Administrator

Administrator

"ኢትዮጵያ በህዳሴ ግድብ ላይ የሰጠቻቸው የቃል
ማረጋገጫዎች በጽሑፍ ስምምነት ይደራጁ"
ኢትዮጵያ በታላቁ የህዳሴ ግድብ ላይ የሰጠቻቸውን የቃል ማረጋገጫዎች በጽሑፍ ስምምነት እንድትደግፍ ግብፅ ጠየቀች። ይህ ጥያቄ የመጣው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ግድቡ በመስከረም ወር እንደሚመረቅ ከገለጹ በኋላ ነው።
የግብፅ ጠቅላይ ሚኒስትር ሙስጠፋ ማድቡሊ፣ በቅርቡ ብራዚል ውስጥ በተካሄደው የብሪክስ ስብሰባ ጎን ለጎን ከጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ጋር መነጋገራቸውን ጠቁመዋል።
በብሪክስ ስብሰባ ወቅት፣ ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ፣ ግድቡን “ግብፅንና ሱዳንን ሳይጎዳ” የማጠናቀቅና ትብብርን የመቀጠል ፍላጎታቸውን ገልጸው ነበር። ይሁን እንጂ ማድቡሊ፣ እነዚህ የቃል ማረጋገጫዎች በሁለቱ ሀገራት ወይም በናይል ተፋሰስ ሀገራት መካከል ያለውን የወደፊት ግንኙነት በሚያደራጅ የጽሑፍ ሰነድ ውስጥ መተርጎም አስፈላጊ መሆኑን አሳስበዋል።
የግብፅ ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ “የግብፅ አቋም በፍጹም አልተለወጠም፤ በአባይ ውሃ ድርሻዋ ላይ ምንም አይነት ጉዳት እንዲደርስ አትፈቅድም” ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል። ግብፅ የልማት ተቃዋሚ ባትሆንም፣ በአባይ ውሃ ላይ ያላትን ህጋዊ መብት እንደምትጠብቅም አስረድተዋል።
ጠ/ ሚኒስትር ዐቢይ ለህዝብ ተወካዮች ምክርቤት በሰጡት ማብራሪያ ፤ ግድቡ በመስከረም ወር እንደሚመረቅና፣ ፕሮጀክቱ ለቀጠናው ትብብር “ዕድል” እንጂ “አደጋ” እንደማይሆን በመጥቀስ፣ ከግብፅ ጋር ውይይት ለመቀጠል ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ቬትናም መዲና ሀኖይ አዲስ በረራ መጀመሩን ያስታወቀ ሲሆን፤ በረራው 28ኛው የእስያ መዳረሻ ነው ተብሏል፡፡
አየር መንገዱ ዛሬ ወደ ቬይትናም የጀመረው የበረራ አገልግሎት በእስያ 20ኛው መዳረሻ መሆኑን የተናገሩት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው፤ ከአፍሪካና ከእስያ ጋር በንግድና በቱሪዝም ጠንካራ ግንኙነትን ለማሳደግ ወሳኝ መሆኑንም ገልጸዋል።
አዲስ የተጀመረው የበረራ መስመር የሁለቱን ሀገራት የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ለማጠናከር እንደሚያግዝም ተጠቁሟል፡፡
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
ኦቪድ ሪል እስቴት ለገቢዎች ሚኒስቴርና ለጉምሩክ ኮሚሽን ሰራተኞች፣ ከ5ሺህ በላይ የመኖሪያ ቤቶችን ገንብቶ በተመጣጣኝ ዋጋ ለማቅረብ የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት በዛሬው ዕለት ግንቦት 22 ቀን 2017 ዓ.ም ከተቋማቱ አመራሮች ጋር ተፈራርሟል።
