ACTION! “

… የመጀመሪያው የሕዝብ ሲኒማ ቤት በ1890 ዓ.ም በአዲስ አበባ ተከፈተ። ሲኒማ ቤቱን የከፈተው አንድ ከአልጄሪያ የመጣ ፈረንሳዊ ነው። ይህን በዘመኑ የማይታመን ምትሀት መሰል ነገር የሚያየው ሕዝብ፤ የሲኒማ ቤቱን ‹‹ሰይጣን ቤት›› ብሎ ሰየመው። በተለይ ቀሳውስቱ #ሕዝቡ ከሰይጣን ቤት እየሄደ ሰይጣን እንዳያይ$ እያሉ ስላወገዙ ሲኒማ ቤቱ ከሰረ።$ (‹‹አጤ ምኒሊክ›› ከጳውሎስ ኞኞ - ገጽ - 337 - ‹‹ሲኒማ››)

          ስንት ውበት ጋረደን የነጎደው ዘመን ግዝት ሀይ ባይ አጥቶ የአዲስ ጥበብ ጥቅሻ ፀዳል ብርሃኗን ፈገግታዋን ፈርቶ አምናን የ ሀገር ሰው አ ይኑ ሲ ራብ ኖረ ቀ ድሞ! - ጭራ ቀርቶ! /‹‹ውበትና ዘመን›› - ያልታተመ።/ እነሆ፤ የፊልም ጥበብ፤ በየትም ስፍራ የመገኘት ልዩ ባህሪው፤ ከሰው ልጆች የእለት ተዕለት ህይወት ጋር ያለውን ቁርኝት ከፍተኛ ደረጃ ላይ አድርሶታል። በ2009 እ.ኤ.አ ፊልም በብዛት በሚታይባቸው ሀገራት የተደረገ ጥናት፤በአንድ አመት ብቻ 6.8 ቢሊዮን ያህል የፊልም መግቢያ ቲኬቶች መሸጣቸውን አረጋግጧል። ከአለም የህዝብ ቁጥር ጋ የሚስተካከል እንደማለት ነው። የቦክስ ኦፊስ ገቢውም 30 ቢሊዮን ዶላር አስመዝግቧል። በዚያው አመት ከተለያዩ የቴሌቪዥን ቻናሎች የተሰባሰበውና 1.1 ቢሊዮን ብዛት ያላቸውን የዲቪዲና ብሉ ሬይን ሽያጭ ጨምሮ በአሜሪካ፣ ካናዳና አውሮጳ ብቻ 35 ቢሊዮን ዶላር አስገኝቷል።

የጥቁር ገበያው ገቢ ሲታከልበት ደግሞ ድምሩ አናት የሚያዞር አሀዝ ያመጣል። ትዝታ ለመምዘዝ ያህል፤እግረ መንገድም ለመነቃቃት፤ጥናቱ የተደረገበት ዘመን፤ኢትዮጵያዊው የፊልም ባለሙያ ፕሮፌሰር ሀይሌ ገሪማ፤ ‹‹ጤዛ›› በተሰኘው ፊልሙ ለበርካታ አለማቀፍ ሽልማቶች የታጨበትና ያሸነፈበት፤በተለይም የታላቁን የፓን አፍሪካን ፊልም ፌስቲቫል FESPACO AWARD ሽልማት፤በአፈ ታሪክ የስምንት ወንዶችን ጉልበት በሚያንበረክከው ጥንካሬዋ በምትታወቀው የምዕራብ አፍሪቃዋ ቡርኪናፋሶ ጥንታዊት ጀግና ንግስት ይኔንጋ እና ፈረሷ ምስል STALONE OF YENENGA በቡርኪናቤ ጠቢባን ቀጥቃጮች በነሀስ የሚሰራው ውብ ቅርፅ TROPHY በስፍራው የፊልማችን አገራዊ ፋይዳ በወኪልነት በተገኘችው እህቱ በወ/ሮ ሶሎሜ ገሪማ በኩራት ከፍ ብሎ የተነሳበት አመት ነበር - 2009 እ.ኤ.አ ።

ምንም እንኳ ትውስታው አሁን ከላይ ለጀመርነው ኢኮኖሚያዊ ንፅፅር ባይበጅም። እትዬ ሶሎሜም ይኸው የኢኮኖሚ መራራቅ ገብቷት ይመስላል፤ ሽልማቱን ስትቀበል በሰፊው የቡርኪናፋሶ ስታዲየም ለታደሙት ከአለም ዙሪያ ለተሰበሰቡ የፊልም አለም ሰዎች ባደረገችው ንግግሯ፤የነጻነት ታጋዩን የማርቲን ሉተርን I HAVE A DREAM ሀረግ ተውሳ ፤ ህልሟን ግን ‹‹አንድ ቀን አፍሪቃ የራሷ መገበያያ ገንዘብ እንዲኖራት›› ለመመኘት የተጠቀመችበት። የፊልም ሙያ፤ በሰው ልጆች የኢኮኖሚ ዑደት ውስጥ ያለው ፋይዳ ላቅ ያለ ነው። ለምሳሌ፤ የእንግሊዝ ካልቸር፡ሚዲያና ስፖርት ኮሚቴ፤ፊልም በብሄራዊው ኢኮኖሚው ውስጥ ያለውን ግብአት አስመልክቶ ስለ ብሪቲሽ ፊልም ኢንዱስትሪ በ2001 እ.ኤ.አ ባቀረበው ሪፖርት ላይ…‹‹በ2001 እ.ኤ.አ ለጉብኝት ወደ ሀገሪቱ ከተመሙትና ለብሪቲሽ ቱሪስት ባለስልጣን visit britain መስሪያ ቤት 11.3 ቢሊዮን ፓውንድ ካስገኙለት 23 ሚሊዮን ቱሪስቶች መካከል 20 ከመቶው ስለ ሀገሪቱ ውበትና የህዝቦቿ ዘመናዊ አኗኗር፣ በፊልምና ቴሌቪዥን በቀረቡት መሳጭ ትእይንቶች ተማርከው የተጓዙ ናቸው።

እንዲሁም፤ በእንግሊዝ እያንዳንዱ ለፊልም ስራ የሚወጣ አንድ ፓውንድ በምላሹ የ1.50 ፓውንድ ትርፍ በማስገባት ኢኮኖሚውን ያስመነድጋል። ከ ራሳችን አ ንፃር ለ መመዘን የ ሚያበቃ አስተማማኝ የገቢና ወጪ መረጃ ቋት እስካሁን የለንም። ሆኖም ግን ይኼ ጊዜ፤ ከፋም ለማም፤ በሀገራችን የፊልም ሙያ በብዛት የተትረፈረፈበት ዘመንና መንግስት፣ ባለሞያዎችና በዘርፉ የተሰማሩ ሁሉ ከየትየለሌ ተግዳሮቶቹ ጋ የየድርሻቸውን የሚቆነጥሩበት ጅማሬ ዘመን ለመሆኑ ምስክሩ ገሀዱ እውነት ነው… ዛሬ እዩት ምዕመኑን ወረፋ ሲጋፋ ‹‹ሰይጣን›› ማየት ሽቶ የሀገሬም ጠቢብ አምሮበት ተውቦ ‹‹ያይኔ ምሳ›› አምርቶ እዩት ‹‹ሴጣን ቤቱ››ም በሰዎች ሲሞላ መቶ አመት ቆይቶ። በመልካም ገፅታ ግንባታው በኩል ግን ፤ ዛሬ ዛሬ በአለም አቀፍ መድረክ ኢትዮጵያን ወክለው የሚቆሙ የፊልም ጥበብ ውጤቶች ባመዛኙ ከይዘትና ቅርፃቸው አኳያ ቢበረበሩ ከመሆን አይድኑም። በተለይም፤ ችግሮችን በፊልም ሙያ አጉልቶ ማሳየት ተገቢነቱ ባይካድም፤ ስንትና ስንት ያልተነኩ ታሪካዊ፣ ባህላዊ፣ ተፈጥሯዊና ማህበራዊ እሴቶች ሞልተውን፤የበጃች ባዕዳንን ትኩረት ለማግኘት ሲባል ፤ የሀገርን ገመና የማስጣት ልምምዶች ባመዛኙ በጭብጥ ምርጫዎችና በተለይም ደግሞ የአጫጭር ፊልሞቻችን መልክ እስኪመስል ድግግሞሹ ተስተውሏልና።

ስለዬህም፤ለንባባችን ማንሸራሸሪያ የተሰደረው ስንኝ፤የሚጠቁም-የሚማፀነው፤ ዛሬም ድረስ በምዕራባዊያን የዜና አውታሮች ብቅ እያለ የሚያስበረግገን፤ ጆናታን ዲምቢልቢ የ1966ቱን ድርቅ አስመልክቶ ስለ ኢትዮጵያ ያቀረበው ዘጋቢ ፊልም፤ የአንድ ወቅት የድህነትና ጉስቁልና ምስል /Distorted Image/ እስከወዲያኛው ይቀረፍ ዘንድ ፤አልፎ አልፎ ጎልተው የሚወጡ የተቆርቋሪ ኢትዮጵያዊያን የፊልም ባለሙያዎች ‹‹በፊልም የጠፋውን መልካችንን በፊልም እንቀይረው›› ድምፆች ከቁጭትም ባለፈ ተግባራዊ ምላሽ መሻታቸውን ነው። እልፍ ውግዘት ሰፍሮብን ኮድኩዶ ያኖረን ራዕይ አራቁቶ ከውበት ቆሌ ያራቀን የካቻምናን ክብር አመንምኖ አክስቶ አለሙም የሚያውቀን በተጠናገረው የዲምቢልቢ ፎቶ። የፊልም ጥበብ፤ ለባህል፡ለትምህርት፡ ለመዝናኛና ለፕሮፖጋንዳነት የሚውል ጡንቻማ መሳሪያ ለመሆን ችሏል። በ1963 እ.ኤ.አ ብሎዶን ዲሂንግራ ለዩናይትድ ኔሽን የትምህርት፣ ምርምርና ባህል ክፍል ባጠናቀሩት ሪፖርት ላይ የጠቅላይ ሚኒስትር ኔህሩን ንግግር እንደጠቀሱት…‹‹በህንድ፤ የፊልም ሙያ በመላው ህዝብ ላይ የሚያሳድረው ተፅእኖ፤ባጠቃላይ የጋዜጦችና መጻሕፍት ህትመቶች ሁሉ ተደምረው ያላቸውን አቅም ያስከነዳል።›› ብለዋል።

የህንድ የፊልም ገበያ በየሳምንቱ ለ25 ሚሊዮን ዜጎች ልዩ ልዩ የስራ ዘርፎችን አስገኝቶ፣ የዕለት ተዕለት ቀለባቸውን ይሰፍር የነበረው ገና ያኔ ከግማሽ ምእተ አመት በፊት ነበር። በ ቅርቡ በ ፊልምና ማ ህበረሰብ ዙ ሪያ በማጠንጠን የ ሚቀርቡ ጥ ናቶች ደ ግሞ፤ የ ፊልም ሙያ ከሰው ልጆች ስነ ልቦና ጋር ያለውን ግንኙነትም ዳስሰዋል። በ2005 እ.ኤ.አ ኖህ ሁህሪግ “‘Cinema is Good for You: The Effects of Cinema Attendance on Self-Reported Anxiety or Depression and ‘Happiness’” በሚል ርዕስ ለኢሴክስ ዩኒቨርሲቲ (University of Essex, UK) ባቀረቡት …የፊልም ጥበብ፤ያቀራረቡ ማራኪነትና ረቂቅነት በሰው ልጆች የአዕምሮ ጤና ላይ ጉልህ ፋይዳ እንዳለው ጠቁመዋል። ፊልም፤ በየትዕይንቶቹ የሚያቅፋቸው ድርጊያዎች ያላቸው ከድብርት የማላቀቅ፣ አእምሮን የማነቃቃትና መላ አካልን የማዝናናት ሀይል፤ ለተመልካቾች ነፃነትንና ዕድለኝነትን በመቸር /በህይወት ዘመናቸው በተአምር ሊደርሱበትና ሊያዩት እንደማይችሉ የሚያስቡትን አካባቢና አርዕስተ ጉዳይ ወይም በሩ…ቁ ያሉ ድንቅ ስብዕናዎችን… አይናቸው ስር ድቅን በማድረግ/ ላቅ ያለ የማይዳሰስ ስሜትና እርካታን ስለማጎናፀፉ ጉዳይ…ወዘተ::

በተጨማሪም ደግሞ ዘመኑ የፈጠረው ቴክኖሎጂ /ከአናሎግ - ዲጂታል/ ፊልምን ተደራሽነቱ በኢኮኖሚ ያልተገደበ እንዲሆን፤ ማንም ሰው ያሻውን ፊልም መርጦ የማየት እድልን አስገኝቶለታል ይላሉ። ሌላው እጅግ አስገራሚ የተባለውና በኮንላን፣ ቢግሬን እና ጆሀንሰን በ2000 እ.ኤ.አ የቀረበው የጥናት ውጤት ደግሞ ‹‹ፊልምን ደጋግመው የሚያዩ ሰዎች የመሞቻ እድሜያቸው የተራዘመ ነው። በዚሁም መሰረት ፊልምን የማያዩ ሰዎች ቢያንስ አንዳንዴም እንኳን ወደ ሲኒማ ቤት በመሄድ ከሚዝናኑ የፊልም ተመልካቾች ጋር ሲነፃፀሩ፤ የመሞት እድላቸው ስሌት በአራት እጥፍ የተራዘመ ነው።›› ይላል። የሦስቱ ምሁራን ጥናት የሚያመላክተው፤ሌሎች የማህበራዊ ተሳትፎዎቻችን በተገደቡበት ሁኔታ ውስጥ ሆነንም እንኳ፤ ከኪነ ጥበባት ውጤቶች ጋር ያለንን ትስስር መቀጠል መቻል፤ በህይወት ከመቆያ ተመራጭ መንገዶች አንዱ መሆኑን ነው። ‹የደላው ሙቅ ያኝካል›ን የሚተርት ቢኖር አይደንቅም። በአሜሪካዊያኑ ዘንድ በስፋት ተነባቢ በሆነው፤ ዛሬ ወጣቶቹ ኢትዮጵያዊያን የፊልም ባለሙያዎች እነ ዘረሰናይ ብርሀነ በተደነቀላቸው ‹‹ድፍረት›› በሯን ካንኳኩት ከአለም የፊልም መዲና ከሆሊዉድ አመሰራረት ጀምሮ፣ ስለ ፊልም ሙያ ዝርዝር መረጃ በተካተተበት An Empire of Their Own መጽሀፍ ደግሞ፤ ጥበቡ ከገንዘብ ምንጭነቱ ባሻገር በማህበረሰብ ላይ ስለሚያሳርፈው አሻራ ትንታኔ ይሰጣል።

ጸሀፊው ኒል ጋብለር፤ ‹‹በእኔ እምነት፤ የፊልም ሙያ በእለት ተዕለት ማህበራዊ ህይወት ላይ ተፅእኖ በማሳደር ማህበረሰቡን ክፉኛ ሊያንገዳግድ ይቻለዋል። እናም የዚህ ዘርፈ ቡዙ ተፅእኖ ጉዳይ ኃላፊነትን የሚጠይቅ ነገር ነው። ማህበረሰብ የተሸመነበትን የባህላዊና መንፈሳዊ እሴቶች እንዲያሰናስል እንጂ እንዳያነትብ ብርቱ ጥንቃቄን የሚሻና ይኸውም ባለሞያውን ግድ ሊለው የሚገባ ነው። የሆሊዉድን ነገር ስናየው ግን ይህን ኃላፊነት የዘነጋ ይመስላል። ዋናው ትኩረት ገቢ ማግኘቱ ላይ ሆኗል። የግብረገብ ጉዳይ ተዘንግቷል። የስነ ምግባር መመሪያዎች የሉም። ምን ያህሉ ፊልሞች ናቸው በጎ ምግባርን የሚሰብኩት?›› ሲሉ ይጠይቃሉ። በበኩሌ ምላሼ ‹‹አዎአይ›› ነው። ምክንያቱም፤ እንደ ኒል ጋብለር፤ አሜሪካዊያን የፊልም ባለሞያዎች ለመላው የሰው ልጆች በሚበጁ ፋይዳዎች ላይ እንዲጠመዱ ጫና ማሳደር መልካም ቢሆንም፣ ልናስገድዳቸው አለመቻላችን ተስፋችንን የተቀነበበ ያደርግብናል እንጂ ምኞቱስ ባልከፋ።ደግሞም አሜሪካዊያኑ የራሳቸውን በጎ መልክ ከፍ አድርገው ከማሳየት ቦዝነው አያውቁም። ባቀራረብም ሆነ በጭብጥ ምርጫ ለዚህ ይተጋሉ።

ብዙ ምሳሌዎችን መጥቀስ ይቻላል። ሩቅ ሳንሄድ፤የዋይት ሀውስ ቀጭን ትዕዛዝ ፕሮዳክሽን ነው በሚባለውና መንታ ህንፃዎቻቸው በፈረሱ ማግስት አጣድፈው ባወጡት Flight 93 ፊልማቸው፤ ያልተፈጠረ ታሪክ አቀናብረው፤ የአይበገሬ አሜሪካዊ አርበኝነትን ስነ ልቦና በምስል ወ ድምጽ ጥበብ ከሽነው፤ በአስከፊው የአሸባሪዎች ጥቃት በርግገው የደነበሩ ምስኪን ዜጎቻቸውን ምን ያህል እንዳረጋጉና የአለም ህዝብንም እንዴት እንዳስደመሙ ያስታውሷል። በተረፈ፤ የስነ ምግባር መመሪያዎችና መሰል ጉዳዮች ከየዘመኑ ስልጣኔና የሰው ልጅ ኑሮ ተለዋዋጭነት ጋር፤ሳይቋረጡ፤ መልካቸውን እየቀያየሩ፤በምድሩ ዙሪያ፤ በየሀገራቱ የፊልም ኢንዱስትሪዎች ውስጥ ጥልቅ ምክክርን የሚሹ የፊልም ሙያ አጀንዳዎች ሆነው የሚዘልቁ ናቸው። ዋናው ትኩረቱ ገቢ ማግኘቱ ላይ ብቻ ማነጣጠሩ ስለተባለው ግን፤የባለሞያው ምርጫ ነው። እንዲሁም የማንክደው የጥበቡም medium አይነት አስገዳጅነት። የፊልም ጥበብ፤ያነሱትን ሀሳብ አንዳች ‹‹ምትሀት››ን ፈጥሮ የማሳየት ጥበብ ነውና ስራውን ለመስራት ብዙ ገንዘብ ማስፈለጉን አይክዱትም። አልፎ አልፎ የሚከሰት ልዩ ዕድል /Fund/ ገጥሞ በጀት ካልተገኘ /Independent film making/ በቀር፤ፊልም ፕሮዲዩሰሩ ያወጣውን ገንዘብ ትርፋማ ለማድረግ መቆሙ ማንም ሊከለክለው የማይገባ መብቱ ነው። ቢዝነስ ነዋ! ሆኖም ግን በርካቶች የናጠጠ ገቢ ማግኘትን የማለማቸውና በሙያው የ‹‹መቆመራቸው››ን ያህል ደ ግሞ፤ ብዙ ፊ ልም ሰ ሪዎችም አሉ፤በማመቻመች፤ ገቢ ማግኛነቱን አምነው ለጥበባዊና የላቀ ፋይዳውም አብዝተው የሚጠበቡ። የዘርፉ ምሁራን ‹‹እኛ እንደደረስንበት ከሆነ›› ብለው እንደሚመሰክሩት፤ ‹‹የፊልም ጥበብ ውጤታቸው በማህበረሰቡ ማህበራዊ መስተጋብር፣ መንፈሳዊና ባህላዊ መዋቅሮች … ወዘተ ላይ የሚያሳድረውን ተፅእኖ የማያምኑ ባለሙያዎች ቁጥራቸው ቀላል እንዳልሆነ›› ነው። እ ኒህ ፊ ልም ሰ ሪዎች፤ ም ንም እ ንኳን አዎንታዊውንም ሆነ አሉታዊ ተፅዕኖውን አናምንም ቢሉ፤ ቢያንስ፤ እጅግ በረቀቀ መንገድ አቀናብረው የሚያወጡት የፊልም ጥበባቸው ፤ተመልካቾች አለምን የሚገነዘቡበትንና ስለ ህይወት የሚያስቡበትን መንገድ ለመቀየድ ምን ያህል አቅም እንዳለው ግን አይክዱም።

