የቻይና ኮሙኒስት ፓርቲ መስራች ማኦ ዜዱንግ በስልጣን ዘመናቸው መጀመሪያ የማንኛውም አይነት የቤተሰብ ምጣኔ ተቃዋሚ ነበሩ፡፡ የወሊድ ቁጥጥር አገሮችን በማዳከም ለጥቃት እንዲጋለ ለማድረግ በካፒታሊስቶች የተ- ነሰሰ ሴራ ነው የሚል አቋም ነበራቸው ቿ ዜዱንግ፡ ፡ ቻይናውያን በተቻለ መ-ን በብዛት ልጅ እንዲወልዱ ይበረታቱ በነበሩት በማኦ የስልጣን ዘመን የቻይና ህዝብ ቁጥር በእጥፍ ጨምሮ ነበር፡፡ አንድ ህፃን ሲወለድ አፍ ብቻ ሳይሆን ሁለት የሚሰሩ እጆችም አብረውት ይወለዳሉ፣ በምድር ላይ ካሉ ነገሮች በሙሉ የሰው ልጅ ክቡር ነው፡ የሚሉት ማኦማንኛውም አይነት የወሊድ መከላከያ ወደ አገራቸው እንዳይገባም አግደው እንደነበር ይታወቃል፡፡ የህዝብ ብዛትን ለጦርነት መመከቻ አድርገው ይ-ቀሙበት የነበሩት ማኦ ሰሜን ኮሪያ ላይ ያዘመቱት የህዝብ ማእበል በታሪክ ሁሌም ተ-ቃሽ ነው፡፡ በስልጣን ዘመናቸው ማብቂያ ላይ የህዝብ ብዛት ምጣኔ ላይ የፖሊሲ ለውጥ ያመት ማኦ፣ የህዝብ ብዛትን ለመቀነስ ሴቶች ዘግይተው እንዲወልዱ ማበረታታት ጀመሩ፡፡ ቻይና ከማኦ ሞት በኋላ የህዝብ ብዛቷን ለመቀነስ የተለያዩ ሙከራዎችን ስታደርግ የቆየች ሲሆን በመጨረሻም በአንድ ልጅ ፖሊሲ በመናት፣ የህዝብ ቁጥሯን ውታማ በሆነ መልኩ ለመቀነስ ችላለች፡፡ የአንድ ልጅ ፖሊሲ የመጀመሪያዎቹ ልጆች የሰላሳ አራት ዓመት ጎልማሶች የሆኑባት ቻይና የአረጋውያን ቁጥር ከወጣቶቿ ጋር ከፍተኛ ልዩነት በማምጣቱ በያዝነው አመት በፖሊሲው ላይ ለውጥ እንደምታደርግ እየተነገረ ነው፡፡ ከሰሞኑ ቻይና ዴይሊ እንደዘገበው የቻይና አረጋውያን ቁጥር እየጨመረ የወጣቱ ቁጥር ደግሞ በአንድ ልጅ ፖሊሲ በመገደቡ ረታ በሚወጣው እና አዲስ በሚተካው የሰው ሀይል መካከል ከፍተኛ ክፍተት እየተፈ-ረ መጥቷል፡፡ የአንድ ልጅ ፖሊሲውን ተከትሎ ወላጆች ንብረታቸውን ለወንድ ልጆች ማውረስ ስለሚፈልጉ ሴት ልጅ ስትረገዝ በሚፈፀም ውርጃ ምክንያት የፆታ አለመመጣ-ኑም ከፍተኛ ደረጃ ላይ በመድረሱ በያዝነው አመት የአንድ ልጅ ፖሊሲ ላይ ለውጥ ሊደረግ ይችላል ብሏል፡፡ የቻይና የህዝብ የተፈጥሮ እና የአካባቢ ጥበቃ ኮሚቴ ባቀረበው ሀሳብ፣ በተለይ በከተማ የሚኖሩ ወላጆች፣ ሁለተኛ ልጅ እንዲወልዱ ሊፈቀድላቸው ይገባል ብሏል፡፡ በአሁኑ ወቅት ሁለት ልጅ እንዲወልዱ የሚፈቀድላቸው በአንድ ልጅ ፖሊሲ የተወለዱ ወላጆች ብቻ ናቸው፡፡