የኦቪድ ሆልዲንግ መስራችና ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ዮናስ ታደሰ፣ ኦቪድ ሪል ስቴትን በመወከል የመግባቢያ ስምምነቱን ከገቢዎች ሚኒስትር ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ እና ከጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ደበሌ ቀበታ ጋር የተፈራረሙ ሲሆን፣ ስምምነቱ የተቋማቱ ሰራተኞች ከኦቪድ ገላን ጉራ ከተማ ቤቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ በአማራጭ እንዲገዙ ያስችላል።
በኦቪድ ገላን ጉራ ከተማ የሽያጭ ማዕከል በተካሄደው የፊርማ ስነስርአት ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኦቪድ ሆልዲንግ መስራችና ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ዮናስ ታደሰ፤ የሁለቱም ተቋማት አመራሮችና ሰራተኞች ኦቪድን በመምረጣቸውና እምነት በመጣላቸው ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ስምምነቱ ኦቪድ የመኖሪያ ቤቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ የመንግስት ሰራተኞችን ለመደገፍ ያለውን ቁርጠኝነት እንደሚያሳይና ሁሉም የኦቪድ እህት ኩባንያዎች ተባብረው ቤቶቹን በጥራትና በፍጥነት ገንብተው እንደሚያስረክቡም ቃል ገብተዋል።
የገቢዎች ሚኒስትር ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ በበኩላቸው፤ የመኖሪያ ቤቶች አቅርቦት በመንግስት ጥረት ብቻ ሊሟላ የማይችል ጉዳይ መሆኑን ጠቁመው፣ ኦቪድ ሪል ስቴት እያከናወናቸው የሚገኙ የቤት ልማት ስራዎች በአብነት የሚጠቀሱ መሆናቸውን አመልክተዋል። ሰራተኞች ይህን ዕድል በአግባቡ እንዲጠቀሙና ገንዘባቸውን ከወዲሁ በመቆጠብ የቤት ባለቤት እንዲሆኑም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ምክትል ፕሬዚዳንት አትሌት መሰረት ደፋርን ያካተተ ልዑክ ቡድን አራተኛ ቀኑን በያዘው በ13ኛው የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታችና 4ኛው ከ18 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ ለመታደም ድሬዳዋ ገብቷል።
ከምክትል ፕሬዚዳንትዋ በተጨማሪ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የኢትዮጵያ አትሌቶች ማህበር ፕሬዚዳንት ሌተናል ኮሎኔል አትሌት የማነ ፀጋይና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጽ /ቤት ኃላፊ አቶ ዮሀንስ እንግዳ ድሬዳዋ ገብተዋል።