ባለሞያዎቹ ተጽዕኖውን ላለማመን ሽንጣቸውን ገትረው የሚሟገቱበትንና ምሁራኑ በበኩላቸው፤ ሙግቱን ለመርታት የሚያቀርቡትን ማስረጃ በቀጣዩ ጊዜ እናይ ዘንድ ተስፋ እያደረግን፤ለዛሬው ከላይ ላነሳነው ‹‹በሞያችን ስለ ማህበረሰቡ እንጨነቅ ዘንድ ግድ ይለናል››ለሚለው ፅንፍ ማሰሪያ እናብጅለት። ፊልሞች፤ ታዳሚያቸውን /እያወቀም ይሁን ሳያውቀው/ ወደ በጎነት ወይም ወደ ጥፋት የመምራት እምቅ ኃይል አላቸው። ‹‹ልክ ህፃን ልጅን እንደመመገብ›› ነው። ጤናማ ወይም የተመረዘ ምግብ ልንመግበው እንችላለን። ህፃኑ ሁለቱን ለይቶ አያውቅም። ይኼ ማለት ግን ተመልካቹ ቀሽም ነው አያሰኝም። አይደለምም፡ ፡ያን ያህል ለመረዳትና ለማገናዘብ ደካማ ላይሆን ይችላል። ግን ደግሞ ሁሉም ተመልካቾች አንድ ናቸው ማለትም አይደለም። ‹‹አንድ ፊ ልም ከ መነሻ ን ሻጤው ( inspiration) ያቀራረቡ ዘዬ፣ ያተራረኩ (narration) ሂደት፣ ያሰራሩ የቴክኒክ አይነት፣ ይዘት፣ በውስጡ ሊያቅፋቸው የሚመርጣቸው ግብአቶቹ crafts እና የጥበባዊ ደረጃው ጉዳይ… ምርጫው በባለሞያው ችሎታና መብት የሚወሰን ስለመሆኑ (Artistic Freedom) ባንደራደርም፤ እንደየፊልሙ ዘውግና አውድ፤ ጭብጥ፣ ታሪክና መልዕክት…ሁለንተናዊ መልክ፤ ‹‹ፊልሙ ተሰርቶ የሚቀርበው እንዴት ያለ የግንዛቤ አድማስ ላለው የህብረተሰብ ክፍል ነው?›› ወደሚለው አፍርሳታ ይመራናል። ምናልባት ፊልም ለተመልካች ከመቅረቡ በፊት ባለው የቅድመ ግምገማ /Prior restraint/ መስፈርትና ገደብ እስከ ጥግ እምነት ጥለን ካልተማመንን በቀር። ያም ቢሆን በቀጥታ ለዲቪዲ ሽያጭ የሚውሉትን አይመለከትም። የሚገርመው ደግሞ አደጋው ጎልቶ የሚታየው በእነዚህኛዎቹ /Popcorn productions/ ላይ መሆኑ ነው። እንግዲህ የፊልም ጥበብ በተመልካቹ ላይ ያለው ተፅእኖ መክረር ነው፤ በተለይ የባለሞያዎችን የኃላፊነት ጉዳይ ከፍ የሚያደርገው። ኋላ ከሚመጣ የዜግነትና የታሪክ ተጠያቂነትም ሆነ ከህሊና ተወቃሽነት /ከተስተናገደ/ ለመዳን። ህፃኑን በመመገብ መመሰሉም፤በምግቡ ውስጥ የተደባለቀ መርዝ ካለ የህፃኑን ህይወት ለመታደግ ያስቸግራል ለማለት ነው። የተሻለው መንገድ፤ቢቻልስ፤ ለህፃኑ ጤና ተስማሚ የሆነና ጣፋጭ ምግብን ሰርቶ ለማቅረብ መሞከር ነው።

ባጋጣሚ ‹‹ነፋስ ያመጣው›› ብናኝ ቢገባበት እንኳ አብላጫ ይዘቱ ብናኝ መርዙን ለማርከስ አቅም ያለው የጥበብ ማዕድ። በመጨረሻም፤‹‹ዞሮ ዞሮ ከቤት›› ይሏልና ወደ ራሳችን /የአሮጊቷ/ የዘመመች ታዛ ጎንብ ብለን ዘልቀን፤ ዝቅ ዝቅ ብለን እንሰነባበት። በመግቢያችን ላይ እንዳልነው፤ ዛሬ ዘመኑ በደረሰበት የዲጂታል ቴክኖሎጂና አማራጭ መገናኛ ዘዴዎች እገዛ፤ የፊልም ጥበብ ባንድ ጊዜ በየትም ስፍራ የመገኘቱ (ubiquity) እንዲሁም ማንኛውም የምስል ወ ድምጽ መረጃ በሰከንድ ክፍልፋዮች ከምድር አፅናፍ፣ አፅናፍ አሳብሮ ለመጓዝ መቻሉ፣ መልካም አጋጣሚነቱ ሀቅ ቢሆንም፤ ከየባለሞያው/ግለሰብና ቡድን ምኞት ጋር አብሮ በዘላቂነት ፀንቶ እንዲኖር የምንሻውን ትልቁን ስዕል፤ ሌሎች የማያውቁትን የተፈጠርንበትን ማህበረሰብ ምንነትና ክብር፤ ሌሎች የሌላቸውና ለእኛ የተቸሩ እፁብ ድንቅ ቅርሶቻችንን ፀ ጋ፤ የ እናት ሀ ገርን መ ልካም ገፅታ… ለአለም የማስተዋወቅ ፋይዳውን ማሰብ አለመተው ደግ ነው። ያኔ ነው የነጆናታን ዲምቢልቢ አይነቶቹ ዘመን ያስቆጠሩ ጥላሸቶች ታጥበው የሚጠሩት። እንዲሁም፤ በጋራ፤ የሌለንን የፊልም ፖሊሲ በመደማመጥና በትጋት በመቅረፅ፤ የጥበቡን አይነተኛ ፋይዳ (relevance) ባለፉት ዘመናት የተጣቡንን የማህበራዊ ቀውስ ነቀርሳዎች ሰንኮፍ የምንነቅልበት፤ዛሬን የምናጠይቅበትና ነጋችንን የምንተነብይበት፤ በአስተማማኝ መሰረት ላይ የቆመ ጥበብ (medium) ማድረግ ነው የሚበጀን።

እናም ለዘመናት ተሸክመናቸው የኖርናቸው ለእድገት ጸር የሆኑ ደዌዎች ታክመው የሚድኑበት እንጂ፤ረቂቅ ጥበቡን ተጠቅመን እንደመፈወስ፤ለጊዜያዊ ዝናና ጥቅም የሀገርን ውበት አጋንኖ ማጉደፍ ፤ከሁሉም በላይ ደግሞ ፤ ጭራሹኑ በነበረው ላይ ሌላ ለከርሞ የማይድን ነቀርሳ ፈጣሪ፣ አጥፊ አርአያን አጉልቶ በማሳየት፤ውል የለሽ ሴራ መጎንጎንና አረፋ ደፈቅ ስሜት ያግተለተላቸውን ረብ የለሽ የታሪክ ጉድፎችን እየለቃቀሙ መቆለል፤ትርፉ፤ አዳዲስ ችግር አምጪ ሀሳቦችን የምንቀፈቅፍበት ማህፀን ማበራከት እና ለነገው ትውልድ የማይወጣውን እዳ ማውረስ ነው። film is a truth twenty four times a second. ባለራዕይ ሲገኝ ለሀገር የሚቆም ራሱን ሰውቶ ፀጋን የተቸሩ የእምዬ ኢትዮጵያን እጆቿን ዘርግቶ ግዝቱን ትብታቡን ወዲያ መመንጠር ነው ባንድነት ተነስቶ! ለአለም አይን ማቅረብ ፈገግ ደርበብ ያለች የትልቋ እማማን የእውን ምስል አሁን በወል አበጅቶ። (የካቲት 13 ቀን 2006 ዓ.ም በሩሲያ የሳይንስና ባህል ማዕከል /ፑሽኪን/ አዳራሽ የቀረበ፤ ለአላቲኖስ የ ፊልም ሰ ሪዎች ማ ህበር ከ ተዘጋጀ የውይይት መነሻ ጽሑፍ።) CUT!

Published in ጥበብ

ላሊጋ ነገ በኑካምፕ ይወሰናል ፤ ለአውሮፓ ሁለት ትልቅ ዋንጫዎች 3 ክለቦች እድል አላቸው
በፉክክር ደረጃው የስፔን ላሊጋ ከአምስቱ የአውሮፓ ሊጎች የላቀ ሆኗል፡፡ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የዋንጫ ጨዋታ ሁለቱ የማድሪድ ከተማ ክለቦች መገናኘታቸው፤ በዩሮፓ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታ ከፖርቱጋሉ ክለብ ቤነፊካ ጋርደግሞ ሌላው የስፔን ክለብ ሲቪያ መገናኘቱ የላሊጋውን ክለቦች አህጉራዊ የበላይነት ያመለክታል፡፡ ዛሬ እና ነገ የሚደረጉት የመጨረሻ ሳምንት ጨዋታዎች ላሊጋውን ማን እንደሚያሸንፍ ብቻ ሳይሆን  ወራጆችንም የሚለዩ ሆነዋል፡፡ ይህ ዓይነቱ የላሊጋ ትንቅንቅ በታሪክ ለ3ኛ ጊዜ ያጋጠመ ነው ተብሏል፡፡
ከሳምንት በፊት አትሌቲክስ ማድሪድ በሜዳው ከማላጋ ጋር 1ለ1 ከተለያየ በኋላ ዋንጫውን የማያነሳበት ዕድል ተበላሽቶበታል፡፡ በሌላ በኩል በሴልታቪጐ ከሜዳው ውጭ 2ለ0 ሽንፈት የገጠመው ሪያል ማድሪድ ከዋንጫ ፉክክር ውጭ ሆኗል፡፡ እነዚህ ሁለት ውጤቶች ደግሞ የባርሴሎናን የሻምፒዮንነት ዕድል ፈጥረዋል፡፡ ስለሆነም በነገው ዕለት በካምፕ ባርሴሎና ከአትሌቲኮ ማድሪድ የሚያደርጉት ግጥሚያ ሻምፒዮኑን ክለብ ይወስናል፡፡ አትሌቲኮ ማድሪድ በ89 ነጥብና በ51 የግብ ክፍያ ሊጉን ሲመራ ባርሴሎና በ86 ነጥብና በ67 የግብ ክፍያ 2ኛ ነው፡፡
ለአትሌቲኮ ማድሪድ በነገው ጨዋታ ማሸነፍ ወሳኝ ነው፡፡  በማንኛውም ውጤት አቻ ከወጣም በ1 ነጥብ ልዩነት ዋንጫውን ከባርሴሎና ሜዳ  ይወስዳል፡፡ ይሁንና ባርሴሎና በሜዳው የሚያደርገውን ጨዋታ የሚያሸንፍ ከሆነ የአሸናፊው እድል በህገ ደንቦች ምላሽ ያገኛል፡፡ በላሊጋው እኩል ነጥብ የሚዳኘው ሁለቱ ክለቦችበእርስ በራስ ግንኙነት ያላቸው ውጤት ተወዳድሮ ነው፡፡ በግብ ብልጫ አሸናፊው ቢለይ እድሉ ያለጥርጥር ለባርሴሎና ነው፡፡
በሌላ በኩል በመውረድ አደጋ ውስጥ ያሉ አራት ክለቦች በመጨረሻ ሳምንት ጨወታዎች ከፍተኛ ትንቅንቅ ውስጥ ይገባሉ፡፡ በዚህ መሠረት ቫልዶሊድ ከግራንግዳ፣ ኦሳሱ መወርዱን ካወቀው ሪያል ቤቲስ ጋር የሚኖራቸው ጨዋታዎች ይጠበቃሉ፡፡

በትርፋማው የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ ሁሉም ይሸለማል፤ ሲቲና የአውሮፓ ጥያቄው
 በማንቸስተር ሲቲ ሻምፒዮንነት ከሳምንት በፊት የተጠናቀቀው  የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ ለሚወርዱ ክለቦችም ከፍተኛ ገቢ በማስገኘት ትርፋማነቱ ተረጋግጧል፡፡ በሳምንቱ አጋማሽ ላይ ዴይሊሜል ባሰራጨው ዘገባ በሊጉ ተሳታፊ የነበሩ 20 ክለቦች በየደረጃው ከሚሰጥ የገንዘብ ሽልማት፣ ከቴሌቭዥን ስርጭት መብትና በተለያዩ ንግዶች ከተገኘው 1.5 ቢሊዮን ፓውንድ እንደየድርሻቸው ተከፋፍለዋል፡፡
የውድድር ዘመኑን በሁለተኛ ደረጃ የጨረሰው ሊቨርፑል ወደዋንጫው በነበረው ግስጋሴ በቀጥታ የቴሌቭዥ ስርጭት በርካታ ጨዋታዎች ተላልፈውለት ተጨማሪ ድርሻ በመያዝ በ97.54 ሚሊዮን ፓውንድ ገቢው 1ኛ ደረጃ ወስዷል፡፡ 20ኛ ደረጃ በመያዝ ከፕሪሚዬር ሊጉ የወረደው ካርዲፍ ሲቲ 62 ሚሊዮን ፓውንድ ማስገባቱ የውድድርዘመኑን ትርፋማነት አረጋግጧል፡፡
ሻምፒዮን ለመሆን የበቃው ማንቸስተር ሲቲ  በገቢ ድርሻ ሁለተኛ የሆነው በ96.56 ሚሊየን ድርሻው ነው፡፡ ቼልሲ በ94.1፣ አርሰናል በ92.9፣ ቶትንሃም በ89.7 እንዲሁም ማን.ዩናይትድ በ89.2 ሚሊዮን ፓውንድ የገቢ ድርሻቸው በተከታታይ ደረጃ የውድድር ዘመናቸውን ጨርሰዋል፡፡
ማንችስተር ሲቲ በ3 ዓመት ጊዜውስጥ ሁለት ጊዜ ሊጉን ማሸነፉ በተለያዩ አጀንዳዎች ሲያነጋግር ቆይቷል፡፡ በተለይ ክለቡ ባለፉት ሁለት የውድድርዘመናት በተጨዋቾችየዝውውር ገበያአላግባብ በማውጣት፤ በኪሳራ ግብይት በመፈፀም እና የደሞዝ ጣራን ባለመገደብ በአውሮፓ እግር ኳስማህበር የፋይናንሳዊ የስፖርታዊ ጨዋነት ህግ ይከሰሳል መባሉ የሻምፒዮንነት ፌሽታውን ያደበዘዘ ነበር፡፡ ክለቡ በአውሮፓእግር ኳስማህበር ይከሰሳሉ ከተበሃሉ 9 ክለቦችአንዱ ከሆነ በ3 ዓመት እስከ 40 ሚሊዮን ፓውንድ ሊቀጣና የተጨዋች ስብስቡን ከ25 ወደ 21 በመቀነስ ስምንት የእንግሊዝ ተወላጅ ተጨዋቾች እንዲያሰልፍ ተወሰኖበታል ነው፡፡ በዚያላይደግሞ ከሻምፒዮንስ ሊግ እንደሚባረር መገለፁ አስደንጋጭ ነበር፡፡ በመጨረሻ ሳምንት ጨዋታዎች ሻምፒዮኑ በተለየው የዘንድሮ ፕሪሚዬር ሊግ  እንደ ማንችስተር ሲቲ የሚያዝናና ክለብ አልነበረም፡፡ በተጋጣሚዎቹ ላይ ያገባቸው 102 ጐሎች ለሪከርድ አንድ የቀራቸው ነበሩ፡፡ ቼልሲ በ2009-10 የውድድር ዘመን ያስመዘገበው የ103 ጐሎች ክብረወሰን  ነው፡፡  ፕሪሚዬር ሊጉን በ89 ነጥብና ግብ ክፍያ አሳምኖ አሸንፏል፡፡ ከተመሰረተ የ129 ዓመታት ታሪክ ያለው ማንችስተርሲቲ ለአራተኛ ጊዜ ነው ፕሪሚዬር ሊጉን ያስገበረው፡፡
ማንቸስተር ሲቲ በዩናይትድ አረብ ኢምሬቲ ሼክ መንሱር ከተያዘ ካለፈት 5 ዓመታት አልፈዋል፡፡ በእነዚህ የውድድርዘመናት ሁለት የፕሪሚዬር ሊግ ዋንጫ፤ሁለት የኤፍኤ ካፕ እና ሌሎች ሁለት ዋንጫዎችሰብስቧል፡፡ የክለቨቡ ባለሃብት በተጨዋቾች ግዢ እና በደሞዝ ክፍያ እስከ 2.5 ቢሊዮን ፓውንድአውጥተዋል፡፡ ሰቲ ሊጉን እንደተቆጣጠረ ማሰብ ይቀላል፡፡ ገና በመጀመርያ የውድድር ዘመናቸው የቺሊው አሰልጣኝ ማኑዌል ፔልግሪኒ ለክለቡ 2 ዋንጫዎችን ማስገኘታቸው አድናቆት አትርፎላቸዋል፡፡ በቀጣይ የውድድር ዘመን የሚጠበቅባቸው ሻምፒዮንስ ሊግ ይሆናል፡፡
ከካርዲፍሲቲ ጋር ከሊጉ ደህና ገቢ አፍሰው መውረዳቸውን ያረጋገጡት ካርደር ሌሎቹ ሁለት ክለቦች ኖርዊችሲቲ እና ፉልሃም  ናቸው፡፡

የጋርዲዮላ ፍልስፍና ማጠቃጨቅ ጀምሯል፤ ባየር ሙኒክ የዋንጫ ሃትሪክ ይፈልጋል
አምና የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግን ያሸነፈው ባየር ሙኒክ በግማሽፍፃሜ በሪያል ማድሪድ ተባርሮ ክብሩን ባለማስጠበቁ ጭቅጭቅ ተፈጥሯል፡፡ በአውሮፓ ሻምፒዮንስሊግ ያለፉት ሃያ ዓመታት ታሪክ የትኛውም ክለብ ባልቻለው ነገር ነው ትርምሱ፡፡ በተለይከሰሞኑ ፔፔ ጋርዲዮላ በአሰለጣጠን ፍልስፍናው ከክለቡ ቁልፍ ተጨዋቾች ጋር የተፈጠረው እሰጥ አገባ ከሻምፒዮንስ ሊጉ ሽንፈት የተገናኘ ነው፡፡
በአውሮፓ ሻምፒዮንነቱ በዓለም ክለቦችዋንጫ የመጀመርያ ድሉን የጀመረው ባየር ሙኒክ ቦንደስሊጋውን እንዳሸነፈ ያረጋገጠው ከወር በፊት ነው፡፡ በአገር ውስጥ ውድድሮች ዓመቱን ለሦስት ዋንጫዎች ለመደመደም አነጣጥሯል፡፡ ከቅርብ ተቀናቃኙ ቦርስያ ዶርትመንድጋር ወሳኝ ፍልሚያ ይቀረዋል፡፡ ባየር ሙኒክ የዘንድሮ የቦንደስ ሊጋ ዋንጫ ድል በተሳትፎ ታሪኩ 24ኛው ነው፡፡

