በ2017 እ.ኤ.አ ላይ ጋቦን ለምታስተናግደው 32ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ የሚደረጉት የምድብ ማጣሪያዎች በ2ኛ ዙር ግጥሚያዎች ዛሬ እና ነገ ይቀጥላሉ፡፡  በምድብ 10 ከአልጀሪያ፣ ሌሶቶና ሲሼልስ ጋር የተደለደለው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ሲሆን በ2ኛ ዙር የምድብ ማጣሪያ ግጥሚያውን ዛሬ በሰፊ የግብ ልዩነት ማሸነፍ ከቻለ የማለፍ ዕድሉን ያሰፋለታል፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የ2ኛ ዙር የማጣሪያ ግጥሚያውን ዛሬ ከሜዳው ውጭ በቪክቶሪያ ከተማ በሚገኘው በስታድ ሊንቴ ስታድዬም ከሲሸልስ አቻው ጋር የሚያደርግ ሲሆን ጨዋታውን በመሃል ዳኝነት የሚመሩና ኮሞሮሳዊው አሊ አዴላይድ እንደሆኑ ታውቋል፡፡ የኢትዮጵያ ቡድን ከዚሁ ወሳኝ የምድብ ማጣሪያ ጨዋታ ሳምንት ቀደም ብሎ የአቋም ፈተሻ ግጥሚያ ከሩዋንዳ አቻው ጋር ከሜዳው ውጭ አድርጐ 3ለ1 መሸነፉ አይዘነጋም፡፡ ዛሬ ከሲሼልስ ጋር በሚያደርገው የነጥብ ጨዋታ በሰፊ የግብ ልዩነት ማሸነፉ የማጣሪያውን ጉዞ ያደላድልለታል፡፡ በምድብ 10 ሌላ ጨዋታ ነገ አልጀሪያ ከሜዳው ውጭ በማሱሩ ከተማ ለሚገኘው ሲተሰቶ ስታድዬም ከሌሶቶ ጋር ትገናኛለች፡፡ በምድብ 10 ላይ አልጀሪያ በመጀመሪያ ጨዋታዋ ሲሼልስን በሜዳዋ 4ለ0 ካሸነፈች በኋላ በሦስት ነጥብና በ4 የግብ ክፍያ ትመራለች፡፡ ኢትዮጵያ በመጀመሪያ ዙር ግጥሚያዋ በሜዳዋ ሌስቶን 2ለ1 አሸንፋ በ3 ነጥብና በ1 የግብ ክፍያ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ናት፡፡ ሌሶቶ ያለምንም ነጥብ በ1 የግብ ዕዳ ሦስተኛ ደረጃ እንዲሁም ሲሼልስ ያለምንም ነጥብ በ4 የግብ ዕዳ መጨረሻ ደረጃ ላይ ናቸው፡፡
በታዋቂው የእግር ኳስ ዘጋቢ ድረገፅ ጐል ንባቢዎች ለምድብ 10 የ2ኛ ዙር የማጣሪያ ግጥሚያዎች የተለያዩ የውጤት ግምቶችን ተሰንዝረዋል፡፡ በአልጀሪያ እና ሌሶቶ ጨዋታ 76% የድረገፁ አንባቢዎች የአሸናፊነቱን ግምት ለአልጀሪያ ሲሰጡ፤ ለኢትዮጵያ እና ለሴሼልስ ጨዋታ ደግሞ 67% የማሸነፍ ዕድሉ ለኢትዮጵያ የተተነበየ ሆኗል፡፡ የምድብ 10 የ3ኛ ዙር ማጣሪያ ጨዋታዎች ከ7 ወራት በኋላ የሚቀጥሉ ሲሆን ሲሼልስ በሜዳዋ ሌሶቶን ስታስተናግድ ኢትዮጵያ በድጋሚ ከሜዳ ውጭ በመጓዝ አልጀሪያን ትገጥማለች፡፡

አለም አቀፍ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ቁጥራቸው ወደ 20%  የሚጠጋ ሴቶች እንዲሁም 5-10%  የሚደርሱ ወንዶች በልጅነት እድሜያቸው የፆታ ጥቃት ይደርስባቸዋል፡፡  በፈረንጆቹ በ2010 በ The United Nations Population Fund is an international development agency (UNFPA) እና Population Council የጋራ ትብብር በሀገራችን በተደረገ ጥናት አስገድዶ መድፈር ተፈፅሞባቸው የህክምና አገልግሎት ያገኙ ሴቶች ቁጥር በገጠር 1.9% እንዲሁም በከተማ 5.7%  ብቻ ናቸው፡፡ የሕግ ድጋፍ ያገኙ ደግሞ በገጠር 0.2%  በከተማ ደግሞ 7.4%  ሲሆን የስነልቦና ባለሙያ ድጋፍ ወይም የምክር አገልግሎት ያገኙት ደግሞ በከተማ 1.9%  እንዲሁም በገጠር 1.1%  እንደሆኑ ለማወቅ ተችሏል፡፡2013 በአለም የጤና ድርጅት በተደረገ ጥናት በአለም ዙሪያ የሚገኙ ቁጥራቸው 1.5 ሚሊዮን የሚጠጉ ሴቶች የዚህ ችግር ተጠቂዎች ናቸው፡፡
ባለፈው እትም በጎንደር ሆስፒታል ውስጥ በኢትዮጵያ ጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር የተቋቋመውን ሞዴል ክሊኒክ የስራ እንቅስቃሴ ለመመልከት በተገኘንበት ወቅት በጥቃቱ ሰለባ የሆኑ ሴቶችን እና የህግ እና የህክምና ባለሙያን ሀሳብ አስነብበናችሁዋል፡፡ በዚህ እትም አንዲት የአስራ አንድ አመት ሕጻን አባት እና የጽንስና ማህጸን ሕክምና ባለሙያን እንዲሁም ከተለያዩ መረጃዎች በጉዳዩ ዙሪያ ያለውን እውነታ እናስነብባችሁዋለን፡፡
//////////////
ጥ/    የተገናኘነው በጎንደር ሆስፒታል በሞዴል ክሊኒክ ነው፡፡ ለምን?
መ/    በጎንደር ሆስፒታል ውስጥ ወደሚገኘው የአስገድዶ መድፈር ወንጀል የተፈጸመባቸው ሴቶች ከሚታከሙበት ክሊኒክ የ11 አመት ሕጻን ልጄን ይዤ የተገኘ ሁበት ምክንያት ልጄ ጥቃት ስለደረሰባት ነው፡፡ ልጅትዋ እናትዋ ስለሞተችባት የምትኖረው ከእኔና ታናሽ ወንድምዋ እንዲሁም ዘመድ ከሆነ ልጅ ጋር ነው፡፡ እኔ     ልጆቼን ለማሳደግ በማደርገው ሩጫ ምክንያት አብዛኛውን ጊዜ በቤት ውስጥ አልገኝም፡፡ በዚህም ምክንያት ያለውን ክፍተት ተጠቅሞ እቤቴ እማኖረው ዘመዴ ጥቃቱን በቤት ፈጸመባት፡፡
ጥ/    ልጅቷ ተገድዳ ስትደፈር የተመለከተ ሰው ነበር? ወይንስ?
መ/    ልጁ አስገድዶ በሚደፍራት ጊዜ ማንም አልደረሰላትም፡፡ እሱዋም እናትዋ ስለሞተች መደፈሬን አባቴ ቢሰማ እሱም ይጎዳብኛል በማለት አርቃ በማሰብዋ ከአንድ ቀን በላይ ዝም ብላ ነው የተኛቸው፡፡ በሁዋላም ምክንያትዋ ምን እንደሆነ ስጠይቃት     በቃ ...እገሌ     እንዲህ አድርጎኝ ነው ብላ ነገረችኝ፡፡ እኔም ወዲያውኑ ወደ ሕክምናና ወደ ህግ     መጥቻለሁ፡፡
ጥ/    የሕክምናው ውጤት እንዴት ነው?
መ/    የህክምናው ውጤት መደፈሩዋን ተደፍራለች፡፡ ሌላውን ሕክምና ግን በአስቸኳይ እየተደረገላት ነው፡፡ የደፈራት ልጅ የኤችአይቪ ቫይረስ በደሙ ውስጥ የሚገኝ በመሆኑ ልጅቷም በቫይረሱ እንዳትያዝ ሐኪሞቹ የተቻለውን ሁሉ እያደረጉላት ነው፡፡ ልጁም     በህግ ቁጥጥር ስራ ውሎአል፡፡
ጥ/    ለህብረተሰቡ የምታስተላልፈው መልእክት አለ?
መ/    እኔ የማስተላልፈው መልእክት ...ሴት ልጆችን በሚመለከት ዘመድ ምናምን እያሉ ማመን አያስፈልግም፡፡ በቃ፡፡ ዝምድና የሚታመንበት ጊዜ አይደለም፡፡ ሴት ልጆች ገና አፋቸውን ሲፈቱ ጀምሮ ሁኔታውን ማስረዳት ያስፈልጋል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ወንዶች የሚሰሩትን የሚያውቁ አይመስለኝም፡፡ ስለዚህ ወላጆች እንዲሁም መላው ህብረተሰብ ክትትሉን አጠንክሮ እንደነዚህ ያሉ አጥፊዎችን ወደ ህግ እንዲቀርቡ በማድረጉ በኩል አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግ እመክራለሁ፡፡
/////////////
የፆታ ጥቃት የደረሰባቸው ሰዎች ለአጭር ወይም ለእረዥም ግዜ የሚቆይ አካላዊ እና ስነልቦናዊ ጉዳት ሊደርስባቸው ይችላል፡፡
ከእነዚህም መካከል፡-
ጥቃቱ የደረሰባቸው ግለሰቦች በሌሎች ላይ ግድያ ሊፈፅሙ ወይም እራሳቸውን ሊያጠፉ ይችላሉ፡፡
ከሀይል ድርጊቱ ጋር በተያያዘ የተለያዩ አካላዊ ጉዳቶች ሊደርስባቸው ይችላል፡፡
በአስገድዶ መድፈር ምክንያት ከሚፈጠር ያልተፈለገ እርግዝና ጋር በተያዘዘ ለውርጃ እንዲሁም ኤችአይቪን ጨምሮ ለተለያዩ የአባላዘር በሽታዎች እና የማህፀን ህመሞች ይዳረጋሉ፡፡
በጎንደር የነበረን ቆይታ ማጠቃለያ የሚሆነው ከጽንስና ማህጸን ሕክምና እስፔሻሊስቱ ዶ/ር ጌታቸው ሽፈራው ጋር ያደረግነው ውይይት ነው፡፡
ዶ/ር እንደሚሉት፡-
“...ጎንደር ውስጥ የሴቶች ጥቃት በተለይም መደፈርን በሚመለከት ድርጊቱ አለ ማለት ይቻላል፡፡ ለዚህም ነው የኢትዮያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር ከሆስፒታሉ ጋር በመነጋገር ይህንን ሞዴል ክሊኒክ የከፈተው፡፡ አገልግሎቱን የሚፈልጉ ሴት ልጆች በቀን ውስጥ ሁለት ሶስት ያህል የሚመጡ ሲሆን ተገደው የተደፈሩት በወር እስከ ሀያ እና ሰላሳ በሚደርስ ቁጥር ለሕክምና ይቀርባሉ፡፡ በእርግጥ ይህ ቁጥር በከተማዋ ወይንም በአካባቢው በጠቅላላ የሚፈጸመው ይህ ነው በሚል ለማመላከት አይረዳም፡፡ ወደ ህብረተሰቡ ስንዘልቅ ጉዳዩን ወደ ህግ ወይንም ሕክምና ሳያደርሱ በቤታቸው ደብቀው በሽምግልና የሚደራደሩትን ሳይጨምር ነው፡፡ ብዙውን ጊዜ ችግሩን ለፍትሕ ወይንም ለሕክምና የማያቀርቡት ሰዎችን ምክንያት ስንመረምር ከእውቀት ማነስ ወይንም ከፍርሀት አለዚያም የራስን ክብር ከመጠበቅ አንጻር ሊሆን እንደሚችል ይገመታል፡፡”
ዶ/ር አክለውም ስለአካባቢው ልምድ ሲመሰክሩ “...በጎንደርም ይሁን በብዙ አካባቢዎች አስገድዶ መድፈር ያልተለመደ ድርጊት የነበረ ቢሆንም አሁን አሁን ግን ወንጀሉ እየተለመደ እና እየሰፋ በመምጣቱ የህብረተሰቡንም የህግ አስፈጻሚ አካላትንም ትኩረት የሚሻ ጉዳይ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ በእርግጥ በቀድሞው ጊዜ ሙሉ ለሙሉ የለም የሚያሰኝ ነገርም የለም፡፡ ምክንያቱም እንደአሁኑ በግልጽ ጉዳቱን ለመናገርና ወደ ፍትህ እንዲሁም የሚደርሰውን ጉዳት ለመከላከል ወደ ጤና ተቋም የመምጣት ልምድ ባልነበረበት ወቅት ተዳፍነው የቀሩ ብዙ ወንጀሎች ሊኖሩ እንደሚችሉ አይጠረጠርም፡፡” ብለዋል፡፡   
በስተመጨረሻም ዶ/ር ጌታቸው ሺፈራው ስለሕክምና አሰጣጡ የሚከተለውን ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ “...አንዲት ልጅ ተደፍራለች ተብላ ወደ ሕክምና ማእከላችን ስትደርስ ከኢትጵያ ጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር የተሰጠንን ፕሮቶኮል ተጠቅመን ለፍትሕ አካላቱ የምንሰጠው ምስክርነት አለ፡፡ በእርግጥ ተደፍራለች አልተደፈረችም የሚል ቃል በቀጥታ አንጠቀምም፡፡ ነገር ግን በሰውነቷ ላይ ያየነውን ጉዳት በመከተል በቅርብ ጊዜ የተፈጸመ ወይንም የቆየ መሆኑን በዝርዝር በስእል ጭምር አስደግፈን እንሰጣለን፡፡ ከዚህ ውጪ ግን ሌሎች ሕክምናዎች ኤችአይቪ... ጉበት... እርግዝና... የአባላዘር በሽታዎችን በሚመለከት ተገቢው ምርመራ ለልጅቷ ይደረግላታል፡፡ በእርግጥ ይህ ክሊኒክ ገና አንድ አመት ገደማ የሚሆነው ሲሆን በሂደት ሁሉንም አገልግሎች ማለትም የህክምና፣ የምክር አገልግሎት፣ የፍትህ እና የስነልቡና ሕክምናን በአንድ ቦታ እንዲያገኙ የሚቻልበት መንገድ ይመቻቻል የሚል ተስፋ አለን፡፡”
“...ወንድ ሴትን የሚደፍርበት ምክንያት ብዙ ጊዜ የስርአተ ጾታ ክፍፍል ልዩነቱ ወይንም ጀንደር ከሚለው ሁኔታ ጋር ይያያዛል፡፡ ሴት እንዲህ ነች ወንድ ደግሞ እንዲህ ነው የሚለውን ህብረተሰቡ የሚያምንበትና ተግባራዊ እያደረገው ካለው ጋር በተያያዘ አስገድዶ መድፈሩ ብዙ ጊዜ ይፈጸማል፡፡ ምክንያቱም ህብረተሰቡ ለወንድ ልጅ ኃይል ወይንም አቅም እንዳለው እየነገረ ስለሚያሳድገው ወንዱ በተፈጥሮው ካገኘው ጥንካሬ ባሻገር በአስተሳሰብም ኃይል እንዲኖረው ያደርገዋል፡፡ ከዚህም በተለየም በልጅነታቸው የመደፈር ወይንም የመገለል እንዲሁም የተለያዩ ጥቃቶች የደረሰባቸው ከሆነ አስገድዶ መድፈርን እንደ እልህ መወጫ ይጠቀሙበታል፡፡ አንድ ወንድ እንደዚህ ያለ ጉዳት እየደረሰበት ያደገ ከሆነና እሱም ጥቃቱን መፈጸሙ በሳይንሳዊው መንገድ ሲተረጎም አእምሮው በሚያድግበት ሰአት የተለያዩ ኢንዛይሞች ማለትም ነርቭ ከነርቭ የሚገናኝበት መልእክት የማስተላለፊያ ኬሚካሎች በደም ውስጥ እየቀነሰ ይመጣል፡፡ አእምሮው እያደገ ሲመጣ ኬሚካሉ ግን እየቀነሰ መምጣቱ በሚያድጉበት ሰአት ላይ ይህንን ወሲባዊ ጥቃትም ሆነ ማንኛውንም ወንጀል እንደሰው መግደል የመሳሰሉትን ጨምሮ የመፈጸም እድላቸው የሰፋ ይሆናል፡፡ ብዙ ጊዜ አስገድዶ መድፈር የሚፈጽሙ ሰዎች ከአንድ ሰው ጋር ወይንም ከተለያዩ ሰዎች ጋር ጥሩ አይነት ግንኙነት መመስረት የማይችሉ ናቸው፡፡ ይህ እንግዲህ ከአስተዳደግ ወይንም ከተለያዩ የህይወት አጋጣሚዎች ሊሆን ይችላል፡፡ በተረጋጋ ሁኔታ ከሰዎች ጋር መኖር ካልተቻለ ወይንም ህብረተሰቡ የሚጠብቀውን ደረጃ ማሟላት ካልተቻለ እንደመሸሻ የሚቆጠረው የአስገድዶ መድፈር ወንጀልን የመሳሰሉ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡
ዶ/ር ዳዊት ደሳለኝ
የጽንስና ማህጸን ሕክምና እስፔሻሊስት