ድሬዳዋ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የድሬዳዋ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ዮናስ በትሩ፣ የድሬዳዋ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አህመድ አብዱና የድሬዳዋ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ ወይዘሮ ፅዮን በለጠ ደማቅ አቀባበል እንዳደረጉላቸው የፌደሬሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡
የፌስቡክ ገጻችንን ፎሎው በማድረግ የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ… የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…https://t.me/AdissAdmas
 
 
 
 
 
 
 
 
 
የስፔኑ ኃያል ክለብ ሪያል ማድሪድ ትሬንት፣ አሌክሳንደር አርኖልድን ማስፈረሙን ይፋ አድርጓል፡፡
አሌክሳንደር አርኖልድ በውድድር ዓመቱ መጨረሻ ከልጅነት ክለቡ ሊቨርፑል ለመልቀቅ መወሰኑን ከሣምንታት በፊት ማሳወቁ ይታወሳል፡፡
በወቅቱም፤ ራሱን በአዲስ ክለብና በተለየ ቦታ ለመፈተሽ በመፈለጉ ከሊቨርፑል ለመልቀቅ መወሰኑን በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አጋርቷል፡፡
ወደ አዲስ ክለብ መሄዱም ያለውን ሙሉ አቅም አውጥቶ እንዲጠቀም እንደሚያስችለው መግለጹ ይታወቃል፡፡
(ኤፍ ኤም ሲ)
የፌስቡክ ገጻችንን ፎሎው በማድረግ የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ… የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
"የተከበራችሁ ወዳጆቼና ጓደኞቼ፤ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ምክትል ዳይሬክተር ጄነራል በመሆን አዲስ ኃላፊነት ተሰጥቶኛል። በቃል አቀባይነት ኃላፊነቴ ወቅት ላደረጋችሁልኝ ድጋፍ አመሰግናለሁ።
የረዥም ጊዜ እረፍት ወስጄ በኢጋድ በኃላፊነት እንድሰራ በተለይ ክቡር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ለሰጡኝ ዕድልና እና ባልደረቦቼ ላሳዩኝ ፍቅር ከልብ አመሰግናለሁ። በቆይታዬ ብዙ ነገር ተምሬአለሁ።
ህይወት እንደ መጽሐፍ ነው። ብዙ ምዕራፎች አሉት። እኔም አዲስ ምዕራፍ በፈጣሪዬ ፈቃድ ጀምሬያለሁ፡፡ ከባልደረቦቼ ጋር በመሆን ኢትዮጵያ ከአፍሪካ አገሮች ጋር ያላት የዲፕሎማሲ ግንኙነት እንዲጠናከር እንሰራለን። መልካም የሳምንት መጨረሻ ይሁንልን። አመሰግናለሁ።"
የፌስቡክ ገጻችንን ፎሎው በማድረግ የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
 
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