ሴሪኤ የቲቪ ገቢው ይጨምራል፤ ጁቬስ ወደአውሮፓ ይመለሳል
የጣልያኑ ሴሪኤ የሚያበቃው ነገ ነው፡፡ ጁቬንትስ የስኩዴቶውን ክብር መጐናፀፍ የቻለው ግን ከሳምንት በፊት ነው፡፡ በክለቡ ታሪክ ለ30ኛ ጊዜ  ነው፡፡ የሊጉ የመጨረሻዎቹ ሳምንት ጨዋታዎች ወሳኝነታቸው በወራጅ ቀጠና ውስጥ ባሉ ክለቦች ነው፡፡ ጁቬንትስ የስኩዴቶውን ክብር በፍፁም የበላይነት ያገኘው በሪኮርዶች በመታጀብ ነው፡፡ በሴሪኤው የመጨረሻ ሳምንት ጨዋታሌላሪኮርድ ያነጣጥራል፡፡ ከካልጋሪ ጋር በሚኖረው ግጥሚያ ሙሉ ነጥብ ከወሰደ የውድደር ዘመኑን በ102 ነጥቦች በማጠናቀቅ አዲስ ክብረወሰን ያስመዘግባል፡፡ ሌሎቹ ሪከርዶች በ25 ጨዋታዎችአለመሸነፉ እና  ለ3ኛ ተከታታይ ዓመት ዋንጫውን በመውሰድከ ዓመት በፊት የነበረውን ክብር መመለሱ ነው፡፡
በሌላ በኩል ተቀማጭነቱን በስዊዘርላንድ ያደረገው ኢንፍሮንት የተባለ ኩባንያ ሴሪኤውን በቲቪ ገቢ ለማጠናከር መወሰኑ ታውቋል፡፡ ኩባንያው በሚቀጥሉት 6 የውድድር ዘመናት የሴሪኤውን የቴሌቭዥን ስርጭት መብት ለመግዛት 4.95 ቢሊዮን ፓውንድ መክፈሉ ታውቋል፡፡ ይህደግሞ የጣሊያን ክለቦችን የገቢ አቅምበማሳደግ የትልልቅ ተጨዋቾችን ትኩረት የሚያስገኝ ይሆናል፡
ዓለም ዋንጫ ያመለጠው ኢብራሞቪችና ፒ ኤስ ጂ
በፈረንሳይ ሊግ 1 ፓሪስ ሴንት ዠርመን ሻምፒዮን መሆኑን ያረጋገጠው ከሳምንት በፊት ነው፡፡ በክለቡ የ54 ዓመታት  4ኛው ነው፡፡
ለክለቡ ውጤታማነት ዓለም ዋንጫና የወርቅ ኳስ ሽልማት ያመለጠው እየተባለ የሚነሳው ስዊድናዊ ዝላታን ኢብራሞቪች ነው፡፡ ግዙፉአጥቂ ወደዓለም ዋንጫው መሄድ ባይሳካለትም በአውሮፓደረጃ ምርጥ ከሚባሉ አጥቂዎችተርታ ሆኖ አሳልፏል፡፡ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ስምንት ጎሎች ያስመዘገበ ሲሆን በሊግ1 ደግሞ በ25 ጐሎች ኮከብ ግብ አግቢ ሆኖ ጨርሷል፡፡ በፈረንሳይ ሊግ የዓመቱ  ኮከብ ተጫዋች ተብሎ ለ2ኛ ተከታይ ዓመት ተሸልሟል፡፡
በገቢ እና ወጪ ሊግ
በዋጋ ግምት
ሪያል ማድሪድ -3.44 ቢሊዮን ዶላር
ባርሴሎና - 3.28
ማን.ዩናይትድ - 2.81
ባየር ሙኒክ - 1.85
አርሰናል - 1.33
ቼልሲ - 868
ማን ሲቲ - 863
ኤሲሚላን - 856
ጁቬንትስ -850
ሊቨርፑል - 691
በገቢ (በሚሊዮን ዩሮ)
ሪያል ማድሪድ - 578.9
ባርሴሎና - 482.6
ማን.ዩናይትድ - 423.8
ባየር ሙኒክ - 431.2
አርሰናል - 284.3
ቼልሲ - 303.4
ማን ሲቲ - 863
ኤሲሚላን - 856
ጁቬንትስ -272.54
ኤሲሚላን -263.5

በብዙአየሁ እሸቱ ተፅፎና ተዘጋጅቶ በጆስ ዳን ፊልም ፕሮዳክሽን ፕሮዲዩስ የተደረገው “ወደ ፍቅር” የተሰኘው ፊልም ነገ በሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት ከቀኑ በ11 ሰዓት ይመረቃል። የሮማንስ ኮሜዲ ዘውግ ባለው በዚህ ፊልም ላይ መስፍን ሃ/ኢየሱስ፣ ጆሴፍ ዳንኤል፣ ቶማስ ቶራ፣ ሰገን ይፍጠር አዲስ አለም ጌታነህና ሌሎችም አንጋፋና ወጣት ተዋንያን መሳተፋቸውን ለማወቅ ተችሏል።

Monday, 19 May 2014 08:46

ጩዛሎ ቶርዛ

                      ከግቢዬ በውጪው በኩል የኮሽም አጥሬ አጠገብ ካለችው ግራር ሥር ተቀምጬ፣ ባሻገር ያለውን መስክ እየተመለከትሁ ነው። ከፊቴ አርባ ወይም ሃምሳ ክንድ ያህል ከእኔ ራቅ ብሎ አንድ ትልቅ የሾላ ዛፍ ይታያል። ዕድሜ ጠገብ በመሆኑ የግንዱ ዙሪያ ስፋት የሁለት ሰው እቅፍ ያህል ነው። የግራ እጄን ክርን ጉልበቴ ላይ ሰክቼው አገጬን ተደግፌ ተቀምጫለሁ። በቀኝ እጄ መሬቱን በበትሬ ጫፍ እየጠቀጠቅሁ በሃሳብ ነጉጃለሁ። በመካከሉ:- “ቶርዛ!” የሚል ድምፅ በድንገት ስለ ሰማሁ፣ ደንግጬ ከገባሁበት ጥልቅ የሃሳብ ባህር “እ…!” ብዬ ወጣሁና ግራ ቀኙን ተመለከትሁ። ማንም የለም። ወዲያው ወደ ኋላዬ ዞሬ በዓይኔ ፈለግሁ። አሁንም የሚታየኝ ሰው የለም። “ምን ጉድ ነው?” ብዬ አሰብሁ። ጆሮዬ ነው ወይስ ይኸ በየሥርቻው ተልከስካሹ ነገር? ብቻ እኔ አላውቅም። ማነው የጠራኝ? አሁንም ዙሪያ ገባውን እያየሁ ነው። ማንም የለም። አማተብኩና ቀና ስል፤ ያው የቅድሙ ድምፅ መልሶ እንደገና፤ “ቶርዛ” ብሎ ጠራኝ።

አሁን ስሜ ወደተጠራበት ድምፅ አቅጣጫ ተመለከትሁ። “ወደ ላይ!... ሾላው ዛፍ ላይ ተመልከት!” አለኝ፤ ይኸው ድምፅ። ቀና በማለት ወደ ሾላው አናት ተመለከትሁ። ከአፍንጫው ሰርጐድ ብሎ መልኩ ጠቆር ያለ ራሰ በራ ሰው አየሁ። ቁመቱ የኔን ክንድ ያህል ቢሆን ነው። በጣም ደነገጥሁ። ያየሁትን ለማረጋገጥ ሁለቱንም ዓይኖቼን አንድ ሁለት ጊዜ ጨፈን ገለጥ አድርጌ መልሼ ወደ እዚያው አየሁ። እዚያው ካለበት ቦታ ላይ ሆኖ ፈገግ እንዳለ ይመለከተኛል። በትሬን ጠበቅ አድርጌ እንደያዝሁ ከተቀመጥኩበት ዝግ ብዬ ብድግ አልሁ። “ተመልሰህ ቁጭ በል! ደግሞም በትርህ አይጠቅምህም። እኔ ልክ እንደ መንፈስ ነኝ። ልዩ ፍጡር!...” አለኝ። እንዲህ ሲለኝ በጣም ስለ ደነገጥሁ በረጅሙ ወደ ውስጥ ትንፋሽ ወስጄ ጥቂት እንደመረጋጋት ስል፤ “የምን መንፈስ? የምን ፍጡር ነህ?” ብዬ የሙት ሙቴን ጠየቅሁት። “አንተ ከማታውቀው ዓለም ነው ወደዚህ የመጣሁ። የሌላ ዓለም ፍጡር…! ስሜ ጩዛሎ ይባላል” “ሰው ነህ ወይስ…?” “ሰው እመስላለሁ፤ ግን አይደለሁም። እኔ አሁን ወደ እዚህ ወዳንተ የመጣሁት ብዙ ነገር ልነግርህና ትዕዛዝም ልሰጥህ ነው።

ስላልገባህ ነገር ብቻ ለመጠየቅ አልፎ አልፎ ስፈቅድልህ ካልሆነ በስተቀር በቃለ - ምልልስ መልክ ከእኔ ጋር እንደፈለግህ መለፋለፍ አትችልም። አንተን ከሌላው ለይቼ የመረጥኩበት የራሴ የሆነ ምክንያት አለኝ። ምክንያቱን ደግሞ አትጠይቅኝ…” አለና፤ ልክ እንደቀለጠ ላስቲክ ሆኖ ምንም ሳይንጠባጠብ ተዥሞልሙሎ፣ ከላይ ከሾላው ቅርንጫፍ ወደ ታች ወርዶ ግንዱ ውስጥ ገብቶ ጠፋ። ደነገጥሁ። ምን እንደማስብ አላውቅም። ተነስቼ ልሮጥ ያሰብሁ ይመስለኛል። ውስጤን አጥወለወለኝ። ወደ ሾላው አየሁ። የሾላው ግንድ ውስጡን የሚያሳይ ረግቶ የቆመ የውሃ ዓምድ ዓይነት ሆነብኝ። ከዚያ የውሃ ግንድ ውስጥ ይኸው ጩላሎ ነኝ ያለኝ ፍጡር እንደ ልቡ ወደ ላይ፣ ወደ ታች እያለ እኔኑ አፍጥጦ ይመለከተኛል። አሁን ከበፊቱ የበለጠ በመደንገጤ ልቤ ከውስጥ ሲዘል ተሰማኝ። “አይዞህ አትደንግጥ!...ብትደነገጥም ደግሞ ጭራሽ አልፈርድብህም።

ማንም ሰው ቢሆን እንዲያ ይሆናል። በተረፈ ግን ከባድ ማስጠንቀቂያ እሰጥሃለሁ። ከባድ ቅጣት ያስከትላልና ይህን ያየኸውን ነገር ለማንም እንዳትናገር ተጠንቀቅ። ነገ ልክ በዚሁ ሰዓት እዚሁ ቦታ እንገናኝ። በደንብ ሳንተዋወቅ ልቀጣህ አልፈልግምና ለመቅረት እንዳትሞክር። እኔ ዛሬ የመጣሁት ላስተምርህ ነው እንጂ አንተን ልጐዳ አይደለም። ከዚህች ሰዓት ጀምሮ ደግሞ ጓደኛሞች ሆነናልና አትፍራኝ። እያደር ወዝ ስንጣገብ ትለምደኝና ትረጋጋለህ። ነገ በዚህ ሰዓት!” ብሎ፤ የግራ ዓይኑን ለጥቅሻ ጨንቆር አድርጐብኝ ጠፋ። ጩዛሎ ቶርዛ ያ የውሃ ዓምድ ሆኖ እንደ መስተዋት ብሩህ ሆኖ የታየኝ ግንድ፣ እንደ ወትሮው ሁሉ ድፍን ግንድ ሆነ። ያው የበፊቱ የሾላ ግንድ…ትዕንግርት ነው! በዚህ ዛር መሰል ፍጡር ሁኔታ ድንጋጤው ባሰብኝ እንጂ ሊለቅቀኝ አልቻለም። የሰጠኝም ትዕዛዝ ጥብቅ ሆነብኝ። ምኑ ጉድ ነው የገጠመኝ እናንተዬ! የነገረኝ ስም እንዳይጠፋኝ ሰግቼ አሁንም አሁንም እየደጋገምሁ፤ “ጩዛሎ…! ጩዛሎ…!” እያልሁ ደንዝዤ ካለሁበት ተነሳሁና የግቢዬን በር አልፌ ወደ ውስጥ ዘለቅሁ። ከቤቴ ገብቼ ጥቂት እንደተቀመጥሁ፣ ይኸው ልዩ ፍጥረት ጩዛሎ በየት እንደተከተለኝ ሳላውቅ፣ ተከትሎኝ መጥቶ ኖሮ፣ ከቤቴ እንጨት ምሰሶ ውስጥ ገብቶ እዚያ የሾላ ግንድ ውስጥ እንደሆነው ሁሉ፣ እዚህም ላይ ታች እያለ ዥሙልሙል ይላል። ልጆቼም ሆኑ ሚስቴ ያዩት አልመሰለኝም። እንዲያውም አንዱ ልጄ የተቀመጠው ያንኑ ምሰሶ ተደግፎ ነው። ልጄ እንደ ወትሮው ሁሉ እሳቱን እየሞቀ፣ ከሌላዋ ልጄ ጋር እያወሩ ይሳሳቃሉ።

በእነሱ ዘንድ ምንም አዲስ ነገር የለም። ለመሆኑ ይኸ መላ ቅጡ የጠፋብኝ ፍጡር የሚታየው ለኔ ብቻ ነው እንዴ? ይህ ደግሞ እንዴት ሊሆን ይችላል? ሚስቴ ፊቴ ሲለዋወጥ አይታ ወዳለሁበት መጣችና ከፊቴ ቁጢጥ ብላ፤ “አሞሃል እንዴ?” አለችኝ። “ኧረ በጣም ደህና ነኝ። ምነው?” አልሁ፤ እኔም መልሼ እየጠየቅኋት። ቀና ብላ አይታኝ ወደ ሥራዋ ሄደች። ምናምኑን አስነክቶኝ የለ! ወደ ምሰሶው አየሁ። ጩዛሎ በጣቱ ወደ ውጪ እያመለከተ፣ የሌላኛውን እጅ ጣት ደግሞ ወደፊት በክብ ቅርፅ በዝግታ ካዞረ በኋላ፣ አመልካች ጣቱን ወደፊት ወደ እኔ ቀስሮ በዛቻ መልክ አወዛወዘ። ቅድም የነገረኝን ቀጠሮ ሳላፈርስ፣ ነገ በሰዓቱ እንድገኝማ ስጠንቀቁ እንደሆነ ገብቶኛል። ማን ጅል አለ? ያውም ቤቴን ለይቶ ከምሰሶዬ ገብቶ የምን መቅረት ነው! ሚስቴና ልጆቼ ላይ አደጋ ቢያደርስስ? ነገ በሰዓቱ ሄጄ የሚያደርገኝን እኔው ራሴ እንደገባሁበት እወጣዋለሁ እንጂ አልቀርም። መቸም ፍርጃ ነው! ዛሬም በተነገረኝ ሰዓት እዚያችው ቦታ መጥቼ ተቀምጫለሁ። የጩዛሎን መከሰት እየተጠባበቅሁ ነው። ከረጅሙ ሾላ አናት ላይ አንዳች የሚንጐዳጐድ ድምጽ ይሰማኛል። ግን ምንም ነገር አይታየኝም።

ቀጥሎም የሾላው ግንድ ፍም እሳት መሰለ። ወዲያው አጅሬ እዚያ ውስጥ ሲልወሰወስ ታየኝ። በግራ እጁ አነስ ብላ ወፈር ያለች መጽሐፍ ቢጤ ይዟል። በውፍረቷ የተነሳ ብዙ ገጾች እንደ ያዘች መገመት ችያለሁ። መጽሐፊቱ የፊት ሽፋን ላይ እኔው በማውቀው ፊደላት “ቶቫ ቶቫ” የሚል በትላልቁ ተጽፏል። በአርባና በሃምሳ ክንድ ርቀት ፊደላቱን እንዴት አይቼ መለየት እንደ ቻልሁ ለራሴው ገርሞኛል። “ጢዞር - ጳዲዝ - ዙርቢ…” አለ ጩዛሎ። በመቀጠልም “…ፍርሃትና ጥርጣሬ ከደም ሥጋህ ይዋሃዱ፤ እንኳን ዛሬ በደህና ተገናኘን። በእጄ የያዝኳትን ትንሽ መጽሐፍ እንዳየሃት አውቄአለሁ። ስለ መጽሐፏ ሙሉ ይዘት ገጽ በገጽ ሳስረዳህ እያደር ይገባሃል። ያልገባህን ለማወቅ ጥያቄ እንድትጠይቀኝ ለዛሬ ፈቅጄልሃለሁ። ወደፊትም እንደ ሁኔታው አልፎ አልፎ ይፈቀድልሃል። ተግባባን መሰለኝ!...” አለና ትክ ብሎ አየኝ። በትናንትናው ቀን ዝም ብሎ መለፋለፍ የለም ብሎ ነግሮኝ ነበርና፣ ዛሬ ስለ ፈቀደልኝ ጥያቄ አቀረብሁ። “ይኸ ጢዞር…ምናምን ያልከው ምንድነው? ደግሞስ ምነዋ ፍርሃትና ጥርጣሬ ይዋሃዱህ ብለህ ረገምከኝ? ምን በድዬህ ነው?” ብዬ ጩዛሎን ጠየቅሁት። ጩዛሎ በረጅሙ ተንከተከተና - “ሰዎች ስትባሉ በጣም ሞኞች ናችሁ። እኛ ጩዛሎዎች ፍርሃትና ጥርጣሬን እንወዳቸዋለን። አየህ!...ካልፈራህ ድፍረት ምን እንደሆነ ሊገባህ አይችልም። ብዙ ብዙ ስትፈራ፣ ባላሰብከውና ባልገመትከው መንገድ የግድህን አንድ ቀን ደፋር ሆነህ ራስህን ታገኘዋለህ። አህያ በፍርሃቷ አይደል ጅብን የምትነክስ!...አንዴ ከደፈርህ ደግሞ ብዙ የኖርክበት ነገር ነውና ተመልሰህ አትፈራም።

ፍርሃትን ትፀየፈዋለህ። በእኛ ዓለም ፍርሃትን የደፈሩ ብዙ ጀግኖች ስላሉ አንድም ፈሪ ሰው አታገኝም። ጥርጣሬም ቢሆን ያው እንደዚያው ነው። ስትጠረጥር ትጠነቀቃለህ። የአካልህ ህዋሳት በሙሉ ንቁ ይሆናሉ። ዝም ብለህ ፈዝዘህ እስከ መቼ ድረስ ትኖራለህ? ካልጠረጠርህ ደግሞ ቀኝ እጅህ ተቆርጦ ሳለ፣ ግራህንም እስኪደግሙህ ትጠብቃለህ። ጠርጣራ ሰው የኮቱን አዝራር እንኳ ይጠብቃል። ታዲያ እንዲህ ስልህ በሆነውም ባልሆነውም በከንቱ ተዝረጥረጥ ማለቴ አ ይደለም… “…ሌላው ጢዞር - ጳዲዝ…ምንድነው? ያልከው ነው። በከባዱ ላስጠንቅቅህ- እነዚህ ቃላት ለእኛ እንጂ እናንተ ሰዎች ለምትባሉ አይፈቀድም። አሁን እኔ ከአንተ ጋር እያለሁ ቃላቱን በመናገርህ እንጂ አደጋ ያስከትልብህ ነበር። ወደፊት እኔ እንድትናገራቸው በፈቀድኩልህ ጊዜ ግን ችግር የለም። የቃላቱን ፍቺና ትርጉማቸውን መሸከም ስለማትችል ይቅርብህ። ይህን ጉዳይ በዚህ ደመደምን። ዛሬ ከመጽሐፉ ገጽ 1 እንጀምራለን። ገጽ 2ን ደግሞ በነገው ቀን እናየዋለን” ብሎ፤ ከዚያ የፋመ ከሚመስለው ግንድ ውስጥ ይወራጭ ያዘ። አንዴ ፈቅዶልኝ የለ! - ጠየቅሁት። “በእጅህ የያዝከው መጽሐፍ ሽፋን ላይ እኔ በማውቀው ፊደላት ተጻፈ እንጂ ትርጉሙ አልገባኝም። ደግሞስ መጽሐፉን ማወቅ ምን ይጠቅመኛል?” የሚል ጥያቄ አቀረብሁ። “ቶቫቶቫ” የሚለውን የመጽሐፉን ርዕስ ትርጉምጨርሶ እርሳው። መጽሐፉ ይጥቀምህ አይጥቀምህ ግን በወደፊቱ ኑሮህ የምታየው ጉዳይ ይሆናል።

