና ጣቢያዎች ወደ ማእከል የሚተላለፈው የመረጃ ስርጭት ደካማ መሆን ፣
የእናቶችን ሞት ምክንያት ለማወቅ የሚደረገውን ዳሰሳ በሚመለከት ትርጉሙን ተረድቶ ወደስራው ያለመግባትና የሕክምና ባለሙያዎችም በጎ ፈቃደኝነት ያለ መኖር ፣
የእናቶችን ሞት ምክንያት በመረዳቱ ረገድ ለስራ የሚመች ፖሊሲ እና ህግ እጥረት፣
ይህ ችግር የመንግስት ችግር እንደሆነ አድርጎ የመውሰድ እና የግንዛቤ እጥረት የሚሉትና ሌሎችም ከአፍሪካ አገራት ተሰብሳቢዎች ተጠቁሞአል፡፡
በኢትዮጵያ ከዘጠኝ ሆስፒታሎችና ከአርባ አምስት የጤና ጣቢያዎች ለስብሰባው የተወከሉ የጤና ባለሙያዎች እንደችግር ከነሱዋቸው መካከል ፣
በጤና ተቋማት መካከል ያለው የስራ ግንኙነት ጠንካራ አለመሆን ፣
ለተሻለ ሕክምና የማስተላለፍ (Referral System) Öንካራ አለመሆን ፣
የእናቶችን ሞት ምክንያት ለማወቅ ዳሰሳ በማድረጉ ረገድ እንደልብ የሚያሰራ ገንዘብ አለመኖር ፣
የእናቶችን ሞት ሁኔታ ለማወቅ የሚደረገው ምዝገባን በሚመለከት ትክክለኛ በሆነ መንገድ ትርጉዋሜውን የመረዳት ችግር ፣
የደረሰውን ችግር እና የተለያዩ መረጃዎችን ለመሰብሰብ እንዲረዳ የተዘጋጀው ቅጽ ብዙ ጥያቄዎችን መያዙ እና እረጅም ማለትም ወደአስር ገጽ መሆኑ እና የቃላቱ ይዘት በቀላሉ የማይተረጎም መሆኑ ፣
የባለሙያዎችን ቁጥር እና ጥራት ማስተካከል፣
ከላይ ለተነሱት ጥያቁዎች በኢትዮጵያ በኩል እንደመፍትሔ ከተጠቆሙት መካከል አንዱመሑሀ የእናቶችን ሞት ምክንያት በማወቁ ረገድ በሚሰራው ፕሮጀክት የገንዘብ ድጋፉን እንዲያጠናክርና በአሰራሩ ላይ ብቃትን ለማግኘት የተለያዩ ስልጠናዎችን ለጤና ባለሙያው እን ዲያዳርሱ ማድረግ እንዲቻል እና በአሁን ወቅት በየሆስፒታሎቹ እና ጤና ጣቢያዎች ስራውን በመስራት ላይ ያለው ኮሚም በጥንካሬ ተግባሩን እንዲያከናውን ተጠቁሞአል፡፡
በአፍሪካ አገራት ተሰብሳቢዎች የተነሱትን የተለያዩ ችግሮች በሚመለከትም የመፍትሔ ሀሳቦች የቀረቡ ሲሆን ከእነሱም መካከል ከመንግስታትና ሌሎች ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተባብሮ መስራት አስፈላጊ መሆኑንና ለጤና ባለሙያው ተከታታይ የሆነ ስልጠና መስጠት ፣የገ ንዘብ ድጋፉም የሚጨምርበትን መንገድ ማመቻቸት እንዲሁም ህብረተሰቡ በተገቢው እና በማንኛውም ጊዜ ወደጤና ተቋማቱ በመሄድ ግልጋሎት ማግኘት እንደሚገባው እንዲያውቅ መረጃ እንዲያገኝ ማስቻል አስፈላጊ መሆኑ ተነስቶአል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ስራውን በመስራት ላይ የሚገኙት የጤና ጣቢያዎች የእናቶችን ታሪክ በሚመለከት የሰበሰቡትን መረጃ በወቅቱ ወደ ሚመለከተ ሆስፒታል እንዲልኩና ሆስፒታሎቹም ወደ ማእከሉ እንዲያደርሱ አሰራሩ መመቻ ቸት እንዳለበት አስገንዝበዋል፡፡ ባጠቃላይም በየትኛውም የአለም ክፍል የሚደርሱ የጤና ችግ ሮች የመንግስት ናቸው ተብለው የሚተው ሳይሆን ሕብረተሰቡ ባጠቃላይ ለችግሮቹ መወገድ የበኩሉን እንዲወጣ የሚያስፈልግ መሆኑ በአፍሪካውያኑ ተጠቅሶአል፡፡
