Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 09 June 2012 11:09

ለስነ ተዋልዶ ጤና ችግር ምክንያቶች...

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

በአለም ደሀ በተባሉት ሀገሮች ያሉ ሴቶች በየቀኑ ፀሎት ያደርሳሉ፡፡

ፀሎት የሚያደርሱበት ምክንያትም...

እርግዝና እንዳይከሰት ፣

እርግዝና ቢከሰት ክትትል ሊያደርጉበት የሚችሉበትን ክሊኒክ ርቀት በማሰብ፣

የእርግዝና ክትትል የሚያደርጉበት የጤና ተቋም ከሚኖሩበት አካባቢ እሩቅ በመሆኑ ...ይህን ሁሉ መንገድ ተጉዤ ብሄድ ተቋሙ ክፍት ሆኖ ይቆየኝ ይሆን ከሚል ስጋት፣ወደ ጤና ተቋሙ በሚኬድበት ጊዜ በትክክል ጥያቄዬን የሚመልስልኝ የጤና ባለሙያ አገኝ ይሆን?

በሚለውና በመሳሰሉት ምክንያቶች ሴቶች ሁልጊዜ ፀሎት ያደርጋሉ፡፡ ከዚህም ሌላ በግብረስጋ ግንኙነት ምክንያት የሚተላለፍ በሽታም እንዳይይዛቸው ሴቶች ፀሎት ያደርሳሉ፡፡ የዚህ ሁሉ ምክንያት ግን የጤና አገልግሎቱ ውስንነትና በአቅራቢያቸው አለመገኘቱ እንዲሁም የጤና ክትትሉን ለማድረግ የማያስችላቸው የተለያየ ምክንያት መኖሩ ነው እንደ ቅሮሻሶሽቃሳስቈ ሽቃስቈቃሮ- ሽቄቃሮቁ  መረጃ ፡፡

ሁኔታው አነጋጋሪ ነው ይላል መረጃው፡፡ እውን ፀሎታቸው ይሰራ ይሆን ?

ሴቶቹ ሊታከሙ የሚሄዱበት የጤና አገልግሎት አስፈላጊው አቅርቦት ይኖረው ይሆን?

አብረዋቸው የሚኖሩት ባሎቻቸው ለሴቶቹ ድጋፍ ያደርጉላቸዋልን?

እርግዝናን ባልተፈለገ ጊዜ እንዳይከሰት ለማድረግ ይቻላልን?

ብዙወን ጊዜ በታዳጊ አገሮች እንደሚታየው ሴቶች በስነተዋልዶ ጤና ዙሪያ በከፍተኛ ሁኔታ ተደጋጋሚ የሆነ ችግር ይደርስባቸዋል፡፡ መረጃውን ለንባብ ያበቃው ክፍል በተለይም በጉልህ የሚታዩትን አስር ችግሮች እንደሚከተለው ጠቅሶአል፡፡

1/የጾታ እኩልነት ፣

በታዳጊ አገሮች በተለይም በገጠሩ አካባቢ ከሚኖሩ ሴቶች አብዛኞቹ በስነተዋልዶ ጤና ዙሪያ የሚደርስባቸውን ችግር በሚመለከት ከባሎቻቸው ጋር ምንም ውይይት አያደ ርጉም፡፡ እንደ ምክንያት የሚቆጠረውም ...የወንዶቹ ፈቃደኛ አለመሆን...ወንዶቹ ብዙውን ጊዜ የበላይነትና የአዛዥነት ስሜት ስለሚታይባቸው... ወዘተ ሲሆን ከዚህ ውጭ ደግሞ ሴቶች አይን አፋር ስለሚሆኑ...በእጃቸው ገንዘብ ስለሌላቸው...እውቀቱ ስለሌላቸው... በቤት ውስጥ ለተጣለባቸው ኃላፊነት ቅድሚያ በመስጠት በመሳሰሉት ምክንያቶች በመ ብታቸው ተጠቅመው ጤናቸውን በሚመለከት ምንም እርምጃ ሳይወስዱ ለሕልፈት ሊዳ ረጉ ይችላሉ፡፡

2/አቅርቦት  ፣

በሁለተኛ ደረጃ የተቀመጠው የአቅርቦት ችግር ሲሆን ይኼውም ሊከሰት የሚችለው በደከመ የእቅድ አፈጻጸም ወይንም ተገቢ የሆነውን ድጋፍ ባለማግኘት አለበለዚያም በስርጭት ዘዴው የተዛባ መሆን ምክንያት ሲሆን እንደምሳሌ ከሚጠቀሱትም መካከል የቤተሰብ እቅድ ዘዴ አንዱ ነው፡፡ የቤተሰብ እቅድ ዘዴ አገልግሎት ለተጠቃሚዎች ያለመዳረስ ሁኔታ ይታያል፡፡