Published in ላንተና ላንቺ

በ3ሺ እና በ5ሺ ሜትር ውድድሮች ገንዘቤ ዲባባ እና አልማዝ አያና የያዙት ትንቅንቅ እስከ ኦሎምፒክ እንደሚቀጥል በስፋት እየተዘገበ ነው፡፡ በ15ኛው የዓለም አትሌተክስ ሻምፒዮና ወደ አስደናቂ የፉክክር ደረጃ ያደገው የሁለቱ አትሌቶች ተቀናቃኝነት በኢትዮጵያ አትሌቲክስ የተስፋ ብልጭታዎችን ፈጥሯል፡፡  
ከ15ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና እና ከ2015 ዳይመንድ ሊግ በኋላ በኦል አትሌቲክስ  ድረገፅ በወጣ የውጤት ደረጃ በሴቶች  ሁሉም ዓይነት የውድድር መደቦች በ1461 ነጥብ አንደኛ ደረጃ ላይ የምትገኘው ገንዝቤ ዲባባ ስትሆን አልማዝ አያና በ1418 ነጥብ በ2ኛ ደረጃ ትከተላታለች፡፡ በሌላ በኩል በ5ሺ ሜትር አልማዝ አያና በ1418 ነጥብ 1ኛ ደረጃን ስትቆናጠጥ ገንዘቤ ዲባባ ደግሞ በ2ኛ ደረጃ የምትከተለው በ1404 ነጥብ ነው፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮናው በኢትዮጵያ የተሳትፎ ታሪክ በ1500 ሜትር የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳሊያ ያስመዘገበችው አትሌት ገንዘቤ ዲባባ፤ ከትናንት በስቲያ ደግሞ የ2015 ዳይመንድ ሊግን በ5ሺ ሜትር ማሸነፏን አረጋግጣለች፡፡ በዚህ ውጤቷም የዳይመንድ ሊግ ዋንጫና 40ሺ ዶላር የገንዘብ ሽልማት አሸንፋለች፡፡
በሌላ በኩል በዓለም ሻምፒዮናው በ5ሺ ሜትር የወርቅ ሜዳልያ በአስደናቂ አሯሯጥና ታክቲክ ለመጐናፀፍ የበቃችው አልማዝ አያና የዓለም አትሌቲክስን ትኩረት ስባለች፡፡ በውድድር ዘመኑ የገንዘቤን ኃያልነት በከፍተኛ ደረጃ በመቀናቀንና ከ2 ጊዜ በላይ አሸንፋት በተፎካካሪነት መጠቀስ የጀመረችው አልማዝ ለኦሎምፒክ ስኬት ከተገመቱ የኢትዮጵያ አትሌቶች ግንባር ቀደም ግምቱን እየወሰደች ነው፡፡  ሁለቱ የዓለም ሻምፒዮኖች በ3ሺ ሜትርና በ5ሺ እያሳዩ ያሉት ተመጣጣኝ ብቃት ከስራቸው ከምትከተላቸው ሰንበሬ ተፈሪ ጋር  እስከ 2016 የሪዮ ዲጄኔሮ ኦሎምፒክ በተለይ በ5ሺ ሜትር የኢትዮጵያን የበላይነት አስተማማኝ እንደሚያደርገው እየተወሳ ነው፡፡