በአዲስ አበባ ከተማ በተደረገ ምዘና 15 ሆቴሎች የኮከብ ደረጃቸውን የተነጠቁ ሲሆን፤ 11 ሆቴሎች ባለ አምስት ኮከብ ደረጃ ማግኘታቸውን ቱሪዝም ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
በሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የቱሪስት አገልግሎት ብቃት ማረጋገጥና ደረጃ ምደባ መሪ ሥራ አስፈፃሚ አቶ ታሪኩ ደምሴ፣ በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ ሆቴሎች ደረጃ ትናንት ይፋ ሲደረግ እንደተናገሩት፤ በ2017 ዓ.ም በሆቴሎች ላይ በተደረገው ዳግም ምዘና አገልግሎት ያቆሙ፤ በሌላ አገልግሎት ዘርፍ የተሠማሩና በምዘና ወቅት ተባባሪ ያልሆኑ 15 ሆቴሎች በተቀመጠው መመሪያ መሠረት፣ የኮከብ ደረጃቸው ሊነጠቅ ችሏል፡፡
በምዘና ወቅት ዲሚትሪ፣ ሲዮናት፣ ክራውን፣ አምባሳደር፣ ፓራማውንት፣ በሻሌ፣ ሐራምቤ፣ አስትራ ሆቴሎች አገልግሎት መስጠት ማቆማቸውን በመግለጻቸው፣ እንዲሁም 22 የሚገኘው እስቴይ ኢዚ ሆቴል፣ ሞዛይክ፣ ናርዳን፣ ሊ ማስተር ሆቴሎች የአገልግሎት ዘርፍ የቀየሩ በመሆናቸው የኮከብ ደረጃቸው መነጠቁን አስታውቀዋል፡፡
በተጨማሪም ዋቢ ሸበሌና ደሳለኝ ሆቴል ለምዘና ተባባሪ ባለመሆናቸው እንዲሁም ሲያቲን ሆቴል የስያሜና የባለቤትነት ለውጥ ያደረገ በመሆኑ የኮከብ ደረጃቸው ሊነጠቅ እንደቻለ አስረድተዋል፡፡
መሪ ሥራ አስፈጻሚው፤ በደረጃ ምዘናው ከውጭ ገጽታ ጀምሮ 12 መስፈርቶች በማስቀመጥ፣ 92 ሆቴሎች ላይ ምዘና የተደረገ መሆኑን አመልክተው፤ ይፋ የተደረገው የ40 ሆቴሎች ደረጃ ነው ብለዋል፡፡
ደረጃቸው ይፋ ከሆነ 40 ሆቴሎች 34 ሆቴሎች ዳግም ምዘና የተደረገላቸው እንደሆኑ ገልጸው፤ ስድስት አዳዲስ ሆቴሎች ወደ ኮከብ ደረጃ የገቡ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
በምዘናው መሠረት እስከ 30 በመቶ የተቀመጠውን መስፈርት ያሟሉ ሆቴሎች፣ በኮከብ ደረጃ ውስጥ መካተታቸውን በመግለጽ፤ ከ90 በመቶ በላይ መስፈርቱን ያሟሉ ሆቴሎች ባለ አምስት ኮከብ ያገኙ ናቸው ብለዋል፡፡
የኮከብ ደረጃ ያገኙ ሆቴሎች የኮከብ ደረጃቸው በሕጉ መሠረት ለሦስት ዓመት እንደሚያገለግል አስታውቀው፤ ነገር ግን ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ በሚያደርገው ደንገተኛና መደበኛ ክትትል ሆቴሎቹ ከደረጃ በታች አገልግሎት መስጠታቸው ከተረጋገጠ በማንኛውም ጊዜ የኮከብ ደረጃቸው የሚነጠቅ መሆኑን አመላክተዋል፡፡
ዳግም ምዘና ለተደረገላቸው ሆቴሎች ከምዘና በፊት ከአዲስ አበባ ባሕል፣ ቱሪዝም እና ስፖርት ቢሮ ጋር በመሆን የድጋፍና የቁጥጥር ሥራ እንደተደረገላቸው የተናገሩት አቶ ታሪኩ፤ በተደረገው ድጋፍ መሠረት ሆቴሎቹ ያሉባቸውን ክፍተቶች እንዲያሟሉ በቂ ጊዜ የተሰጠ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የዳግም ክትትል ሥራው በተቀመጠው አሠራር መሠረት እንዲከናወን ከክልል የተውጣጡ ባለሙያዎችን በማደራጀት መከናወኑን በመግለጽ፤ የምዘና ሥራውን ፍትሐዊ ለማድረግ ስድስት የሙያና የሆቴል ዘርፍ ማህበራት በታዛቢነት እንዲሳተፉ መድረጉን ጠቁመዋል፡፡
