33 ተቃዋሚ ፓርቲዎች ለጠ/ሚሩ ደብዳቤ ሊያስገቡ ነው
በአዲስ አበባ እንዲሁም በወረዳና ቀበሌ ምርጫ ዙሪያ ለጠ/ሚ ኃይለማርያም ደሳለኝ የፃፉት ደብዳቤ ማህተም የለውም ተብሎ የተመለሰባቸው 33 ተቃዋሚ ፓርቲዎች፤ እንደገና የሁሉም ማህተም ያረፈበት ደብዳቤ ለማስገባት እየጣሩ ነው፡፡
የምርጫ ቦርድ ባዘጋጀው የምርጫ የጊዜ ሰሌዳ ላይ ውይይት ተዘጋጅቶ የነበረ ቢሆንም፤ የሚዲያ አጠቃቀም፣ የህግ የበላይነትና የውድድር ሜዳው ለሁሉም እኩል እንዲሆን መደራደር እንፈልጋለን ሲሉ የ33ቱ ፓርቲዎች ተወካይ አቶ አስራት ጣሴ ተናግረዋል፡፡ የኢህአዴግ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ሬድዋን፤ የወረዳና የቀበሌ ምርጫ ለታይታ ስለማይመች ተቃዋሚ ፓርቲዎች አይፈልጉትም፤ ለምርጫ ሳይሆን ኢህአዴግ አስቸገረን ብለው ለመውጣት ነው የሚዘጋጁት ብለዋል፡፡
የኢትዮጵያ ቤተ እስራኤላውያን ሴቶች የወሊድ መከላከያ እንዲወስዱ ተገደዋል ተባለ
ከስምንት ዓመት በፊት ከኢትዮጵያ የተወሰዱ ቤተ እስራኤላውያን ሴቶች ለረዥም ጊዜ የሚያገለግለውን ዴፖ ፕሮቬራ የተባለ የወሊድ መቆጣጠሪያ መድሃኒት ለመወጋት ካልተስማሙ ወደ እስራኤል ሊገቡ እንደማይችሉ ይነገራቸው እንደነበር “ቫኩም” የተሰኘው የእስራኤል ትምህርታዊ የቴሌቪዥን ፕሮግራም ሰሞኑን ባሰራጨው ዘገባ ጠቁሟል፡፡ ወደ እስራኤል ከመወሰዳቸው በፊት በኢትዮጵያ ጊዜያዊ የመጠለያ ካምፕ የቤተሰብ ምጣኔ ዎርክሾፕ ይሰጠን ነበር ያሉት ሴቶቹ፤ የወሊድ መከላከያውን እንዲወስዱ ያግባቧቸው እንደነበር ተናግረዋል፡፡
ቅ/ሲኖዶሱ ተመራጩ ፓትርያርክ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ብቻ እንዲኾን ወሰነ
‹‹የጳጳሱ ቅሌት›› መጽሐፍ ጸሐፊ በ‹‹የጳጳሱ ስኬት›› መጽሐፍ ይቅርታ ጠየቀ
በፓትርያርክ ምርጫ ሕግ ረቂቅ ላይ ውይይት እያካሄደ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ* የተመራጩ ፓትርያርክ ዜግነት ኢትዮጵያዊ ብቻ መኾን እንደሚገባው ወሰነ፡፡
በሃይማኖቱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታይ ኾኖ ሥርዐተ ቤተ ክርስቲያንን ጠንቅቆ ያወቀ፣ በትምህርተ ሃይማኖት በቂ ችሎታ ያለውና በግብረ ገብነቱ የተመሰገነ፣ በትውልዱም በዜግነቱም የውጭ ዜጋ የኾነ አባት* ለፓትርያርክነት በተቀመጠው መመዘኛ መሠረት በዕጩነት ለመቅረብ የሚችልበት ዕድል እንዳለ በሲኖዶሱ መጤኑን የስብሰባው ምንጮች ተናግረዋል፡፡
ሐረር ሬዲዮ ተዘጋ
በ1957 ዓ.ም በማቀባበያ ጣቢያነት ተቋቁሞ ላለፉት 48 ዓመታት ለምስራቅ ኢትዮጵያና ለአካባቢው ሀገሮች አገልግሎት ሲሰጥ የቆየው ሐረር ሬዲዮ ተዘጋ፡፡ ካለፈው ነሐሴ ወር ጀምሮ የጣቢያው ስርጭት እንደተቋረጠ ታውቋል፡፡ በአሁኑ የኢትዮጵያ ሬዲዮ እና ቴሌቭዢን ድርጅት (ኢሬቴድ) በያኔው የኢትዮጵያ ሬዲዮ በማቀባበያ ጣቢያነት የተቋቋመው ሐረር ሬዲዮ፤
ዋልያዎቹ
ከ31 ዓመታት መራቅ በኋላ በ29ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የሚካፈለው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን መደበኛ ልምምዱን ከጀመረ አንድ ሳምንት ሲያልፈው በደቡብ አፍሪካ የሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ አንድ ወር ቀርቶታል ፡፡ብሄራዊ ቡድኑ ካሳንችስ በሚገኘው ኢንተር ኮንትኔንታል ሆቴል በማረፍ በቀን ሁለት ጊዜ ልምምዱን እየሰራ ይገኛል፡፡
“በወተት ብቻ አይደለም ያደግሁት፤ በቡናም ነው” - አቶ አሊ ሁሴን
እንዴት ነው ለሽልማት የበቃችሁት?
