Administrator

Administrator

 የፖለቲካ ሹመኞች በሙያተኞች ላይ በሚያሳድሩት ጫና የመንግሥት ሥራ እየተደናቀፈ ነው ሲሉ በተለያዩ የመንግስት ተቋማት ውስጥ የሚሰሩ ባለሙያዎቹ ለአዲስ አድማስ ተናገሩ። በብዙዎቹ የመንግስት መ/ቤቶች ሃላፊዎች ሥልጣን ላይ የሚቀመጡት በፖለቲካ ታማኝነት እንጂ በዕውቀትና በብቃት ባለመሆኑ በሙያተኞች ላይ የሚያሳድሩት ጫና ሥራውንም ባለሙያውንም እየጎዳው መሆኑንም ያስረዳሉ። እየጎዳው ነው ተብሏል፡፡
በአንድ የመንግስት መ/ቤት ውስጥ በከፍተኛ ኤክስፐርትነት የሚሰሩት ግሩም ኤሊያስ (ዶ/ር) የተባሉ ግለሰብ ለአዲስ አድማስ እንደተናገሩት፤ በመ/ቤቱ ውስጥ  በከፍተኛ ኤክስፐርትነት ቢቀጠሩም፣ በሃላፊነት የተመደበው ዋና ሥራ አስፈጻሚ የፖለቲካ ሹመኛ በመሆኑ ሙያተኞች ሥራቸውን በቅጡ መስራት አልቻሉም ብለዋል።
እንደ ኤክስፐርቱ ገለፃ፣ ለሀገር ይጠቅማል ብለን የምናጠናው ጥናት፣ የምናቅደው ስትራቴጂክ ዕቅድ በሙሉ በዋና ስራ አስፈጻሚው ውድቅ ይደረጋል። የተሻለ ሀሳብ አይቀርብም፣ የተለፋበት ጥናትና እቅድ መና ይቀራል፡፡ እኛ ግን ከፍተኛ ደሞዝ እየተከፈለን ቀጥለናል። ይህ ደግሞ ህሊና ላለው ሰው ከባድ ነው ብለዋል፤ ግሩም ኤልያስ (ዶ/ር)።
ለደህንነታቸው ሲሉ የመስሪያ ቤታቸው ስም እንዳይጠቀስ የፈለጉት እኚህ ከፍተኛ ኤክስፐርት፤ በሥራ ባልደረቦቻቸው ዘንድ በማያምኑበት ጉዳይ ሁሉ ከአለቃቸው በመቃወም የሚታወቁ ሲሆን በዚህም ሳቢያ ከአንዴም ሶስት ጊዜ በዲሲፕሊን ጥሰት የደሞዝ ቅጣት፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ ከደረጃ ዝቅ የመደረግ ዕጣ ፈንታ እንደገጠማቸው ለአዲስ አድማስ ገልፀዋል።
ግሩም ኤርምያስ ላለፉት ዓመታት ሲሰሩ በቆዩበት መስሪያ ቤት፣ ሥራቸውን በብቃትና በትጋት ከሚሰሩ ኤክስፐርቶች  ይልቅ ለበላይ አካል ወሬ የሚያቀብሉና የሚላላኩ፣  የመስሪያ ቤቱ “ቁንጮ ሰራተኞች” ተብለው ይሸለማሉ፣ ደሞዛቸው ያድጋል ይመነደጋል፤ የደረጃ እድገትም ያገኛሉ መንግስት ይህን፤ አገርንም ህዝብንም የሚጎዳና እድገትን የሚጎትት የፖለቲካ ሹመኞች ፈላጭ ቆራጭነት በጊዜ ማስተካከል ካልቻለ፣ አገር ወደፊት መራመድ አትችልም ብለዋል። እርሳቸው በሙያቸው አገር ማገልገል ስላለባቸው ወደ ግል ተቋማት እያማተሩ መሆኑንም ገልፀዋል፡፡
ሌላው በኢትዮ ቴሌኮም በከፍተኛ ባለሙያነት የሚሰራው ዘሪሁን አማን (ስሙ ተቀይሯል) የተባለ ወጣት ኤክስፐርት በበኩሉ፤ ከደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ ዩኒቨርሲቲ ሁለተኛ ዲግሪውን ይዞ ወደ ሀገሩ መመለሱን ይናገራል። በለውጡ ሰሞን በኢትዮ ቴሌኮም የተቀጠረው ይሄው  ወጣት ባለሙያ፤ ለውጡ የመጣ ሰሞን የነበረውን ተስፋና የለውጡ መንግስት ሥልጣን በያዘ ሰሞን በአገሪቱ የተስተዋለውን መነቃቃት በመተማመን ሀገሩን ለማገልገል ወጣትነቱን፣ ትኩስ ጉልበቱንና እውቀቱን ይዞ ወደዚህ መስሪያ ቤት መግባቱን ገልጿል።