የፔኪንግ ዩኒቨርሲቲ የሶስዮሎጂ ፕሮፌሰር እና የቤተሰብ ምጣኔ ኮሚሽነር ሉ ጂዮሀ እንደሚሉት፣ በቻይና እየጨመረ የመጣው የአረጋውያን ቁጥር በአዲስ የሰራተኛ ኃይል ሀይል ካልተተካ የኢኮኖሚ እድገቱ አደጋ ላይ ይወድቃል፡፡ በሁለቱ ፆታዎች መካከል ያለው ከፍተኛ ክፍተትና ከጊዜ ወደ ጊዜ እጅግ እየጨመረ የመጣው የሌላ አገር ዜጋ፣ ቻይና የአንድ ልጅ ፖሊሲዋ ላይ ለውጥ እንድታደርግ አስገድዷታል፡፡ ተንታኞች እንደሚሉት፣ የወጣቶች ቁጥር መቀነስ ኢኮኖሚውን ክፉኛ ይጎዳዋል፡፡ ቻይና ይህን ፖሊሲ ካልለወ-ች ጫናውን በቅርቡ ታየዋለች፡፡ በቻይና የሚገኙ የትላልቅ ፋብሪካ ባለቤቶች ከፍተኛ የሰው ሀይል እጥረት እየገ-ማቸው እንደሆነ ሪፖርት ማድረግ ከጀመሩ ሰነባብተዋል፡፡ የፖሊሲ ለውጥ ስለመኖሩ ቁርጥ ያለ አስተያየት ያልሰት የአገሪቱ ፕሬዚዳንትፖሊሲው እንደሚላላ -ቁመዋል፡፡ የቻይና የልማት እና የምርምር ፋውንዴሽን ደግሞ ከ2015 ጀምሮ አገሪቱ ወደ ሁለት ልጅ ፖሊሲ እንድትገባ ሀሳብ አቅርቧል፡፡ በመላው ቻይና የአንድ ልጅ ፖሊሲን የሚያበረታቱ ማስታወቂያዎች አሁንም ጎላ ብለው እንደተሰቀሉ  ናቸው -ቻይና የቤተሰብ ምጣኔ ያስፈልጋታል፣ ዘግይቶ መውለድ አስፈላጊ ነው (ሽበታም ሴት አዲስ የተወለደ ህፃን ታቅፋ ከሚያሳይ ምስል ጋር)፣ የቤተሰብ ቁጥርን በመመ-ን ለቀጣይ ትውልድ ያስተላልፉ፡ ወዘተ የሚሉ፡፡ በተደጋጋሚ የህዝብ ቁጣ በመቀስቀሳቸው ምክንያት እንዲወርዱ የተደረጉ ማስታወቂያዎችም አሉ፡፡ጥቂት ህፃናት በዛ ያሉ አሳማዎችን ያሳድጉ፡ የሚለውናአንድ ልጅ ማለት አንድ ተጨማሪ መቃብር ማለት ነው፡ የሚሉት ይገኙበታል፡፡ የቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎት ሀላፊዎች የኮሚኒስት ፓርቲ ሀላፊዎች ሲሆኑ ከአንድ በላይ ልጅ በወለዱም ሆነ ባረገዙ ሰዎች ላይ የፈለጉትን ውሳኔ ማሳለፍ ይችላሉ፡፡