እናንተ ሰዎች ስትባሉ ግን አንድን ነገር በወጉ ሳትረዱ ቀድማችሁ መፈረጅ ትወዳላችሁ። ይመጣ ዘንድ የግድ የሆነውን ጥሩ ነገር አታምኑም። ያላችሁበትን መጥፎ ነገር ደግሞ አቅፋችሁ መኖር ትችሉበታላችሁ። እስቲ አስበው። ከመጽሐፉ አንዲት ቃል እንኳ ሳትሰማ፣ ቀድመህ እንደማይጠቅምህ ደመደምህ። እኔ ጩዛሎ ግን ወደድህም ጠላህ መጽሐፉን እግትሃለሁ። ያኔ እኔን ታመልካለህ፤ እኔንም ትከተላለህ። ያሁኑ ቅል አንኮላነትህ በነጠረ ብርሌነት ይለወጣል…” እያለ ጩዛሎ ጭቃ ጅራፉን አወረደብኝ። ትቼው እንዳልሄድ እንዲያ ፈርቼው፤ ችዬ እንዳልሰማው ወሬው ሁሉ እኔ ከምችለው በላይ ቅጥ አምባሩ የወጣ ውስብስብ ሆኖብኝ፤ እንዲሁ ሳልወድ አፌን ከፍቼ የሚለኝን ሁሉ እየሰማሁት ግብኔን ተቀምጫለሁ። የሆዴን በሆዴ ይዤ በምላሴ ልተባበረው ወሰንሁ። ጩዛሎ መናገሩን አላቆመም። “…የገጽ 1 መመሪያ ጠቅለል ባለ መልኩ የሚናገረው ጠቃሚ ስለሆኑ የበዓላት አከባበር ነው። በጥሞና ተከተለኝ። አሁን የምነግርህን ሁሉ በተግባር ታውለዋለህ። ትዕዛዝ መሆኑን የምትረዳ ይመስለኛል። የቀን በዓላትን እንደ አስፈላጊነቱ ታከብራለህ። ለምሳሌ ያህልም የዝናብ ቀን፣ የፀሐይ ቀን፣ ወዘተ እያልህ ሰይመህ እንዲከበሩ ታደርጋለህ። የዝናብን ቀን ዕለቱን አክብረህ ትረሳዋለህ። ብዙ ተከታዮች ግን ያፈራልሃል። ቅቤ ነጋዴዎች፣ ችግኝ አፍዪዎች፣ ከብት አርቢዎች እና የመሳሰሉት ሁሉ ይወዱልሃል።

በዚህም የፀሐይ ቀን እስኪመጣ ድረስ ዕድሜ ይገዛልሃል። የፀሐይ ቀን ሲመጣ ደግሞ የዝናብ ቀኑን ረስተህ እሱን ብቻ ታደምቃለህ። እሱ ደግሞ በበኩሉ የዝናብ ቀን እስኪመጣ ድረስ ይዞህ ይሄዳል። የፀሐይን ቀን ስላከበርህ ደግሞ ጨው አምራቾች፣ ኳስ ተጫዋቾች፣ መንገድና ድልድይ ሠሪዎች…የመሳሰሉት አብረውህ ይሆናሉ። ልብ አልህ አይደል! በሁለት በዓላት ብቻ ብዙ ወዳጆች አፈራህ ማለት ነው…“ ሃሳቡን ሳይለውጥ የፈቀደልኝን የመጠየቅ መብት ተጠቅሜ በንግግሩ መሃል ጣልቃ ገባሁና፤ “ቆይ!...ቆይ! እኔ ከፊደል ገበታ ውጪ ሌላ ነገር የማላውቅ ተራ ሰው ሆኜ፣ የምትነግረኝ ሁሉ ምን ይጠቅመኛል?” “ለካ የዋህ ሰው ነህ ቶርዛ! ዓይንህን ከፍተህ አካባቢህን በተመለከትህ ጊዜ ያኔ ትረዳዋለህ። ‘ሁሉ ጠምጣሚ፣ ዳዊት ደጋሚ’ ሲባል አልሰማህም?” አለኝ። “ቆይማ! የኔን ቋንቋ እንዴት ልታውቅ ቻልህ?” “የዓለሙ ቋንቋ ሁሉ የኛ የጩዛሎዎች ቋንቋ ነው” “እግዚአብሔርን ታውቃለህ?” “በሆነ ወቅት የማውቀው መሰለኝ” “ለአንድ ጊዜ ብቻ አውቀኸው ልክ እንደ ሰው ረሳኸው?” “ዝጋ…ስለዚህ ነገር አቁም!” ብሎ በንዴት አንባረቀብኝ። በጣም ተናደደ መሰል መላ አካሉ ፍም እሳት መሰለ። ዓይኑ ቀላ። የዛሬን ያውጣኝ እንጂ ይህን ነገር ዳግም ላላነሳ በውስጤ ለራሴው ማልሁ። ስፈራ ስቸር ካቀረቀርኩበት ቀና ብዬ አየሁት። “ያቺ ቀን እስክትመጣ ድረስ ለራሴው ስል እታገስሃለሁ” አለ ጩዛሎ፤ የጐሪጥ እያየኝ። በውስጤ ያቺ ቀን ምንድናት? ብዬ አሰብሁ። ደግሞም ይ ኸ ዛ ር ው ላጅ ፈ ጣሪ የ ለውም እ ንዴ? የሚል ሃሳብም አደረብኝ። ብቻ ነገሩ ሁሉ እንዲያው ግራ ነው የሆነብኝ።

ምን አባቴ እንደሚሻለኝ ለጊዜው የማውቀው ነገር የለም። “ገጽ 2ን ነገ እንቀጥላለን” ብሎ ጩዛሎ ሲናገር፤ አስብ የነበረውን ድንገት ተውኩና ወደ እሱ ማየት ጀመርሁ። “…ነገ በተለመደው ሰዓት ጢዞር…ጳዲዝ… ዙርቢ…” ብሎ እዚያው ካለበት ከሰመ። ግንዱም የሾላ ግንድ ሆነ። ይህን ዛር መሰል ፍጡር ግን እንዴት ነው የምገላገል? ለነገም ቀጥሮኛል እኮ! መቼ ይሆን የሚለቅቀኝ? ምን የሚሉት ልክፍት ነው እባካችሁ? ማነውሳ በፀረ መናፍስት ድጋም ይህን ጩዛሎን የሚያጠፋልኝ? መቸም መላ እስካገኝ ድረስ ብዙ ማሰቤ የማይቀር ነው። ዛሬ ተገናኘንና ከገጽ 2 ላይ ስለ ተንኮል፣ ስለ ማታለል፣ ስለ ማስመሰል፣ ስለ ትንኮሳ፣ ስለ ውሸት፣ ስለ ክህደት …አወራልኝ። በተለይ ተንኮልና ውሸት እኒህ ሁለቱ እንዴት እንደሚደጋገፉ፣ ልዩነታቸውንና አንድነታቸውን አንድ በአንድ እያመላከተ የሰጠኝ ማብራሪያ ትኩረቴን ስቦት ነበር። ተንኮልን ለመወጠንና ለመፈፀም ለዚያ የተዘጋጀ አዕምሮና ብቃት በቅድሚያ መኖር ማስፈለጉ፤ ዕኩይ ሰይጣናዊ አስተሳሰብን መልአከዊ ለማስመሰል የውሸት ሠራዊት ሚና፤ የመሳሰሉትን በዝርዝር ከነገረኝ በኋላ፤ “ለዓላማህ ስኬት ያመንክበትን ተንኮል ሁሉ አድርግ። ተንኮልህ ጨርሶ ባይጠፋልህ እንኳ በውሸት ከበሮ ድብዝዝ እንዲል ከማድረግ ቸል አትበል። ሌሎች ሰዎች ስለሚሉት ፈጽሞ አትጨነቅ፣ ጆሮህን ጠቅጥቅ!” የሚል ሰፊ መግለጫ ሰጠኝ። ይህንን እና ሌሎች ሁኔታዎችን ሲያስረዳኝ፣ እኔም እሱን የሆንሁ እየመሰለኝ ተመስጬ ሰማሁት። በመጨረሻም:- “ለተደላደለ የወደፊት ኑሮህ ይጠቅምሃልና እንካ ውሰደው!” ብሎ መጽሐፉን ወረወረልኝ።

እኔም አፈር ከነካ የሚረክስ ስለመሰለኝ፣ በአየር ላይ እንዳለ አፈፍ አድርጌ ቀለብኩት። መጽሐፉ ከእጄ ሲገባ ምኑ እንዳናገረኝ ሳላውቀው፤ “ጢጳዙ - ርዝቢ” አልሁ። እሱ ቀደም ሲል ይላቸው ከነበሩ ሦስት ቃላት ላይ በቅድሚያ የመጀመሪያዎቹን ፊደላት ከየቃሉ ወስጄ በመገጣጠም። ቀጠል አድርጌም የየቃሉን የመጨረሻ ፊደላት ወስጄ ገጣጠምኩና ሌላ ሁለተኛ ቃል ፈጠርሁ። “ጢጳዙ - ርዝቢ”… በዚህች ቅጽበት የመጽሐፉ ሙሉ ምስጢር ተገለጠልኝ። ገጾቹን መግለጥ ያለብኝ በጥንቃቄና ጊዜው ሲመጣ እንደሆነ የሚመክር መመሪያ አለው። የተጻፈበት ቋንቋ የኔ ሳይሆን በእነ ጩዛሎ መናፍስታዊ ቋንቋ ቢሆንም፤ ሳነብበው ግን በቀላሉ መረዳት ቻልሁ። በመጽሐፉ ይዘት ተመስጬ እያለሁ:- “መጽሐፉን ወደድከው?” በማለት ጩዛሎ ጠየቀኝ። “መቸም …አዎ!” አልሁ። “ምነው ቅር አለህ?” ብሎ ቆጣ አለ። “ኧረ የነፍሴን ያህል ነው የወደድኩት” ብዬ መለስሁ። “በል እሺ!…እኔን የራሴን ተወጥቼዋለሁ። መንገዴም አንተ ድረስ ነው። እንዳትሳሳት ተጠንቅቀህ እኔ እናገራቸው የነበሩትን ሦስት ቃላት በቅደም ተከተላቸው፣ እያንዳንዱን ቃል ወደ ግራ አምስት ጊዜ አንብብ። አሁን ጀምር!” ብሎ አዘዘኝ። “ከዚያ በፊት አንድ ጥያቄ አለኝ” አልሁት። “ቀጥል!” “የመጽሐፉን ገጾች አንብቤ በጨረስሁ ጊዜ ምን እሆናለሁ?” “ያኔ ሥራህ ያወጣሃል! አሁን አነብንብ!” ብሎ ተቆጣ። አቤት! ፍርጃ እኮ ነው ሰዎች! መቸም አንዴ የገባሁበት ነገር ነውና እምቢ ለማለት አልደፍርም።

መዘዘኛ ጩዛሎ!... “ርዞጢ! - ዝዲጳ ቢርዙ” አልሁ፤ አምስት ጊዜ። አነብንቤ ከጨረስሁ በኋላ፣ ውስጤን ደስ የሚል ሙቀት ስለ ተሰማኝ፣ ወደ ጩዛሎ አየሁ። ከሾላው ግንድ ወጥቶ ልክ ውሃ እንደተሞላ በጣም ስስ ላስቲክ መሬቱ ላይ እየተዥሞለሞለ ሲንከባለል መጥቶ እግሬ ሥር ሲደርስ፣ አካሉ ትንሽ በትንሽ እየተቆራረጠ፣ አፈሩ ውስጥ ገብቶ ጠፋ። ሳላስበው እንባዬ ዱብ ዱብ አለ። ወዲያው ከየት መጣ ሳይባል ዶፍ ዝናብ ዘነበ። እኔም ከዝናቡ ለመሸሽ፤ ጢዞር…ጳዲዝ… ዙርቢ ርዞጢ…ዝዲጳ…ቢርዙ እያልሁ፣ የአጥሬን በር ከፍቼ ሮጥ ሮጥ በማለት፣ ወደ ውስጥ የምዘልቅ ይመስለኛል። በዚያ የህልም ውስጥ ዓለም ከባድ ዶፍ ዝናብ የተነሳ ከከባዱ እንቅልፌ ድንገት ነቃሁ። ከእንቅልፌ ስነቃ ገላዬ በላብ ተጠምቋል። ውሃ ጠምቶኛል። ራሴ ሊፈነዳብኝ ነው። ከጐኔ የተኛችውን ባለቤቴን ቀስቅሼ የምጠጣው ውሃ እንድታመጣልኝ ነገርኳት። ነቅቼ አልጋዬ ላይ ተቀምጬም እያለሁ፣ አሁንም እዚያው ህልም ወስጥ ያለሁ ነው የመሰለኝ። ቅጥቃጤው ገና አለቀቀኝም። ምን ጉድ ነው እባካችሁ? ሌሊቱ ይንጋ እንጂ በጧት ቤቴን ፀበል አስረጨዋለሁ። አ…ቤ…ት!…ያንተ ያለህ!!…. ጩዛሎ ቶርዛ - ቶርዛ ጩዛሎ!!

Published in ልብ-ወለድ

(የፕሮግራም ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር፤ አቶ ጥበቡ ታደሰ)

          ለአምስት ዓመት በጣቢያችሁ ሲተላለፍ የቆየው “ትንንሽ ፀሐዮች” የተሰኘ ተወዳጅ የሬዲዮ ድራማ እንዴት ድንገት ሊቋረጥ ቻለ? እንዳልሽው ድራማው በፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ለአምስት አመታት ያህል ተላልፏል፡፡ የተቋረጠው በሁለት ምክንያቶች ነው፡፡ አንደኛው እንደማንኛውም ድራማ የሆነ ጊዜ ላይ ተጀምሮ ማለቅ ስላለበት ነው፡፡ ሁለተኛውና ዋነኛው ምክንያት ደግሞ ድራማውን ከአድማጭ በሚመጣ አስተያየት እንገመግመዋለንና ከጊዜ ወደ ጊዜ “ይዘት አልባ” ሆነ የሚሉ አስተያየቶች ተበራከቱ። እንደ አጀማመሩ መልእክት የሚያስተላልፍና የሚያስተምር እየሆነ አይደለም የሚሉ አስተያየቶችን አሰባስበን፣ እንዲህ እየተባለ ስለሆነ በተቻለ መጠን አጠንክረው፣ አስተካክለው እያልን በተደጋጋሚ ጠይቀነዋል፤ እንዲያስተካክልም ለአንድ አመት ያህል ጊዜ ሰጥተነው ነበር፣ ያንን ጊዜ ተጠቅሞም አላስተካከለም፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ድራማው ላይ የነበሩት ዋና ዋና ገፀ ባህሪያት በተለያየ ምክንያት ከድራማው ወጡ፡፡

በዚህ በዚህ ምክንያት ድራማው በተወዳጅነቱ መቀጠል ባለመቻሉ ሊቋረጥ ችሏል፡፡ ተዋንያኑ የለቀቁበትን ምክንያት ሊነግሩኝ ይችላሉ-- ለምሳሌ “ቅቤው” የተባለው እና ተወዳጁ ገፀ-ባህሪ አሜሪካ በመሄዱ በድራማው መቀጠል አልቻለም፡፡ “አመዶ” የተሰኘውን አዝናኝ ገፀ-ባህሪ ወክሎ የሚጫወተው በረከት በላይነህም ድራማው ከጊዜ ወደ ጊዜ ይዘቱ እየወረደ በመሄዱ ለክብሬ አይመጥንም ብሎ በራሱ ጊዜ አቁሞታል፡፡ እነዚህ ከምክንያቶች ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ ደራሲና አዘጋጁ፣ ከፈቃዴ ውጭ የታሪኩ ሂደት ሳይቋጭ በተፅዕኖ ነው ድራማው የተቋጨው ብሏል፡፡ ድራማውን በምን መልኩ አቋረጣችሁት? ድራማው ሲ ቋረጥ ዝ ም ብ ሎ አ ይደለም የተቋረጠው፡፡ እኛ በመጀመሪያ ድራማው በተገቢው መንገድ እንዲጠናቀቅ በደብዳቤም በቃልም ነግረነው ነበር፡፡ ለዚህ ፈቃደኛ አልሆነም፡፡ ስለዚህ የህዝቡ አስተያየት በድራማው ላይ ጥሩ አይደለም፣ ይዘቱ ወርዷል፣ ዋና ዋና ተዋንያኑ በተለያየ ምክንያት ለቀዋል፡፡ በእነዚህ ምክንያቶች አድማጭ ስላጣ፣ እሱም ለመቋጨት የተሰጠውን ጊዜ ስላልተጠቀመ ጣቢያው ድራማው እንዲቋረጥ አድርጓል፡፡

ደራሲው ዮናስ “ታሪኩ ይዘቱ አልቀነሰም፣ የጣቢያውየተወሰኑ ኃላፊዎች ለእኔ ካላቸው ጥሩ ያልሆነ አመለካከት ሆን ተብሎ ነው እንዲቋረጥ የተደረገው”ብሏል፡፡ እርስዎ በዚህ ላይ ምን ይላሉ? ዝም ብለሽ አንቺ እንኳን ስታስቢው፣ አምስት አመት በስምምነት አብረን ሰርተናል፡፡ ጥላቻና አለመግባባት በመካከላችን ቢኖር፣ ለአምስት አመት ቀርቶ ለአምስት ቀን እንኳን አብሮ መስራት አይቻልም፡፡ በተለይ ለአራት አመታት ድራማው ጥሩ አድማጭና ተቀባይነት ኖሮት ተስማምተን ቆይተናል፡፡ አሁን ድራማው አድማጭ አጣ፣ ይዘቱ ቀነሰ ሲባል “የግል ጥላቻ ነው፣ እኔን አለመፈለግ ነው” የሚለው ሰበብ፣ ለእኔ ውሀ የሚያነሳ አይደለም፡፡ የግል ጥላቻ ቢኖር “ተደማጭነቱ ቀነሰ፣ እንዲስተካከል አድርግ” ብለን ከአንድ አመት በላይ ጊዜ እንሰጠው ነበር? በተደጋጋሚ መጥቶ እንዲያናግረን ሞክረን ፈቃደኛ ሊሆን አልቻለም፡፡ በመጨረሻም ሂደቱን ጠብቆ ድራማው እንዲጠናቀቅ የሶስት ሳምንት ጊዜ ሰጠነው፡፡ ከዚህ በላይ ጣቢያው ምን ማድረግ ነበረበት ትያለሽ? “እማማ ጨቤ”ን “አባባ ጨቤ” በሚል ገፀ ባህሪ በመለወጥ ከጀርባ “መፈንቅለ ድራማ” ተደርጎብኛል ሲል በጣቢያው መተላለፍ የጀመረውን አዲስ ድራማ ይጠቅሳል፡፡ እርስዎስ ምን ይላሉ? እውነት ለመናገር እሱን ለማፈናቀል ድራማ አልተሰራም፡፡