በተለይ የመሥሪያ ቤቱ ዋና ስራ አስፈጻሚ ወይዘሪት ፍሬህይወት ከተሾመች በኋላ ኢትዮ ቴሌኮም ብዙ ፈጣን ለውጦችን እንዲሁም አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን  ማስተዋወቁን የሚናገረው ወጣቱ፤ ከሃላፊዋ ስር ያሉ የፖለቲካ ሹመኞች ግን ተቋሙ የበለጠ እድገት እንዳያስመዘግብ ሙያተኞች ላይ የሚያሳድሩት ጫና ከፍተኛ ነው ይላል በምሬት። “ለሙያውና ለቴክኖሎጂው ያለኝን ቅርበትና የውጪ ተሞክሮዎችን በመጠቀም ተቋሙ የሌላው አገር ቴሌኮሙኒኬሽን የደረሰበት ደረጃ ላይ እንዲደርስ ሌት ተቀን የማደርገው ጥረት ለአለቃዬ ምቾት አይሰጠውም፣ ያለው ወጣቱ፤ ከፍተኛ ኤክስፐርት፤ ይህም በሀገሬ በሙያዬና በአጠቃላይ ባለው በሁኔታ መሰላቸትና ተስፋ መቁረጥ ውስጥ እያስገባኝ ነው ብሏል።
ወጣቱ አክሎም፤ ቢያንስ የፖለቲካ ሹመኞች የፖለቲካ ታማኝነታቸው እንዳለ ሆኖ ለሚመሩት መስሪያ ቤትና የስራ ጠባይ ቢቻል ሙያውን የተማሩና በዘርፉ እውቀት ያላቸው፣ ካልተቻለ ተቀራራቢ ሙያ ውስጥ ያሉ ቢሆኑ አገርን ከዘርፈ ብዙ ችግር መታደግ ስለሚችል መንግስት ጉዳዩን ያስብበት ጥሪ አቅርቧል።

 • ገዳሙን ለመታደግ 100 ሚ.ብር ያስፈልጋል


        ለአቡነ ሐራ ድንግል አንድነት ገዳም፣ በዛሬው ዕለት ከቀኑ 10  ሰዓት ጀምሮ፣ በካፒታል ሆቴል ዓለማቀፍ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃግብር የሚካሄድ ሲሆን፤ገቢው በገዳሙ ይዞታ ላይ ለሰፈሩ ነዋሪዎች ካሣ በመክፈል ይዞታውን ለገዳሙ ለማስመለስ ነው ተብሏል፡፡ የገዳሙ ገቢ ማሰባሰቢያ ኮሚቴ እንደገለጸው፤ ገዳሙን ለመታደግና ለማስፋፋት በአጠቃላይ 100 ሚሊዮን ብር ያስፈልጋል፡፡
 ገዳመ ወንያት አቡነ ሐራ ድንግል የአንድነት ገዳም፣ በ1574 የተመሰረተና የጻዲቁ አባት አቡነ ሐራ ድንግል ገድልና ገቢረ ተዓምራት የሚካሄድበት ገዳም ነው - ይላሉ የገዳሙ መነኮሳት፡፡
ከ400 ዓመት በላይ ታሪክ ያለው ይህ ትልቅ ገዳም በሰሜን ጎጃም፣ ባህርዳር ዙሪያ የሚገኝ ሲሆን፣ ጻዲቁ አቡነ ሐራ ድንግል፣ ከፈጣሪያቸው በተገባላቸው ቃልኪዳን መሠረት፣ ደዌን ሲፈውሱና ተዓምራትን ሲሰሩ የቆዩበትና አሁንም የሚሰሩበት ጥንታዊ ገዳም መሆኑን፣ የገዳሙ ገቢ አሰባሳቢ ኮሚቴ ባወጣው  መግለጫ ጠቁሟል፡፡ ይሁን እንጂ ይህ ገቢረ ተዓምር የሚሰራበት ታሪካዊ ገዳም፣ ትልቅ ችግር እንደተጋረጠበት መነኮሳቱ ተናግረዋል፡፡
“ለፈውስና ለድህነት ከመላው አገሪቱ ወደ ገዳሙ የሚመጡ ምዕመናን ድህነትና ፈውስ ካገኙ በኋላ፣ ገዳሙን ተጠግተው ቤት በመሥራት እዚያው እየኖሩ፣ ገዳሙ ይዞታውን እየተነጠቀ ከመጣበቡም በላይ፣ የገዳሙን ቅድስና የሚያረክሱ ተግባራት እየተፈጸመበት ይገኛል፡፡”  ይላል፤ የኮሚቴው መግለጫ፡፡