በምዘናው ላይ ቅሬታ የሚያቀርቡ ሆቴሎች በሚኒስቴሩ የተዋቀረ የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ አሠራር የተዘረጋ በመሆኑ ቅሬታቸውን ማቅረብ እንደሚችሉ አመላክተዋል፡፡
በኦሮሚያ፣ ሲዳማና በሌሎች ክልሎች የሚገኙ ሆቴሎች ምዘና የተጠናቀቀ መሆኑን ጠቁመው፤ በቀጣይ ባሉት ጊዜያት ይፋ እንደሚደረግም አመልክተዋል፡፡ ከሆቴሎች በተጨማሪ የሎጆችና ሬስቶራንቶች ምዘና ስለተጠናቀቀ በቀጣይ ደረጃቸው ይፋ ይደረጋል ሲሉ ገልጸዋል፡፡
(ጋዜጣ+)
የፌስቡክ ገጻችንን ፎሎው በማድረግ የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ… የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…

 አርቲስት ኪሮስ ኃ/ሥላሴ ከ1975 ጀምሮ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በትያትር ጥበባት በቢኤ ዲግሪ ተመርቆ ሀገር ፍቅር ቴአትር ተመደበ። የወጣትነቱንና ጉልምስና እድሜውን በዚያ አሳለፈ። ሀገር ፍቅር ቴአትር ለኪሮስ ኃ/ሥላሴ መ/ቤቱ ብቻ ሳይሆን ትዳሩም ሕይወቱም ጭምር ነው። ከባለቤቱ አርቲስት ፀዳለ ግርማ ጋር ትዳር የመሰረተውና ልጆች ያገኘው ከሀገር ፍቅር ቴአትር ነው።
ኪሮስ ኃ/ሥላሴ ከመደበኛው ስራ ጡረታ ይውጣ እንጂ ዛሬም ሀሳብና ውሎው፣ ማህበራዊ ሕይወቱ ሀገር ፍቅር ቴአትር ነው። “ሳልሳዊው ባልንጀራ” ፣ “የቬኑሱ ነጋዴ “ ፣ “ናትናኤል ጠቢቡ” ፣ “ጣውንቶቹ “ ፣ “አሉ” ፣ “ባልቻ አባነፍሶ” ን የመሳሰሉ ትያትሮች ላይ በተዋናይነት ተሳትፏል። በርካታ ፊልሞችና የቴሌቪዥን ድራማዎች ላይ ተውኗል። ሀገር ፍቅር ቴአትር እና የአዲስ አበባ ባሕልና ቱሪዝም ቢሮን በተለያዩ ጥበባዊ ሀላፊነቶች መርቷል። በሚሊኒየሙ ጊዜ የአዲስ አበባ ሚሊኒየም ጽ/ቤትን በሊቀመንበርነት መርቷል።
ኪያ ወደ ሀገር ፍቅር ቴአትር የተመደበበት ወቅት አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በትያትር ጥበባት በመጀመሪያ ዲግሪ ማስመረቅና በየጥበብ ቤቶች መመደብ የጀመረበት ወቅት ስለነበረ፣ በወቅቱ በነባሮቹ አንጋፋ የጥበብ ሰዎችና በወጣቶቹ ምሩቃን መካከል የተፈጠረውን መጓተት ለማርገብና ዘመናዊውን እውቀት በልምድ ከካበተው ችሎታ ጋር አቀናጅቶ ለመስራት የኪሮስ ሚና ትልቅ ነው።
 በአዲስ አበባ ባሕልና ቱሪዝም ኃላፊነቱ ወቅትም ወጣቶች የተለያዩ የትያትር ክበባትና ኢንተርፕራይዞች ተደራጅተው ተሰጥኦዋቸውን ወደ መድረክ እንዲያመጡ የኪያ አበረታች አቀራረብ ግዙፍ ነው። ከወጣቶች ጋር እንደ ወጣት፣ ከአዛውንቶቹ ጋርም እንደ እነሱ መሆን የሚችል በሁሉም የተወደደና የተመሰገነ ብቁ የጥበብ ሰው ነው። በዚህም “ኪሮስ” የሚለው ስሙ ቀርቶ በወዳጆቹ ዘንድ “ኪያ” መጠሪያ ስሙ ሆኗል።