Saturday, 05 September 2015 09:49

ማሬ ዲባባ ማራቶንን ትመራለች

 * ዘንድሮ ብቻ ገቢዋ ከ1 ሚሊዮን ዶላር አልፏል

    በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የኢትዮጵያ የተሳትፎ ታሪክ በማራቶን የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳሊያ የወሰደችው ማሬ ዲባባ፤ ማራቶንን በየዘርፉ በመሪነት ተቆጣጥራለች፡፡ በኦል አትሌቲክስ ድረገፅ በሰፈረው አሃዛዊ መረጃ መሠረት በሴቶች ማራቶን ማሬ ዲባባ በ1351 ነጥብ አንደኛ ናት፡፡ ባለፈው ሰሞን በማራቶን የዓለም ሻምፒዮን ከሆነች በኋላ ደግሞ በ2015 የዓለም ታላላቅ ማራቶኖች (World Marathon Major Series) ሊግ በነጥብ 1ኛ ሆና እየመራች ሲሆን፤ የውድድር ዘመኑን በአሸናፊነት ልትጨርስ ትችላለች፡፡
በሌላ በኩል በቤጂንጉ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የማራቶን ሻምፒዮን ስትሆን በሽልማት ካገኘችው 60ሺ ዶላር በተጨማሪ ከቡድን ሽልማትና ከስፖንሰር ጥቅሟ ጋር ገቢዋ በዕጥፍ  የጨመረላት ማሬ ዲባባ ከማራቶን ሊግ አሸናፊነቷ ጋር የዘንድሮ ገቢዋ ብቻ ከ1 ሚሊዮን ዶላር ሊያልፍ ችሏል፡፡ በዓለም አቀፉ የጐዳና ላይ ሩጫዎች ማህበር (ARRS) ማሬ ዲባባ ከ2008 እ.ኤ.አ በጐዳና ላይ ሩጫዎች ከ15 በላይ ድሎች በማስመዝገብ 534,465 ዶላር በሽልማት ገንዘብ መሰብሰቧ ለማወቅ ተችሏል፡፡ በውድድር ዘመኑ በዓለም ዙሪያ የሚካሄዱ 6 ታላላቅ የማራቶን ውድድሮችን ተንተርሶ በሚሰጥ ነጥብ የማራቶን ሊግ አሸናፊ የሚወሰን ሲሆን፤ በየፆታ መደቡ በነጥብ መርተው የሚጨርሱ አትሌቶች እያንዳንዳቸው 500ሺ ዶላር ይሸለማሉ፡፡  
ማሬ ዲባባ ቤጂንግ ላይ የዓለም ሻምፒዮና ከሆነች በኋላ የማራቶን ሊጉን በ42 ነጥብ አንደኛ ሆና እየመራች ሲሆን፤ በቅርብ ርቀት የምትፎካከራት የኬንያዋ ሄለን ኬፕሮን በ32 ነጥብ ነው፡፡
ሌሎቹ ኢትዮጵያውያን ብርሃኔ ዲባባ እና ትዕግስት ቱፋ እንዲሁም ሌላዋ ኬንያዊት ካሮሊን ሮቲች በ25 ነጥብ 3ኛ ደረጃን ተጋርተው ይከታተላሉ፡፡ በተያያዘ በወንዶች ምድብ በ25 ነጥብ የማራቶን ሊጉን መሪነት የተቆጣጠረው ቤጂንግ ላይ የብር ሜዳሊያ ያገኘው የማነ ፀጋዬ ነው፡፡ ኤሊውድ ኪፕቾጌ ከኬንያ፣ ግርማይ ገ/ስላሴ ከኤርትራ እንደሻው ንጉሤ እና ሌሊሣ ዴሲሳ ከኢትዮጵያ በእኩል 25 ነጥብ ይከተላሉ፡፡
የማራቶን ሊግ አሸናፊዎች የሚወሰኑት በ6 የዓለማችን ታላላቅ ማራቶኖች ባስመዘገቡት ውጤት በሚሰጠው ነጥብ ይሆናል፡፡ ማሬ ዲባባ በ2014 የቦስተን ማራቶን 3ኛ እንዲሁም በቺካጐ ማራቶን 1ኛ ደረጃ ከማግኘቷም በላይ፤ በ2015 በቦስተን ማራቶን 2ኛ እንዲሁም በዓለም ሻምፒዮና 1ኛ ከሆነች በኋላ ያስመዘገበችው ነጥብ 42 አድርሳለች፡፡  በወርልድ ማራቶን ሜጀር ሲሪዬስ ታሪክ ኢትዮጵያ ለ3 ጊዜያት የማራቶን ሊጉን አሸናፊዎች አስመዝግባለች፡፡
በ2007 እና በ2008 እ.ኤ.አ አከታትላ ያሸነፈችው ጌጤ ዋሚ ስትሆን በ2003 እ.ኤ.አ ደግሞ ፀጋዬ ከበደ ሊጉን በነጥብ መሪ ሆነው በማጠናቀቅ በነፍስ ወከፍ 500ሺ ዶላር አግኝተዋል፡፡