የገዳሙ መነኮሳት የታሪክ ዶሴና ማስረጃ ላይ ተንተርሰው እንደሚናገሩት፤ ዓጼ ዮሐንስ በነቀርሳ ተይዘው በአቡነ ሐራ ድንግል ጸበል በመዳናቸው ነበር ለገዳሙ የአንድ ሰዓት የእግር መንገድ ያህል ስፋት ያለው ቦታ ለገዳሙ የሰጡት፡፡ ደርግ ሥልጣን ሲይዝ በገዳሙ 800 የሚደርሱ መናንያን እንደነበሩ የሚያስታውሱት መነኮሳቱ፤ በወቅቱ “መሬት ላራሹ” የሚል አዋጅ በመታወጁ የገዳሙን ይዞታ አርሶ አደሮች እየተቆጣጠሩት እንደመጡና መናንያኑ ገዳሙን ጥለው መኮብለላቸውን ያስረዳሉ፡፡
በአሁኑ ወቅት በገዳሙ ይዞታ ላይ ከ250 በላይ አባወራዎች ሰፍረው እንደሚገኙ የሚገልጹት መነኮሳቱ፤ ይህን ችግር ለመቅረፍ ለመንግሥት በተደጋጋሚ አቤቱታ ካቀረቡ በኋላ፣ መንግሥት ነዋሪዎቹን አንስቶ ሌላ ቦታ ለማስፈር ፈቃደኛ ቢሆንም፣ ለነዋሪዎች ካሣ ለመክፈል በጀት እንደሌለው በመግለጽ፣ ገዳሙ ካሣውን እንዲከፍል መወሰኑን ይናገራሉ፡፡
ሆኖም የሚከፈለው ካሣ ከገዳሙ አቅም በላይ በመሆኑ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃግብር ማዘጋጀት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል የሚለው  የገዳመ ወንያት አቡነ ሐራ ድንግል አንድነት ገዳም የገቢ ማሰባሰቢያ ኮሚቴ፤ ባለፈው ሐሙስ  በጠቅላይ ቤተክህነት አዳራሽ፣ ስለ ገዳሙ አሁናዊ ሁኔታና ስለ ገቢ ማሰባሰቢያ   መርሃ ግብሩ  ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል፡፡
በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ እንደተነገረው፣ የአማራ ክልል ካቢኔ ለገዳሙ ሁሉንም ይዞታውን ባይሆንም 60 ሄክታር የሚደርስ ቦታ እንዲመለስለት የወሰነ ሲሆን፤ ገዳሙ በበኩሉ ለአርሶ አደሮቹ የሚገባቸውን የመሬት ካሣ መክፈል ይጠበቅበታል፡፡  ይህን የመሬት ካሣ ለመክፈልና ለገዳሙ የማስፋፊያ ልማት ለማከናወን፣ ዛሬ  ቅዳሜ ሚያዝያ 19 ቀን 2016 ዓ.ም በካፒታል ሆቴል፣ በቀጥታ የቴሌቪዥን ሥርጭት፣ ከቀኑ 10 ሰዓት ጀምሮ እስከ ሌሊቱ 6 ሰዓት የሚቆይ  ዓለማቀፍ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃግብር እንደሚያካሂድ  ኮሚቴው  አስታውቋል፡፡ ለአርሶ አደሮቹ የመሬት ካሣውን ለመክፈልና የገዳሙ ይዞታ ከተለቀቀ በኋላ በሥፍራው ለሚከናወኑ ልማቶች በአጠቃላይ 100 ሚሊዮን ብር እንደሚያስፈልገው የገለጸው የገቢ አሰባሳቢ ኮሚቴው፤ በመላው ዓለም የሚገኙ የቤተክርስትያን ልጆችና የጻድቁ አቡነ ሐራ ወዳጆች በዚህ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር ላይ በንቃትና በትጋት እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርቧል፡፡
በአሁኑ ወቅት በገዳሙ የሚገኙ መናንያን ቁጥር 5ሺ እንደሚደርሱና በጾም ወቅት የጸበልተኛው ቁጥር ከ50 ሺ በላይ መሆኑን የጠቆመው  የገቢ አሰባሳቢ ኮሚቴው፤ እኒህን ሁሉ በአግባቡ የሚያስተናግድ በቂ መጠለያና የልማት ሥራዎች ማከናወን አስፈላጊ እንደሆነ በአጽንኦት ተናግሯል፡፡