እንዳልኩሽ “ትንንሽ ፀሐዮች” ድራማ ይዘቱ መቀነስና አድማጭንም ማጣት የጀመረውከአንድ አመት በፊት ነው፡፡ ስለዚህ ይህ ድራማ በራሱ ጊዜ እያበቃለት ነው በሚል ነው ድራማ ማዘጋጀት የጀመርነው፡፡ አዲሱ ድራማም አዲስ ይዘት፣ አዲስ ገፀ ባህሪያት፣ አዲስ አቀራረብና አዲስ ርዕስ ያለው እንጂ ከ“ትንንሽ ፀሐዮች” ጋር በምንም መልኩ የሚገናኝ አይደለም፡፡ በድራማው ውስጥ “አባባ ጨቤ” የሚባል ገፀ ባህሪም በፍፁም የለም፡፡ ገና አንድ ሳምንት መተላለፉ ነው፡፡ ርዕሱም “መሀል ቤት” ይሰኛል፡፡ አምስት አመት የዘለቀን ድራማ በሶስት ሳምንት ማጠናቀቅ ይቻላል ብለህ ታስባለህ? ደራሲም ባትሆን ጋዜጠኛ በመሆንህ ስሜቱ ይገባሃል ብዬ ነው፡፡ ደራሲው በሶስት ሳምንት የአምስት አመትን ድራማ ማጠናቀቅ ከባድ ነው ብሏል ---- ቅድም እንዳልኩሽ እኛ ሶስት ሳምንት የሰጠነው፣ የመጨረሻውን መጨረሻ እንዲያጠቃልል እንጂ ድራማው በራሱ ጊዜ አልቋል ብለን ካመንን አንድ አመት አልፎናል፡፡ አመቱን ሙሉ ደብዳቤ እየፃፍን ይዘቱን እንዲያስተካክል ጥረናል፡፡ ቀደም ብዬ እንደገለፅኩት ከአንድ አመት በፊት ነው ድራማው ይዘቱን፣ ዋና ዋና ተዋንያኑን እና አድማጮቹን ያጣው፡፡ በዚህ ምክንያት ድራማው በራሱ ጊዜ ያለቀ ስለሆነ፣ ፎርማሊቲውን ጠብቆ እንዲጠናቀቅ ነው የሦስት ወር ጊዜ የሰጠነው፡፡ ይህን የምንለው ከአድማጭ በሚደርሰን አስተያየትና እኛም እንደጋዜጠኛ በኤዲቶሮያል ቦርድ ገምግመነው ነው፡ ፡

በነገራችን ላይ ተከታታይነት ያለው ታሪክ የያዘ ድራማ አይደለም፡፡ በየሳምንቱ አዳዲስና የተለያዩ ታሪኮች ይዞ የሚመጣ ድራማ ነው፡፡ ስለሆነም እርሱ ቅን ቢሆንና ቢያስብበት፣ በሶስት ሳምንት ለማጠቃለል የሚያስቸግር ነው ብዬ አላስብም፡፡ ዋናው ነገር ድራማው ያለቀለት ከአንድ አመት በፊት ነው፡፡ ድራማው ከተቋረጠ በኋላ ለሁለት ሳምንታት አስተያየት ስትሰበስቡ ነበር፣ የአድማጮች ትክክለኛ አስተያየት ምን ይመስል ነበር? እንዳልሽው ሁለት ሳምንት የአድማጭ፣ አንድ ሳምንት የተዋንያን አስተያት ሰብስበናል። እንደማንኛውም ረ ጅም ጊ ዜ እ ንደቆየ ረ ጅም ድራማ፣ ጊዜ ሰጥተን ጥበቡ አካባቢ ካሉ ምሁራንና ከተዋንያኑ ጋር ቆይታ አድርገን፣ በሶስተኛው ሳምንት ለማጠቃለል ሞክረናል፡፡ የአድማጮችን አስተያየት በተመለከተ እውነት ለመናገር ለረጅም ጊዜ ተወዳጅ ድራማ እንደነበር ነው የገለፁት፡፡ ብዙ አድማጭም አፍርቶልናል፡፡ ይህን አንክድም እናደንቃለን፡፡ በኋላ ላይ ግን ቀደም ስል በነገርኩሽ ምክንያቶች ድራማው ተቀዛቅዟል፡፡ አድማጭም ያለው ይሄንኑ ነው፡፡ ድራማው ቀደም ሲል ያዝናናን ነበር፣ የተለያዩ መረጃዎችን እናገኝበት ነበር፣ በጣም የቅርባችን የሆኑ የምንወዳቸው ገፀ ባህሪያት አሉት፣ ብለዋል፡፡ የጠቃቀስኳቸው ምክንያቶች እንዳሉ ሆነው፣የሚያልቁት ማለቅ ስላለባቸው ነው እንጂ ስለማይወደዱ አይደለም፡፡ ጠቅለል ባለ መልኩ ለማስቀመጥ፣ የአድማጩ አስተያየት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየደከመ መጣ እንጂ ተወዳጅና አዝናኝ ድራማ መሆኑን መግለፃቸውን ልደብቅሽ አልችልም፡፡

ለተወዳጅነቱም ምስክሩ አምስት አመት በጣቢያው ላይ መቆየቱ ነው፣ ይሄ ምንም ጥርጥር የለውም፡፡ እንደ መጀመሪያው መጨረሻው ሊያምር አልቻለም ነው፣ የመቋረጡ ምስጢር፡፡ አጨራረሱም በዚህ መልኩ የሆነው እሱ ተባባሪ ባለመሆኑ ነው፡፡ ጥፋቱ የማንም ይሁን የማን አምስት አመት ተወዳጅ ድራማ ይዛችሁ ዘልቃችሁ፣ ከድራማውም ውጭ ዮናስ የእናንተ ቀደምት ጋዜጠኛ እንደመሆኑ በዚህ መልኩ መለያየታችሁ--- ለሁለታችሁም (ለጣቢያውም ሆነ ለዮናስ) ጥሩ ነው ብለው ያስባሉ? (ሳ….ቅ) በነገራችን ላይ ድራማውን የጀመረው እዚሁ ጋዜጠኛ ሆኖ እየሰራ መሆኑን ታውቂያለሽ? አዎ አውቃለሁ! ያን ጊዜ የመዝናኛ ክፍል ኃላፊ ሆኖ ተመድቦ ይሰራ ነበር፡፡ እኛ የምናውቀው ጋዜጠኛ መሆኑን እንጂ ደራሲ መሆኑን አናውቅም ነበር፡፡ በፋና ህግ መሰረት ጋዜጠኛ ሆነሽ ድርሰት መፃፍ፣ መተወን አትችይም ነበር፡፡ እንደነገርኩሽ በወቅቱ እሱ የመዝናኛ ክፍል ኃላፊ ስለነበረ እንዲከታተለው ተመድቦ፣ እንደ ጋዜጠኛ ብቻ ነው ሲሰራ የነበረው፣ በኋላ ከእኛ ጋ ስራ ከለቀቀ በኋላ ነው የ“ትንንሽ ፀሀዮች” ደራሲ እሱ መሆኑን ያወቅነው፡፡ አልገባኝም! እኛ ዮናስን የመዝናኛ ክፍል ኃላፊ አድርገን መድበነው ድራማውን ይከታተለው ነበር እንጂ የድራማው ደራሲ እሱ መሆኑን አናውቅም ነበር፡፡

ደራሲው ነው ተብሎ ገንዘብ እየመጣ የሚወስደው ሌላ ሰው ነበር፡፡ የድራማውም ደራሲ ስም ያን ጊዜ ያ ብር እየመጣ የሚወስደው ሰው ስም ነበር፡፡ ያንን ሰው የድራማው ደራሲ ነው ብሎ የሚያረጋግጥልን ራሱ ዮናስ ነበር፡፡ ምክንያቱም የመዝናኛው ክፍል ኃላፊ ስለነበር ማለት ነው፡፡ ከዚያስ? ከዚያማ ያኛው ሰው ደራሲ ነኝ ብሎ መጥቶ ገንዘብ ይወስዳል፡፡ በኋላ ስንገነዘበው ገንዘቡ የሚደርሰው ዮናስ ጋ ነበር፡፡ ይህንን ሁሉ ያወቅነው ከጋዜጠኝነት ስራው ከፋና ከለቀቀ በኋላ ነው፡፡ ነገር ግን ድራማው ሲጀመር አንስቶ በህብረተሰቡ ዘንድ ተወዳጅ በመሆኑ፣ ለአድማጭ ክብር ሲባል ድራማው እንዲቀጥል ተነጋግረን፣ በይፋ ደራሲነቱን አውጆ መስረት ጀመረ፡፡ ያን ጊዜ ዮናስ ጋዜጠኛ እንጂ ደራሲ መሆኑን አናውቅም ነበር፡፡ በሌላ አማርኛ ድራማው ከጅምሩ አንስቶ የፋና እንጂ የዮናስ አይደለም፣ምክንያቱም ለሰራበት ስራ ይከፈለዋል፡ ፡ በነገራችን ላይ ከፍተኛ ክፍያ ነበር የሚከፈለው፡ ፡ በየሚዲያው ከሚከፈለው አንፃር በጣም በተሻለ ሁኔታ ለእሱም ለተዋንያኑም እየከፈልን ነው የቀጠልነው፡፡ ይህን እሱንም ብትጠይቂው ይነግርሻል፡፡ ዮናስ ደግሞ ለሙያው ሲል እንጂ ድራማው ከሚያስገባው ገቢ አንፃር የሚከፈለኝ እዚህ ግባ የሚባል አይደለም ባይ ነውይሄ እንግዲህ ሰዎች አንድን ነገር ማጥላላት ከፈለጉ የሚናገሩት ነገር ስለሆነ ምንም ማድረግ አይቻልም፡፡ እኔ ግን ጥሩ ክፍያ እንደሚከፈለውና በዚህም ደስተኛ እንደነበር ነው የማውቀው፡፡

በመጨረሻ የተለያያችሁበትን ሁኔታ በተመለከተ አልመለስልክልኝም---- አዎ ስለ መጨረሻችን ያነሳሽው ነገር አለ---- አዎ አምስት አመት አብረን ቆይተናል፡፡ ቀደምት ጋዜጠኛችንም ነ ው፤ ይ ህንን የ ሚክድም የ ለም፡፡ ስለስንብቱም ቢሆን ጣቢያው የሚያስባቸው ነገሮች አሉ፤ እነዚህ ነገሮች የሚከናወኑት ተቀራርበሽ ስትሰሪ ነው፤ ሌላው ቀርቶ እንደ ደራሲ ማጠቃለያው ላይ አስተያየት እንዲሰጥ ብዙ ጊዜ ወትውተነው ለዚህ ጉዳይ ፈቃደኛ ሊሆን አልቻለም፡፡ የመለያየታችን መጨረሻ አለማማር የጣቢያው ችግር ሳይሆን የእሱ ተባባሪ አለመሆን ነው፡፡ ለመጨረሻ ጊዜ የተፃፈልኝ ደብዳቤ የአንድ ሙያተኛ ክብር የማይመጥን ነው ሲል ዮናስ ወቅሷል፡፡ የደብዳቤው ይዘት ምን ይመስላል? ምናልባት ደብዳቤውን ብታይው ደስ ይለኛል፡፡ ባጋጣሚ ደብዳቤውን የፃፍኩትም እኔ ነኝ፡፡

የድራማው ይዘት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየወረደ መምጣቱን፣ ከአድማጮች የሚመጣውም አስተያየት ይህንኑ የሚያረጋግጥ መሆኑን፣በኤዲቶሪያል ቦርዱ በተደረገው ግምገማም ድራማው በጥሩ ሁኔታ መቀጠል እንዳልቻለ፣ እንደገናም የድራማው ዋና ዋና ገፀ ባህሪያት ከድራማው እየወጡና እያለቁ ስለመሆናቸው፤ በዚህም ምክንያት ድራማው የነበረው ተወዳጅነት እየቀዘቀዘ መምጣቱን፣በዚህም ለጣቢያው እየመጠነ ስላለመሆኑ፣ ይህንንም ከአመት በላይ በደብዳቤም በቃልም ማሳወቃችንንና ይህንንም ለማስተካከል ፈቃደኛ እንዳልሆነ፣በዚህም ምክንያት በሶስት ሳምንት ውስጥ መጠቃለል እንዳለበትና ከሶስት ሳምንት በኋላ በጣቢያው እንደማይተላለፍ መወሰናችንን ገልፀን---- በአክብሮት፣ ፎርማል በሆነ መንገድ ነው የፃፍነው፡፡ ከዚህ ሌላ የሚናገር ደብዳቤ ሰጥተውኛል የሚል ከሆነ ማስረጃ ያቅርብ። ከዚያ ውጭ ሞ ራልና ክ ብር የ ሚነካ ሃ ሳብም ን ግግርም አልተካተተበትም፡፡ ይሄው ነው ምላሼ፡፡

Published in ጥበብ

(የ“ትንንሽ ፀሐዮች” ደራሲና አዘጋጅ፤ ዮናስ አብርሃም)

            በፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ላለፉት አምስት አመታት ቅዳሜ ረፋድ ላይ ሲተላለፍ የቆየው “ትንንሽ ፀሐዮች” የሬድዮ ድራማ፣ ከሶስት ሳምንት በፊት ተቋርጧል፡፡ የድራማው ደራሲና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ዮናስ አብርሃም፤ የጀመርኩት ታሪክ ሳይቋጭና ሳያማክሩኝ በጣቢያው ሌላ ድራማ ተጀምሯል፣ እሱ ደግሞ “አባባ ጨቤ” በሚል ከእኔ ድራማ ባልተለየ ድባብ የተቃኘ ነው በማለት ድራማው ያለፈቃዱ መቋረጡንና “መፈንቅለ ድራማ” እንደተፈፀመበት ተናግሯል፡፡ የጣቢያው የፕሮግራም ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጥበቡ ታደሰ በበኩላቸው፤ ድራማው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየደከመና ይዘቱን እያጣ በመሄዱ፣ ለአንድ አመት ማስጠንቀቂያ ከሰጠነው በኋላ ባለማስተካከሉ፣ በሶስት ሳምንት ውስጥ ድራማውን እንዲቋጭ በደብዳቤ ጠይቀነው ምላሽ ሳይሰጥ በመቅረቱ፣ ድራማውን ለማቋረጥ ተገደናል ብሏል፡፡

የአዲስ አድማስ ጋዜጠኛ ናፍቆት ዮሴፍ፤ ከሁለቱም ጋር ያደረገችውን ቃለምልልስ እንደሚከተለው አጠናቅረነዋል፡፡ “ትንንሽ ፀሀዮች” ድንገት ነው እንዴ ያለቀው ? ለአምስት ዓመት ያህል የዘለቀው “ትንንሽ ፀሀዮች” የሬድዮ ድራማ በእኔ ሀሳብ አላለቀም። እንዲቋረጥ የተደረገው በጣቢያው ፍላጎት ነው። በቂ ጊዜ ሳላገኝ አቋርጥ የሚል ደብዳቤ ደረሰኝ። ደብዳቤው በሶስት ሳምንት ውስጥ ድራማውን እንዳጠናቅቅ የሚያዝ ነበር፡፡ ሆኖም የአምስት ዓመት ታሪክ በሶስት ሳምንት ውስጥ መቋጨት በጣም አስቸጋሪ ስለሆነብኝ ጥዬ ወጥቻለሁ፡፡ በሶስት ሳምንት ውስጥ ታሪክ መቋጨት ያን ያህል አስቸጋሪ ነው እንዴ? በጣም እ ጅግ በ ጣም ያ ስቸግራል! አ ንድን ትልቅ ዘገባ በጋዜጠኝነት ስትሰሪ እንኳን፣ በሁለት ሳምንት እጨርሳለሁ ብለሽ አራት ሳምንት ሊወስድ ይችላል፡፡ ጉዳዩ እየሰፋ ተጨማሪ ግብአቶች እያስፈለጉ ሊራዘም ይችላል፡፡ አምስት አመት የሄደው የኔ ድራማ ደግሞ ትልልቅ ጉዳዮችን ይዟል፣ ከ120 በላይ ተዋንያን እና ጉዳዮቻቸው አሉ፡፡

ይህንን ሰፊ ጊዜና ሰፊ ሀሳብ የያዘ ድራማ፣ በሶስት ሳምንት ማጠቃለል አስቸጋሪ ነው፡፡ ምክንያቱም እንዳንዱ ጅምር ታሪክ፣ ምላሽ ይፈልጋል። ስለዚህ ድራማውን ለማጠቃለል የሚበቃኝን ጊዜ እኔ ነኝ የምወስነው፣ ነገር ግን እኔን ያማከረኝ የለም፡፡ በተደጋጋሚ አብረን እንድንሰራ እና አፅመ-ታሪኩን (ሲኖፕሲስ) እንዳቀርብ ተጠይቄያለሁ፡፡ ሲኖፕሲስ ማቅረብ የምችለው የጀመርኩትን ታሪክ ከሰበሰብኩ በኋላ፣ድራማው እረፍት አድርጎና የሰው አስተያየትተሰብስቦ፣ እንደገና ሁለተኛ ዙር የሚቀጥል ከሆነ፣ ምን መስራት እንዳሰብኩኝ አሳውቃለሁ፡፡ ነገር ግን ረጅም ድራማ ከጫፍ እስከ ጫፍ በሲኖፕሲስ ማስቀመጥ አይቻልም---- የሚል ምላሽ ሰጥቻለሁ፡፡ ቀደም ሲል የጣቢያው ጋዜጠኛ ነበርክ፡፡ የእነማማ ጨቤን ታሪክም እዚያው በጋዜጠኝነት እየሰራህ ነበር የጀመርከው፡፡ በመሀል የጋዜጠኝነት ስራህን ለቀቅህ፡፡ ድራማው ታዲያ እንዴት ቀጠለ? ልክ ነው፡፡ በጣቢያው ጋዜጠኛ ሆኜ እየሰራሁ ነው የጀመርኩት፣ነገር ግን በመሀል በደረሰብኝ በደል ከስራዬ ስለቅ፣ ድራማው ተወዳጅ ስለነበር፣ ለአድማጭ ሲባል በደሌን ወደ ጎን ትቼ በዲኬቲ ኢትዮጵያ ስፖንሰርነት በዚያው መቀጠል ችሏል። በኋላም ዲኬቲ በስፖንሰርነት ለአራት አመት ቀጥሏል፡፡ ዲኬቲ ስፖንሰርነቱን ሲያቆም፣ የድራማውን የወደፊት አፅመ ታሪክ አስቀምጥና፣ አብረን እንስራ አሉኝ፡፡ እኔ ደግሞ በጋዜጠኝነት ታዝዤ ይህን ስራ ተብዬ ልሰራ እችላለሁ፡፡

የድርሰት ስራ ግን ፈጠራ ስለሆነ የሰዎችን ሀሳብ እቀበል ይሆናል እንጂ በዚህ አውጣው፣ በዚህ አውርደው ተብዬ ልሰራ አልችልም፡፡ በዚህ አቅጣጫ ላይ ብታተኩር የሚል ሀሳብ በደፈናው ልቀበል እችላለሁ፡፡ ነገር ግን እንዴት እንደምፅፍ ጭምር እጄ እየተጠመዘዘ የምፅፍ ከሆነ፣ እኔ ደራሲ ሳልሆን ሪፖርት ፀሐፊ ነኝ ማለት ነው፡፡ ይህንን ደግሞ እኔ ራሴ በመርህ ደረጃም የምቀበለው አይደለም፡፡ ድራማውን የማቋረጥ ነገር የተነሳው አሁን ልገልፃቸው በማልፈልጋቸው ግላዊ ጉዳዮች ምክንያት ነው፡፡ ዞሮ ዞሮ ረጅም ድራማ በባህሪው፣ ደራሲውም ቢሆን መንገድ ያመላክታል እንጂ ወደፊት የሚፈጠረውን ነገር ቀድሞ መተንበይ አይችልም፡፡ ወቅታዊ ክስተቶች ይፈጠራሉ፣ እኔ ወደፊት አንድ ነገር እንደሚከሰት የምተነብይበት መለኮታዊ ባህሪ የለኝም፣ ነገር ግን ወቅቱ የሚወልዳቸውን ነገሮች አድማጭን በሚያሳዝንና በሚያስተምር መልኩ በድራማው አካትታለሁ፡፡ ስለዚህ የዛሬ ስድስት ወር ወደፊት ስለሚከሰት ነገር በድራማው ባህሪ መሰረት መተንበይ አልችልም፡፡ ከአንዳንድ አድማጮች በድራማው ዙሪያ አስተያየት ሳሰባስብ፣ “ትንንሽ ፀሐዮች” በወቅታዊ ነገሮች ላይ የሚያተኩር በመሆኑ መቋጫ የለውም---ያሉኝ ነበሩ። አንተ ከጣቢያው ጋር ያለህ ግንኙነት ባይቋረጥ ኖሮ፣ ድራማውን ለመቋጨት ምን ያህል ጊዜ ይበቃህ ነበር? ይህ በጣም የምፈልገው ጥያቄ ነው! ምን መሰለሽ---- ህይወት ይቀጥላል፣ ሰዎች ሊንጠባጠቡ ይችላሉ፡፡