ተስፋ የኪነጥበብ ኢንተርፕራይዝ እና የኪሮስ ኃ/ሥላሴ ልጆች ሕብረት ፈጥረው በዛሬው ዕለት  መጋቢት 27 ቀን 2017 ዓ.ም  ከቀኑ 9:30 ሰዓት ጀምሮ በሀገር ፍቅር ቴአትር አዳራሽ ደማቅ የክብርና የምስጋና መርሐ ግብር አዘጋጅተውለታል።
በመርሃ ግብሩም፦
ሙዚቃ (በሀገር ፍቅር ቴአትር እና መሐሪ ብራዘርስ ባንድ) ከታዋቂ ድምጻውያን ጋር፤ በስሙ የተዘጋጀና በታዋቂ ተዋንያን የሚቀርብ አጭር ድራማ፤ በፖሊስ ሰራዊት የማርሽ ባንድ ልዩ ልዩ ጣዕመ ዜማዎች፤ ዶኩመንታሪ (ሕይወቱንና ስራዎቹን የሚዘክር) እና ሌሎች መርሐ ግብሮች ይቀርባሉ።
የአርቲስት ኪሮስ ኃ/ሥላሴ ወዳጆችና አድናቂዎች በሰዓቱና በቦታው ተገኝታችሁ ኪያን በጋራ እንድናመሰግነውና እንድናከብረው፣ ልጆቹ እና ተስፋ የኪነጥበብ ኢንተርፕራይዝ በአክብሮት ጋብዟችኋል፡፡



 የተረት - አባት የሆነው ኤዞፕ እንዲህ ይለናል፡፡
ከእለታት አንድ ቀን ተኩላዎች ተመካከሩና መልክተኞች ወደ በጎች ላኩ፡፡
የተኩላዎቹ ልዑካን እበጎች መንደር ደረሱ፡፡ በጎች ተኩሎች መጡብን ብለው ተሸሸጉ፡፡ አድፍጠው ጋጣቸው ውስጥ አድብተው ተቀመጡ፡፡ ተኩሎቹ ግን ረጋ ብለው፣ አደብ ገዝተው፣ “በጎች አትደንግጡ፤ እንደምን ዋላችሁ” አሉ፡፡
“ለድርድር ነው የመጣነው” አሉ ተኩሎቹ፡፡
በጎቹ ቀስ በቀስ ከተደበቁበት ወጡ፡፡
“እኛ በድርድር እምናለን”
“እህስ? ምን እግር ጥሏችሁ መጣችሁ? ምን የድርድር ሃሳብ ይዛችሁ መጣችሁ” አሉ በጎች
“አንድ የቸገረ ነገር ገጥሞን ነበርና ልናዋያችሁ ፈልገን ነው”
“ምንድነው? ከተመካከርን የማይፈታ ምንም ነገር አይኖርም፡፡ ዋናው ተቀራርቦ መነጋገር ነው፤ ንገሩን፡፡”
ተኩሎችም፤
“እግዚአብሄር ይስጥልን፡፡ የቸገረን ነገር ምን መሰላችሁ? ይኸው ከተፈጠርን ጀምሮ ከውሾች ጋር ነጋ- ጠባ  እንታገላለን፡፡ የችግራችን መነሻም መድረሻም ውሾች ናቸው፡፡ እርኩስ ውሾች እኛን ባዩ ቁጥር ይጮሃሉ፡፡ ይተነኩሱናል፡፡ ሰፈር ይረበሻል፡፡ ለእኛና ለእናንተ ወዳጅነትና ሰላም  ዋናዎቹ እንቅፋቶች ውሾች ናቸው፡፡”
በጎችም፤
“ታዲያ ምን እናድርግ? ምን ዘዴ ብንፈጥር እንቅፋቶቹን ማስወገድ እንችላለን”
ተኩሎችም፤
“እናንተ እሺ ካላችሁማ ዘዴ አይጠፋም ነበር”
“እኮ ዘዴ ካለ ንገሩና?”
“ለጌታችሁ ንገሩ፡፡ ውሾች እንዳልተመቿችሁ ሰላምም እንደነሷችሁ አስረዱ፡፡ ይባረሩልን በሉ”
“ይሄማ ቀላል ነው፡፡ እንነግረዋለን”
በዚህ ተስማሙና ተኩሎቹ ሄዱ፡፡
በጎቹ ውሾቹ እንዲባረሩ ለጌታቸው አመለከቱ፡፡ ጌታቸውም ስንት ዘመን ቤት ደጁን ሲጠብቁ የኖሩትን ውሾች ከቤት አስወጥቶ አባረራቸው፡፡
ከዚያን ቀን በኋላ የዋሆቹ በጎች የዘመናት ጠባቂዎቻቸውን አጡ፡፡ ተንኮለኞቹ ተኩሎች እየተዝናኑ፣ በጎቹን አንድ በአንድ እየለቀሙ፣ በሏቸው፡፡