ስብሐቲዝም የሀሳብ ውይይት የፊታችን እሁድ ሚያዝያ  20 2016 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ በኢትዮጵያ ቤተመዛግብት እና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት(ወመዘክር) አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል።

"የሕላዌ እንቆቅልሽ " የተሰኘ መጽሐፍ ነገ ይመረቃል

የደራሲ ማንደፍሮ ማሩ "የሕላዌ እንቆቅልሽ" የተሰኘ አዲስ መጽሐፍ ቅዳሜ ሚያዝያ 19 2016 ዓ.ም ከቀኑ 10:00 ጀምሮ በወመዘክር አዳራሽ ይመረቃል።

በደራሲ ባየህ ንጉሴ የተዘጋጀው “ፋሽን” የተሰኘ በፋሽን እና ሞዴሊንግ ላይ ትኩረቱን ያደረገ መጽሐፍ ቅዳሜ ሚያዝያ 19/2016 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ጀምሮ የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር) አዳራሽ ጥሪ የተደረገላቸው
የጥበብ ቤተሰቦች እና እንግዶች በተገኙበት ይመረቃል ይመረቃል።በስድስት ምዕራፍ የተከፈለው መጽሐፉ ስለ ሞዴሊንግ አይነቶች፣ ሞዴል የመሆን ትሩፋቶች እና ተግዳሮቶች፣ የቁንጅና ውድድር፣ ሻምፖ እና ኮድሽነር አመራረጥ፣ ፖርትፎሊዮና ሌሎችም ዝርዝር ጉዳዮችን ይዟል።

ዘመን ባንክ የሠራተኞቹን ዕውቀትና ክህሎት ለማሳደግ፣ በዓለም  ትልቁ የኢንተርኔት የመማሪያ መድረክ ከሆነው ሊንክድኢን ሊርኒንግ ጋር የአጋርነት ስምምነት ተፈራረመ፡፡

የዘመን ባንክ የሰው ሀብት ምክትል ዋና ኦፊሰር አቶ ታከለ ዲበኩሉ ስለ ስምምነቱ ሲገልጹ፤ “ዘመን ባንክ ለሰራተኞቹ ቀጣይነት ያለው የመማርና የሙያ እድገት ባህልን ለማሳደግ ቁርጠኛ ነው። ከሊንክድኢን ለርኒንግ ጋር ያደረግነው ስምምነት፣ ይህንን ቁርጠኝነት የሚያጎላ ከመሆኑም በላይ ሠራተኞቻችን በፋይናንስ ዘርፉ የሚጠይቀውን ችሎታ፣ እውቀትና ክህሎት እንዲያሳድጉ የሚረዳ ነው፡፡" ብለዋል፡፡

የሊንክድኢን ታለንት ሶሉዩሽን ዋና ኃላፊ ማቲው ግሬይ በበኩላቸው፤ ”ከዘመን ባንክ ጋር ያደረግነው ስምምነት የሰራተኞቹን የክህሎትና የእውቀት ክፍተቶችን ለማሟላት እድሉን የሚሰጠን ከመሆኑም በላይ ሊንክድኢን ለርኒንግ በአፍሪካ ተመራጭ የክህሎት ልማት መድረክ ሆኖ  መቀጠሉን ስለሚያሳይ እጅግ ተደስተናል። የዘመን ባንክ የሰው ሃብት ስትራቴጂ በቀጣይ አመታት ይበልጥ እንዲጎለብትና ውጤታማ እንዲሆን አብረን እንሰራለን።" ብለዋል፡፡

የእነዚህ ኮርሶች ወጪ ሙሉ በሙሉ በዘመን ባንክ የተሸፈነ ሲሆን፤ የባንኩ ሠራተኞች ሥልጠናውን  በነፃ እንደሚያገኙ  ታውቋል፡፡

ኢንጂነር ቢጃይ ናይከር ግማሽ ሚሊዮን (500ሺህ) ብር፣
ድምፃዊ ዳዊት ፅጌ 100ሺ ብር በመስጠት ጀምሯል ደጋግ ኢትዮጵያውያኖች የአቅማችሁን በማድረግ የትዕግስት ሶስት መንታ ልጆች የአይን ብርሃናቸው እንዲመለስ የበኩላችንን እናድርግ።
ሼር በማድረግ እንጀምር!