ሴቶች በግድ እንዲያስወርዱ ወይም መካን እንዲሆኑ የመወሰን ስልጣንም አላቸው፡ ፡ ከባድ ቅ-ትም መጣል ይችላሉ፡፡ ፖሊሲው ተግባራዊ ከተደረገ ከሰማኒያዎቹ ዓመታ ጀምሮ ባሉት አመታት የቻይና መንግስት በቅጣት የሰበሰበው ገንዘብ ከ314 ቢሊዮን ዶላር በላይ መሆኑ ይነገራል፡፡ ጥንዶች ከማርገዛቸው በፊት የነሱን ፈቃድ ማግኘት አለባቸው፡፡ ለዚህም የጋብቻ ሰርተፊኬታቸውንና የመኖሪያ ፈቃዳቸውን እንዲሁም ሴቷ ቢያንስ ሀያ ወንዱ ደግሞ ሀያ አራት አመት እንደሞላቸው ማሳየት አለባቸው፡፡ ከሀላፊዎቹ የተጣለባቸውን ቅጣት ያልፈፀሙ ሰዎች አሳማዎቻቸውን፣ ከብቶቻቸውንና ቤታቸውን እንዲሁም ልጆቻቸውን ሊነ-ቁ ይችላሉ፡፡ ሀላፊዎቹ ፖሊሲው መጣሱን ለማየት በየጊዜው ያለመታከት ይቆጣ-ራሉ፡፡ ፖሊሲውን መተግበር የተለያዩ ጥቅማጥቅሞችን ያስገኛል፡፡ የተወለደው ህፃን አስራ አራት አመት እስኪሞላው የደሞዝ +ማሪ፣ ከወለድ ነፃ ብድር፣ የረታ ፈንድ፣ ማዳበሪያ በርካሽ ዋጋ፣ የተሻለ ቤት፣ የና አገልግሎት እና ትምህርትን የመሳሰሉት ማበረታቻዎች ሲሰጥ ከሀያ አምስት አመት እድሜያቸው በኋላ ለሚወልዱ ሴቶች ደግሞ ረዘም ያለ የወሊድ ፈቃድ በተጨማሪ ይሰጣቸዋል፡፡ የጥቅማጥቅሞቹ ተ-ቃሚዎች ፖሊሲውን ከጣሱ ያገኟቸውን መብቶች ይነ-ቃሉ፡፡ እ.አአ በ2008 . በሲችዋን ግዛት በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ልጆቻቸው የሞቱባቸው ወላጆች በ2011. ነው ልጆች እንዲወልዱ የተፈቀደላቸው፡፡ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት፣70.7 በመቶ የሚሆኑ የቻይና ሴቶች ተጨማሪ ልጆች መውለድ ይፈልጋሉ፡፡ ፖሊሲው የህዝብ ብዛትን በመቀነስ ከፍተኛ ሚና የተጫወተ ቢሆንም አካላዊ መንፈሳዊ እና ማህበራዊ ቀውሶችን ማስከተሉ አልቀረም፡፡ ሁለተኛ ልጅ አርግዛ የተገኘች ለመውለድ የተቃረበች ሴት ሳትቀር ንሱን በግድ እንድታስወርድ መገደዷና ሴቶችን ያለፍላጎታቸው መካን እንዲሆኑ ማድረግ ከፍተኛ የና እና የስነልቦና ቀውስ በሴቶቹ ላይ መፍ-ሩ ከሴቶች መብት ጋር የተያያዙ በፖሊሲ ማስፈፀም ስም እየተተገበሩ ያለ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ናቸው፡፡ ፆታን መሰረት ያደረገ ውርጃም በተመሳሳይ ከሴቶች መብት ጋር ተያይዞ ጥያቄ ውስጥ የሚገባ ሲሆን የዩኒሴፍ የቻይና ተወካይ እንዳሉት፣ የአንድ ልጅ ፖሊሲ ለህፃናት ሴቶች ብዙ ለውጦችን አምጥቷል፡፡ ነገር ግን ሴቷ መጀመሪያ ከተወለደች ብቻ ነው፡፡ በገ-ራማ ቻይና የሚኖሩ ቻይናውያን ለእርሻ ስራ ወንድ ልጅ የግድ ስለሚያስፈልጋቸው የመጀመሪያ ልጃቸው ሴት ከሆነች ሁለተኛ ልጅ መሞከር ይችላሉ፡፡