***
የድርድርን ትርጉም አለማወቅ እርግማን ነው፡፡ ከማን ጋር ነው የምደራደረው? ተደራዳሪዩስ ሊደራደረኝ ያሰበው ምን አስቦ ነው? ጠላቴ እንኳ ቢሆን ድርድሩ ያዋጣኛል ወይ? ከቅርብ ጊዜ ግቤ አንፃር ምን እጠቀማለሁ? ከዘላቄታ ግቤ አንፃርስ ምን እጠቀማለሁ? ትላንትና ምን ዓይነት ግንኙነት ነበረኝ? ዛሬስ? ዛሬን በዛሬው ክስተት መዳኘት እንዴት እችላለሁ? ብሎ ማሰብ የአባት ነው፡፡
 በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት የአሜሪካው ጄኔራል ማካርተር በፈሊፒንስ የአሜሪካ ጦር አዛዥ ተደርጎ ሲሾም አንድ ረዳት መኮንን አንድ መጽሐፍ ይሰጠዋል፡፡ መጽሐፉ ከዚህ ቀደም የነበሩት አዛዦች የተዋሉባቸውን ጦርነቶች ዝርዝር የያዘ ነው፡፡ ማካርተር “የዚህ መጽሐፍ ስንት ቅጂ አለ?” ብሎ ጠየቀው፡፡ ረዳቱም፤ “ስድስት አለ” አለው፡፡ ጄኔራሉም፤ “መልካም፤ በል ስድስቱንም መጻሕፍት ሰብስበህ አቃጥልልኝ፡፡ እኔ የትላንትና ውሎዎች ባሪያ መሆን አልፈልግም፡፡ ችግር ሲከሰት እዛው ወዲያውኑ መፍትሄ እሰጠዋለሁ፡፡ መጽሐፍቱን በሙሉ አቃጥልና ሁኔታዎች በተከሰቱ ሰዓት እንደ ሁኔታው ግዳጅህን ፈጽም” አለው፡፡ ታሪክ የራሱ ዋጋ ቢኖረውም ይህንን እንደ ተመክሮ መውሰድ ተገቢም ደንብም ነው፡፡ በትላንት ለመመካት ከሆነ ግን የግብዝ አመድ- አፋሽ መሆን ነው!
“ነበርን ማለት ግን ከንቱ ነው፤ ተውነው መጀነኑ በቅቶን
ጉራ መንዛት መዘባነን፣ የሚያዛልቅ ዘዴ ባይሆን” ይለናል ኦቴሎ የሼክስፒሩ፣ በፀጋዬ ገ/መድህን ብዕር ልሳን! ስለታሪክ ስለትላንት ማውራት ሳይሆን ዛሬን ማሸነፍ ነው የፖለቲካ ፋይዳው፡፡ ይሄን ያወቁ ላቁ! ይሄን የናቁ ወደቁ! እንደማለት ነው፡፡
ከ1966 ጀምሮ የተከሰቱ የሀገራችን የፖለቲካ ፓርቲዎች አበሳዎች፣ እከሌ ከእከሌ ሳይባል በትንሹ አስር መሰረታዊ ጉዳዮች ላይ የተንተራሱ ይመስላሉ፡፡ ከአበሳዎቹ አንደኛው/በትንሽ በትልቁ መከፋፈል፣ ያለመስዋእትነት ድል መመኘት፣ ውሎ አድሮ ጧት የማሉበትን ማታ መካድ፡፡ “ዕምነት ሲታመም ሺ ወረቀት መፈራረም” ነው፡፡ 2ኛው/ለባላንጣቸው ሰርጎ - ገብነት መጋለጥ ነው፡፡ 3ኛው /እርስ በርስ አለመከባበር፣ አለመተሳሰብ፡፡ 4ኛው/ የመስመር ጥራት አለመኖር፤ ርዕዮተ-ዓለማዊ ብስለት ማጣት፡፡ 5ኛው/በትንሽ ድል መወጣጠርና በትንሽ ሽንፈት መፍረክረክ፡፡ 6ኛው/ተጋጣሚን መናቅና ወሬን /አሉባልታን እንደ አቋም መውሰድ፡፡ 7ኛው/ የጊዜን ፋይዳ በትክክል መረዳት፣ ባልፈውስ? አለማለትና የኃይል ሚዛን የማን ነው አለማለት፣ ከተፈፀመም አለመመዘን፣ ይሄ ዓላማ ባይሳካ ምን ሁለተኛ ዘዴ ቀይሻለሁ? ብሎ አለመዘጋጀት፡፡
8ኛው/ ባለፈው ያደረግነው የት አደረሰን? ታሪኩ ተተንትኖ ተገምግሞ ሳያልቅ በነዚያው ተዋንያን ተውኔቱ መቀጠሉ 9ኛው/ እምቢ አላረጅም ማለት ነው፡፡ አዲሱ ያሸንፈኛል አለማለት “the new is invincible የሚለውን መርሳት፤ “ካፈርኩ አይመልሰኝ” ማለት፡፡ 10ኛው/እኔ ባልሆንስ መፍትሄው? ሌላ ቢኖርስ? ከኔ የተሻለ አለ ብሎ ፈጽሞ አለማሰብ!