3/ የባለሙያ እጥረት ፣

በእድገት ወደሁዋላ ቀርተዋል በሚባሉ አገሮች የህክምና ባለሙያ ማለትም የዶክተሮች... ነርሶች እና አዋላጅ ነርሶች እጥረት ከፍተኛ መሆኑ እሙን ነው፡፡በመሆኑም በታዳጊ አገሮች ውስጥ የሚኖሩ ሴቶች ብዙውን ጊዜ ለመውለድ የሚጠቀሙበት ዘዴ ልማዳዊ ዘዴ በመሆኑ አገልግሎቱ የሚሰጣቸውም በመኖሪያ ቤታቸው ንጽህናው ባልተጠበቀና ምንም ጥንቃቄ በሌለው ሁኔታ ነው፡፡ ብዙዎች በእንደዚህ ያለው አገልግሎት ሳቢያ በጤናቸው ላይ እክል ሲደርስባቸው ይታያል፡፡

4/ የጤና ተቋማት እርቀት፣

ሌላው በታዳጊ አገሮች ውስጥ በእናቶች የስነተዋልዶ ጤና ዙሪያ ችግር እንዲከሰት ምክንያት የሚሆነው የጤና አገልግሎት መስጫ ተቋማቱ ከመኖሪያ መንደሮች በርቀት መገኘት ነው፡፡ በገጠር የሚኖሩ ሰዎች የመጉዋጉዋዣ ዘዴውን በቅርብ አለማግኘታቸው አንዱ የችግር መንስኤ ሲሆን የተቻለውን ያህል ጥረት ተደርጎ እንኩዋን መኪና ቢገኝ ሊከፈል የሚገባውን ገንዘብ አለማግኘት ለብዙዎች ችግር ሆኖ ይስተዋላል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ለምሳሌ ሴቲቱ በምጥ ብትያዝ መጉዋጉዋዣው እንኩዋን ቢገኝ ከጤና ተቋሙ ለመድረስ ጊዜ ስለሚወስድ በመንገድ ላይ ሊከሰት የሚችለውን ችግር መገመት አያስቸግርም፡፡

5/ መረጃ ፣

ትክክለኛ መረጃ አለማግኘት ሌላው ችግር ነው፡፡ ስለኤችአይቪ ስርጭትም ይሁን ወይንም ሌሎች ከስነተዋልዶ አካላት ጤና ጋር በተያያዘ የሚነገሩ ነገሮች ምን ያህል በትክክል ግንዛቤ ሊያስጨብጡ የሚችሉ ናቸው? ወይንም ምን ያህል ትክክለኛ መረጃ ለሰዎች ይደርሳል የሚለው በጥንቃቄ ሊፈተሸ የሚገባው ነው፡፡ ምክንያቱም መረጃውም ከተገቢው ቦታ መውጣቱንና መረጃውን የሚሰጠው ባለሙያ ለስራው በተገቢው መንገድ የተሰየመ ካልሆነ ምናልባት በተሳሳተ መንገድ መረጃው ለህብረተሰቡ ሊደርስ የሚችል በት መንገድ ሊፈጠር ይችላል፡፡ ለምሳሌ መድሀኒት የሚያስከትለውን ውጤት ወይንም ወደ ሕክምና ተቋም ከመሄድ ይልቅ በልማዳዊ መንገዶች ጤናን መጠበቅ እንደሚገባ በመሳሰሉት የተሳሳቱ ንግግሮች ሰዎች ሊሳሳቱና ሊጎዱ ይችላሉ፡፡

6/ የጊዜ አጠቃቀም ፣

ሴቶች ብዙውን ጊዜ በኑሮአቸው ከባድ ጫና ስለሚኖርባቸው ከማለዳ እስከ ሌሊት ድረስ በተለያዩ ስራዎች የመጠመድ እድል ይኖራቸዋል፡፡ በቤት ውስጥ ለቤተሰቡ የተለያዩ ስራዎችን መስራት...በእርሻ ቦታ አረም ማረም ... ኩትኩዋቶ መኮትኮት የመሳሰለውን ማከናወን ...ወደገበያ ተሰማርቶ የጎደሉ ነገሮችን ማሟላት ...ወዘተ... በእንደዚህ ያለ ሁኔታ ለሚኖሩ ሴቶች ሲታመሙ ወደ ክሊኒክ መሄድ ወይንም ለጤና ክትትል ወደ ሆስፒታል ማምራት ማለት ጊዜን እንደማጥፋት ስለሚቆጥሩት በጸጥታ ሕመማቸውን ማዳመጥ ይመርጣሉ፡፡