የ 7/8 ዓመት እና የቀናት ልዩነት
    በኢትዮጵያና በአውሮፓ የዘመን አቆጣጠር መካከል የ7 ወይም 8 ዓመት ልዩነት ይታያል። ከጥር እስከ ጳጉሜ መጨረሻ የ8 ዓመት፣ ከመስከረም እስከ ታህሳስ መጨረሻ የ7 ዓመት ልዩነት አለ። የዚህ ልዩነት የተፈጠረው ክርስቶስ በተወለደበት ዘመን ላይ በነበረው የግምት አንድ አለመሆን ላይ ነው። እንደ አውሮፓ አቆጣጠር በመጪው ጥር የክርስቶስ ዕድሜ 2016 ነው። በኛ አቆጣጠር ደግሞ 2008 ይሆናል። የቅርብ ጊዜ ምርመራዎች ባሳዩት መሠረት በቀጣዩ ዓመት የክርስቶስ ዕድሜ 2023 ነው። ፈረንጆቹ በ7 ዓመት፣ እኛ ደግሞ በ15 ዓመት ተሳስተናል። ይኸው ነው።
በኢትዮጵያና በአውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር የቀናት ልዩነትም አለ። የኛ መስከረም 1 በነሱ ሴፕቴምበር 11 (በሠግር ዓመት 12 ይሆናል)። የዚህ የ10ቀን ልዩነት እንዴት መጣ? የልዩነቱ መነሻ ያለው በግሪጎሪያዊና በጁሊያን አቆጣጠር ውስጥ ነው።
በፀሐይ አቆጣጠር አንድ ዓመት 365 ዕለት፣ 5 ሰዓት፣ 48 ደቂቃ እና 46 ሰከንድ ነው። ይህ በጁሊያን ካላንደር ወደ 365 ዕለት፣ ከ 6 ሰዓት (ሩብ ዕለት ወይም የዕለት አንድ አራተኛ) ተጠጋጋ። በዚህ መሠረት 3 ዓመቶች 365 ዕለት ይኖራቸውና አራተኛው ዓመት 366 ዕለት ይኖሩታል። አራቱ ሩብ ዕለት በአራት ዓመት አንድ ዕለት ይሆናሉ። ይህን አንድ ዕለት ፈረንጆቹ 28 የነበረውን ፌብሯሪ 29 ያደርጉታል። እኛ ደግሞ ለሦስት ተከታታይ ዓመታት 5 የሆነችውን ጳጉሜ 6 እናደርጋታለን።
5 ሰዓት፣ 48 ደቂቃ፣ 46 ሰከንድ  ወደ 6 ሰዓት ሲሸጋሸግ 11 ደቂቃ፣ 14 ሰከንድ በትርፍ ተጨምሯል። ይኸ በ400 ዓመት ውስጥ አነሰ ቢባል የ3 ዕለት ትርፍ ያስከትላል። ከዚህ በመነሳት እ.ኤ.አ. በ1582 በአባ ጎርጎሪዮስ አማካይነት ማስተካከያ ተደረገ። ከ325ቱ የኒቂያ ጉባኤ እስከ 1582 ባለው የ 1, 257 ዓመት ውስጥ የ10 ዕለት ትርፍ እንዳለ ተሰላ። ኦክቶበር 5፣ 1582 ላይ 10 ዕለቱ ተጨምረው ያ ዕለት ኦክቶበር 15፣ 1582 ተባለ። ያን ዕለት በኛ አቆጣጠር ጥቅምት 8፣ 1575 ነበር። በዚያ ዕለት የ7ቀን ልዩነት ተፈጠረ።
አሁን ግን ልዩነቱ የ10 ቀናት ነው። ይህ ደግሞ እንዴት እንደሆነ እንይ። የጎርጎሮሳውያኑ የዘመን አቆጣጠር ከጁሊያን እንደተለየ ላለፉት የ1,257 ዓመታት የ10 ቀናት ተረፉን ካስተካከለ በኋላ ለመጪዎቹም ዘመናት የ11 ደቂቃዎች እና የ14 ሰከንዱን የትርፍ ጊዜ ማስተካከያ ቀመርም አስቀመጠ።
ቀመሩ በ400 ዓመት ውስጥ ሦስት ጊዜ የሦስት ዕለት ጭማሪ (በሊፕ ዪር ወይም ሠግር)  እንዳይደረግ ያቅባል። ፌብሯሪ 29 የሚሆነው ለ 4 ሲካፈሉ ቀሪያቸው ዜሮ በሚሆኑ ዘመኖች ነው። ዘመናቱ በ100 ቤት በሆኑ ጊዜ ግን ለ400 ተካፍለው ቀሪ ዜሮ ባላቸው ብቻ ፌብሯሪ 29 ይሆናል።
በዚህ መሠረት በ1600 ዓ.ም ለ400 ተካፍሎ ቀሪው ዜሮ ስለሆነ በዚያ ዓመት ፌብሯሪ 29 ሆኗል። በ1700፣ በ1800፣ እና በ1900 ግን በነዚያ ዓመታት ፌብሯሪ 29 መሆን ሲገባው ተዘሎ 28 ሆኗል። በመደበኛው አደማመር 1700, 1800, እና 1900 ለ4 ተካፍለው ቀሪው ዜሮ ስለሆነ ፌብሯሪ 29 ይሆን ነበር። በአዲሱ ሕግ ግን እነዚህ ለ400 ሲካፈሉ ቀሪው ዜሮ ስለአልሆነ ፌብሯሪ በ28 ቀጥሏል። በነዚህ ሦስት ዓመታት የተቀነሱት 3 ዕለታት በፊት 7 ዕለት የነበረውን የኛን እና የነርሱን ልዩነት ወደ 10 ዕለት ከፍ አድርጎታል። የዘመን ቆጠራ ልዩነታችን በአጭሩ ይኼ ነው።
ከጁሊያን የዘመን አቆጣጠር ጋር የተቀራረበውን የኛን የዘመን አቆጣጠር በጎርጎሮሳውያን መሠረት አስተካክለነው ቢሆን ኖሮ የሚከተለውን ይኖረን ነበር። ጥቅምት 8፣ 1575 የአስር ዕለቱ ማስተካከያ ሲደረግ የኛ ቀን በዚያ ዕለት ጥቅምት 18፣ 1575 ይሆን ነበር። ከዚያ በኋላ ደግሞ በ1700, በ1800, እና በ1900 ላይ 6 ልትሆን የሚገባት ጳጉሜ በ5 ትቆጠራለች። እንደዚያ መጥተን ቢሆን ኖሮ የአውሮፓውያኑ ሴፕቴምበር 1 እና የኛ መስከረም 1 አንድ ቀን ባይውልም ይቀራረብ ነበር።
ጳጕሜ 7 ልትሆን ትችላለችን?
በኢትዮጵያውያን የዘመን አቆጣጠር መሠረት በአንድ በኩል በየ300 ዓመቱ በሌላ በኩል ደግሞ በየ600 ዓመቱ አንድ ጊዜ ጳጉሜ 7 ልትሆን ትችላለች የሚል ትወራዊ አስተያየት አለ። በዚህ ላይ የራሴን ሐሳብ እሰነዝራለሁ። ሐሳቡን በደፈናው ከመቃወምና ከመደገፍ ይልቅ የውይይት ነጥቦች ማዋጣት ይሻላል።
በየዓመቱ ያለ አግባብ እየተጨመረ ሲቆጠር የሚኖር የ11 ደቂቃና የ14 ሰከንድ ትርፍ አለ። ይህ ጊዜ አሁን በተጠጋጋ ስሌት በ400 ዓመት ውስጥ አነሰ ቢባል የ3 ዕለት ልዩነት ያመጣል። [በመቶ ዓመት የሦስት ሩብ ዕለት በሁለት መቶ ዓመት የአንድ ዕለት ተኩል ትርፍ ነው።] ይህን ለማስተካከል በ400 ዓመት ውስጥ የ3 ዕለት ቅናሽ ይደረጋል። ይኸ ማለት በ400 ዓመት ውስጥ ጳጉሜ 6 መሆን ይገባት ከነበረው ውስጥ ሦስት ጊዜ በ5 ትቀጥላለች። በዚህ አካሔድ ጳጉሜ በሠግር ዓመት (ሊፕ ዪር) 6 የማትሆንበት ዓመት አለ፤ ወይም ደግሞ 5 የምትሆንበት ዓመት አለ ይባላል እንጂ እንዴት በየ300 ዓመቱ ጳጉሜ 7 ትሆናለች ይባላል? [በየ600 ዓመት የሚለው ሐሳብ አሳማኝ መነሻ ስላለው እሱን ወደ ኋላ እመጣበታለሁ።]
ሦስቱ ትርፍ ዕለት በ400 ዓመት አንዴ ይቀነስም ከተባለ የምናገኘው ውጤት እንደሚከተለው ነው። ቅናሹ ጳጉሜ 6 በምትውልበት በሉቃስ ዓመት ከሆነ ያኔ ጳጉሜ 3 ትሆናለች። ያለበለዚያ ጳጉሜ 5 በምትውልበት ዓመት ከሆነ ያኔ ጳጉሜ 2 ትሆናለች። በየ300 ዓመቱ ጳጉሜ 7 ልትሆን ትችላለች ማለት ግን ግራ ያጋባል።
ተጨማሪ ንፅፅር እና ማብራርያ
