Saturday, 23 June 2012 08:37

.....በእርግዝና ወቅት የወር አበባ.....

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(34 votes)

በዚህ እትም ለንባብ ያቀረብነው በእርግዝና ወቅት የወር አበባ ይታያልን ?የሚለውንና የወር አበባ ሳይታይ መኖር ይቻላልን ? በሚል ከሁለት ተሳታፊዎች የደረሱንን ጥያቄ ዎች መሰረት በማድረግ የተጻፈ ነው፡፡ የመጀመሪያው ጥያቄ እንዲህ ይላል፡፡

...የተከበራችሁ የላንቺና ላንተ ፕሮግራም አቅራቢዎች እንደምን ሰነበታችሁ? እኔ የፕሮግራማችሁ አድማጭ ስሆን አሁን ግን ልጠይቃችሁ የተዘጋጀሁት አንድ ጥያቄ አለኝ፡፡ ጥ ያቄዬን ትቀበሉኛላችሁ ብዬ መልእክን እነሆ ብያለሁ፡፡ ብላናለች... ሰርክአዲስ ተፈራ ከቃሊቲ.....ጉዳዩ እህን የሚመለከት ነው፡፡ እህ የምትኖረው በመርሐቤ አካባቢ ሲሆን የሁለት ልጆች እናት ነች፡፡ አሁን ሶስተኛ ልጅዋን እርጉዝ ስትሆን በጤናዋ ላይ የተለየ ነገር ስላየች ወደእኔ መልእክትዋን ልካለች፡፡ የተጻፈው ደብዳቤ እንዲህ ይላል፡፡...እማንቺ ሆይ ...እነሆ  እግዚአብሔር ይመስገ ን ደህና ነኝ፡፡ ልጆቼም ደህና ናቸው፡፡ አሁን ግን በጤናዬ ላይ ቀድሞ ከነበረው ሁኔታ የተለየ ነገር ስላጋጠመኝ አንቺን ላማክርሽ ብዬ ነው፡፡ እርግዝናዬ ወደ አራት ወር የሆነው ሲሆን የወር አበባዬ ግን አሁንም ይታየኛል፡፡ በአቅራቢያችን ያለችውን የጤና ሰራተኛ ባማክራት ከፍ ወዳለ ሕክምና ሂጂ አለችኝ፡፡ ከፍ ያለው ሕክምና እንግዲህ አለም ከተማ ሲሆን እነሱም ካልቻሉ ያው ዞሮ ዞሮ ወደአዲስ አበባ መላኬ አይቀርም፡፡

ስለዚህ እኔ አንደኛውን ወደአንቺጋ ወደ አዲስ አበባ መምጣትን አሰብኩ፡፡  እናም ከመምጣ በፊት ልንገርሽ ብዬ ነው፡፡ ብትችይ እ ሆይ መላ በይኝ፡፡....ይላል የእህ ደብዳቤ፡፡ እኔም እህ ወደ እኔጋ ስትመጣ የምትፈልገውን እርዳታ ታገኝ ዘንድ ለመተባበር ዝግጁ ነኝ፡፡ ነገር ግን የገረመኝ ነገር በእርግዝና ጊዜ የወር አበባ ይታያል እንዴ? ወይንስ የሕመም ነው? የላንቺና ላንተ ፕሮግራም አዘጋጆች...እባካችሁ ባለሙያም ሆነ የጥናት ውጤት አይታችሁ መልስ ንገሩኝ፡፡ እኔም እህን በተስተካከለ አእምሮ ተዘጋጅቼ እንድጠብቃት ይረዳኛልና.....