አካውንታቸው ይህው እባካችሁ
ሼር አድርጉት
* СВЕ 1000622473872
* Dashen Bank 5563671317021
* Abyssinia bank 91613069
* ኦሮሚያ ኅብረት ስራ ባንክ 1023500172828
* አዋሽ ባንክ 013471254339600
ትግስት ካሳ ቀፀላ
ስልክ
* 0911868306
* 0911137097
go fund me
ይህን ሼር ማድርግ መልካም ነገር መስራት ነውና እባካችሁ ሼር አድርጉላቸው
• ገዳሙን ለመታደግ ቅዳሜ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃግብር ይካሄዳል
ገዳመ ወንያት አቡነ ሐራ ድንግል የአንድነት ገዳም በ1574 የተመሰረተና የጻዲቁ አባት አቡነ ሐራ ድንግል ገድልና ገቢረ ተዓምራት የሚካሄድበት ገዳም ነው - ይላሉ የገዳሙ መነኮሳት፡፡
ከ400 ዓመት በላይ ታሪክ ያለው ይህ ትልቅ ገዳም በሰሜን ጎጃም፣ ባህርዳር ዙሪያ የሚገኝ ሲሆን፣ ጻዲቁ አቡነ ሐራ ድንግል፣ ከፈጣሪያቸው በተገባላቸው ቃልኪዳን መሠረት፣ ደዌን ሲፈውሱና ተዓምራትን ሲሰሩ የቆዩበትና አሁንም የሚሰሩበት ጥንታዊ ገዳም መሆኑን፣ የገዳሙ ገቢ አሰባሳቢ ኮሚቴ ያወጣው መግለጫ ይጠቁማል፡፡
ይሁን እንጂ ይህ ገቢረ ተዓምር የሚሰራበት ታሪካዊ ገዳም፣ ትልቅ ችግር እንደተጋረጠበት መነኮሳቱ ተናግረዋል፡፡
“ለፈውስና ለድህነት ከመላው አገሪቱ ወደ ገዳሙ የሚመጡ ምዕመናን ድህነትና ፈውስ ካገኙ በኋላ፣ ገዳሙን ተጠግተው ቤት በመሥራት እዚያው እየኖሩ፣ ገዳሙ ይዞታውን እየተነጠቀ ከመጣበቡም በላይ፣ የገዳሙን ቅድስና የሚያረክሱ ተግባራት እየተፈጸመበት ይገኛል፡፡” ይላል፤ የኮሚቴው መግለጫ፡፡
የገዳሙ መነኮሳት የታሪክ ዶሴና ማስረጃ ላይ ተንተርሰው እንደሚናገሩት፤ ዓጼ ዮሐንስ በነቀርሳ ተይዘው በአቡነ ሐራ ድንግል ጸበል በመዳናቸው ነበር ለገዳሙ የአንድ ሰዓት የእግር መንገድ ያህል ስፋት ያለው ቦታ ለገዳሙ የሰጡት፡፡ ደርግ ሥልጣን ሲይዝ በገዳሙ 800 የሚደርሱ መናንያን እንደነበሩ የሚያስታውሱት መነኮሳቱ፤ በወቅቱ “መሬት ላራሹ” የሚል አዋጅ በመታወጁ የገዳሙን ይዞታ አርሶ አደሮች እየተቆጣጠሩት እንደመጡና መናንያኑ ገዳሙን ጥለው መኮብለላቸውን ያስረዳሉ፡፡
በአሁኑ ወቅት በገዳሙ ይዞታ ላይ ከ250 በላይ አባወራዎች ሰፍረው እንደሚገኙ የሚገልጹት መነኮሳቱ፤ ይህን ችግር ለመቅረፍ ለመንግሥት በተደጋጋሚ አቤቱታ ካቀረቡ በኋላ፣ መንግሥት ነዋሪዎቹን አንስቶ ሌላ ቦታ ለማስፈር ፈቃደኛ ቢሆንም፣ ለነዋሪዎች ካሣ ለመክፈል በጀት እንደሌለው በመግለጽ፣ ገዳሙ ካሣውን እንዲከፍል መወሰኑን ይናገራሉ፡፡