አልፎዝ ከ95 በመቶ በላይ የግብርና ምርቶችን ወደ ውጭ በመላክ ነው የሚታወቀው፡፡ ለሽልማት የበቃነው የንግድ ስራ ሂደታችን ተገምግሞ ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ የቡናና የግብርና ምርቶች ወደተለያዩ አገራት በመላክ ለአገራችን ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ በማስገባታችን ነው፡፡በዚህም ከንግድ ሚኒስቴር ድርጅታችን የዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል፡፡
ከቡና ሌላ ምንድን ነው ወደ ውጭ የምትልኳቸው ምርቶች?
የትያትር መግቢያ ዋጋ ጭማሪ ውዝግብ
የትያትር ባለሙያዎቸ ወደ አዲስ አበባ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ አዳራሽ ለስብሰባ ሲገቡ
*በ15 ብር ማሳየት ለመንግሥት ትያትር ቤቶችም ያንሳል - የቢሮው ሃላፊ
*ቢሮው የግል ኢንተርፕራይዞችን ዋጋ የመተመን አግባብ የለውም - አርቲስት ገነት አጥላው
“ቁርጥ ያለ ምላሽ ስጡን፤ዋናው ማነቆ ያለው እናንተ ጋ ነው - አርቲስት ሽመልስ አበራ
በጐረቤት ሀገራት እንኳን አርቲስቶች በግል አውቶሞቢላቸው ይጓጓዛሉ እንጂ ታክሲ አይጠቀሙም የሚሉት የአገራችን የትያትር ባለሙያዎች፤እኛ ግን ስንሞት እንኳን የሬሳ ሳጥን መግዣ እየቸገረን በመዋጮ ነው የምንቀበረው ሲሉ ያማርራሉ፡፡
በየዓመቱ 6 ሚሊዮን ሰዎች በስትሮክ ህይወታቸው ያልፋል ስትሮክ - ድንገተኛው አደጋና ቅጽበታዊው ሞት
የሰውነታችን አጠቃላይ አዛዥና ተቆጣጣሪ በሆነው አንጐላችን ላይ በድንገት ተከስቶ ለአካል ጉዳተኛነትና ለሞት የሚዳርገው ስትሮክ፣ ዛሬ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የዓለማችን ህዝቦች አሳሳቢ የጤና ችግር ሆኗል፡፡
የዓለማችን ታላላቅ መሪዎችን ጨምሮ በርካታ ስመጥርና ተፅእኖ ፈጣሪ የተባሉ ሰዎችን ሁሉ በድንገት ለሞት አብቅቷል - ስትሮክ፡፡
ሰውነታችን የሚያከናውናቸውን ተግባራት በበላይነት የሚቆጣጠረውና ትዕዛዝ የሚያስተላልፈው አንጐላችን ጉሉኮስና ኦክስጅን በየደቂቃው በደም አማካኝነት እንዲደርሰው ያስፈልጋል፡፡ ይህ ስርዓት ተስተጓጐለ ማለት አንጐላችን ሙሉ በሙሉ ሥራውን አቆመ ማለት ነው፡፡ ይህ ደግሞ የሰውነት ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል አለመታዘዝ ወይም በተለምዶ ፓራላይዝድ መሆን የምንለውን የጤና ችግር ያስከትላል፡፡
አቶ ሬድዋን ስለምርጫ፣ ስለተቃዋሚዎች፣ ስለመተካካት---ምን ይላሉ?
የአዲስ አድማስ ጋዜጠኛ አበባየሁ ገበያው ከኢህአዴግ ፅ/ቤት ሃላፊ ከአቶ ሬድዋን ሁሴን ጋር በተለያዩ አነጋጋሪና አወዛጋቢ ፖለቲካዊ ጉዳዮች ዙሪያ ያደረገችው ሰፊ ቃለምልልስ እንደሚከተለው ቀርቧል።
ኢህአዴግ ከመድረክ ጋር ለመነጋገር፤ በቅድሚያ መድረክ የስነ ምግባር ደንቡን መፈረም አለበት ይላል። በሌላ በኩል፤ ደንቡ በፓርላማ ፀድቆ የአገሪቱ ህግ ሆኗል። የፈረመም ሆነ ያልፈረመ ፓርቲ፤ የህጉ ተገዢ ነው፡፡ መድረክ ደንቡን እንዲፈርም ቅድመ ሁኔታ ማስቀመጥ የፖለቲካ ነጥብ ለማስቆጠር ካልሆነ በቀር ትርጉም የለውም ይባላል---
የተጠማ ከፈሳሽ - የተበደለ ከነጋሽ
ሉ ሱን የተባለው የቻይና ገጣሚ የፃፈውን ግጥም ፀሐፌ-ተውኔት ገጣሚ መንግሥቱ ለማ ወደ አማርኛ መልሰውታል - “ሐሳብን ለመግለፅ” በሚል ርእስ፡፡ ይህን ግጥም በስድ ስናስበው የሚከተለውን አይነት ጭብጥ ይዞ እናገኘዋለን፡፡ ስለዚህም እንዲህ እንተርተዋለን፡፡
ተማሪ አስተማሪውን ይጠይቃል፡፡
“መምህር ሆይ! አንድ የቸገረኝ ነገር ገጥሞኛል”
“ምን ገጠመህ የኔ ልጅ?”
“ላስረዳዎት” ይልና ሁኔታውን እንደሚከተለው ያስረዳል፡-