አንድ ሴት መንትዮች ካረገዘችና ማሳደግ የምትችል ከሆነም ከቅጣት ነፃ ናት፡፡ ሁለቱም ወላጆች ወንድም እና እህት ከሌላቸውም ሁለት ልጆች መውለድ ይፈቀድላቸዋል፡፡ የሚጣልባቸውን ቅጣት መክፈል የሚችሉ ጥንዶች ደግሞ ፖሊሲውን ይጥሳሉ፡፡ ምንም እንኳን የኮሚኒስት ቻይና ፓርቲ አባል የሆኑ ባለስልጣናት ፖሊሲውን ሲተላለፉ ሊቀ ቢችሉም ባለስልጣን በማወቅ ብቻም ከአንድ በላይ ልጅ ሊወልዱና ለከፋ ችግር ላይዳረጉ ይችላሉ፡፡ ለባለስልጣናት ጉቦ መስ-ት እና በህክምና ከአንድ በላይ ልጅ መውለድም ሌሎቹ ፖሊሲውን በመተላለፍ ከአንድ በላይ ልጅ ለመውለድ የሚያስችሉ መንገዶች ናቸው፡፡ በአለማችን በህዝብ ብዛት ቀዳሚ የሆነችው ቻይና፣ ከሰላሳ አመት በላይ የተከተለችው የአንድ ልጅ ፖሊሲ፣ ለሰው ሀይል እጥረት ሊዳርጋት እንደሚችል መረጃዎች እያመለከቱ ባሉበት በአሁኑ ሰአት፣ የፖሊሲ ለውጥ ማድረጓ አይቀሬ እንደሆነ እየተነገረ ነው፡፡ ብዙ ውዝግቦችን ያስተናገደውና ቀላል የማይባል ወጪ የወጣበት የአንድ ልጅ ፖሊሲ እጣ ፈንታ ምን ይሆን? ቻይናውያን በወንድምና እህት፣ በአክስትና አጎት ይንበሸበሹ ይሆን?

Published in ከአለም ዙሪያ
Saturday, 19 January 2013 14:58

“ደስታ መንደር ...”

ለዚህ እትም በርእስነት የቀረበው ...ደስታ መንደር... የአንድ መንደር መጠሪያ ነው፡፡ መንደሩ ከአዲስ አበባ ወደ 17/ ኪሎሜትር የሚርቅ ሲሆን ታጠቅ እየተባለ በሚጠራው ገፈርሳ መኖ በሚባለው አካባቢ የተመሰረተ ነው፡፡ የዛሬ 53/ አመት ገደማ ዶክተር ሄግ እና ዶ/ር ካትሪን ሐምሊን የተባሉ የጽንስና ማህጸን ሕክምና እስፔሻሊስቶች ወደኢትዮጵያ ለስራ መጡ፡፡ እነዚህ ባልና ሚስት በኢትዮጵያ ሳሉ በወሊድ ምክንያት ሴቶች ፌስቱላ የተባለ ከፍተኛ የሆነ የጤና ጉዳት ሲደርስባቸው ለመመልከት ቻሉ፡፡ ስለዚህም እነዚህ ባልና ሚስት አንድ ነገር ወሰኑ፡፡ እሱም በኢትዮጵያ የፌስቱላ ታማሚዎችን በደንብ ማከም የሚያስችል ተቋምን መመስረት ነበር፡፡