በአንድ ዓመት ውስጥ 365 ዕለት፣ 5 ሰዓት፣ 48 ደቂቃ እና 46 ሰከንድ እንዳለ አይተናል። ከ365 ውጭ ያለው ጊዜ ምን ያህል ዕለት ነው ካልን 0.2421991 ዕለት ነው። ይህ ከሩብ ዕለት (ከ0.25) በትንሹ አነስ ይላል። በአራት ዓመት ውስጥ ሲሰበሰብ አንድ ዕለት በቅጡ አይሞላም። ጥቂት ይቀረዋል። 0.2421991 ሲበዛ 4 የሚሆነው 0.9697964 ነው። ተረፉ በ400 ዓመት የሚሆነው ደግሞ 96.97964 ዕለት ነው።  
ይህ ማለት 96 ዕለት፣ ከ21 ሰዓት፣ ከ6 ደቂቃ፣ ከ40 ሰከንድ ነው። 97 ዕለት ለመሙላት 2 ሰዓት፣ 53 ደቂቃ እና 20 ሰከንድ ይቀረዋል። መቶ ዕለት ለመሙላት ደግሞ 3 ዕለት፣ 2 ሰዓት፣ 53 ደቂቃ እና 20 ሰከንድ ያስፈልገዋል።
የጁሊያን የዘመን አቆጣጠር መጠነኛ ማጠጋጋት ያደርግና የዓመቱን ጊዜ 365 ከ 0.25 ዕለት ያደርገዋል። ይህ በሌላ አገላለጽ 365 ¼ ኛ ዕለት ይሆናል። የጁሊያን የዘመን አቆጣጠር ትርፉን ዕለት የሀያ አራት ሰዓት አንድ አራተኛ ያደርገውና 6 ሰዓት ይሆናል። አሁንም በሌላ አገላለጽ፣ በጁሊያን አካሔድ አንድ ዓመት 365 ከ25/100ኛ ዕለት ነው። በጁሊያን አካሔድ ትርፉ ሩብ ዕለት በ 4 ዓመት አንድ ሙሉ ዕለት ይሆናል። በ400 ዓመት ደግሞ 100 ዕለት ይወጣዋል።
የጁሊያን የዘመን አቆጣጠር በ400 ዓመት ውስጥ የ74 ሰዓት፣ የ53 ደቂቃ እና የ20 ሰከንድ ትርፍ ያመጣል። በሌላ አገላለጽ በ400 ዓመት ውስጥ 3 ዕለት፣ 2 ሰዓት፣ 53 ደቂቃ እና 20 ሰከንድ ስህተት ያሣያል።
የግሪጎሪያን የዘመን አቆጣጠር አንድ ዓመትን 365 ከ 97/100ኛ ዕለት ያደርገዋል። ተረፉ 97/100ኛ ወይም 0.2425 ዕለት ነው። ይህ ተረፍ በአራት ዓመት ውስጥ 0.9690 ዕለት ስለሚሆን አንድ ሙሉ ዕለት አይሞላም። ተረፉ በ400 ዓመት ደግሞ (400 X 0.2425) 97 ዕለት ይሆናል። ይኸ የ97 ዕለት ተረፍ ቀጥተኛ ከሆነው ከ 96.87764 ዕለት ጋራ የተቀራረበ ነው። ጥቂት ጭማሪ ግን አድርጓል። ይህም 2 ሰዓት፣ ከ53 ደቂቃ ከ 20 ሰከንድ ነው። እንዲህም ሆኖ ታዲያ በ400 ዓመት የ 3 ዕለት፣ ከ 2 ሰዓት፣ ከ 53 ደቂቃ፣ ከ 20 ሰከንድ ስህተት ከሚያሳየው ከጁሊያን የዘመን አቆጣጠር አካሔድ የተሻለ ነው።
ከጁሊያን ስሌት ይልቅ የግሪጎሪያን ወደ ትክክለኛ አቆጣጠር ይቀርባል። ከግሪጎሪያን የበለጠ ደግሞ ወደ ትክክለኛው የሚቀርብ ስሌት አለ። ይህ ስሌት የተቀመረው ዑመር ኻያም በተባለው የሥነፈለክ ሊቅ ነው። በዑመር ኻያም ስሌት አንድ ዓመት 365 እና 8/33ኛ ዕለት ይሆናል። የ8/33ኛ ዕለት ተረፍ በሌላ አገላለፅ 0.242424 ነው። ይህ ተረፍ በ400 ዓመት ውስጥ 96.9696 ዕለት ይሆናል። ይህም ቢሆን ከግሪጎርያን የበለጠ ለፍፁምነት ይቀርባል እንጂ ጉድለት ያሣያል።
ጳጕሜ 7 ልትሆን ትችላለች!
በአንድ ዓመት ውስጥ ያለው 365 ዕለት፣ 5 ሰዓት፣ 48 ደቂቃ እና 46 ሰከንድ ነው። ከ365 ዕለት የተረፈው 5 ሰዓት፣ 48 ደቂቃ እና 46 ሰከንድ 6 ሰዓት ለመሙላት 11 ደቂቃ እና 14 ሰከንድ ይቀረዋል። ሆኖም ለአሠራር እንዲቀል ተብሎ ወደ 6 ሰዓት ተጠግቷል። 365 ዕለታት ለ12 ወራት ሲካፈል ለሁሉም 30 ዕለት ይደርሰውና 5 ዕለት ይተርፋል። ይኸ 5 ዕለት 13ኛው ወር ጳጉሜ ተብሎ እዚያው ተመድቧል። ከየዓመቱ ደግሞ በማጠጋጋት የሚተርፈው 6 ሰዓት በ4 ዓመት 24 ሰዓት ይሆናል። 24 ሰዓት አንድ ዕለት በመሆኑ ይኸ በ4 ዓመት ተጠራቅሞ የሚገኝ ዕለት በ4 ዓመት አንዴ ጳጉሜ ላይ ይጨመራል። ስለዚህ ጳጉሜ ለሦስት ተከታታይ ዓመታት 5 ትሆን እና በ4ኛው ዓመት 6 ትሆናለች።
ይህን ምሳሌ እንይ።
ጳጉሜ 6 የምትሆነው ሁሌም በሉቃስ ዘመን ነው። ወይም ደግሞ ዓመቱን ለ4 አካፍለን ቀሪው ሦስት በሆነበት ዘመን ጳጉሜን 6 እናደርጋለን። ለምሳሌ ዘንድሮ 2007 ለ 4 ሲካፈል ቀሪው ሦስት በመሆኑ የ2007 ጳጉሜ 6 ነች። በሌላ አነጋገር ሁሌም ወደ ዮሐንስ ዘመን ስንሸጋገር ከርሱ ቀድሞ ያለው የሉቃስ ዘመን ጳጉሜን 6 ያደርገዋል። የዮሐንስ ዘመንም ከሌሎቹ በተለየ አንድ ቀን ዘግይቶ ይገባል ወይም ይጀምራል። በየዓመቱ ከ365 ላይ ትርፍ ሆኖ የሚገኘው 5 ሰዓት፣ 48 ደቂቃ እና 46 ሰከንድ በ4 ዓመት ሲጠቃለል የሚሆነው 23 ሰዓት፣ 15 ደቂቃ እና 4 ሰከንድ ነው። ይኸ አሁንም 24 ሰዓት አይሞላም። ስለዚህ አንድ ሙሉ ዕለት አይደለም። አንድ ዕለት ለመሙላት የ44 ደቂቃ እና የ56 ሰከንድ ጉድለት ያሣያል።
በዓመት የ5 ሰዓት፣ የ48 ደቂቃ እና የ48 ሰከንድ የሆነው ትርፍ በ 400 ዓመት ሲሰበሰብ 96 ዕለት፣ 21 ሰዓት፣ 46 ደቂቃ እና 40 ሰከንድ ይወጣዋል። በጁሊያን ቆጠራ በየ4 ዓመቱ አንድ ዕለት ስለሚጨመር፣በ400 ዓመት የሚጨመረው 100 ዕለት ነው። ትክክለኛው ጭማሪ ግን በ400 ዓመት  96 ዕለት፣ 21 ሰዓት፣ 46 ደቂቃ፣ እና 40 ሰከንድ ነው። ይኸ 100 ዓመት ለመሙላት 3 ዕለት፣ 2 ሰዓት፣ 53 ደቂቃ እና 20 ሰከንድ ይቀረዋል። ስለዚህ በ400 ዓመት ውስጥ በትንሹ የ3 ዕለት ትርፍ ይፈጠራል።
የጎርጎርዮስ አቆጣጠር ያስተካከለው ይህንን ነው። የጁሊያን አቆጣጠር በየ4 ዓመቱ አንድ ዕለት ፌብሯሪ ላይ ይጨምራል። ይኸ በ400 ዓመት 100 ዕለት ይሆናል። የጎርጎርዮስ አቆጣጠር ግን በ400 ዓመት ውስጥ 97 ዕለት ብቻ እንዲጨመር አደረገ። በሌላ አገላለፅ በየ400 ዓመቱ የሦስት ዕለት ቅናሽ አደረገ።
ቅናሹ የተደረገው እንደሚከተለው ነው። በመቶ ብዜት በሚገኙ ዓመተ ምሕረቶች ለ400 ተካፍለው ቀሪው ዜሮ ከሆነ በዚያ ዓመት ፌብሯሪ በመደበኛው አካሔድ መሠረት 29 ይሆናል። አንድ ዕለት ይጨመርለታል። ቀሪው ዜሮ ካልሆነ ግን በዚያ ዓመት ፌብሯሪ የሚደረግለት ጭማሪ ይቀርና በ28 ይፀናል። በዚህ አካሔድ በ400 ዓመት ውስጥ የ3 ዕለት ቅናሹ ይከናወናል።
የኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠርም አንዱን የፀሐይ ዓመት የሚወስደው በተጠጋጋ ስሌት 365 ዕለት ከ 6 ሰዓት አድርጎ ነው። የ 6 ሰዓቱ ተረፍ በ 4 ዓመት 24 ሰዓት ወይም አንድ ዕለት ይሆናል። ይህ ዕለት ጳጉሜን በ4 ዓመት አንዴ 6 ያደርጋታል። (ይቀጥላል)