የዚህ ድራማ ባህሪ የሚያሳየው ታሪኮች ይጀመራሉ፣ ይቋጫሉ ግን አንድ ሰው ታሪኩ የሚጠናቀቀው በሞት ሲሰናበት ነው፡፡ እዚህ ድራማ ታሪክ ውስጥም ሰዎች ያድጋሉ፣ እነ አመዲ ወደ ዩኒቨርሲቲ ደረጃ ይገባሉ፡፡ እማማ ጨቤ አርጅተው እስከ ኑዛዜ ይደርሳሉ፣ ከዚያም ህይወት አለ፡፡ በዚህ ስሌት መሰረት የሚያልቅ አይደለም፡፡ እኔ ማቆም የምፈልገው ህዝቡ (አድማጩ) በዚህ ድራማ ጣዕም ካጣ ወይም መስማት ካልፈለገ ብቻ ነው፡፡ እኔ መለኪያዬ የህዝብ አስተያየት ነው፣ እያንዳንዱን ሁኔታና አስተያየት እከታተላለሁ፡፡ በህዝቡ በኩል እንደተወደደ ነበር የቀጠለው፡፡ ለዚህ ረጅም ድራማ መነሻህ ምንድነው? መነሻዬ ለ40 ዓመታት በተከታታይ የሄደ አንድ የውጭ ድራማ ነው፡፡ ለአምስት አመት በተከታታይ የተደመጠ በአገራችን የመጀመሪያው ድራማ ነው - “ትንንሽ ፀሀዮች”፡፡ ከዚህ በኋላም የሚመጡት ድራማዎች “ትንንሽ ፀሐዮች” ተቀባይነት ስላገኘ፤ ተፅዕኖው እንደሚያርፍባቸው ጥርጥር የለኝም፡፡ ምን ያህል ጊዜ ለማጠናቀቅ ይበቃሀል ላልሺው---- እድሜ ልኬን ቢቀጥል ደስ ይለኛል፡፡ “መፈንቅለ ድራማ” ደርሶብኛል ስትል ሰምቻለሁ፡፡ ሌላ ድራማ ጣቢያው ተክቷል? እኔን አጣድፈውና ገፍተው አስወጥተውኝ ሲያበቁ፣ “እማማ ጨቤ” ን “አባባ ጨቤ” ብለው ተክተዋል፡፡ ድባቡ ሁሉ ከእማማ ጨቤ የተለየ አይደለም፡፡

ይህን ወደፊት ህዝብ ይፈርደዋል፡፡ በእኔ እድሜ ልክ ድራማው መቀጠል ይችላል ብለሀል፡፡ አሰልቺ አይሆንም? በፍፁም!! ከጣቢያው ጋር ስምምነት ኖሮ መፃፍ እስከቻልኩ ድረስ በእኔ እድሜ ልክ መጓዝ የሚችል ባህሪ ያለው ድራማ ነው፡፡ በመሀከል እረፍት እያደረገ፣ የህዝብ ገንቢ አስተያየት እየተጨመረበት በጥሩ ሁኔታ መቀጠል ይችላል፡፡ ህዝቡ በአስተያየቱ ሰለቸኝ፣ በቃን፣ ካለ ደግ መቆም ይችላል፡፡ ምክንያቱም የድራማው ግብ አድማጭ ነው፡፡ አሁን እኮ የድራማው ተዋንያን ገፀ-ባህሪ ብቻ ሳይሆኑ ህያው ሆነዋል፡፡ ስለዚህ እነሱን መሰረት አድርጎ፣ ትልልቅ አገራዊ ጉዳዮችን በማንሳትና አዳዲስ ሀሳቦችን በማካተት እንደጣፈጠ እንዲዘልቅ የማድረግ ብቃትም አቅምም አለኝ፡፡ በዚህ አጋጣሚ ይህን ለሚያነቡ ሁሉ የምናገረው፣ ድራማው በውስጤ አላለቀም፣ የመፃፍ አቅምም አላጠረኝም፡፡ ድራማው ከተቋረጠ በኋላ የአድማጮችን ምላሽ ለማወቅ ሞክረሃል? በሚገርም ሁኔታ--- ለድራማው አድማጮች የግል ስልኬ ተሰጥቷል፡፡ ሰዎች በማናቸውም ሰዓት ስልክ ይደውላሉ፣የሚጠቅመኝ ግብአት ስለማገኝበት ሳልሰለች አዳምጣለሁ፡፡ የሚደወልልኝ ስልክ ቁጣም ጭምር አለበት፡፡ አንድ መዝናኛችንና ብዙ የምንማርበት ነው፣ ለምን ቆመ የሚል ቁጣ። በዚህ መልኩ መቋረጥ የለበትም፣ ችግር ካለም ፍቱትና ይቀጥል እያለ ነው - አድማጭ፡፡ እኔ የምፅፈው ህይወትን ነው፡፡ እኔ የምፅፈውን ህይወት የሚኖሩ ሰዎች ያማክሩኛል፡፡ እንደውም የሆነ ወቅት ላይ “የአድማጭ ደራሲያን” ማለት ጀምሬ ነበር፡፡ አድማጮች ይሄ ቢሆን፣ ይሄ ነው ብለው ተነጋግረው የወሰኑትን አንድ ሰው ይደውልልኛል፡፡ ከዚህ በኋላስ እነ እማማ ጨቤን በሌላ ጣቢያ የመቀጠል ሀሳብ አለህ? አድማጮች እንደዚህ እያሉ ነው፡፡

በሌላ የሬድዮ ጣቢያው ቢቀጥል ደስ ይለናል ብለዋል፡፡ ነገር ግን ይህን አደርጋለሁ አላደርግም የሚለውን አሁን አልወሰንኩም፡፡ ማስመር የምፈልገው ድራማውን በተፅዕኖ ሳልፈልግ ማቋረጤን አድማጮች እንዲያውቁ ነው፡፡ ድራማውን በሶስት ሳምንት እንድታጠናቅቅ የተፃፈልህ ደብዳቤ አጠቃላይ ይዘት ምን ይላል? ለድራማው በአስቸኳይ መቋጨት ጣቢያው ያቀረበው ምክንያት ምንድን ነው? መነሻ ችግሮቹ ሌላ ሆነው ሳለ፣ እዚያ ያሉ ጥቂት ሰዎች የራሳቸው ፍላጎት ስላለ የሚሰጡኝ አስተያየት ትክክለኛ አልነበረም፡፡ ረዘመ፣ ታሪኩ አይራመድም፣ የበፊቱን ያህል ጣዕም የለውም--- የሚሉ ሀሳቦችን ሰምቻለሁ፡፡ ሰምቼም ዝም አላልኩም፡፡ የድራማው የታሪክ ፍሰት ምንም ችግር እንደሌለበት ባውቅም ሀሳብና አስተያየት ነው፣ ለማሻሻልና የበለጠ ለማጣፈጥ ጥረት ሳደርግ ቆይቻለሁ፡፡ ነገር ግን ለድራማው መምረርና መጣፈጥ መለኪያዎቼ አድማጮቼ ናቸው፡፡ የዚህ ድራማ አድማጭ - ከገጠር እስከ ከተማ፣ ከህፃን እስከ አዛውንት፣ከምሁሩ እስካልተማረው--- ሁሉንም መደብ ያካተተ ነው። እነሱ ናቸው መመዘኛዎቼ፡፡ ከወራት በፊት በጋራጥሩ የሚሆነውን እናዘጋጅ ተብዬ በአቶ ብሩክ ከበደ ተጠይቄያለሁ፡፡ ሀሳብ መስማት እችላለሁ፡፡ ልታዘዝ ግን አይገባም፡፡ በምን ጉዳይ ልሰራ እንደሚገባ ሀሳብ ልቀበልና የማምንበትን ልወስድ እችላለሁ፡ ፡ ከጣቢያው ሰዎች አ ይደለም ከየትኛውም ሰው ሀሳብ እወስዳለሁ፡፡ ይሄ ለመማርና ለመሻሻል ያለኝን ሀሳብ ያመለክታል፣ መታዘዝ ግን አልችልም፡፡ ዝም ብዬ ስራዬን ቀጠልኩ፡፡ በቃልም ተነጋግረናል፡፡ ድራማውን አንድ መሰረት ካስያዝኩት በኋላ በምን አቅጣጫ እንደምሄድ፣ አንኳር አንኳር ሀሳቦችን ላነሳ እችላለሁ ብዬ ተናገርኩኝ፣ ከዚያ በኋላ ሌላ ደብዳቤ መጣ፡፡

ምን አይነት ደብዳቤ? የመጣው ደብዳቤ የአንድን ሙያተኛ ክብር የሚጠብቅ አይደለም፡፡ ከአንድ ትልቅ ጣቢያም የሚወጣ አይነት አይደለም፣ ስድብ አዘል ነው። ድራማው ደከመ፣ ለዛውን አጣ፣ የሚል አይነት ተገቢ ያልሆኑ ቃላት የሰፈረበት ነው፡፡ በነገራችን ላይ ደግሜ የምነግርሽ መመዘኛዎቼ አድማጮቼ ናቸው፡፡ አድማጩ ድራማውን ባይፈልግ ጣቢያው ለእኔ የወር ደሞዝ አይከፍለኝም፡፡ ስለዚህ መለኪያዬ መላው ህብረተሰብ ነው፡፡ ስለ ስነፅሁፍ ባያውቅ ስለ ህይወት ይረዳል፡፡ ስለ አንዲት የቤት ሰራተኛ ስፅፍ፣ ብዙ የቤት ሰራተኞች ነባራዊ እውነታውን ይነግሩኛል፡፡ ስለዚህ አለቆችና ህብረተሰቡ አንድ አይነት አስተያየትና ግምገማ የላቸውም፡፡ የሆነ ሆኖ የጣቢያው ሰዎች ለእኔ ያላቸው ጥሩ ያልሆነ አመለካከትና ከጀርባው ሌላ ፍላጎት ተጨምሮበት ነው እንጂ፣ ህዝቡ ሰጠ የተባለውና በደብዳቤው ላይ የተገለጸው አስተያየት ለእኔ የሚመጥን አይደለም፣ አድማጩም ይህን አላለም፣ በየቀኑ የሚደርሰኝ አስተያየት የጣቢያው ሰዎች ከፃፉት ደብዳቤ ፍፁም የተለየ ነው፡፡ የግል ጥላቻ፣ መጥፎ አመለካከት እያልክ በተደጋጋሚ ነግረኸኛል፡፡ በጣቢያው ከሚሰሩ ሰራተኞች አሊያም ኃላፊዎች ጋር የተጣላህበት ጉዳይ አለ? ብዙ ታሪክ ያለው የረጅም ጊዜ ሂደት ስለሆነ፣በአሁኑ ወቅት እንዲህ ነው እንደዚያ ነው ለማለት እቸገራለሁ፡፡

ድራማውን ስትፅፍና ስታዘጋጅ ከጣቢያው ጋር ያለህ ስምምነት ምን ይመስላል? ድራማውን አምስት አመት ሙሉ ስፅፍና ሳዘጋጅ የቆየሁት በአጠቃላይ ኃላፊነቱን ይዤ የምሰራው እኔ ነኝ፡፡ ኃላፊዎቹ ድራማውን የሚያዳምጡትም አይመስለኝም፣ ተዋንያኑንም አያውቋቸውም፡፡ እነሱ ደሞዝ ብቻ ነው የሚከፍሉት፣ ይህንን ሁሉ ነገር አስተባብሬ በየሳምንቱ እየተሰራ የሚቀርበው በእኔ የግል ጥረት ነው፡፡ እኔ እሰራለሁ፣ እነሱ ደሞዝ ይከፍላሉ በቃ! ይህ በራሱ ትልቅ እውቅና ሊሰጠው ሲገባ፣ በፍቅርና በሰላም መሰነባበት እየተቻለ--- -ለእኔ ይህ አይገባኝም፣ የብዙ ድራማዎች ፍፃሜ እንዲህ አይደለም፣ በደስታና በፌሽታ፣ ተደግሶና በሰላም ተቋጭቶ ነው የሚሰነባበቱት፡፡ ድራማው በአምስት አመት ጉዞው በገቢ ደረጃ እንዴት ነበር? በገቢ ደረጃ ጥሩ ነበር፣ ስፖንሰር አለው ከዲኬቲ ጋር ነው የተጀመረው፡፡ ለስድስት ወር እንምከረው ብለው እስከ አራት አመት ዘልቀዋል። በየቀኑ ማስታወቂያዎች አሉት፡፡ እኔ ከሚገባው ገቢ በደቂቃ ተሰልቶ በወር ነው የሚከፈለኝ፣ ደሞዝተኛ ነኝ፡፡ ለጣቢያው ጥሩ ገንዘብ አስገብቷል። እኔ አሁን ብስጭቴ ከጣቢያው በማቆሜ አይደለም፣ የተቋረጠበት ሂደት ላይ ነው፡፡

በማቋረጤ ሌላ ቦታ ስለምሰራ፣ ብዙ ገንዘብ አገኛለሁ፡፡ እስካሁንም ስራውን ስለማከብር እንጂ ጣቢያው ከሚያስገባው ገቢ አኳያ ለእኔ የሚከፍለኝ በቂ አይደለም፡፡ በገቢ ብቻ ሳይሆን በተደማጭነትም ድራማው የጣቢያው ጌጥ ነበር ብዬ አፌን ሞልቼ እናገራለሁ፡፡ ተወዳጅ ስለመሆኑ እነሱም አይክዱትም፡፡ ነገር ግን ለእኔ እውቅና ላለመስጠት ከፍተኛ ጥረት አድርገዋል፡፡ በስልክ ደውለው እንኳን እግዜር ይስጥልኝ አላሉኝም! ይሄ በጣም ያሳዝናል፡፡ አሁን ድራማው የፋና ነው ወይስ የአንተ? እስካሁን ወጪ አውጥቶ ያስተላለፈው ራሱ ጣቢያው ነው፡፡ እኔም አልፈልገውም፡፡ ከዚህ በኋላ ያለው እና ገፀ ባህሪያቱ ግን የእኔ ናቸው፡፡ እዚህ ሆነህ ስለጀመርከው እኛ በፈለግነው ምገድ እናስቀጥለዋለን የሚል ሀሳብ ነበራቸው፡፡ ይሄ ፈፅሞ እንደማይሆን እኔም በአፅንኦት ተናግሬያለሁ፡፡ ወደፊት ምን ሀሳብ አለህ? ይሄንን አንድ አመት ካለፈው በኋላ ወደ ቴሌቭዥን ልንለውጠውም በሲዲም ለህዝብ እንድናደርስ አስተያየቶች ይጎርፋሉ፡፡ ጥያቄውም የሚቋረጥ አይደለም፡፡ እኔ ይሄንን ድራማ እየፃፍኩ ሌላም ነገር አዘጋጃለሁ፡፡ ጥሩ ልምድ አግኝቻለሁ። ስለሆነም ከዚህ በላቀ ጭብጥና በማራኪ አቀራረብ በሌላ ጣቢያ ልቀጥል እችላለሁ፡፡ ይሄንን የግድ መቀጠል ላያስፈልገኝ ይችላል፡፡ ነገር ግን አንዴ ህያው የሆኑ ገፀ ባህሪያት ሆነዋልና በተለያየ መንገድ ይገለጋሉ፡፡ የህዝቡን አስተያየት አይቼ እንደሁኔታው አደርጋለሁ፡፡ ነገር ግን እኔ በተሻለ ሁኔታ መምጣት የምችልበት አቅምም ብቃትም ዝግጅትም አ ለኝ፡፡ “ ትንንሽ ፀሐዮች”ን መልሶ በሬድዮ የማምጣት ጉዳይ ላይ ገና አስቤ አልጨረስኩም፡፡ ገፀ ባህሪያቱ የማይረሱና የሚፈለጉ ከሆነ አንድ ነገር ለማድረግ እገደዳለሁ፡፡ ይሄ የኔ መብት ነው፡፡

Published in ጥበብ

                      ስለ ንባብ ጠቃሚነት ብዙ ተብሏል። የንባብ ልምድን ባህል ለማድረግ ደግሞ ንባብ ከልጅነት መጀመር እንዳለበት፣ ለልጆቻችን የህፃናት መፅሐፍ ማንበብና እነሱንም ማስነበብ እንዳለብን የምናውቅ ይመስለኛል። ግን ብዙ የማንሰማውና ክፍተት የሚታይበት የንባብ ጉዳይ የታዳጊ ወጣቶች የንባብ ሁኔታ ነው። ስለ ሕፃናት መፃሕፍት እና የንባብ ልምድ ብዙ ይባልና፣ ህፃናቱ አድገው 12 ወይም 13 አመት ላይ ሲደርሱ፣ ልጆቹ ወደ ምን አይነት መፃሕፍት መሸጋገር እንዳለባቸው ብ ዙ ሲ ታሰብ ወ ይም ሲ ነገር አ ናይም። እድሜያቸው ከ13-18 የሆኑ ታዳጊዎች ልዩ የሆነ ባህሪያት አላቸው። ህፃናት አይደሉም፤ ስለዚህ ስዕልና ደማቅ ቀለማት ያላቸው አስቂኝ የእንስሳት ታሪኮች እንደ ድሮ አይመስጧቸውም። ወይም ደግሞ እንደ ትልቅ ሰዎች የታሪክ ወይም የአዋቂ ልብ ወለድ መፃሕፍት ላይስቧቸው ይችላሉ።

እነኚህ ታዳጊዎች (teenagers) በባህሪያቸው ስለ ራሳቸውና ስለ አካባቢያቸው እውነታ ለመጀመሪያ ጊዜ እየተረዱ ያሉ እና የመረዳትም ከፍተኛ ፍላጐት ያላቸው ናቸው። ነገር ግን በልጅነታቸው የጀመሩትን የንባብ ልምድ ሊያስቀጥል የሚችል እና የእድሜያቸውን ፍላጐት ታሳቢ ያደረጉ የፅሑፍ ስራዎች ካላገኙ፣ ሌሎች ትኩረቶቻቸውን የሚሻሙ ብዙ ክፉ ጊዜ ማሳለፊያዎች አሉላቸው። በኢትዮጵያ እጅግ ጥቂት ቢሆኑም ለታዳጊ አንባቢያን የተፃፉ መፃሕፍት አሉ። ከነዚህ መሀል የዳንኤል ነጋሽ Breaking the Chain አንዱ ነው። መፅሐፉ በእንግሊዝኛ የተፃፈ ሲሆን 138 ገፆች አሉት። ዳንኤል ነጋሽ ከስምንት በላይ የህፃናት እና የአዋቂዎች መፃሕፍት ያሳተመ ደራሲ ነው።

ይህ መፅሃፍ የዳንኤል የመጀመሪያው የእንግሊዝኛ ስራ ቢሆንም ከፍተኛ የገንዘብ ሽልማት የሚያስገኘውን የ2013 Burt Award for African Literature የተሰኘ ውድድር በአንደኝነት አሸንፎበታል። “ብሬኪንግ ዘ ቼይን” ስለ “ቀውጢዋ” ሙኒት ይተርካል። ሙኒት አስቸጋሪ ኑሮ ትመራለች። በወጣት እድሜዋ ታናሽ ወንድሟን እና ጠጪ አያቷን ትንሽ ሱቅ ውስጥ በመነገድ ታስተዳድራለች። ቤት ውስጥ የምትጋፈጣቸው ችግሮች ሳያንሳት፣ ወንድሟን ከአደጋ ለመጠበቅ በምታደርገው ጥረት በአካባቢዋ ያሉ ወንጀለኞች የሚሰሩትን ሙስና እና በደል ትደርስበታለች። እናም ዳንኤል ነጋሽ ለ138 ገጾች የሙኒትን ውጣ ውረድ ያስነብበናል። የታዳጊዎችን ልብ ሊይዝ በሚችል መልኩ ስለ ሰዎች ህገ-ወጥ ንግድ፣ ስደት እና ሙስና ጉዳዮች ያነሳል።ከላይ ለማስረዳት እንደተሞከረው፣ ታዳጊዎች በልጅነታቸው የጀመሩትን የንባብ ልምድ መቀጠል አለባቸው። እንደ “ብሬኪንግ ዘ ቼይን” ያሉ መፃሕፍት መኖር ደግሞ ይህንን ለታዳጊዎቻችን ማድረግ እንድንችል ያግዙናል። መጽሐፉ፤ በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ቤተ - መፃሕፍት እና በሜጋ መፃሕፍት መደብር ይገኛል።

“276 ሴት ተማሪዎች መጠለፋቸውን ብቻ ታወራላችሁ። በሦስት እጥፍ የሚበልጡ ተማሪዎችን ጠልፈናል። ሰሞኑን በአንድ ቦታ 300 ሰዎች ገድለናል። ለምን ይሄ አይወራም?”