ሆኖም የሚከፈለው ካሣ ከገዳሙ አቅም በላይ በመሆኑ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃግብር ማዘጋጀት አስፈላጊ ሆኖ አግኝቶታል የሚሉት የገዳመ ወንያት አቡነ ሐራ ድንግል አንድነት ገዳም የገቢ ማሰባሰቢያ ኮሚቴ አባላት፤ ዛሬ ከቀኑ 9 ሰዓት ላይ በጠቅላይ ቤተክህነት አዳራሽ ስለ ገዳሙ አሁናዊ ሁኔታና ስለገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብሩ ሊቃነ ጳጳሳት፣ የገዳሙ መነኮሳት፣ የቤተክህነት አባቶችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ እንደተነገረው፣ የአማራ ክልል ካቢኔ ለገዳሙ ሁሉንም ይዞታውን ባይሆንም 60 ሄክታር የሚደርስ መሬት እንዲመለስለት የወሰነ ሲሆን፤ ገዳሙ በበኩሉ ለአርሶ አደሮቹ የሚገባቸውን የመሬት ካሣ መክፈል ይጠበቅበታል፡፡
ይህን የመሬት ካሣ ለመክፈልና ለገዳሙ የማስፋፊያ ልማት ለማከናወን፣ የፊታችን ቅዳሜ ሚያዝያ 19 ቀን 2016 ዓ.ም በካፒታል ሆቴል፣ በቀጥታ የቴሌቪዥን ሥርጭት፣ ከቀኑ 10 ሰዓት ጀምሮ እስከ ሌሊቱ 6 ሰዓት የሚቆይ ዓለማቀፍ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃግብር እንደሚያካሂድ ኮሚቴው አስታውቋል፡፡
ለአርሶ አደሮቹ የመሬት ካሣውን ለመክፈልና የገዳሙ ይዞታ ከተለቀቀ በኋላ በሥፍራው ለሚከናወኑ ልማቶች በአጠቃላይ 100 ሚሊዮን ብር እንደሚያስፈልገው የገለጸው የገቢ አሰባሳቢ ኮሚቴው፤ በመላው ዓለም የሚገኙ የቤተክርስትያን ልጆችና የጻድቁ አቡነ ሐራ ወዳጆች በዚህ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር ላይ በንቃትና በትጋት እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርቧል፡፡
በአሁኑ ወቅት በገዳሙ የሚገኙ መናንያን ቁጥር 5ሺ እንደሚደርሱና በጾም ወቅት የጸበልተኛው ቁጥር ከ50 ሺ በላይ መሆኑን የጠቆሙት የገቢ አሰባሳቢ ኮሚቴ አባላቱ፤ እኒህን ሁሉ በአግባቡ የሚያስተናግድ በቂ መጠለያና የልማት ሥራዎች ማከናወን አስፈላጊ እንደሆነ በአጽንኦት ተናግረዋል፡፡
ለገዳሙ ድጋፍ ማድረግ የሚሹ ወገኖች፡-
በንግድ ባንክ የሒሳብ ቁጥር፡- 1000610362463
በአባይ ባንክ የሒሳብ ቁጥር፡- 9221111060954312
እንዲሁም የዶላር ሒሳብ ቁጥር፡- 634110814 መለገስ ይችላሉ ተብሏል፡፡
እባክዎ!..አንድ የጎዳና ሰው የበዓል ምሳውን ይሸፍኑልን?