Published in ህብረተሰብ
Saturday, 05 September 2015 08:55

የነፃነት ጣምራ ክፋዮች

     ነፃነት በጥንድ እኩሌታዎች  መስተጋብር አውን የሚሆን ገጽ በረከት ነው። እኩሌታዎቹ እያንዳንዳቸው በራሳቸው የሚነጉዱበት ሐዲድ አላቸው። በእየራሳቸው ሐዲድ ላይ በተናጥል ሾረው በማሳረጊያው ቀለበቱ ይደፍናል። ያኔ የነፃነት ኡደት ተጠናቀቀ ይባላል፡፡ የመጀመሪያው ገሚስ ቀለበት ነፃነት ከምን (Freedom From )የሚለውን ግዙፍ ጽንሰ-ሐሳብ ውስጡ የታቀፈ ሲሆን ቀሪው እኩሌታ ደግሞ ነፃነት ለምን( Freedom For ) በሚለው ዓላማ ይገለጣል። ለምን እና ከምን የነፃነት አፍንጫና ዓይን ናቸው፡፡ በታሪክ ብዙ ሕዝቦች የመጀመሪያውን ጥያቄ መልሰው በሁለተኛው ላይ ለዘመናት ተንከላውሰዋል። በእንግሊዝ ቅኝ ግዛት ሥር የነበሩት ህንድና ፓኪስታን ሕዝቦች ከእንግሊዝ ቅኝ አገዛዝ ለመውጣት ከፍተኛ ትግል አድርገዋል። ከእንግሊዝ ቅኝ አገዛዛ ነፃ እንሁን (Freedom From ) ብለው ታገሉ፣ ተሳካ። ነገር ግን በነፃነቱ ማግስት  በቅኝ አገዛዝ ሥር ከነበሩበት በባሰ የኃይማኖትና የጎሳ ግጭት ውስጥ ተዘፈቁ። ያገኙት ነፃነት እሳት ሆኖ በላቸው። የመጀመሪያውን ግብ ማሳካት ለሁለተኛው ዋስትና ሊሆን አይችልም።
በ1789ኙ የፈረንሳይ አብዮት ወቅት ለዘመናት ከወህኒ ቤት ተከርችሞባቸው የኖሩ እስረኞች ከወህኒ ቤቱ ነፃ ከወጡ በኋላ ታስረው የነበሩበት ካቴና እንዲመለስላቸው ተማፅእኖ ያቀርቡ ነበር። ከወህኒ ቤት ነፃ መሆን (Freedom From )የመጀመሪያ እንጂ የመጨረሻ ግብ አይደለም። ለምን አላማ (Freedom For) ይከተላል።
ማርከስ ጋርቬይ፤ “Liberate the minds of men and ultimately you will liberate the bodies of men.” ማለቱ የነፃነትን ምሉዕ ኡደትን በላቀ ደረጃ ለማሳየት መውተርተሩ ነበር፡፡ በእርግጥም ነፃ አእምሮ ያልተሸከመ ሰውነት በድን ነው። የሥጋ ግዞት በአእምሮ መለቀቅ ያከትማል። የመጀመሪያው የነፃነት እኩሌታ አካልን እንጂን አእምሮ ነፃ ለማድረግ ዋስትና አይሰጥም፡፡ የሁለቱም የነፃነት ግማዶች አካሄድም ሆነ ግብ ለእየቅል ነው፡፡ አንዱ አንደ አንበሳ ደፋር፣ ሌላው ደግሞ እንደ እርግብ የዋህ መሆንን ይጠይቃል፡፡
በብረት ፍርግርግር ታሽጎ ሙዳ ሥጋ እየተጣለለት መቀለብ የለመደ አንበሳ፣ ድንገት ከዱር ቢለቀቅ እንደ ዱር አቻዎቹ ተሯሩጦ ለማደን ወኔው ይንሰንፋበታል፡፡ በጌቶቹ የሚወረወርለትን በድን ሥጋ ማወራረድ የለመዱት ሥል ጥርሶቹ፤ በድህረ ባርነት ወቅት  እግር ፣ ዓይን፣ የደም ዝውውር፣ እስትንፋስ ካለው ሥጋ ለባሽ ታዳኝ ፍጡር ጋር ይፋጠጣሉ። ድህረ ባርነቱ ይዞ የመጣው ብሥራት ብቻ ሳይሆን ፈተናም ጭምር ነው፡፡ ነፃነቱ የሚፈልገው ትጋት ከአንበሳው ዘንድ ስለነጠፈ ማሳረጊያው በጠኔ ተቆራምዶ ማክተም ይሆናል። ከብረት ፍርግርግ ማጎሪያ ነፃ መሆን……..ለቀጣዩ የነፃነት ምዕራፍ መንደርደሪያ  እንጂ  መቋጫ አይሆንም፡፡
ሊቢያዊያን የመሐመድ ጋዳፊ አምባገነናዊ አገዛዝ ግፍ አንገታችን ደረሰ ብለው አደባባይ ወጡ። ነፃነት ከመሐመድ ጋዳፊ በሚል መፈክር ለመጀመሪያው የነፃነት ቀለበት ውድ ሕይወታቸውን ከፍለው ማሳካት ቻሉ፡፡ በጋዳፊ አገዛዝ መቃብር ላይ አዲስ ስርዓት ተቀለሰ፡፡ በእዚህም ምክነያት በመላው ሊቢያ ፈንጠዝያ ሆነ። ሁሉም ሊቢያዊያን የወደፊት ሕይወቱ የተቃና፣ ብሩህ አድርጎ ደመደመ። በአካል የተፈቱት ሊቢያዊያን ለአአምሮ ነፃነት ዝግጁ ስላልነበሩ የምናየው መተላለቅ ገሃድ ሆነ፡፡ ቀን ሌት የባተቱለት ነፃነት ጠኔ እንደአላጋው አውሬ እያደባ ፍዳቸውን ሲያበላቸው ማስተዋል ከጀመርን ሰነባበትን፡፡ ከመሐመድ ጋዳፊ አገዛዝ ነፃነትን መቀዳጀት……የቀለበቱ ከፊል አካልን ቢገልጽ እንጂ ሙሉ ቁመናውን አይወክልም፡፡
የነፃነት ኡደትን በአግባቡ በማገባደዱ ረገድ የተሳካለቸው ሕዝቦች ነፃነትን እጀ ሰበራ አላደረጉትም። ልዕለ ኃያሏ አሜሪካ እንዲህ እንደአሁኑ የሰው ዘር በሙሉ በእልፍኟ ለመከተት የሚቋምጥባት ነፃ መሬት ከመሆኗ በፊት ዜጎቿ የሰላም ዓየር ለመተንፈስ ለዘመናት ቃትተዋል፡፡ የእንግሊዛዊያን የቅኝ-ገዢነት እብሪት በቀዳሚነት የፈነዳው በአሜሪካ ምድር ላይ ነበር፡፡ አሜሪካዊያን የቅኝ ግዛቱን ቀምበር ለመስበር ከወራሪው ኅይል ጋር አንገት ለአንገት ተናነቁ፡፡ ይህም ትግላቸው ፍሬ አፍርቶ   አብዝተው ከጓጉለትና ከባታተሉለት ነፃነት ጋር በዓይነ ሥጋ ለመተያየት በቁ፡፡ ከፊሉ ሥኬት ገሃድ ሆነ ማለት ነው፡፡ የነፃነቱ ኡደት ግን ገና በእንጥልጥል ላይ ነበር፡፡ ከእንግሊዝ ቅኝ አገዛዝ መላቀቅን እንደፍጻሜ የቆጠሩት አሜሪካዊያን ሳይውል ሳያድር በሰሜንና በደቡብ ጎራ ተከፋፍለው ጦር ሰብቀው እርስ በእርስ መፋለም ጀመሩ፡፡ በእዚህም ጦርነት ጦስ በ100 ሺ የሚጠጉ አሜሪካዊያን ጭዳ ሆኑ፡፡
ፍርቱና ግን ከአሜሪካዊያን ጋር ነበረች፡፡ እንደ አብርሃም ሊንከን ያለ ባለራዕይ መሪ ጥንግርግሩን የነፃነት ገጽታ ምሉዕ ለማድረግ በታሪክ ፊት ተሰየመላቸው፡፡ ሊንከን ነፃነትን በሞት፣ ሽረት ግብር ነው የገለፀው፡፡
America will never be destroyed from the outside. If we falter and lose our freedoms, it will be because we destroyed ourselves.
ይህ የአብርሃም ሊንከን ዲስኩር ከልቦናቸው ያደረው አሜሪካዊያን፤ መላው ዓለም የሚቀናበትን ሁለንተናዊ ብልጽግናን እንደ ዓይን ጥቅሻ ፈጥነው ለመፈጣጠም ብዙ አልተቸገሩም፡፡ በጥቂት አስርተ ዓመታት ውስጥ ሁሉም ነገር ተአምራዊ በሆነ ፍጥነት ተቀየረ፡፡ የመጀመሪያው የነፃነት ጥያቄ በአጣማጁና በቀሪው ቀለበት ኡደቱ ተገባደደ፡፡
ሰፊውን ሕዝብ እንደ ሙሴ የሚመራ ባለራዕይ መሪ ከፊት ለፊት ሲሰለፍ የኡደቱ ጎዳና የተቃና ይሆናል፡፡ አብርሃም ሊንከን አሜሪካዊያንን፣ጋንዲ ሕንዳዊያንን፣ማንዴላ ደቡብ አፍሪካዊያንን ከኋላ አሰልፈው ከቀሪውና ከወሳኙ የነፃነት እኩሌታ ጋር ያወዳጁ ታላቅ ሰብዕናዎች ናቸው፡፡
የእኛም ታሪክ በነፃነት እኩሌታዎቹ ፊት ባይተዋር አልነበረም፡፡ በአገም ጠቀምም ቢሆን በእዚሁ መሪር ሃቅ ስንደባበስ ኖረናል፡፡ መሬት ላራሹ በሚለው ተዋቂ መፈክር ሥር ሚሊየኖች ተስለፉ። የሚሊየኖች ትኩረት፣ በወቅቱ የነበረውን ጨቋኝ ዘወዷዊ አገዛዝ ከሥር ለመመንገል ነበር። ለጥቆ ስለሚመጣው ጉድ ግን ግድ ያለው አካል አልነበረም። ሕዝብን በሁለት ጎራ አሰልፈው ሲተጋተጉ የነበሩት ሁለቱ ትልልቅ ዘውግ-ዘለል የፖለቲካ ፓርቲዎች መኢሶንና ኢህአፓ ቢሆኑም የንጉሱን አገዛዝ መገዳደር ብሎም መጣል ላይ ያተኮረ የፖለቲካ ቁርጠኝነት እንጂ ከድህረ አብዮት በኋላ ሰፊውን ሕዝብ የስልጣን ባለቤት ማድረግ ስለሚቻልበት ጉዳይ ላይ መክረው ዘክረው የመፍትሄ አቅጣጫ ለማስቀመጥ ዝግጁ አልነበሩም። በእዚህም የተነሳ የአነስተኛ ወታደራዊ መኮንኖች ስብስብ የሆነው ደርግ በአቋራጭ አሳብሮ የሥልጣን  መዘውሩን በመጨበጥ ሠፊው ሕዝብ የጓጓለትን ነፃነት እንደ ጉም አበነነው፡፡
ኢህአዴግ ደርግን ለመደምሰስ ነፍጥ አንስቶ ፋኖ ተሰማራ ብሎ ጫካ ገባ። ይህንንም ጥያቄ ደርግን በመጣል መመለስ ቻለ።(Freedom From ) ወይም የኡደቱ እኩሌታን አሳካ። ነፃነትን ለምን ዓላማ(Freedom For) በሚለው ላይ ግን አሁን ድረስ ጥይት እርሳስ አስወንጭፎ ከማያባርረው ባለጋራ ጋር ፊት ለፊት እንደተፋጠጠ ይገኛል። ሁለተኛውን የነፃነት እኩሌታ ለመመለስ ሌላ ተፈጥሮና ሌላ ሰብእናን ይጠይቃል።
ከእዚህ መማር ካልተቻለ አዙሪቱ ይቀጥላል። የአንዱ አገዛዝ መተካት አንዱን ቀለበት ሸርፎ ከመውሰድ ጋር ይተካከላል፡፡ የስርዓቱ መተካት (Freedom From) አድራሽ እንጂ ፍጻሜ አይደለም።  በተቀረው የነፃነት ቀለበት ላይ ካልተሰራ ከቀደመው በባሰ አዘቅት ውስጥ መዳከርን ያስከተላል።
ነፃነት ከምን(Freedom From ) እውን ከሆነ በኋላ ነፃት ለምን(Freedom For) በሚለው ላይ የሚጠበብ ሆደ ሰፊ ግርማ ሞገስ ያለው ፖለቲካ አመራር ግድ ይላል። ይህ ኀይል ሠፊው ሕዝብ ትኩሳቱ እንዳይፈጀው አብርዶ የሚሰጠው፣ገፈቱን ገሸሽ እድርጎ የሚያስጎነጭ፣ የነፃነትን ሀሁ የሚያስቆጥር… ገራገር አገዛዝ፣መሪ መሆን ይገባዋል። ይህ ሲሆን ብቻ ነው ሁለተኛውን እኩሌታ በተገቢ መንገድ ማጣጣም የሚቻለው፡፡