በውሳኔያቸው መሰረትም በአዲስ አበባ ሐምሊን ፊስቱላ ሆስፒታልን መስርተው እነሆ በአሁኑ ወቅት በተለያዩ መስተዳድሮችም ቅርንጫፍ ሆስፒታሎች ተከፍተው አገልግሎቱ በመሰጠት ላይ ናቸው፡፡ ፌስቱላ የሚከሰተው ሴቶቹ በምጥ ወቅት በፍጥነት ወደሐኪም ቤት ሳይደርሱ ለቀናት በመሰቃየት ምክንያት በሚፈጠር የአካል መቀደድ ምክንያት ሽንትን ያለመቆጣጠርና የመሳሰሉት ችግር ሲገጥማቸው ነው፡፡ ዶ/ር ሄግ ሕይወታቸው ያለፈ ሲሆን ሚስታቸው ዶ/ር ሐምሊን ካትሪን ግን እስከዛሬም ድረስ ታካሚዎችን በማገልገል ላይ ይገኛሉ፡፡ ለዛሬው እትም ለንባብ ያቀረብነው ደስታ መንደር የተሰኘውን በሐምሊን ሆስፒታል አማካኝነት የተመሰረተውን መንደር ሁኔታ ነው፡፡ በሐምሊን ፌስቱላ ኢትዮጵያ የመንደሩ ስራ አስኪያጅ የሆኑትን ወ/ሮ በለጥሻቸው ታደሰን ለዚህ እትም ጋብዘናል፡፡ ኢሶግ/ ደስታ መንደር ማለት ምን ማለት ነው? ስ/አ ደስታ መንደር ማለት በፊስቱላ ሕመም ምክንያት የተሰቃዩ እና ለተወሰነ ጊዜ ወይንም ለዘለቄታው የሀኪም ክትትል ያስፈልጋቸዋል የተባሉ ችግሩ ጠባሳ ትቶባቸው ያለፉ ሴቶች የሚቆዩበት ነው፡፡ ደስታ መንደር ሲባልም በዚህ መንደር እስከአሉ ድረስ ተስፋ የሚፈነጥቅላቸው ስለሌላ ነገር ወይንም ችግር ሳያስቡ ኑሮአቸውን በደስታ ሞልተው ስለቀጣይ ሕይወታቸው በማቀድ እንዲኖሩ የሚፈለግበት እና ጥረት የሚደረግበት ነው፡፡ ኢሶግ/ የፌስቱላ ታማሚዎች በሕክምናው ሙሉ በሙሉ መዳን ይችላሉን? ስ/አ የፌስቱላ ታማሚዎች ሙሉ ለሙሉ የሚድኑ ቢኖሩም ግን ሁሉም መቶ በመቶ ይድናሉ ማለት አይቻልም፡፡

በእርግጥ አንዳንዶች ታክመው ድነው ወደመጡበት ሕብረተሰብ የሚመለሱ ሲሆን አንዳንዶቹ ደግሞ ጭርሱንም ከሐኪም እርቀው መኖር የማይችሉ ይሆናሉ፡፡ ከ 4-5 ኀየሚሆኑት የፌስቱላ ታካሚዎች በምጥ ወቅት በጣም የተጎዱ ስለሚሆኑ ሊድኑ አይችሉም፡፡ ስለዚህ ከውስጥ አካላቸው ውጭ የሆነ ለመጸዳዳት የሚያገለግል የላስቲክ ቦርሳ ከሰውነታቸው ጋር ተያይዞ እንደሽንት የመሳሰለውን እንዲቀበሉበት ይሆንና በሕይወት እስከአሉ ድረስ እራሳቸው እየፈቱ እየገጠሙ እንዲገለገሉበት ከልብሳቸው ስር ይቀመጣል፡፡ ይህንን አይነት ሕክምና የሚሰጣቸው ሴቶች ወደመጡበት መንደር ተመልሰው እንዲሄዱ አይመከርም፡፡ ምክንያቱም የሽንት መቀበያውን ቦርሳ ሲያወጡ ሲያስገቡ ኢንፌክሽን ሊፈጠር ከመቻሉም በላይ የሚቀላቀሉት ሕብረተሰብ ሁኔታውን በምን ደረጃ እንደሚቀበለው ስለማይታወቅ የመገለል እጣ ሊኖራቸው ይችላል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በገጠር ያለው የአኗኗር ዘዴ ለእንደዚህ ያሉ ታካሚዎቸ አመቺ ባለመሆኑ የበለጠ ጉዳት ሊደርስባቸው እንደሚችል ይገመታል፡፡ ከምንም በላይ ግን ከሕክምናም እርቀው እንዲሄዱ አይመከርም፡፡ ኢሶግ / በከፍተኛ ሁኔታ የታመሙትን ሴቶች ለዘለቄታው ለመርዳት ምን እርምጃ ተወሰደ? ስ/አ እነዚህ ከ4-5 ኀየሚሆኑ በከፍተኛ ደረጃ የህክምና እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ሴቶች በየአመቱ ቁጥራቸው እየጨመረ ሲሄድ ለሆስፒታሉ መስራች ሐምሊን ካትሪን እና አብረዋቸው ለሚሰሩ ባልደረቦች አሳሳቢ ነበር፡፡ በእርግጥ ስልጠና እየተሰጣቸው በሆስፒታሉ ውስጥ የተለያዩ ስራዎችን እንዲሰሩ ቢመቻችም ከአመት አመት ቁጥራቸው እየጨመረ ሲመጣ የስራ እና የስልጠና ቦታው ግን በቂ ሊሆን አልቻለም፡ ፡ በዚህም ምክንያት ሁኔታውን ለመንግስት ማመልከት ግዴታ ነበር፡፡ መንግስትም ችግሩን ተረድቶ ከአዲስ አበባ 17/ ኪሎ ሜትር እርቀት ገፈርሳ መኖ ቀበሌ ላይ 60/ ሄክታር መሬት ሰጥቶ የዛሬ 9/ አመት የደስታ መንደር ተመሰረተ፡፡