7/ የአገልግሎት ሰጪዎች የተዛባ አመለካከት፣

ባለሙያዎች አገልግሎት በሚሰጡበት ጊዜ የተዛባ አመለካከታቸውን በተቻለ መጠን ማስተካከል ይገባቸዋል፡፡ ተገልጋዮች በቤተሰብ እቅድ ዘዴም ይሁን ወይንም ጽንስን በማስወረድ እንዲሁም ተያያዥ በሆኑ የስነተዋልዶ ጤና ጉዳዮች ለሕክምና ወይንም ለምክር አገልግሎት ወደ ጤና ባለሙያ በሚቀርቡበት ጊዜ ያለምንም ችግር ተገቢውን አገልግሎት ማግኘት ይገባቸዋል፡፡ ከዚያ ውጭ ግን እንደጥፋተኛ በመቁጠር ወይንም እንደአላዋቂ በመመልከት በተሳሳተ መንገድ ተገልጋዮቹን ማንገላታት ወይንም ማሳዘን ተገቢ አይደለም፡፡

8/ ሕጋዊ አሰራሮች ፣

በማንኛውም የጤና ጉዳይ የተቀመጡ ሕጋዊ አሰራሮች መኖራቸው እሙን ነው፡፡ በስነተ ዋልዶ ጤና አገልግሎት ዙሪያም የተቀመጡትን ሕጋዊ አሰራሮች ተገልጋዮች ምን ያህል ያውቁታል? ምንስ ያህል ይጠቀሙበታል? የሚለው ትኩረት የሚገባው ነጥብ ነው፡፡ ለም ሳሌ ... ጽንስ ማቋረጥን በሚመለከት በህግ የተቀመጠው አፈጻጸም ምን ይመስላል? የሴቶቹስ መብት እስከምን ድረስ ነው? የጤና አገልግሎቱስ ድርሻ ምን መሆን አለበት? ማ... ምን ቢያደርግ በህግ ይጠየቃል?...ወዘተ የሚለውን በትክክል ህብረተሰቡ እንዲያው ቀው ማድረግ ተገቢ ነው፡፡ ህብረተሰቡም ይህንኑ አውቆ በተግባር እንዲያውለው ይጠ በቃል፡፡

9/ ባህላዊና ልማዳዊ አሰራሮች፣

ባህላዊና ልማዳዊ ድርጊቶች በተለይም በታዳጊ አገሮቹ ለሚከሰቱ የስነተዋልዶ ጤና ሁነቶች ችግርን ከሚያስከትሉ መካከል ናቸው፡፡ ለምሳሌ...አንዳንድ አካባቢዎች ላይ እንደሚታየው ሴቶች የጤና አገልግሎቱን በልምድ ከጉዋደኞቻቸው የሚያገኙ ሊመስ ላቸው ይችላል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ሴቶች ሕክምናውን ማግኘት ያለባቸው ከሴቶች ብቻ ሊመስላቸው ይችላል፡፡ አልፎ አልፎ በእምነት ምክንያት ገላን ገልጦ ለሀኪም ማሳ የት እንደነውር ሊቆጠር ይችላል፡፡እንደዚህ ያለውን ሁኔታ ለማስቀረት ህብረተሰቡን በጋራ ማስተማር ተገቢ ይሆናል፡፡

10/ የድጋፍ እጥረት፣

በመጨረሻ የተጠቀሰው የድጋፍ እጥረት ነው፡፡ በአለምአቀፍ ደረጃ የስነተዋልዶ ጤና በበቂ ሁኔታ ድጋፍ የማይደረግለት ነው፡፡ ለምሳሌ ከሁለት መቶ ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ሴቶች የቤተሰብ እቅድ ዘዴን ማግኘት ቢፈልጉም ግን የማዳረስ እጥረቱ ይታያል፡፡ በታ ዳጊ ሀገራቱም ይሁን በአለም አቀፍ ደረጃ የሚደረገው ድጋፍ እጥረት ስለሚታይበት ሴቶች ለብዙ የስነተዋልዶ ጤና ችግሮች ይጋለጣሉ፡፡

 

 

Read 6584 times Last modified on Saturday, 09 June 2012 11:16