Published in ህብረተሰብ
Saturday, 05 September 2015 08:53

የፀሐፍት ጥግ

(ስለ ግጥም)
- ግጥም በደስታ ተጀምሮ በጥበብ
ይቋጫል፡፡
ሮበርት ፍሮስት
- ማንኛውም ጤነኛ ሰው ያለ ምግብ
ለሁለት ቀ ናት ሊ ቆይ ይ ችላል፡፡ ያ ለ
ግጥም ግን አይሞከርም፡፡
ቻርለስ ባውድሌይር
- ለእኔም ለራሴ የማይገቡኝ ጥቂት
ግጥሞችን ፅፌአለሁ፡፡
ካርል ሳንድበርግ
- ሙዚቃን መተርጎም እንደማይቻል
ሁሉ፣ ግጥምንም መተርጎም
አይቻልም፡፡
ቮልቴር
- ለእኔ ግጥም ዓላማ ሆኖ አያውቅም፤
ፍቅር እንጂ፡፡
ኤድጋር አላን ፖ
- ዓይን የገጣሚ የማስታወሻ ደብተር
ነው፡፡
ጄምስ ረስል ሎዌል
- ግጥም የተጣራ ህይወት ነው፡፡
ግዌንዶሊን ብሩክስ
- ግጥም ከብርሃኑ መጨረሻ ያለው ዋሻ
ነው፡፡
ጄ. ፓትሪክ ሌዊስ
- ግጥም ል ክ እንደ ጨ ረቃ ም ንም ነ ገር
አያስተዋውቅም፡፡
ዊሊያም ብሊሴት
- ግጥም ሁሉ ቦታ አለ፤ የሚፈልገው
አርትኦት ብቻ ነው፡፡
ጄምስ ታት
- ግጥም ፈጠራ ነው፤ ገጣሚነት ዓለምን
ዳግም መፍጠር ነው፡፡
አሌክሳንድሬ ቪኔት
- ጸሎትህ ግጥም፤ ግጥምም ፀሎትህ
ሊሆኑ ይችላሉ፡፡
ቴሪ ጉይሌሜትስ
- ግጥም ግግር እሳት ነው፡፡
ጄ. ፓትሪክ ሌዊስ
- ግጥም ቢያንስ ውበት፤ ቢበዛ ራዕይ
ነው፡፡
ሮበርት ፊትዝጌራልድ
- በግጥም ትቀሰቅሳለህ፤ በስድ ፅሁፍ
ታስተዳድራለህ፡፡
ማርዮ ኩርኖ
- ግጥም ሙያ አይደለም፤ እጣ ፈንታ
ነው፡፡
ሚክሃዬል ዱዳን
- ገጣሚያን ዕውቅና ያልተሰጣቸው
ዓለም ህግ አውጪዎች ናቸው፡፡
ፔርሲ ባይሺ ሼሊይ

Published in የግጥም ጥግ

     በሀገራችን በሙያቸውም ሆነ በመልካም ምግባራቸው ከተገኙበት ዘመን አልፎ ተከታታይ ትውልዶችን የሚጠቅም ነገር ያደረጉ ብዙ ሰዎች አሉን፡፡ ይቻል እማይመስለውን ችለው ያሳዩን፤ ይሄድበት በማይመስል ጐዳና ተጉዘው አርአያ የሆኑን፤ በመረዳታቸው ምጥቀት ከፍ ብለው እኛንም ጨምረው ከፍ ያደረጉን የህልቆ መሣፍርት ባለውለታዎቻችን እዳ አለብን፡፡ መታደልም አለመታደልም ሆኖብን፤ በታደልን ጊዜ አንዳንዶቹን አመስግነናል፡፡
ካመሰገንባቸው ጊዜያት መካከል በአጼ ኃይለሥላሴ ዘመን ይሰጥ የነበረው ሽልማት አንዱ ተጠቃሽ ነው፤ ምንም እንኳ ሽልማቱ በሥነጽሑፍ ላይ የተለየ አትኩሮት ቢያደርግም፡፡ በደርግ ጊዜ ደግሞ በስልጣን ላይ የነበረው መንግሥት፣ የሀገር ባለውለታዎች ናቸው ብሎ ያመነባቸውን የጦር ጀግኖቹን፣ የአስረኛውን ዓመት የስልጣን ዘመኑን ሲያከብር ሸልሟል፡፡
ከደርግ ወዲህም የተለያዩ ተቋማት የሀገር ባለውለታ ናቸው ብለው ያመኑባቸውን ግለሰቦች አመስግነዋል፡፡ ይህን ያደረጉ ሁሉ በምላሹ ሊመሰገኑ ይገባቸዋል እላለሁ፡፡ በዚሁ ባለንበት መንግስት ተከታታይነቱን ጠብቆ ይኸው ለሦስተኛ ጊዜ የሚካሄደው የበጐ ሰው ሽልማት የቅርባችን ነው፡፡
የበጐ ሰው ሽልማት የተጀመረው በዲያቆን ዳንኤል ክብረት ጦማር ነው፡፡ ዲያቆን ዳንኤል የሀገር ባለሙለታዎችን አስቦ በሌሎች እንዲታሰቡ ማድረጉ በራሱ መልካም ሠሪ ያደርገዋል፡፡ ሰዎች በግል የተዋለላቸውን ውለታ እንኳ አስበው ለማመስገን አቅቷቸው ምክንያት በሚደረድሩበት በዛሬው ጊዜ ብዙ ኃላፊነት ያለበት ሰው የሚሊዮኖችን ባለውለታዎች በግለሰብ ደረጃ አስቦ መልሶ በሚሊዮኖች እንዲታሰቡ በማድረጉ እልፍ ምስጋና ይገባዋል፡፡
የበጐ ሰው ተሸላሚ መሆን አለበት ግን አላልኩም፡፡ ይህን ማለቴ ሽልማቱ ይገባዋል አይገባውም የሚል አተካራ ለማስነሳት አስቤ አይደለም፡፡ የበጐ ሰው ሽልማት ሥያሜው ስላልገባኝ እንጂ! “በጐ” ምንድን ነው? ምንስ ያደረጉ ሰዎች ናቸው በጐ የሚባሉት? መስፈሪያውስ ምንድን ነው - እገሌ በጐ ነው ለማለት አልያም ላለማለት? በጐ ሰዎችን ማወዳደር የተያዘስ ጊዜ አንዱን በጐ ሰው ከሌላው በጐ ሰው ማበላለጫው ምንድን ነው? በአንጻሩ ደግሞ ያልተሸለመው በጐ ሰው በምን ሲያንስ ነው እጩ ብቻ ሆኖ የሚቀረው?
እነዚህና ከእነዚህ የሚወለዱ አሊያም የሚዛመዱ ጥያቄዎች በውስጤ ይጉላላሉ፡፡
“እላይ ከቀረው ምንባብ ቀጥሎ ለተሰጡት ጥያቄዎች መልስ ስጡ” እየተባልኩ ተምሬ ስላደግሁ ነው መሰል ላንዳንዶቹ ጥያቄዎቼ ከራሱ ከሽልማቱና ከተሸላሚዎቹ መልስ ፍለጋ እገባለሁ፡፡ በጐ ማለት ለሌሎች የሚያዝንና የራሱን ምቾት ትቶ ለሌሎች መኖር የሚተጋ ማለት ቢሆን ነው፣ የሜቄዶንያው ቢንያም የተሸለመው ብዬ ትርጉሙ የገባኝ ሲመስለኝ፤ ለካ በዚያው ዓመት ታታሪዋ፣ በየእንግዶቿ ልክ ራሷን መመጠን የምትችለው፣ ጨዋታ ፈጥራ ጨዋታ የምታደምቀዋ፣ ቅዳሜ ዞሮ በመጣ ቁጥር ሸገር ላይ ቅዳሜያችንን የምታስውብልን፣ ስምን መላክ ያወጣዋል እንዲሉ ስሟ ግብሯን የሚገልጽላት መዓዛ አንዷ ተሸላሚ ነበረች፡፡ ይህን ሳስብ “በጐ ምን ማለት ነው?” ስል እጠይቃለሁ፡፡
ነፍሷን በገነት ያኑርልኝና አያቴ ብዙ ጊዜ ታማሚ ስለነበረች ስለ ጤናዋ ስትጠየቅ፤ “በጐ ነኝ” ነበር የምትለው፡፡ ፍጹም ጤነኛ ባልሆንም ከመክረሚያው ሻል ብሎኛል አይነት፡፡ ታዲያ “በጐ” ማለት ከከፋው ነገር የተሻለ ማለት ይሆን? “የበጐ ሰው ሽልማት ምን ማለት ነው?” መጠየቄን እቀጥላለሁ፡፡
“እገሌ እንዴት አሸነፈ?” ሲባል፣ “ብዙ ድምጽ ስለነበረው” ይባላል፡፡ (“ብዙ ድምጽ” የሚለው አባባል ከሌላ ቋንቋ የተቀዳ ስለሆነ እሱም ግራ አጋቢ ነው፡፡ ትርጉሙ አሸናፊው ከጉሮሮው የሚያወጣው የተለያየ ቅላጼ ኖሮት ሳይሆን ደጋፊዎቹ የሰጡት ይሁንታ ስለበዛ እንደማለት ነው አሉ)፡፡
እንዴ እንዴት ነው ነገሩ? ብዙዎች እንደሚያደርጉት በጐ ነገር እኮ በምላሹ በብዙዎች ላይታወቅ ይችላል፤ አሊያም ድጋፍ አሰጣጡ የቴክኖሎጂ እውቀትን ይጠይቃልና የሚገባቸውን ያህል ድምጽ ላያገኙ ይችላሉ፡፡ ይህ ደግሞ ተሸናፊ በጐ ሰው ያደርጋቸዋል፡፡
አዲስ አድማስ ጋዜጣ በነሐሴ 9 ቀን፣ 2007 ዓ.ም ዕትሙ የዘንድሮ በጐ ሰው ሽልማት እጩዎች ዝርዝር ወጥቷል፡፡ ከአቻምና አምና፣ ከአምናም ዘንድሮ ተሻሽሎ ይመጣል ብዬ የማስበው ድርጅት ልበል አሊያም ሰው (ይህንን ማለቴ አምና ለመጪው አመት ድርጅት ይሆናል ስለተባልን ነው፤ አሁን ድርጅት ይሁን ሰው አልገባኝም) ይባስ ጥያቄዎቼን አበዛቸው፡፡
ሰው ነው የምንሸልመው ተብለን ድርጅት ቀርቦልናል፡፡ (ምናልባት ሕጋዊ ሰውነት ስላላቸው እንደሆን እንጃ) ችግሩ ደግሞ ድርጅቶቹ የሃይማኖት ተቋም መሆናቸው ነው፡፡ ሕገ መንግሥቱ እንኳ መንግሥትንና ሃይማኖትን በነጣጠለበት በዚህ ጊዜ “በጐ ሰው” ብሎ ድርጅት ማጨት ብዙ ተፋልሶ እንዳለው ነው የተሰማኝ፡፡ በዚያ ላይ ደግሞ ይህንን የሽልማት ተቋም የጠነሰሱት ግለሰብ፣ከእጩዎቹ ድርጅቶች መካከል ያንዱ የቀድሞ ከፍተኛ ኃላፊ መሆን ለሃሜት ይመቻል፡፡
በጐነት ከሃይማኖት የተነጠለበት መስመሩ የቱ ጋ ነው? ከሃይማኖት ተቋማት መሃል የቱ ነው ይበልጥ በጐ? ያው ድምጽ አይደል ማሸነፊያውና መሸነፊያው? በድምጽ እንጠብቃለን፡፡ ብዙዎቻችን ያልተከለከልነው ነገር ተፈቅዶልናል ነውና እምነታችን፣ ይህንን ማድረግ በሕገ መንግሥቱ ስላልተከለከለ አንዱ ሃይማኖታዊ ድርጅት የበጐ ሰው እጩ ሆኖ ቀርቦልናል፤ መቼም የሚሸለመው አሸናፊው በጐ ነውና ተሸናፊውን ለማወቅ ጓጉቻለሁ፡፡
በዚሁ በዘንድሮው የበጐ ሰው እጩዎች ዝርዝር ውስጥ አንድ ሙያ ተጠቅሶ ተወዳዳሪዎቹም በስም ተዘርዝረዋል፡፡ ከእነዚህ መካከል አንጋፋና በሰው የጊዜ ሠፈራ ገና ብዙ ይሠራሉ የሚባሉት ወጣት ባለሙያዎች ባንድ ተመድበዋል፡፡ አሸናፊና ተሸናፊ ሊባሉ እመወዳደሪያው መድረክ ላይ ቀርበዋል፡፡
እንዲህ ግራ የገባው ሌላ ምድብም መልሶ ገጥሞኛል፡፡ ይኸውም በመልካም ሥራቸው ሊሸለሙ ከታጩት መካከል ወ/ሮ አበበች ጐበና እና ሌሎች ተወዳዳሪዎች የተዘረዘሩበት ነው፡፡ በጐነታቸው ገንኖ በሀገር የተሰማን ግለሰብ፣ ግራቸው ያደረገውን ገና ቀኛቸው እንኳ ካላወቀው ግለሰብ ጋር ማፎካከር ምን ማለት ነው?
ይሄን አስተያየቴን የጻፍኩት የበጎ ሰው መመዘኛ በቅጡ ስላልገባኝ ነው፡፡ እናም የበጎ ሰው ሽልማት፤ መልካም ሠርቶ መጥፎ ትዝታን ጥሎ ማለፍ እንዳይሆን፣ አዘጋጆቹ ጉዳዩን በጽሞና ቢመረምሩት ሸጋ ነው እላለሁ፡፡   