ኢሶግ/ ይህ የደስታ መንደር ዘለቄታዊ መኖሪያ ነውን? ስ/አ የደስታ መንደሩ ስራ ሲጀምር በእርግጥ ታስቦ የነበረው ለዘለቄታው ተጎጂዎች እንዲኖሩበትና እንዲቋቋሙበት ነበር ፡፡ ነገር ግን ሰዎችን በተቋም ደረጃ ነጥሎ ማኖር ትክክል ካለመሆኑም በላይ ሰዎቹ እራሳቸውን መርዳትና ኑሮአቸውን መመስረት እንደሚገባቸው እንዲሁም በሕመሙ ምክንያት በቀጣይነት ለሚመጡት ሴቶች ቦታ መልቀቅ እንዳለባቸው ይታመናል፡፡ በእርግጥ የሚፈለገው ነገር ከሆስፒታል እንዳይርቁና ክትትል እንዲደረግላቸው ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ ለመጸዳጃ የሚገለገሉበት የላስቲክ ቦርሳ በየሳምንቱ ይሰበሰባል፡፡ ከሕክምናው ጋር በተያያዘ የሚኖረውን የደም ግፊት እንዲሁም የኩላሊት የመሳሰለውን ጤናቸውን እንዲከታተሉ ከማድረግ አንጻር የጤና ሁኔታቸው እስኪስተንከል እና ጎን ለጎንም ስልጠናቸውን እስኪያጠናቅቁ የሚቆዩበት መንደር ነው፡፡ በእርግጥ ለዘለቄታው እንዲኖሩ የሚወሰንላቸው ጥቂት ሴቶች ይኖራሉ፡፡ ኢሶግ/ ለዘለቄታው በመንደሩ የማይኖሩት ምን ድጋፍ ደረግላቸዋል? ስ/አ አንዲት ሴት ደስታ መንደር ስትመጣ በቀጥታ መደበኛ ወደ አልሆነው የጎልማሶች ትምህርት እንድትገባ ይደረጋል፡፡ ትምህርቱም አምስት ሞዱሎች አሉት፡፡ 1/ እራራሴንና ችግሬን ማወቅ፣ 2/ የህይወት አማራራጮች፣ 3/ እስቲ ልሞክረው፣ 4/ የህይወት ክህሎት፣ 5/ የንግድ ክህሎት እነዚህ ከላይ የተዘረዘሩት አምስት ሞዱሎች ለፌስቱላ ታማሚዎች የተዘጋጁ ናቸው፡፡