   “አገር በቀል እውቀት” በሚል ሰበብ ስልጣኔን እያንቋሸሸ፤ አልያም የአሜሪካና የአውሮፓ የሳይንስ ትምህርትን እያብጠለጠለ፣ ኋላቀርነትን የሚሰብክ ፕሮፌሰርና ዶክተር ሞልቷል። ቦኮ ሐራም ከዚህ የተለየ አላማ የለውም። ስሙ ራሱ፤ “የምዕራባዊያን ትምህርት ሐራም ነው” እንደማለት ነው። ቦኮ ሐራም፤ ከወገኛ ምሁራን የሚለይበት ዋነኛ ባህርይው፤ ኋላቀርነትን በመስበክ ብቻ የሚመለስ አለመሆኑ ነው። ስብከቱን በተግባር ያሳያል። አዳሪ ትምህርት ቤት ውስጥ ገብቶ ከ50 በላይ ተማሪዎችን መግደል፤ የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ማዕከልን አቃጥሎ ደርዘኖችን መጨፍጨፍ፣ ሴት ተማሪዎችን መውሰድ... የሳይንስ ትምህርትን ከማንቋሸሽ አልፎ፤ ሳይንስ የሚያስተምሩና የሚማሩ ሰዎችን ያሳድዳል።

ቦኮ ሐራም በሚፈነጭበት ሰሜናዊ የናይጄሪያ አካባቢ፣ “276 ሴት ተማሪዎች መጠለፋቸውን ብቻ ታወራላችሁ። በሦስት እጥፍ የሚበልጡ ተማሪዎችን ጠልፈናል። ሰሞኑን በአንድ ቦታ 300 ሰዎች ገድለናል። ለምን ይሄ አይወራም?” የቦኮ ሐራምና የአቡበከር ቁጣ፡ “የገደልነውና የጠለፍነውን ያህል አልተወራልንም” የሽብር ፍርሃት ስለነገሰ ብዙዎቹ ትምህርት ቤቶች ተዘግተዋል። የአመቱ ፈተና እንዳያመልጣቸው በአንድ ትምህርት ቤት ለመሰባሰብ የደፈሩት ሴት ተማሪዎችም፤ ከቦኮ ሐራም አላመለጡም። ትምህርት ቤቱን በመውረር ነው 276 ሴት ተማሪዎችን የጠለፋቸው። ከወላጆችና ከቤተሰቦች እሮሮ ጋር የባኮ ሐራም ዝና በመላው አለም የገነነው፤ ከዚሁ ጠለፋ ጋር ተያይዞ ነው። ተቃውሞና ውግዘት ከየአቅጣጫው ከሁሉም የአለም ማዕዘናት ጐረፈ። የባኮ ሐራም አለቃ ነውጠኛው አቡባከር ባለፈው ሰኞ በቁጣ እየደነፋ ለአለማቀፉ እሪታ ምላሽ ሰጥቷል።

ውግዘት ስላበዛ አይደለም አቡበከር የተናደደው። “ጥፋት አልሰራሁም፤ ጥፋቴ ተጋነነ” የሚል አይደለም የአቡበከር ምላሽ። በተቃራኒው፤ “የሰራሁትን ነገር አሳነሳችሁብኝ” በማለት ቁጣውን የገለፀው አቡባከር፤ ከተወራለት የሚበልጥ ጠለፋና ግድያ እንደፈፀመ ድርጊቶቹን በመዘርዘር ተናግሯል። አለም ሁሉ የሚያወራው ስለተጠለፉት ሴቶች ብቻ መሆኑ አናድዶታል። በአመት ውስጥ በሶስት እጥፍ የሚበልጡ ታዳጊዎችን እንደጠለፍን ለምን ይዘነጋል? አለም ሁሉ ይህንን የ ማ ያ ወ ራ ው ለ ም ን ድ ነ ው ? በማለት ብስጭቱን ገልጿል አቡበከር። የተናደደው በዚህ ብቻ አይደለም። ቦካ ሐራም ሴት ተማሪዎችን ከመጥለፉ በፊትም ሆነ በኋላ የፈፀምኳቸው ብዙ “ጀብዱዎች” ቸል ተብለውብኛል ባይ ነው - አቡበከር። ከወር በፊት በናይጄሪያ ዋና ከተማ በአቡጃ የአውቶብስ መነሃሪያ ላይ ባደረሰው የፍንዳታ ጥቃት 71 ሰዎች ተገድሏል።

ይሄስ ለምን ተረሳ? ለምን አይወራም? አቡበከር በዚህ ሁሉ ይንገበገባል። በቅርቡ ከሳምንት በፊትም ቦኮ ሐራም በአንዲት ከተማ መስጊድ ውስጥ የተጠለሉ 300 ሰዎችን ጨፍጭፏል። ይሄም መነጋገሪያ መሆን እንዳለበት አቡበከር አሳስቧል። እውነትም፤ ቦኮ ሐራም፤ በአማካይ በየእለቱ 10 ናይጀሪያዊያን እየገደለ በሁለት ዓመታት ውስጥ ከሰባትሺ በላይ “ግዳይ” ጥሏል። በኋላቀር ባህልኮ ክብር እና ማዕረግ የሚገኘው “ስንት ሰው ገደለ?” በሚል ነው። አቡበከርም “ገዳዬ፣ ገዳዬ” እየተባለ እንዲዘፈንለት ቢጠብቅ አይገርምም። አለም ሌላ ሌላውን ሁሉ ትቶ፣ ስለ ተጠለፉት ሴቶች ብቻ ማውራቱን የሚቀጥል ከሆነስ? አቡበከር፤ ለዚህም ምላሽ አለው። ብዙዎቹ ሴት ተማሪዎች... ገና የ9 አመት፣ ቢበዛ የ12 አመት ታዳጊዎች ናቸው።

“ፈጣሪ ምስክሬ ነው፤ ገበያ አውጥቼ እሸጣቸዋለሁ። የ12 አመት... 9 አመት ልጃገረዶቹን ሁሉ ባል እንዲያገቡ አደርጋለሁ” ሲል ዝቷል - በቪዲዮ ባሰራጨው መልእክት። እስካሁን የተወሰኑት ልጃገረዶች በ12 ዶላር እየተሸጡ ሚስት ለመሆን እንደተገደዱም ተዘግቧል። አቡበከር፤ ለናይጄሪያውያን ያስተላለፈው መልእክት የእልቂት አርአያነቱን እንዲከተሉ የሚጋብዝ ነው። “ሳታመነቱ ገጀራችሁን ጨብጣችሁ ተነሱ። በየቤቱ ሰብራችሁ እየገባችሁ ግደሉ። ያገኛችሁትን ሰው ሁሉ እዚያው በተኛበት ግደሉ” ብሏል - አቡበከር።

Published in ከአለም ዙሪያ

በከተማችን ካሉ የጥርስ ህክምና ክሊኒኮች በትክክለኛ ባለሙያ የታገዘ ህክምና የሚሰጡት ከግማሽ በታች ናቸው

ለጥርስ ህክምና እስከ 25 ሺህ ብር ድረስ የሚያስከፍሉ ክሊኒኮች አሉ

               በፒያሣው አትክልት ተራ አካባቢ መደዳውን ከተደረደሩት የጥርስ ህክምና ክሊኒኮች በአንደኛው ነበር ቀንና ሌሊት እየጠዘጠዘ እንቅልፍ የነሳትን ጥርሷን ከ2 ዓመት በፊት ያስነቀለችው። በክሊኒኩ ያገኘችው ህክምና ለጊዜው ከሥቃይዋ ገላግሏታል። ትዕግስት (ለዚህ ዘገባ ስሟ የተቀየረ) ወደ ክሊኒኩ ገብታ፣ የጥርስ ህክምናዋን ለማድረግ ስትወስን፣ ምንም ዓይነት የጤና ችግር ያጋጥመኛል ብላ አላሰበችም። በዚያ ላይ በክሊኒኩ መግቢያ ደጃፍ ላይ በጉልህ ተፅፎ የተሰቀለው ማስታወቂያ፣ ህክምናው በሥራው ብቁ በሆኑ ባለሙያዎችና ንፅህናቸው በአግባቡ በተጠበቀ መሳሪያዎች እንደሚሰጥ ይገልፃል። ህክምናውን ያደረገላት “ሃኪም”፣ ህመምተኛ ጥርሷን ከነቀለ በኋላ፣ የህመም ማስታገሻ መድኃኒቶችንና አሞክሳሲሊን የተባለውን ክኒን ሰጥቶ አሰናበታት። ትዕግስት ሌትና ቀን ያሰቃያት ከነበረው የጥርስ ህመሟ መገላገሏ ደስታን የፈጠረላት በወራት ለሚቆጠር ዕድሜ ብቻ ነበር። ከጥቂት ወራት በኋላ የተነቀለው ጥርሷ አካባቢ ሃይለኛ የህመም ስሜት ይሰማት ጀመር። ቀስ በቀስ ህመሙ እየጨመረ ሥቃዩ እየበረታባት ሄደ።

እዛው ጥርሷን የተነቀለችበት የጥርስ ክሊኒክ ሄደች። በክሊኒኩ ያገኘቻቸው “ሃኪሞች” ምንም አይነት ችግር እንደሌለባት ገልጸው፤ የህመም ማስታገሻ ክኒን ብቻ እንድትወስድ አዘው አሰናበቷት። ሥቃይዋ ግን ከምትችለው በላይ ሆነባት። በመንጋጋዋ አካባቢ ብቻ ተወስኖ የነበረው የህመም ስሜቷ፤ ጭንቅላቷን ክፉኛ ወደሚበጠብጥ ከባድ የራስ ምታት ህመም ተለወጠ። ዓይኗን መግለጥ እስከሚያቅታት ድረስ በራስ ምታት ህመሙ ተሰቃየች። አፏን እንደልቧ መክፈት መዝጋቱ የማይታሰብ ሆነባት። በስቃይ ለመናገርም ሆነ ምግብ ለመዋጥ አፏን በከፈተች ቁጥር የሚሰነፍጥና እጅግ የሚያስጠላ መጥፎ ጠረን ከአፏ መውጣት ጀመረ። ይህም ህይወቷን የበለጠ መራራና ከባድ አደረገባት። ቀናት እየጨመሩ በሄዱ ቁጥር፣ ሥቃይዋ ከአቅሟ በላይ እየሆነ ሔደ። ቢቸግራት እዛው ፒያሳ ወደሚገኝ ሌላ የጥርስ ክሊኒክ ለህመሟ ማስታገሻ ፍለጋ ሄደች። “የክሊኒኩ ሃኪም የረባ ምርመራ እንኳን ሳያደርግልኝ ሁለቱ መንጋጋዎቼ መነቀል እንዳለባቸው ነገረኝ” ትላለች። በቂ ገንዘብ አልያዝኩም በሚል ሰበብ ከክሊኒኩ ለ ቃ እንደወጣችም ት ናግራለች።

የ ህመም ስሜት ያላት ቀደም ሲል በተነቀለችው ጥርስ ቦታ የጥርስ ህክምና ክሊኒኮች አሳሳቢ ደረጃ ላይ ናቸው ተባለ በከተማችን ካሉ የጥርስ ህክምና ክሊኒኮች በትክክለኛ ባለሙያ የታገዘ ህክምና የሚሰጡት ከግማሽ በታች ናቸው ለጥርስ ህክምና እስከ 25 ሺህ ብር ድረስ የሚያስከፍሉ ክሊኒኮች አሉ ላይ መሆኑን እያወቀች፣ ሌላ ጥርስ መነቀል አለበት የሚለውን ውሳኔ አላመነችበትም። የትዕግስት ስቃይ እረፍት አልባ መሆኑ ካሳሰባቸው ጓደኞቿ አንዷ፣ ትዕግስትን ይዛ ወደ ራስ ደስታ ሆስፒታል ሄደች። በሆስፒታሉ በተደረገላት ምርመራ፣ የጥርሷ ዋንኛው አቃፊ ውስጠኛው ክፍል (Root Canal) ቀደም ሲል በተፈፀመና አግባብ ባልሆነ የጥርስ መንቀል ሂደት ሳቢያ በከፍተኛ ሁኔታ መጎዳቱንና መመረዙን፣ ህክምናውንም በአገር ውስጥ ለማከናወን አስቸጋሪ እንደሆነ ተነገሯት። አስቸኳይ ህክምና ካላደረገችም ችግሩ እየጨመረ ሄዶ፣ ወደ ሌሎች የሰውነትዋ ክፍሎች በተለይም ወደ ጭንቅላት ነርቮቿ የሚሰራጭ መሆኑን ዶክተሮች አረዷት። ለህክምናው ያስፈልጋል የተባለችውን ገንዘብ ስትሰማ ሰማይ ምድሩ ዞረባት። “ውጪ አገር ሄደሽ ከ290 ሺህ ብር በላይ የሚፈጅ ህክምና ማድረግ አለብሽ” ተባለች። ይህንን ወጪ ሸፍና ህክምናውን ለማግኘት አቅም የላትም። ለዓመታት በስምንት መቶ ብር ወርሃዊ ደመወዝ የመርካቶው ይርጋ ሃይሌ ህንፃ ውስጥ በልብስ መሸጫ መደብር ውስጥ ነው የሰራችው።

እሱንም ቢሆን በዚሁ የጥርስ ህመሟ ሳቢያ ከለቀቀች ወራት አልፈዋል እናም ለህክምናዋ የሚሆን ገንዘብ የምታገኝበት አማራጭ በማጣትዋ ቀደም ሲል በሥራ አጋጣሚ የተዋወቀቻቸውን ሰዎችና ሌሎች በጎ አድራጊ ግለሰቦችን እርዳታ ለመጠየቅ ተገዳለች። በአሁኑ ወቅት በሆስፒታሉ የሚደረግላትን የህክምና እርዳታ በመከታተል፣ ከህመሟ ጊዜያዊ እፎይታን ለማግኘት እንደቻለችም ትናግራለች በራስ ደስታ ሆስፒታል በተደረገላት ህክምና የድዷ ቁስለት እየዳነ መሄዱን፣ ከሰዎች ጋር እንዳትነጋገር አድርጓት የነበረው የአፍ ጠረኗ፣ በእጅጉ እየተሻሻለ እንደሆነ ገልፃለች። ትዕግስት በጥርስ ህክምና ሰበብ የደረሰባትን ይህንን የጤና ችግር ልትነግረኝ አብረን የቆየንባቸው ጥቂት ደቂቃዎችን ለእኔ እጅግ የፈተና ነበሩ። “አሁን እጅግ ተሻሽሏል” የተባለው የአፍ ጠረኗ ቀደም ሲል ምን አይነት ቢሆን ነው አስብሎኛል። ትዕግስት በጥርስ ህክምና ሰበብ በየመንደሩና በየጉራንጉሩ ውስጥ እየተከፈቱ በታካሚው ህይወትና ጤና ላይ “ቁማር የሚጫወቱ” የምትላቸውን የጥርስ ክሊኒኮች የሚቆጣጠርና አሰራራቸውን የሚከታተል አካል ባለመኖሩ ምክንያት እንደእሷ ሁሉ እጅግ በርካቶች አደገኛ ለሆኑ የጤና ችግሮች መጋለጣቸውን ትናገራለች።

ክሊኒኮቹ የህክምና መሳሪያዎቻቸውን በንፅህና የማይጠብቁ በመሆናቸው፣ ኤችአይቪን ጨምሮ ሌሎች ተላላፊ በሽታዎችን ከአንዱ ወደ አንዱ በቀላሉ የሚያስተላልፍ የበሽታ መፈልፈያ ቦታዎች ሆነዋል ስትል በምሬት ገልፀለች። ለካርድ ተብላ በከፈለችው 50 ብር እና ለጥርስ መንቀያ ባስከፈልዋት 120 ብር ጤናዋን ሳይሆን የእድሜ ልክ በሽታዋን ሸምታ መውጣቷ እጅግ እንደሚያሳዝናት የምትናገረው ትዕግስት፤ መንግስትና ጉዳዩ የሚመለከታቸው ወገኖች የጥርስ ህክምና ክሊኒክ እየተባሉ በየጉራንጉሩ የሚከፈቱትንና በከተማዋ ውስጥ እንደ አሸን የፈሉትን ክሊኒኮች ቁጥጥር ሊያደርጉባቸውና አሰራራቸውን ሊከታተሏቸው ይገባል ትላለች። ለወገኖቻቸው ህይወት ቅንጣት ደንታ በሌላቸው አንዳንድ ራስ ወዳድ ሰዎች፣ የብዙ ሰዎች ህይወት ሊበላሽ አይገባውም ስትልም በቁጭት ትቆዝማለች። “ህብረተሰቡም ለጥርስ ህክምና በሚሄድበት ጊዜ ህክምናው በምን ዓይነት ሁኔታና በማን እንደሚሰጠው ማወቅ ይኖርበታል። ከእኔ ሊማርም ይገባል ባይ ናት።

የጥርስ ህክምና ሊሰጥ የሚገባው በሙያው በአግባቡ በሰለጠኑና ስፔሻላይዝድ ባደረጉ የህክምና ባለሙያዎች ሲሆን ሃኪሞቹ ማንነታቸውንና ደረጃቸውን የሚገልፅ ባጅ፣ በግልጽ በሚታይ ሁኔታ በደረታቸው ላይ ማንጠልጠል እንደሚኖርባቸው የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ያወጣው የህክምና መመሪያ (Guideline) ይጠቁማል። የህክምና መገልገያ መሳሪያዎቹ ጥራትና ንፅህናቸው በአግባቡ የተጠበቀ፣ የህክምና መስጫ ስፍራው የታካሚውን ደህንነት በአስተማማኝ ሁኔታ የሚጠብቅና ለድንገተኛ የጤና ችግሮች አስተማማኝ ዝግጅት ያለው መሆን እንደሚገባውም ይገልፃል። ይሁን እንጂ ይህንን ዘገባ ለማዘጋጀት ተዘዋውሬ ካየኋቸው፣ በጎጃም በረንዳና በአትክልት ተራ አካባቢ ከሚገኙ የጥርስ ህክምና ክሊኒኮች በአንደኛውም ከላይ የተገለፁትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ክሊኒኮችን አላየሁም። አብዛኛዎቹ ክሊኒኮች ለህክምና ሥራ አመቺ ባልሆነ ሥፍራ የተሰሩና የንፅህናቸው ሁኔታ እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላ ይ ነ ው። ከ ዚህ በ ተጨማሪም በ ክሊኒኮቹ ደጃፍ ላይ እንደተሰቀለው ማስታወቂያ ሁሉ ህክምናው በስቴራላይዘር ከበሽታ ንፁህ ሆነው በፀዱ መሳሪያዎች የሚሰጥ መሆኑን የሚያረጋግጡ ነገሮችን ለማየት አልቻልኩም።