እኛ ስማችን ከዚህ በታች የተጠቀሰ ጋዜጠኞችና በጎ አድራጊዎች ሶሻል ሚድያን በመጠቀም ለመጪው የፋሲካ በዓል አስታዋሽ የለሾቹን የጎዳና ተዳዳሪ ወገኖች ምሳ በማብላት በዓሉን አብረን ለማሳለፍ አቅደናል። እርስዎም ከጎናችን ይሁኑ!..ከቻሉ አብረውን ያሳልፉ?..ቢያንስ የአንድ ሰው የምሳ ወጪ በመሸፈን አጋርነትዎን ይግለፁልን?!
መርሐግብሩን ለማዘጋጀት ያቀድነው በተለያዩ ምክንያቶች ጎዳና ለወጡ ወገኖች ቢያንስ አለኝታነታችንን ለመግለፅ እና በዓሉን ደስ ብሏቸው እንዲያሳልፉ በማሰብ ነው።
ከእርስዎ የምንፈልገው እገዛ ቢያንስ አንድ ሰው በመመገብ ዓላማችንን ደግፈው ከጎናችን እንዲቆሙ ነው።
የአንድ ሰው ምገባ ወጪ ግምት 500 ብር ነው። አቅምዎ ከፈቀደ ሁለትም ሶስትም ...ወገኖችን በመመገብ ከበረከቱ መቋደስ ይችላሉ።
የ 1 ሰው ምሳ ወጪ ለመሸፈን .................500 ብር
የ 3 ሰዎችን...ለምትሸፍኑ...1500 ብር
የ 6 ሰዎችን ...ለምትሸፍኑ.... 3000 ብር
የ 10 ሰዎችን.... ለምትሸፍኑ......5000 ብር
የ15 ሰዎችን ...ለመሸፈን...7500 ብር
የ20 ሰዎችን ....ለመሸፈን...10000 ብር
***
የምገባውን ዝርዝር መርሐግብር በቀጣይ የምናሳውቅ ይሆናል።
አሁን መላክ ጀምሩ?!...
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ስላሴ ቅርንጫፍ
ሒሳብ ቁጥር
1000620235818...(ቴዎድሮስ፣ፍሬው እና አለምነሽ)
***ለተጨማሪ መረጃ አስተባባሪዎች
1.ቴዎድሮስ ካሳ(+251 98 900 0089)
2.ፍሬው አበበ (+251911617935)
3..አለምነሽ ኩምሳ (+25191 164 5458)
4.ቤቴልሄም ለገሰ (+251911335511)
5.ቆንጂት ሁሴን (+251911408541)
ሲያስገቡ ደረሰኙን መላክ አይዘንጉ!!
ማኀበራዊ ሚድያን ለበጎ ተግባር በመጠቀም ለውጥ እናመጣለን!!
እናመሰግንዎታለን!!