የረጅም ጊዜ ወይንም ለዘለቄታው ከህክምናው መራቅ የለባቸውም የተባሉ የፌስቱላ ታማሚዎች በደስታ መንደር ገብተው ይህንን ስልጠና ለመጨረስ በትንሹ እስከ አንድ አመት ተኩል ድረስ ጊዜ ይወስድባቸዋል፡፡ በደስታው መንደር ቁጭ ብለው በሚማሩበት ጊዜ ሙሉ ወጪዋን ሐምሊን ፌስቱላ ሆስፒታል ይሸፍናል፡፡ ኢሶግ/ ፌስቱላ ታማሚዎች ስልጠናውን ሲጨርሱ ቀጣዩ ሂደት ምን ይመስላል? ስ/አ ማንኛዋም በደስታ መንደር እንድትቆይ የተደረገች ሴት አንድ አመት ተኩል ያህል ስልጠናውን ከወሰደች በሁዋላ ተግባራዊ ልምምድ እንድትቀጥል ይደረጋል፡፡ ተግባራዊ ልምምዱም በግቢው ውስጥ ባሉት የዶሮ...ከብት እርባታ..ካፌ እና የጉዋሮ አትክልት በመሳሰሉት ስራዎች ላይ እንድትሳተፍ እና በወደፊቱ ሕይወትዋ የትኛውን መርጣ እንደምትሰማራ የእራስዋን ምርጫ ጠብቀን የማቋቋም ስራ እንሰራለን፡፡ በልብስ ስፌት ወይንም በጥልፍ ስራ መሰማራት ለሚፈልጉ ሁኔታዎች ተመቻችተው ስልጠና እየተሰጠ ነው፡፡ ባጠቃላይም በየትኛው ዘርፍ የበለጠ ውጤታማ ትሆናለች የሚለውን እና በሰልጣኝዋ በእራስዋ ፍላጎት ለማቋቋም ከክልሉ መስተዳድር መሬት እየተሰጠን እንዲሰማሩ በማድረግ ላይ ነን፡፡ ለምሳሌ... በግብርናው ዘርፍ የከብት ማርባት ስራ የጀመሩ አሉ፡፡ እንዲሁም የካፌ ስራ መስራት ለሚፈልጉም የኦሮሚያ ክልል ቦታ ሰጥቶን ያስጀመርናቸው አሉ፡፡ በደስታ መንደር ውስጥ ባለው ካፌም የሚሰሩት እነዚሁ ሴቶች ናቸው፡፡ ሁለት ሴቶችም የልብስ ስፌት ስራን እየሰሩ ይገኛሉ፡፡ ኢሶግ/ ከደስታ መንደር ወጥተው በህብረተሰቡ ውስጥ ተደባልቀው ኑሮ የሚመሰርቱ ይገኛሉን? ስ/አ በእርግጥ ለሕክምናው ቅርብ እንዲሆኑ ሲባል በዚህ መንደር ሰልጥነው በዚሁ መንደር ወይንም በየመስተዳድሩ የፌስቱላ ሐኪም ቤቶች እና አካባቢያቸው ላይ ብቻ በስራ ይሰማራሉ ማለት አይደለም፡፡