Published in ህብረተሰብ
Saturday, 05 September 2015 08:50

“ሌላ አገር ያለን…”

እንዴት ሰነበታችሁሳ!
ይቺን ስሙኝማ…አንድ ጊዜ አንድ ዳያስፖራ አገሩን ሁሉ ከበር መልስ ጋብዞ ጉድ ሊያሰኝ ይመጣል፡፡ ስንት መሰላችሁ የያዘው…ሁለት ሺህ ዶላር! እናላችሁ…የሆኑ አብሮ አደጎቹን ይዞ ማታ ይወጣል፡ ታዲያላችሁ…በየቦታው ሲገባ ለካ አገሪቱ የ‘ሎካል ዳያስፖራ’ አገር ሆናለች፡፡
እሱ በሁለት ብር ምናምን የመታተን ገንዘብ እየቆነጠረ ሲያወጣ ‘ሎካል ዳያስፖራዎች’…አለ አይደል…ከአንድ ኪስ ዶላር፣ ከሌላው ፓውንድ፣ ከሌላው ዩሮ ምናምን ሲመዙ ሲያይ፣ ምን አለፋችሁ… በቀን ሁለት ሰዓት ጂም የሚሠራው ሰው ልብ ድካም ሊይዘው ምንም አልቀረውም!  
እናላችሁ…ወር ሊቆይ የመጣው ሰው በሳምንቱ ተመለሰ እላችኋለሁ፡፡
ስሙኝማ… እንደ ሰሞኑ ከሆነ… አለ አይደል… “ምነው ሞንጎሊያም፣ ሀይቲም ብቻ የሆነ አገርም ሆነ ሚጢጢ ደሴት ሄጄ መንገድም ጠርጌ፣ ጠረዼዛም ወልውዬ፣ ኡበርም ነድቼ ዲያስፖራ በተባልኩ!” ያሰኛል፡፡
ልክ ነዋ…እኛ እዚህ እንደ ኮብልስቶን ከግራና ቀኝ እንላጋለን ‘ዳያስፖራ’ ደንቀፍ እንኳን ሳያደርገው… “እኔን ይድፋኝ!” አይነት ነገር እየተባለ አይደል!
በነገራችን ላይ አይደለም ኢንቬስት ሊያደርጉ በዓመት ሁለቴ ለቤተሰብ የሚልኳትን መቶ ዶላር እንኳን ወደ ሀምሳ የቀነሱ ያየን አንጠፋም፡፡፡
የምር ግን…እንግዲህ ጨዋታን ጨዋታ ያነሳው የለ… አንዳንድ ኮሚክ ነገሮች አሉ፡፡ እነእንትና ደግሞ ኮምፕ እንዳያስመስልብን ያላችሁት ነገር
እኔ የምለው… መቼ ይሆን ለእኛ የ“እንኳን ደህና መጣችሁ…” ሳይሆን፣ “ስንቱን ነገር ችላችሁ እንኳን አገር ውስጥ ቆያችሁ…” ተብሎ ልዩ የእራት ግብዣ የሚደረግልን! ልክ ነዋ…
በቀደም ሸገር በተደረገ ውይይት ላይ አንድ አስተያየት ሰጪ የሆነ ፕሮጀክት ለመተግበር የደረሰባቸውን መንገላታት ሲገልጹ አንድ ያሏት ነገር አለች፡፡ ምን አሉ መሰላችሁ…
“ሌላ አገር ያለን ነው የሚመስለኝ…” አሪፍ አባባል አይደል፡፡
“ሌላ አገር ያለን ነው የሚመስለኝ…” ከማለት ይሰውረንማ!  
ስሙኝማ…እንግዲህ ጨዋታም አይደል… እኛ ‘ቤት ጠባቂዎቹ’ ምንም ነገር ላይ ‘ፕሪቪሌጅ’ ምናምን የማይሰጠንሳ! እንደውም ‘ፕሪቪሌጅ’ ማግኘቱ ይቅርብንና ወረቀቱ ላይ በተቀመጠው እንኳን የማስተናግድሳ!
አንዳንዴ ትንሽ ይሄ የግለኝነት ነገር እናያለን፡
“መኖሪያ ቤት ይሰጠን…”
“ቤት የምንሠራበት ቦታ ይሰጠን…”
“ልዩ አስተያያት ይደረግልን…”
ምናምን አይነት ‘እኔ፣ እኔና እኔ ብቻ!’ አይነት ቃና ያላቸው አስተያየቶች ስንሰማ…አለ አይደል…የሆነ የማይመች ነገር አለው፡፡
ልክ ነዋ…ለስንትና ስንት ዓመት መኖሪያ ቤት እንዲሰጣቸው የሚጠብቁ ስንት መቶ ሺህ ምስኪኖች ባሉባት አገር፣ ለስንትና ስንት ዓመት የድርጅት መገንቢያ ምቹ ቦታ በአቅማቸው እንዲሰጣቸው የሚጠብቁ የአገር ውስጥ ባለገንዘቦች እያሉ… “ልዩ አስተያየት ይደረግልን…” “ቅድሚያ ይሰጠን…” ምናምን አይነት አባባሎች አሪፍ አይደሉም፡፡  
አገር ማለት እኛ አይደለን! ልክ ነዋ…“ፕሪቪሌጅ ይሰጠን፣” “ማበረታቻ ይመቻችልን…” ምናምን ማለቱ ቀርቶ ፈረንካው ያላቸው… አለ አይደል… ፈራንካቸውን ሆጭ አድርገው ፋብሪካውን፣ አንዱስትሪውን፣ ትላልቅ እርሻውን…ምናምን መሥራት አሪፍ ነው፡፡
የምር…ለኢንተርኔት ካፌው፣ ለምግብ ቤቱ፣ ለሞባይል መሸጫው ምናምን ለመክፈት እኮ የእኛ ባለፈረንካዎች ይበቃሉ፡፡
ለክፉም ለደጉም… አንዱን ዳያስፖራ እናናግረውማ፡፡
እኛ፡— እሺ ዳያስፖራ ወዳጄ…በሽ አደረግናችሁ አይደል!
ዳያስፖራ፡— ወዳችሁ ነው፡፡ በሽ ባታደርጉን ወደመጣንበት ተመልስን ለሽ ነዋ የምንለው፡፡ ያኔ ማን መጥቶ ኢንቬስት እንደሚያደርግ እናያለን፡፡
እኛ፡— እሱ ላይ እንኳን ስቀህ አታስቀን፡፡ ይልቅ… ‘ለምን ይዋሻል!’ የምትባል አነጋገር ሰምተህ ታውቃለህ?
ዳያስፖራ፡— እ…ሌት ሚ ሲ… ዲሲ ሬስቱራንት ውስጥ የሰማሁ መሰለኝ፡፡
እኛ፡— ለምን ይዋሻል ከመባባላችን በፊት… ጥያቄ እንጠይቅህ…
ዳያስፖራ፡— ፕሊስ…
እኛ፡— ለምሳሌ አንተ አሜሪካ ከሄድክ ስንት ጊዜህ ነው?
ዳያስፖራ፡— አሥራ ምናምን ዓመት…
እኛ፡— እና አሁን ምንድነው የምትሠራው?
ዳያስፖራ፡— የምሠራው ምን ያደርግላችኋል…
እኛ፡— ኢንቬትስ ልታደርግ አይደል እንዴ የመጣኸው!
ዳያስፖራ፡— ዌ…ል…
እኛ፡— እሺ፣ ስንት ዶላር አጠራቅመሀል…ምነው ተኮሳተርክ?
ዳያስፖራ፡— ስንት ዶላር አጠራቅመሀል ነው ያላችሁኝ…
እኛ፡— አዎ፣ ስንት አጠራቅመሀል?
ዳያስፖራ፡— ምን ነበር ሲሉ የሰማሁት…ቆይ፣ ሌት ሚ ቲንክ…አዎ፣ ሙድ እየያዛችሁብኝ ነው እንዴ!
እኛ፡— ምን በወጣህ…
ዳያስፖራ፡— አይ ማጠራቀም…የእኔ ጌታ የቤቱ፣ የመኪናው፣ የሶፋው፣ የፍሪጁ ምናምን ብድር አናቴ ላይ እያናጠረ ስንት አጠራቀምክ ትሉኛላችሁ!
እኛ፡— ታዲያ ምንህን ነው ኢንቬስት የምታደርገው?
ዳያስፖራ፡— ማን ኢንቬስት አደርጋለሁ አላችሁ!
እኛ፡— አሀ… በቀደም እዛ አዳራሽ መዳፍህ የዝንጀሮ እንትን እስኪመስል ስታጨበጭብ በቲቪ አላየንህም…
ዳያስፖራ፡— ‘ኮምፕሌክስ’ ነው እንዴ..
እኛ፡— ተው እባክህ…አሁን እኮ ስንትና ስንት ሎካል ዳያስፖራዎች አሉ መሰለህ…ይልቅ እናንተ ፈረንካ ባይኖራችሁ እንኳን በአንዳንድ ነገር ዕድለኞች ናችሁ…
ዳያስፖራ፡— እንዴት ማለት…
እኛ፡— እንዴት ማለትማ… ማንም አይጨቀጭቃችሁ፣ ‘አንዳንድ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች’ ልክ ልካችሁን አይነግሯችሁ፣ አዲስ ሸሚዝ በለወጣችሁ ቁጥር ገንዘብ ከየት አምጥቶ ነው አይሏችሁ፣ ከእነእከሌ ጋር መዋል አብዝቷል ተብላችሁ አትፈረጁ…በሆነ ባልሆነው ወዮላችሁ አትባሉ… ይሄ ሁሉ ግን እርስ በእርስ ያላችሁን ግንኙነት አይመለከትም፡፡
ዳያስፖራ፡— ጀስት ኤ ሚኒት… ትኩረት ሲሰጠን ምን ያበሳጫችኋል..
እኛ፡— እንደውም፡ ከተበሳጨንም የሚያበሳጨን እናንተ ትኩረት ማግኘታችሁ ሳይሆን እኛ ችላ መባላችን ነው….እንደ እናንተ እንክብካቤ ለማግኘት የግድ ውጪ አገር መሄድ አለብን እንዴ! ስማማ…እኛ ገንዘቡ እንዳለ ሆኖ በጣም የሚያስፈልገን ምን እንደሆነ ታውቃለህ?
ዳያስፖራ፡— ምንድነው?
እኛ፡— ዕውቀት! ይሰማሃል…ያስቸገረን የዕውቀት እጥረት! የተማሩ የበቁ፣ የነቁ ዳያስፖራ ሀበሾች ዕውቀታቸውን ይዘው ቢመጡልን አሪፍ ነው፡፡
የምር ግን…አለ አይደል…አቅም ያላቸው ወገኖቻችን ከየትም ቢመጡ ከየትም አሪፍ ነው፡፡ ገንዘብ ያስፈልገናል፣ ዕውቀት ያስፈልገናል…ብዙ የሚያስፈልጉን ነገሮች አሉ፡፡ ግን ደግሞ…‘እንደ ስለት ልጅ ተንከባከቡን’ አይነት አሪፍ አይደለም፡፡ እዚህ ያለ ዜጋ አልፈታለት ያሉ አንድ ሺህ አንድ ችግሮች አሉበት፡፡ እናማ…ምን መሰላችሁ…ከልጅ ልጅ መለየት ሳይሆን የሁሉም ችግሮች አንድ ላይ የሚፈቱበት ነገር ቢኖር አሪፍ ነው፡፡
እናማ አቅም ያላቸው… “እንደ ዕንቁላል ሳሱልን…” ምናምን አይነት ነገር ቀንሰው ፈረንካቸውን ሥራ በሚፈጥሩና ምርት በሚያስገኙ ነገሮች ላይ ቢያውሉ አሪፍ ነው፡፡
እግረ መንገዳችንን… አሰሱን ገሰሱን ይዘው የሚመጡ ዳያስፖራ ወገኖቻችን እንዳሉም ማስታወሱ አሪፍ ነው፡፡  በቀደም በአዳራሹ ከሞላው አንድ መቶኛው እንኳን ኢንቬስት ቢያደርግ ስንትና ስንት ሰው የሥራ ዕድል ያገኝ ነበር፡፡
ብቻ እስከ ተከታዩ ዓመት የዳያስፖራ በዓል አዳራሹን ሞልቶት ከነበረው ህዝብ ስንቱ “ይኸው ኢንቬስት ለማድረግ ካጠራቀምኩት ጥሪት ቀንሼ አምጥቻለሁ…” እንደሚልና ስንቱ ደግሞ “ለምንድነው ለመኖሪያ ቤት መሥሪያ ቦታ እስካሁን ያልተሰጠን…” እንደሚል ለማየት ያብቃንማ!
“ሌላ አገር ያለን ነው የሚመስለኝ…” ከማለት ይሰውረንማ!  
ደህና ሰንብቱልኝማ!

Published in ባህል

የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር፤ ከ900 በላይ የቤተ ክርስቲያኒቱን ልኡካን እያወያየ ነው
“እንደ ሌላው መድረክ አታስቡት፤ ለዓላማና ለለውጥ የሚደረግ ጉባኤ ነው” /ሚኒስትሩ/

      በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት፣ በቤተ ክርስቲያኒቱ ንብረቶች አላግባብ ሀብት ያፈሩና ለግል ጥቅማቸው ሲሉ ቤተ ክርስቲያኒቱን ለምዝበራ ያጋለጡ የአድባራት ሓላፊዎች ጉዳይ በሕግ እንዲታይ የቀረበውን ውሳኔ ቋሚ ሲኖዶስ አጸደቀ፡፡
በሙሰኛ የአድባራት ሓላፊዎች ላይ ለተላለፈው ውሳኔ መሠረት የኾነውንና በ58 አድባራት የገቢ ማስገኛ ተቋማት ዙሪያ በሚታዩ የአፈጻጸም ችግሮች ላይ የተዘጋጀውን ጥናታዊ ሪፖርት ያዳመጠው ቋሚ ሲኖዶሱ፣ የመፍትሔ ሐሳቦቹንም በሙሉ ድምፅ ተቀብሎ ለጠቅላይ ጽ/ቤቱ ተጨማሪ መመሪያዎችን ሰጥቷል፡፡
ለቤተ ክርስቲያኒቱ መገልገያነት ከመንግሥት የተሰጡ መሬቶች፣ የተገነቡ ሕንጻዎች፣ ሱቆች፣ መካነ መቃብርና ሌሎች የገቢ ማስገኛ ተቋማት ሕጋዊ፣ ፍትሐዊና ቤተ ክርስቲያኒቱን ተጠቃሚ በማያደርጉ ውሎች ለሦስተኛ ወገን እየተከራዩ ለግለሰቦች በመሸጥ ላይ እንደኾኑ ጥናታዊ ሪፖርቱ ይዘረዝራል፡፡የአድባራት ሓላፊዎች ጥፋት በሕግ አግባብ እየታየ ክሥ ለመመሥረትም፤ ጥናቱ በሸፈናቸው አድባራትና ገዳማት የተደረጉ ሕገ ወጥ ውሎች የተፈጸሙበትን ትክክለኛ ጊዜ፣ የወቅቱን የአካባቢ የመሬት ዋጋ፣ በውል አሰጣጡ የተሳተፉ ሓላፊዎችና የመሳሰሉት ዝርዝር መረጃዎች በጠቅላይ ጽ/ቤቱ ተጣርተው መታወቅ እንደሚገባቸው ቋሚ ሲኖዶሱ ለጠቅላይ ጽ/ቤቱ ተጨማሪ መመሪያ ሰጥቷል፡፡
በተያያዘ ዜና፣ የሀገረ ስብከቱን የአድባራት አስተዳዳሪዎች፣ ማኅበረ ካህናት፣ ሰባክያነ ወንጌል፣ የሰንበት ት/ቤቶች ሊቃነ መናብርት እና የአንድነት አመራሮች በተናጠል ሲያነጋግር የቆየው የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር፣ ከትላንት ጀምሮ ኹሉንም አካላት ያቀፈ የማጠቃለያ ውይይት በማካሔድ ላይ ነው፡፡
937 ያኽል የቤተ ክርስቲያኒቷ ልኡካን በሚሳተፉበት በዚኹ የኹለት ቀናት ውይይት፣ በሃይማኖት ተቋማት የውስጥ አሠራር ችግሮች ላይ ያተኰረ ጽሑፍ በሚኒስትሩ ዶ/ር ሺፈራው ተክለ ማርያም የቀረበ ሲኾን በቡድንና በጋራ ውይይት ይካሔድበታል፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቀደምትና ጥንታዊት መኾኗን ያወሱት ሚኒስትሩ÷ በአካባቢና በጥቅመኝነት ላይ የተመሠረተ የሰው ኃይል አሿሿምና አመዳደብ፣ ግልጽነት በጎደለው የፋይናንስ ዝውውርና አጠቃቀም በውስጥ የሚነሣው አለመግባባት እየሰፋ መምጣቱ ጥያቄ እያስነሣ መሆኑን አብራርተዋል፡፡
እኔ ብቻ ልጠቀም በሚል ከሕግና ሥርዐቱ ውጭ የመንቀሳቀስ ስሜት በራሱ የሚፈጥረው አደጋ እንዳለ ያሳሰቡት ዶ/ር ሺፈራው፣ መድረኩም እንደሌላው መርሐ ግብር የሚታይ ሳይኾን ለዓላማና ለለውጥ የሚካሔድ የምክክር ጉባኤ ነው በማለት ውይይቱን ተከትሎ በተከታይ ሊወሰድ የሚችል ርምጃ እንደሚኖር ጠቁመዋል፡፡

Published in ዜና
Page 14 of 16