ለቅኝት በተዘዋወርኩባቸውና በፒያሣው አትክልት ተራ አካባቢ በብዛት ከሚገኙት የጥርስ ህክምና ክሊኒኮች በአንዱ ውስጥ ያገኘሁት አንድ “የህክምና ባለሙያ” በክሊኒካቸው የስቴራላይዘር መሳሪያ አለመኖሩን ገልፆ “ህክምናውን የምንሰጠው ለአንድ ሰው አንድ በሆነ ወይንም ከአንድ ጊዜ በላይ አገልግሎት ላይ በማይውሉ መሳሪያዎች ነው ብሎኛል። ይህ አባባሉ ግን እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ደሃ አገራት ቀርቶ በለፀጉ በሚባሉት አገራት ውስጥ እንኳን ሊሆን እንደማይችል ግልፅ ነው። እጅግ ውድ ዋጋ የሚያወጡ መሳሪያዎችን ከአንድ ጊዜ በላይ አንጠቀምባቸውም ማለቱ የማይመስል ነገር ነው። ላለፉት 10 ዓመታት በጥርስ ህክምና ሙያ ውስጥ የቆዩት ዶክተር የኋላሸት ስመኘው ይህንኑ ጉዳይ አስመልክተው ሲናገሩ፤ በአሁኑ ወቅት በከተማዋ ከሚገኙት የጥርስ ህክምና ክሊኒኮች አብዛኛዎቹ እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሳቸውን ጠቁመው የመሣሪያዎቹ ንፅህና አጠባበቅና የባለሙያዎቹ ብቃት ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ናቸው ብለዋል። የጥርስ ህክምና መሳሪያዎች ለአንድ ሰው አገልግሎት ከሰጡ በኋላ ለሌላ ሰው ጥቅም ላይ ከመዋላቸው በፊት እስከ 30 ደቂቃ ለሚሆን ጊዜ በበረኪና በሚገባ መዘፍዘፍና በሚገባ መታጠብ ይኖርባቸዋል፤ በአግባቡ ተዘፍዝፈውና ታጥበው የፀዱት ዕቃዎች አውቶክሌቭ ወደተባለውና ዕቃዎቹን በአግባቡ ለመቀቀል ወደሚያስችለው መሳሪያ መግባት ይኖርባቸዋል።

ከዚህ በኋላ ነው ዕቃዎቹ ከበሽታ ነፃ ሆኑ የሚባለው። በዚህ ሁኔታ የፀዱ መሳሪያዎች፣ የታካሚውን ጤንነት በአስተማማኝ ሁኔታ የሚጠብቁ ናቸው ብለዋል። ግን በተጠቀሱት ስፍራዎች ይህንን የዶክተር የኋላሸት ስመኘውን አባባል የሚያረጋግጡ አንዳችም ክሊኒኮች ለማየት አልቻልንም። ለቅኝት ከተዘዋወርንባቸው የጥርስ ህክምና ክሊኒኮች ውስጥ በተሟላ መሳሪያና በሙያው በሚገባ በሰለጠኑ ብቁ ባለሙያዎች ተደራጀተው ለታካሚው አገልግሎት በመስጠት ላይ ያሉ ጥቂት ክሊኒኮችንም ታዝበናል። ፒያሳ እሪ በከንቱ አካባቢ፣ ሃያ ሁለትና መገናኛ አካባቢ ያየናቸው የጥርስ ህክምና ክሊኒኮች መካከል የሚጠቀሱ ናቸው። በእነዚህ ክሊኒኮች ለደንበኞቻቸው አግባብ ያለው ህክምና ሲሰጡ ከተመለከትናቸው ጥቂት ክሊኒኮች የሚሰጠው የጥርስ ህክምና በሙያው በሚገባ በሰለጠኑ ብቁ ባለሙያዎች እና ንፅህናቸው በአግባቡ በተጠበቀላቸው መሳሪያዎች መሆኑን በስፍራው ተገኝተን ለመታዘብ ችለናል። ክሊኒኮቹ ለአገልግታቸው የሚስከፍሉት ዋጋ ከሌሎች ክሊኒኮች ጋር ሲነፃፀር ዳጎስ ያለ ነው ሊባል ይችላል። በእነዚህ ክሊኒኮች ውስጥ አንድ ጥርስ ከመነቀሉ በፊት ሊታከም መቻል አለመቻሉ በራጅ ምርመራና ሌሎች መሰል የምርመራ አይነቶች እንዲረጋገጥ ይደረጋል። ታካሚው ለህክምናው የሚያወጣው ወጪም እነዚህን ጉዳዮች ከግምት ውስጥ ያስገባ ነው።

ታካሚው ጥርሱ ተጨማሪ ምርመራ እንዲደረግለት የማይፈልግና መነቀል ብቻ እንደሚፈልግ ከተናገረ ባለሙያዎቹ አገልግሎቱን እጅግ በተመቻቸና ብዙም የህመም ስሜት በሌለበት ሁኔታ ያከናውኑታል። ለዚህ ህክምናም እስከ 400 ብር የሚደርስ ክፍያ ደንበኛው ይጠየቃል። ከዚህ በተረፈ የተወላገዱ፣ ያለአግባብ የበቀሉ፣ ነርቮቻቸው የተበላሹና ህክምና የሚያስፈልጋቸው ጥርሶች ሁሉ በእነዚህ ሥፍራዎች ተገቢው ህክምና ይደረግላቸዋል። ክሊኒኮቹ ለአገልግሎታቸው እስከ ሰላሳ ሺህ ብር የሚደርስ ገንዘብ ያስከፍላሉ። በዓለማችን የተለያዩ አገራት ለጥርስ ህክምና የሚወጣው ወጪ (የሚከፈለው ክፍያ) እጅግ ከፍተኛ ነው። በካናዳ አንድን ጥርስ ለመነቀል አሊያም ለማስሞላት እስከ አንድ ሺህ ሁለት መቶ የካናዳ ዶላር የሚያስከፍል ሲሆን ይህም በእኛ ገንዘብ ሲመነዘር ከሃያ ሁለት ሺህ ብር በላይ የሚጠይቅ ነው። በስዊድን ተመሳሳይ ህክምና ለማግኘት ከአራት እስከ አምስት ሺህ ክሩነር (በእኛ ከ12 እስከ 15 ሺ ብር) የሚደርስ ገንዘብ ይጠይቃል።በዚህ ምክንያትም አብዛኛዎቹ ዲያስፖራዎች ቤተሰቦቻቸውን ለመጎብኘት ወደ ኢትዮጵያ ብቅ ባሉ ቁጥር፣ የጥርስ ህክምና ክሊኒኮችን ሳይጎበኙ አይሄዱም።

የፒያሣው ጎጀብ ክሊኒክ በበርካታ ዲያስፖራዎችና የውጭ አገር ዜጎች በመጎብኘት ቀዳሚውን ሥፍራ ይይዛል። ዲያስፖራዎቹና የውጭ አገር ዜጎቹ የተበላሸና የሚታከም ጥርስ ባይኖራቸው እንኳን ስምንት መቶ ብር እየተከፈለ የሚሰጠውን ሙሉ የጥርስ እጥበት አገልግሎት ፍለጋ የክሊኒኩን በር ያንኳኳሉ። በአገራችን የሚገኙትንና በጣት ሊቆጠሩ የሚችሉትን የጥርስ ህክምና ስፔሻሊስት ሐኪሞች በእነዚህ ሥፍራዎች እንደልብ ማግኘት ይቻላል። አቅምዎ ከፈቀደና መክፈል ከቻሉ በመረጡትና ቀልብዎ በወደደው ብቁ ባለሙያ መታከም ይችላሉ።

Published in ዋናው ጤና

ሴንትራል አፍሪካ ለሁለት ከመሰንጠቅ የሚያድናት አልተገኘም

             በአገር ስ ም እ ና ዘ ረኝነት ወ ይም ደ ግሞ በሃይማኖት ሰበብና በአክራሪነት ሳቢያ የሚቃወሱ አገራት እየተበራከቱ፤ በተቃራኒው የመፍትሔ ሃሳቦች እየተመናመኑ መምጣታቸውን ከደቡብ ሱዳንና ከሴንትራል አፍሪካ ትርምስ ማየት ይቻላል። የዘመናችን ነገር! የግጭቱ መነሻ የኢኮኖሚ ችግርና ሙስና፣ የስልጣን ሽኩቻና የምርጫ ውዝግብ ሊሆን ቢችልም፤ ዞሮ ዞሮ ወደ አስፀያፊ ዘረኝነት ወይም ወደ አስቀያሚ አክራሪነት መዝቀጡ የተለመደ ሆኗል። ዩክሬንን አይቶ ደቡብ ሱዳንን፤ ሶሪያን አይቶ ሴንትራል አፍሪካን ማየት ነው። ለሁለቱ አገራት ቀውስ እልባት ለማፈላለግ ደፋ ቀና የሚሉ አልታጡም። ከጐረቤት አገራትና ከአፍሪካ ህብረት ጀምሮ እስከ አሜሪካና አውሮፓ ህብረት፣ እስከ ቻይናና የተባበሩት መንግስታት... ሰላም ለማምጣት ጉድጉድ ያላለ የለም። ነገር ግን እስካሁን ሁነኛ መፍትሔ አልተገኘም።

እናም በ10ሺ የሚቆጠሩ ሰዎች ተገድለዋል፤ ሚሊዮኖች ተሰደዋል። በእርግጥ፤ ሰላም ለመፍጠር የሚካሄዱ ሙከራዎች ዋጋ ቢስ ናቸው ማለት አይደለም። ቢያንስ ቢያንስ፤ በአፍሪካ እንደ ድሮው ያለ ከልካይ “አገር በቀል እውቀት” በሚል ሰበብ ስልጣኔን እያንቋሸሸ፤ አልያም የአሜሪካና የአውሮፓ የሳይንስ ትምህርትን እያብጠለጠለ፣ ኋላቀርነትን የሚሰብክ ፕሮፌሰርና ዶክተር ሞልቷል። ቦኮ ሐራም ከዚህ የተለየ አላማ የለውም። ስሙ ራሱ፤ “የምዕራባዊያን ትምህርት ሐራም ነው” እንደማለት ነው። ቦኮ ሐራም፤ ከወገኛ ምሁራን የሚለይበት ዋነኛ ባህርይው፤ ኋላቀርነትን በመስበክ ብቻ የሚመለስ አለመሆኑ ነው። ስብከቱን በተግባር ያሳያል። አዳሪ ትምህርት ቤት ውስጥ ገብቶ ከ50 በላይ ተማሪዎችን መግደል፤ የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ማዕከልን አቃጥሎ ደርዘኖችን መጨፍጨፍ፣ ሴት ተማሪዎችን መውሰድ... የሳይንስ ትምህርትን ከማንቋሸሽ አልፎ፤ ሳይንስ የሚያስተምሩና የሚማሩ ሰዎችን ያሳድዳል።

ቦኮ ሐራም በሚፈነጭበት ሰሜናዊ የናይጄሪያ አካባቢ፣ “276 ሴት ተማሪዎች መጠለፋቸውን ብቻ ታወራላችሁ። በሦስት እጥፍ የሚበልጡ ተማሪዎችን ጠልፈናል። ሰሞኑን በአንድ ቦታ 300 ሰዎች ገድለናል። ለምን ይሄ አይወራም?” የቦኮ ሐራምና የአቡበከር ቁጣ፡ “የገደልነውና የጠለፍነውን ያህል አልተወራልንም” የሽብር ፍርሃት ስለነገሰ ብዙዎቹ ትምህርት ቤቶች ተዘግተዋል። የአመቱ ፈተና እንዳያመልጣቸው በአንድ ትምህርት ቤት ለመሰባሰብ የደፈሩት ሴት ተማሪዎችም፤ ከቦኮ ሐራም አላመለጡም። ትምህርት ቤቱን በመውረር ነው 276 ሴት ተማሪዎችን የጠለፋቸው። ከወላጆችና ከቤተሰቦች እሮሮ ጋር የባኮ ሐራም ዝና በመላው አለም የገነነው፤ ከዚሁ ጠለፋ ጋር ተያይዞ ነው። ተቃውሞና ውግዘት ከየአቅጣጫው ከሁሉም የአለም ማዕዘናት ጐረፈ። የባኮ ሐራም አለቃ ነውጠኛው አቡባከር ባለፈው ሰኞ በቁጣ እየደነፋ ለአለማቀፉ እሪታ ምላሽ ሰጥቷል።

ውግዘት ስላበዛ አይደለም አቡበከር የተናደደው። “ጥፋት አልሰራሁም፤ ጥፋቴ ተጋነነ” የሚል አይደለም የአቡበከር ምላሽ። በተቃራኒው፤ “የሰራሁትን ነገር አሳነሳችሁብኝ” በማለት ቁጣውን የገለፀው አቡባከር፤ ከተወራለት የሚበልጥ ጠለፋና ግድያ እንደፈፀመ ድርጊቶቹን በመዘርዘር ተናግሯል። አለም ሁሉ የሚያወራው ስለተጠለፉት ሴቶች ብቻ መሆኑ አናድዶታል። በአመት ውስጥ በሶስት እጥፍ የሚበልጡ ታዳጊዎችን እንደጠለፍን ለምን ይዘነጋል? አለም ሁሉ ይህንን የ ማ ያ ወ ራ ው ለ ም ን ድ ነ ው ? በማለት ብስጭቱን ገልጿል አቡበከር። የተናደደው በዚህ ብቻ አይደለም። ቦካ ሐራም ሴት ተማሪዎችን ከመጥለፉ በፊትም ሆነ በኋላ የፈፀምኳቸው ብዙ “ጀብዱዎች” ቸል ተብለውብኛል ባይ ነው - አቡበከር። ከወር በፊት በናይጄሪያ ዋና ከተማ በአቡጃ የአውቶብስ መነሃሪያ ላይ ባደረሰው የፍንዳታ ጥቃት 71 ሰዎች ተገድሏል። ይሄስ ለምን ተረሳ? ለምን አይወራም? አቡበከር በዚህ ሁሉ ይንገበገባል። በቅርቡ ከሳምንት በፊትም ቦኮ ሐራም በአንዲት ከተማ መስጊድ ውስጥ የተጠለሉ 300 ሰዎችን ጨፍጭፏል። ይሄም መነጋገሪያ መሆን እንዳለበት አቡበከር አሳስቧል።

እውነትም፤ ቦኮ ሐራም፤ በአማካይ በየእለቱ 10 ናይጀሪያዊያን እየገደለ በሁለት ዓመታት ውስጥ ከሰባት ለደቡብ ሱዳን 5 ፕሬዚዳንቶች ያስፈልጓታል ተባለ ሴንትራል አፍሪካ ለሁለት ከመሰንጠቅ የሚያድናት አልተገኘም እንደልብ እየተዋጉና እየተጨፈጨፉ አመታትን የመቁጠር ልምድ ቀንሷል። በአንድ በኩል የግጭቱ መሪዎች አለማቀፉ የወንጀል ፍ/ቤት ጥርስ ውስጥ እንዳይገቡ ትንሽ ትንሽ ይፈራሉ። በሌላ በኩል፤ ጥላ ከለላ የሚሆንላቸውና “አይዞህ ጨፍጭፍ” እያለ የሚያበረታታ ሃያል አገር በቀላሉ አያገኙም። “ተደራደሩ” እያለ የሚገፋፋና ጫና የሚያሳድር ሲበዛባቸው፤ የሰላም ስምምነት መፈራረማቸው አይቀርም። ግን ምን ዋጋ አለው? ሳምንት ሳይቆይ ግጭቱ ያገረሻል። በሃይማኖትና በዘር የተቧደኑ ነውጠኞችየገነኑበት አስቀያሚ ግጭት ለገላጋይ አስቸጋሪ ሆኗል። አዲስ አበባ መጥተው የሰላም ስምምነት የተፈራረሙ ተቀናቃኞች፤ በማግስቱ ወደ ደቡብ ሱዳን ሲመለሱ ነው የግጭት ዘመቻ የሚጀምሩት። በመሃል፤ ሕይወት ይረግፋል፤ ኑሮ በስደት ይመሳቀላል። አንዲት የደቡብ ሱዳን ከተማ በአንድ ወር ውስጥ ብቻ፣ ተቀናቃኝ ጦሮች በየተራ አንዱ በሌላው ላይ እየዘመቱ፣ አምስት ጊዜ ተፈራርቀውባታል። ታዲያ ዘመቻው በተቀናቃኝ ጦር ላይ ብቻ ያነጣጠረ አይደለም። በውጊያው አሸንፎ ከተማዋን የሚቆጣጠር ጦር፣ የከተማዋ ነዋሪዎች ላይም ይዘምታል - በዘር እየለየ። ደግሞም በድብቅ የሚካሄድ ዘመቻ አይደለም።

የጦር መሪዎች የጭፍጨፋ ዘመቻ የሚያውጁት በሬድዮ ነው። የዘመናችን ግጭቶች መነሻቸውም ምንም ይሁን ምን፤ በአጭር ጊዜ ውስጥ መልካቸው ይቀየርና፣ የጭፍጨፋ ዘመቻ የሚያውጁ ጨካኝ አረመኔዎችገንነው ይወጣሉ። የአንዱን ጐሳ ተወላጆች በጠላትነት እየፈረጁ “ከተማዋን ለቀው ካልወጡ ከየቤታቸው እየለቀማችሁ ግደሏቸው። ሴቶቹን በሙሉ ድፈሯቸው” እያሉ ይቀሰቅሳሉ። እና የሰላም ስምምነት በተፈራረሙ ማግስት የእልቂት ዘመቻ የሚያውጁ ከሆነ ምን ይሻላል? የአገሪቱ የቀድሞ ባለስልጣናት፤ ታዋቂ የህግ ባለሙያዎችና የፖለቲካ ምሁራን ተሰባስበው ያመጡትን የመፍትሔ ሃሳብ ተመልከቱ። “አሉ የተባሉ” የደቡብ ሱዳን ታላላቅ ሰዎች የመፍትሔ ሃሳባቸውን ሲያቀርቡ፤ በመጀመሪያ አገሪቱ አንድ ጠቅላይ ሚኒስትር፣ ሁለት ምክትሎች እንዲሁም 18 ሚኒስትሮች ያስፈልጓታል በማለት ይጀምራሉ። ለአገሪቱ ቀውስ መነሻ የሆነው የፕሬዚዳንት ቦታስ? “አገሪቱ አምስት ፕሬዚዳንቶች ይኖሯታል። በግማሽ አመት እየተፈራረቁ ስልጣን ይይዛሉ” ብለዋል የደቡብ ሱዳን ታላላቅ ሰዎች። የጨነቀው ብዙ ያወራል! የፕሬዚዳንቶችን ቁጥር በማብዛት፤ የስልጣን ሽኩቻንና ኋላቀር የዘረኝነት ፖለቲካን ማስወገድ ይቻላል እንዴ? የሴንትራል አፍሪካ ቀውስም እንዲሁ መላ የሌለው ሆኗል።

በስልጣን ሹክቻ የተጀመረው ቀውስ፤ ያፈጠጠ ያገጠጠ የሃይማኖት አክራሪነት ነግሶበት ወደ እልቂት ለማምራት ጊዜ አልፈጀበትም። “ሰላም አስከባሪ ሃይል” ቢሰማራም፤ የአፍሪካና የአውሮፓ መንግስታት አገር ለማረጋጋት ተፍተፍ ቢሉም፤ መፍትሔ አላመጡም። እንዲያውም “መፍትሔ ሊገኝ ይችላል” የሚል ተስፋም ርቋቸዋል። በሃይማኖት የተቧደኑ አክራሪዎች የገነኑበት ግጭት ምን መላ አለው? ሙስሊም፣ ክርስቲያን እያሉ የጭፍጨፋ ዘመቻ ያካሂዳሉ። እና ምን ይሻላል? ሙስሊሞችን ወደ ሰሜን፣ ክርስቲያኖችን ደግሞ ወደ ደቡብ አቅጣጫ ማሸሽ ብቻ! ከዚህ ውጭ ለጊዜው መፍትሔ አልተገኘም። ለዘለቄታውም አገሪቱ ለሁለት ከመሰንጠቅ የሚያድናት አልተገኘም - እስካሁን።

Published in ከአለም ዙሪያ
Page 12 of 21