ሰርክአዲስ ተፈራ ከቃሊቲ ፡፡

ለዚህ ጥያቄ መልስ እንዲሆን ከተለያዩ የጥናት ስራዎች መረጃን አገላብጠናል፡፡እንዲሁም የጽንስና ማህጸን ሕክምና እስፔሻሊሰት አነጋግረናል፡፡ ሠቄቂስቃቋ ሻስሮቁሻ የሚል ድህረገጽ ባሰፈረው የምርምር ውጤት እርግዝናና የወር አበባ የሚለው አገላለጽ ያልተለመደና ለማድመጥ የሚያስቸግር ነገር ግን አልፎ አልፎ የሚያጋጥምን ደም መፍሰስ እንደወር አበባ ከመቁጠር የመነጨ ነው ይለዋል፡፡ምክንያቱም ይላል ድህረገጹ አንዲት ሴት አርግዣለሁ ልትል በምትችልበት ጊዜ የወር አበባዋ ወዲያውኑ እንደሚቋረጥ እሙን በመሆኑ ነው፡፡ አንዲት ሴት አርግዣለሁ ካለች የወር አበባ አይኖራትም ፡፡ በቃ ፡፡የተለመደው ይህ ነው፡፡ ነገር ግን እንደማናኝውም የአለም ሁኔታ በእርግዝና ዙሪያ የሉ ነገሮችም  (nothing is carved in stone) ልክ በተለመደው ወይም በሚታወቀው ሁኔታ ሊቀጥል ይችላል ተብሎ የሚገመት ሳይሆን በተለያዩ ምክንያቶች የየራሱን የጤና እና የተፈጥሮ ሁኔታ ባማከለ መንገድ ሊለያይ ይችላል፡፡ አንዲት ሴት የወር አበባዋ ከቀረ እለት ጀምሮ እርግዝናው በተገቢው መንገድ እያደገ ያለምንም እንከን እስከሚወለድ ድረስ ይቆያል ማለት ሁልጊዜ ላይሳካ ይችላል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ሴቶች ከማርገዛቸው አስቀድሞ በተፈጥሮ ያዩት የነበረው የወር አበባ በእርግዝና ጊዜም የሚቋረጥ ቢሆንም ልክ ያዩት የነበረውን የወር አበባ በመሰለ መልኩ የሚቀጥል የደም መፍሰስ ሊኖር ይችላል፡ በእርግጥ በተለይ የመውለጃ ጊዜ ሲቃረብ የሚታይ የደም መፍሰስ ሊኖር የሚችል ሲሆን በተረፈ ግን በተለያየ ምክንያት እስከመውለጃ ጊዜ ድረስ የሚታይ ሴቶቹም ልክ እንደወር አበባ የሚቆጥሩት ደም ሊያዩ ይችላሉ ፡፡ በእርግዝና ጊዜ ምጠብታ መልክም ደም ሊታይ ይችላል፡፡

የወር አበባ ባለበት ሁኔታ እርግዝና ሊኖር ይችላልን? በሚል ለተነሳው ጥያቄ መረጃ

ከማገላበጥ ባለፈ ያነጋገርነው ዶ/ር አብዱልፈታህ አብዱልቃድርን ነው፡፡ ዶ/ር አብዱልፈታህ የጽንስና ማህጸን ሕክምና እስፔሻሊስትና በፓውሎስ ሆስፒታል የጽንስና ማህጸን ሕክምና ክፍሉ ኃላፊ ናቸው፡፡

ዶ/ር አብዱልፈታህ አብዱል ቃድር፡-

..እርግዝናና የወር አበባ በተመሳሳይ ወቅት አይኖሩም፡፡ ምክንያቱም አንድ ጊዜ እርግዝና ከተፈጠረ በድጋሚ የዘር ፍሬ ከኦቫሪ ከሚባለው የሰውነት ክፍል ወጥቶ እንደገና እርግዝና የመፈጠር እድል ስለማይኖር ነው፡፡ አንዲት ሴት በማህጸኑዋ እርግዝና ካልተፈጠረ ከሰውነቷ የውጣው የዘር ፍሬ በየወሩ የማህጸን ግድግዳ ውስጥ ካረፈ በሁዋላ በወር አበባ መልክ ይወገዳል፡፡ አንድ ጊዜ እርግዝና ከተፈጠረ ግን በምንም ምክንያት የወር አበባ መታየት የለበትም፡፡ በእርግጥ በእርግዝና ጊዜ ወር አበባ ሳይሆን ደም ሊታይ ይችላል፡፡ የዚህም ምክንያት ከማህጸን በላይ እርግዝና ወይንም በመኮላሸት ላይ ያለ እርግዝና አለበለዚያም ከሀያ ስምንት ሳምንት በፊት ከሆነ እንደውርጃ የሚቆጠር ሊሆን ይችላል፡፡ ያረገዘችው ሴት ደም የምታየው ከሀያ ስምንት ሳምንት በሁዋላ ከሆነ ደግሞ ከእንግዴ ልጅ ጋር በተያያዘ ወይንም በማህጸን በር አካባቢ እጢዎች ሊኖሩና አለበለዚይም ኢንፌክሽን የደም መፍሰስን ሊያስከትል ይችላል፡፡ ከዚህ ውጭ በምንም ምክንያት በእርግዝና ጊዜ የወር አበባ ሊታይ አይችልም፡፡ .. በሳይንሱ An ectopic pregnancy አን ኤክቶፒክ ፕሬግናንሲ በመባል የሚጠራ አለ፡፡ እሱም ምንድነው እርግዝናው አልፎ አልፎ በማህጸን ውስጥ በትክክለኛው ሁኔታ ሳይቀመጥ ፋሎፒያን ቲዩብ በተባለው መስመር ውስጥ የሚቆይ ከሆነ ልክ በወር አበባ መጠን መድማትን ሊያስከትል ይችላል፡፡ በተለይም እርግዝናው ገና እንደተከሰተ ከሆነ በአፋጣኝ ወደ