(በብርሃኑ በላቸው አሰፋ ፣ የ”ክቡር ልጆች” መጽሐፍ ደራሲ)
ዓለም አቀፍ የመጽሐፍ ቀን፤ የንባብ ባህልን ለማዳበር፣ ደራስያንንና አታሚዎችን ለማበረታታት ይከበራል፡፡ እ.ኤ.አ. በ1995 ዓ.ም ነበር ፣ ለመጀመሪያ ጊዜ የመጽሐፍ ቀን የተከበረው፡፡ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት ቀኑን የንባብ ልማድ እንዲዳብርና በተለይም ወጣቱን ትውልድ በማነቃቃት፣ የመረጃ ፍሰቱ በንባብ እንዲጎለብት ለማበረታታት በየዓመቱ ያስበዋል፡፡
በሀገራችንም ሀርመኒ ሂልስ ት̸ ቤት በትላንትናው ዕለት በተለያዩ ዝግጅቶች ቀኑን አክብሯል፡፡ ት̸ ቤቱ ደራሲያን መጽሐፍቶቻቸውን ለተማሪ ወላጆች እንዲያስተዋውቁ በማድረግ፣ የልጆች መጽሐፍ ደራሲያን ለተማሪዎች መጽሐፍ እንዲያነቡ በማድረግና የተማሪዎችና መምህራን መጽሐፍ የማንበብ ስነ ስርዓት በማካሄድ ዓለማቀፍ የመጽሐፍ ቀንን በድምቀት አስቦታል፡፡ በመርሃግብሩ ላይ የልጆች መጽሐፍ ደራሲ እምነቴ ድልነሳን ጨምሮ ሌሎችም ታድመዋል፡፡
የት̸ ቤቱ ዳይሬክተር ሩት መንበረ፣ ተማሪዎች የንባብ ባህላቸውን እንዲያሳድጉ ታስቦ ቀኑን አክብረነዋል ብለዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት ኤሌክትሮኒክስ የመጽሐፍ ንባብ ትልቁ ተግዳሮት በመሆኑ ልጆች በፍቅር እንዲያነቡ ምቹ ሁኔታን እየፈጠሩ መሆኑን አመልክተዋል፡፡
ልጆች እና መጻሕፍት
በቅርቡ የተካሄደ አንድ ጥናት እንዳመለከተው፤ ምንም እንኳን 70 በመቶ ወላጆች ማታ ማታ ለልጆች ጣፋጭ ታሪኮችን ማንበብ አስፈላጊነቱን ቢያምኑም፣ ግማሽ ያህሉ ብቻ ይተገብራሉ፡፡ ከአምስት ቤተሰቦች አንዱ ደግሞ በስራ ብዛት የተነሳ ለልጆች የማንበብ ልማድ የለውም፡፡
ይሁን እና ማምሻውን የሚነበቡ ተረቶች ምን ጥቅም አላቸው ?
በወላጅና በልጅ መካከል ያለውን ግንኙነት ያጠናክራሉ
የልጆችን የማንበብ ክህሎት ያዳብራሉ
የልጆችን የፈጠራ አቅም ያጎለብታሉ
የልጆችን የቃላት ችሎታ ያሳድጋሉ
የልጆችን የስሜት ብስለት ያዳብራሉ
የልጆችን የአእምሮ ጤና ያበለፅጋሉ
ለአካላዊ ጤንነት ምግብና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እንደሚያስፈልግ ሁሉ ለአእምሮ እድገት ደግሞ ንባብ ወሳኝ ሚና አለው፡፡ ከመዋዕለ ህጻናት እስከ አራተኛ ክፍል ልጆች ለማንበብ መሰረታዊ ክህሎትን ይማራሉ፡፡ ከአራተኛ ክፍል ጀምሮ ደግሞ ለመማር ያነባሉ፡፡ የፔዳጎጂ ፅንሰ ሃሳብም ተማሪዎች በራሳቸው እንዲማሩና በቀላሉ እንዲገነዘቡ በማድረግ ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ ይህ ደግሞ የማንበብ ፍላጎትና ተነሳሽነት ይጠይቃል፡፡
መረጃዎች እንደሚያመለክቱት፤ የልጆች የንባብ ክሂል ብቃት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሽቆለቆለ ነው፡፡ የሃገራችን ተማሪዎች የመጀመሪያ እርከን ሲጨርሱ ለምን ማንበብ ያዳግታቸዋል ? የተነበበላቸውን ለምን መረዳት ይቸግራቸዋል ? የሚሉት ጥያቄዎች መልስ ያሻቸዋል፡፡
ልጆች የማንበብ ልማድን እንዲያዳብሩ
በየቀኑ ማንበብ ማለማመድ
የስነ ልቦና ባለሙያዎች እንደሚሉት፤ በየቀኑ ለ20 ደቂቃ ተረት ማታ ማታ የሚነበብላቸው ልጆች፣ የአእምሮ ጤናቸው ከመጠበቁ ባሻገር የፈጠራ አቅማቸው ከፍ ያለ ነው፡፡
ወላጆች መጽሐፍትን በማንበብ አርአያ ሊሆኑ ይገባል
ምቹ የንባብ ከባቢ መፍጠር
ከልጆች ጋር ቤተ መጽሐፍት መጎብኘት
ልጆች የሚፈልጉትን መጽሐፍ እንዲመርጡ እድል መስጠት
ልጆች ደስ የሚላቸውን መጽሐፍ ደጋግመው እንዲያነቡ ማበረታታት ይገኙበታል፡፡
Page 2 of 704