ዶ/ር ይርጉ ገ/ሕይወት በኢትዮጵያ በኩል የተነሱትን ጥያቄዎች በሚመለከት እንደ ገለጹት ..መረጃውን ለመከታተል እንዲያመች የተዘጋጀውን ቅጽ በሚመለከት የተነሳው ጥያቄ አግባብነት ያለው ሲሆን ወደፊት አጭር እና ግልጽ የሆነ ቅጽ እንዲዘጋጅ ጥረት ይደረጋል ብለዋል፡፡ ESOG የጤና ተቋማትን አቅም በመገንባት ላይ ይገኛል፡፡ አንዱ ሆስፒታል አምስት ከሚሆኑ ጤና ጣቢያዎች ጋር ትስስር በመፍጠር ስራውን እንዲያከናውን ሁኔታዎችን ያመቻቸን ስለሆነ ሕመምተኛውን ከፍ ወዳለ የጤና ተቋም የማስተላለፍ (Referral ) አሰራርን ቀልጣፋ እንደሚያደርገው እናምናለን፡፡ ሆስፒታሎቹም ተቀብለው እርዳታ መስጠት ብቻም ሳይሆን ለላከላቸው ጤና ጣቢያ ስለሁኔታው ምላሽ የሚሰጡበትን አሰራር ዘርግተናል፡፡ አብረውን የሚሰሩት ዘጠኝ ሆስፒታሎችም ችግር እስኪፈጠር ዝም ብለው የሚጠብቁ ሳይሆን ችግሩ ከመፈጠሩ በፊት ወደጤና ጣቢያዎች ወርደውም የድጋፍ ስራ የሚሰሩበት ሁኔታም አለ፡፡ በእርግጥ በዚህ ዙሪያ ለተነሱት ጥያቄዎች እስከአሁን የሄድንበት መንገድ በቂ ነው ለማለት ሳይሆን ከዚህ በበለጠ አሰራራችንን ወደፊት እያሻሻልን የእናቶችን ጤንነት ሁኔታ መከታተል እንዳለብን እናምናለን፡፡ የገንዘብን ችግር በተመለከተም ለዚህ ስራ የሚውል የተወሰነ ገንዘብ ያለ ሲሆን ነገር ግን በዚህ መቀጠል ያለበት አይመስለንም፡፡ ምክንያቱም የእናቶች ጤንነት በጤና አገልግሎት ዘዴው ታቅፎ በዘላቂነት መሰራት ያለበት እንጂ ገንዘብ ሲኖር የሚሰራ ገንዘብ ሳይኖር የሚቋረጥ መሆን የለበትም፡፡ ስራው ገንዘብ ላይ የሚያተኩር ከሆነ የእናቶች ጤንነት ሁኔታን ወደተሸለ ለማድረስ የሚያስችለውን ስራ የሚፈታተን በመሆኑ በአገሪቱ አቅም ወደሚ ሰራበት አቅጣጫ ማተኮር እንደሚገባ እናምናለን፡፡ ከዚህ በተረፈ የባለሙያዎችን ብቃትና ጥራት ማስተካከል የሚለውን በሚመለከት የኢትዮጵያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር ESOG ከአለም አቀፉ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር FIGO ጋር በመተባበር በተቻለ መጠን ስልጠና በመስጠት የጤና ባለሙያው እውቀት እንዲዳብር እና ለስራው ተነሳሽ ነቱን እንዲያሳይ ጥረት በማድረግ ላይ ሲሆን የባለሙያውን እና የጤና ተቋማትን ቁጥር በማሳደጉ ረገድ የኢፊድሪ ጤና ጥበቃ ሚኒስርም የበኩሉን እያበረከተ ይገኛል.. ብለዋል ዶ/ር ይርጉ ገ/ሕይወት ;