ከነዚህ ሁሉ ይሰውረን፡፡ እነዚህን ሁሉ ከልብ ከመረመርን ፓርቲዎቹ ሁሉ የቆሙት በአንድ ወይም በሁለት ቡድን ህብለ ሰረሰር (Spinal cord) ዙሪያ ነው፡፡ ይሄ እንግዲህ የሚሆነው
“ከተኳሾቹም - አሉ በልዩ
ማህል - አገዳ የሚለያዩ”
በምንልበት አገር ነው፡፡ ከፖለቲካ ንቃት- ባህሉ (ትምክህቱ፣ ጥበቱ፣ ዕምነቱ፣ የፖለቲካ ጥንቆላው፣ ሟርቱ ወዘተ) ባለበት አገር ልማድን አለመመርመር ጦሱ ብዙ ነው፡፡ አጠቃላይ የፖለቲካ ተመክሮአችን ገና አልተፈተሸም፡፡ “ዳሩ ሲነካ መሀከሉ ዳር ይሆናል” ይላል ያበሻ አባባል፡፡ ዞሮ ዞሮ ግን ግንዱ ሲመታ ቅርንጫፉና ቅጠሉ መርገፉ አይቀሬ ነው፡፡ ቻይናዎቹ “ዛፉ ሲወድቅ ዝንጀሮዎቹ ይበተናሉ” የሚሉን መሰረታዊ ነገር የሚሆነው ለዚህ ነው፡፡ “ቁልቋል የወደቀው ቅርንጫፍ ስላበዛ ነው” የሚለውም የትግሪኛ ተረት አዙረን ስናየው እንደ ቻይናዎቹ ነው፡፡


 “ዳግላስ ጴጥሮስ” በሚለው የብዕር ስሙ የሚታወቀውና በርካታ መጣጥፎችን ያስነበበው ደራሲ ጌታቸው በለጠ፤ ‘የትዝታዬ ማሕደር’ በሚል ርዕስ ያዘጋጀውን  በሕይወቱ ዙሪያ የሚያጠነጥን መጽሐፍ በመጪው ሳምንት  መጋቢት 5 ቀን 2017 ዓ.ም  ያስመርቃል፡፡
የጌታቸው በለጠ ግለ-ታሪክ  መፅሐፍ በ448 ገፆች የተቀነበበ  ሲሆን፤ ከልጅነት እስከ ዕውቀት ያሳለፈውን ሕይወቱን  የሚተርክ  ነው ተብሏል፡፡  ‘የትዝታዬ ማሕደር’  በ1ሺ ብር ለገበያ የቀረበ  ሲሆን፤ በምረቃ ሥነስርዓቱ  ላይ ታዋቂ ደራሲያንና የቅርብ ወዳጆቹ ንግግር እንደሚያደርጉ ይጠበቃል፡፡ ከእነዚህም መካከል  ዶ/ር ንጉሴ ተፈራ፣ ደራሲ አበረ አዳሙ፣ ደራሲ ኃይለመለኮት መዋዕል፣ጋዜጠኛ ጥበቡ በለጠና ሌሎችም ይገኙበታል፡፡ ደራሲ ጌታቸው በለጠ፣ የደራሲያን ማህበር ፕሬዚዳንት በመሆን ያገለገለ ሲሆን፤ በማህበራዊና  ኪነ ጥበባዊ  ሂሶቹም ይታወቃል፡፡

Page 1 of 762