--------------///---------------

አሁን የምናልፈው ወደሌላዋ ጠያቂያችን ነው፡፡ እሱዋም ያቀረበችው ጥያቄ ስለወር አበባ ነው፡፡እንዲህ ይላል፡፡

..እኔ እድሜዬ ወደ 23 አመት ይሆነኛል፡፡ ነገር ግን የወር አበባ የሚባል ነገር አይቼ አላውቅም፡፡ ለመሆኑ የወር አበባ ሳይታይ ይህንን ያህል እድሜ ይቆያልን? ወይንስ እንደህመም የሚቆጠር ይሆን? እባካችሁ ባለሙያ አነጋግራችሁ መልስ ስጡኝ ብላለች፡፡ ይህች ጠያቂ ስሙዋ እንዲጠቀስ አልፈለገችም፡

የወር አበባን በሚመለከት ያገኘነው መረጃ   BuZZLe.com ÃvLM::

ሴቶች የወር አበባ ማየት ሲጀምሩ አጠራራቸው ወ/ት ወይንም ልጃገረድ ወደመባል ይለወጣል፡፡ እድሜውም በአብዛኛው ከ11 አመት እስከ 15 አመት በሚደርስ ጊዜ ውስጥ ነው፡፡ አልፎ አልፎ እንዲያውም ወደ 10 እና ዘጠኝ አመት ዝቅ ብሎ መምጣት እንደሚጀምር አንዳንድ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ የወር አበባ በሁሉም ሴቶች በእኩል ወይንም በአንድ አይነት አፈሳሰስ እና የቀን ቀመር የሚታይ አይደለም፡፡ በአንዳንዶች በጣም የበዛ ፍሰት ሲኖረው በሌሎች ደግሞ የጠብታ ያህል የሚታይበት ሁኔታ ያጋጥማል፡፡ አንዳንድ ሴቶች ላይ ደግሞ የመፍሰሻ ጊዜው ሲደርስ ጀምሮ እስከሚያልፍ ድረስ ከፍተኛ የሆነ ሕመም የሚያስትል የወር አበባ ፍሰት ያጋጥማል፡፡

ጠያቂያችን ያሉት ግን በሀያ ሶስት አመት እድሜዬ እስከጭርሱንም የወር አበባ አላየሁም የሚል ነው፡፡ ይህንንም ጥያቄ ለማብራሪያ ለጋበዝነው ለዶ/ር አብዱልፈታህ አቅርበነዋል፡፡

ዶ/ር ፡- ሴቶች በእድሜያቸው ከአስራ አንድ አመት እና ምናልባትም ከዚያም በታች በሆነ እድሜ ሲደርሱ የወር አበባ የሚታያቸው ሲሆን አልፎ አልፎ ግን የወር አበባ ሙሉ በሙሉ የማያዩ ሴቶች ይኖራሉ፡፡ አንዳንድ ሴቶች ደግሞ ማየት ከጀመሩ በሁዋላም ሊቋረጥባቸው ይችላል፡፡ የወር አበባ በትክክል ሂደቱን ጠብቆ አለመፍሰሱ በተለያዩ ችግሮች መንስኤ ነው፡፡ የሆርሞን፣ የማህጸን አፈጣጠር ፣የክብረንጽህና መደፈን፣ የመሳሰሉት ችግሮች የወር አበባን ፍሰት ያውካሉ፡፡ በእርግጥ በእነዚህ ሁኔታዎች የደም መፍሰሱ ከተቋረጠ በየወሩ የተለያየ የህመም ስሜት ሊኖር ይችላል፡፡ ይህ ከሆነ የወር አበባው አለ ነገር ግን የሚፈስበት መንገድ አጥቶ ሊሆን ይችላል፡፡ ይህ ግን በህክምና ሊስተካከል የሚችል ነው፡፡

ኢሶግ / የወር አበባ ከተፈጠረ በሁዋላ አለመፍሰሱ ወዴት እየቆየ ነው?

ዶ/ር ሴቶቹ በአብዛኛው በየወሩ የወር አበባ የመምጣት ስሜት ይኖራቸዋል፡፡ ይህ ከሆነ ማህጸኑ ላይ የአፈጣጠር ችግር ከሌለበት በክብረንጽህና አካባቢ ልክ እንደመጋረጃ የግርዶሽ ሁኔታ ሊኖር ይችላል፡፡ ከዚህም በተለየ በእጢ ወይንም ክብረንጽህናው በተፈጥሮ የተዘጋ ሊሆን ይችላል፡፡ ስለዚህ ከግርዶሹ ጀርባ  በማህጸን በቱቦ እንዲሁም በሆድ ውስጥ ጭምር ደም ሊከማች ይችላል፡፡ ይህ በምርመራ ሊታወቅ የሚችል ሲሆን በህክምና አገልግሎቱ መፍትሔ የሚያገኝ ነው፡፡ በእርግጥ ከፍተኛ ሕመም ሊሰማቸው ይችላል፡፡ ከዚህ ውጭ ማንኛዋም ሴት በተፈጥሮ የወር አበባ ልታይ ግድ ነው፡፡

 

 

Read 59399 times Last modified on Saturday, 23 June 2012 10:51