ከባድ የሆነ የስራ ጫና በሌለበት ሁኔታ ...ለምሳሌ ከባድ እቃን መሸከም ወይንም ቀና ጎንበስ የሚያደርግ እንደቁፋሮ ያለ ስራ በሌለበት ሁኔታ ሌላውን የእለት ተእለት እንቅስቃሴ እያደረጉ ኑሮአቸውን የመሰረቱ አሉ፡፡ ከዚህ ወጥተው ትዳር የመሰረቱም ይገኛሉ፡፡ እነዚህ ሴቶች በከፍተኛ ደረጃ ጥንቃቄ ማድረግ ያለባቸው በመውለድ ሁኔታ ላይ ነው እንጂ ወሲብን በመፈጸም ረገድ ብዙም ችግር የለባቸውም፡፡ በእርግጥ እንደጉዳታቸው አይነት ነገሮች እንደሚለያዩ መገመት አያስቸግርም፡፡ ነገር ግን በምንም ምክንያት ያለሐኪም እርዳታ ለመውለድ ማሰብ አይጠበቅባቸውም፡፡ ዋናው ከእነሱ የሚፈለገው ነገር ከሕክምናው አለመራቅ ነው፡፡ በእርግጥ በከፍተኛ ሁኔታ የተጎዱት ሴቶች ከሕክምናው ብቻም ሳይሆን ከመንደሩም እርቀው እንዲኖሩ አይፈቀድም፡፡ ኢሶግ/ የደስታ መንደር በ9/ አመት ጊዜው ምን ያህል ሴቶችን ተቀብሎ አስተናግዶአል? ስ/አ ቀጣይነት ላለው የህክምና ክትትል ወደ ደስታ መንደር የሚገቡ ሴቶች ከአመት አመት ቁጥራቸው ቢለያይም ከተቋቋመ እና ስራ ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ወደ መቶ የሚሆኑ ሴቶችን ተቀብሎ አስተናግዶአል፡፡ እነዚህን ሴቶችም በማሰልጠን ለተለያዩ ክህሎት ብቁ እንዲሆኑ በማድረግ ከአንድ አመት ተኩል ጊዜያቸው ጀምሮ እንደአቅማቸው በአዲስ አበባና በየመስተዳድሩ ባሉ የፌስቱላ ሐኪም ቤቶች እንዲሁም በኮሌጁ ባሉ የስራ እድሎች እንደችሎታቸው ተቀጥረው የሚሰሩ ሲሆን በተጨማሪም በግላቸው በንግድና በመሳሰሉት ስራዎች ተሰማርተው የሚኖሩ መጠነኛ ቁጥር ያላቸው ሴቶች አሉ፡፡

Published in ላንተና ላንቺ

የጐንደር ከተማ አስተዳደር በአንድ ነጥብ ሁለት ሚሊየን ብር ሶኒክ ስክሪን አሰርቶ ከትናንት ወዲያ አስመረቀ፡፡
የከተማ አስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ አቶ አታላይ ዓለም ለአዲስ አድማስ እንደገለጹት፤ ግዙፉ ሶኒክ ስክሪን የተሰራው ለከተማ ወጣቶች የመዝናኛ አማራጭ ለመስጠት፣ ባለሀብቶች ምርት እንዲያስተዋውቁበትና ለአጠቃላይ የመረጃ ልውውጥ ነው፡፡
በከተማው የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት የሚንቀሳቀሰው ሶኒክ ስክሪን ከ3 መቶ ሺህ በላይ ለሚሆነው የከተማዋ ነዋሪ አገልግሎት ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡


በደብረዘይት ከተማ ኪነ - ጥበብ አፍቃሪዎች የተቋቋመውና ላለፉት ዓመታት ወርሃዊ ኪነ - ጥበባዊ ዝግጅቶችን እያቀረበ ያለው "ሆራ ጉላ" የስነጽሑፍ ማህበር "ቃና ጥበብ" የተሰኘ ዝግጅቱን ለመውሊድ በዓል በመጪው ሐሙስ ከቀኑ 7፡30 ጀምሮ በቢሾፍቱ ሁለገብ ሲኒማ አዳራሽ እንደሚያቀርብ አስታወቀ፡፡ የዕለቱ የክብር እንግዳ እንደምትሆን በምትጠበቀው አንጋፋዋ አርቲስት አዳነች ወ/ገብርኤል ፊት የማህበሩ አባላትና ሌሎች እንግዶች የግጥም፣ መነባነብና ወግ ሥራዎቻቸውን ያቀርባሉ፡፡

ሚዩዚክ ሜይዴይ "ፍልስፍና 1" በተባለው የብሩክ አለምነህ መጽሐፍ አንድ ርዕስ ላይ ውይይት እንደሚያደርግ አስታወቀ፡፡ ነገ አምስት ኪሎ በሚገኘው ብሔራዊ ሙዚየም አዳራሽ በሚካሄደው ውይይት ላይ "ማህበራዊ ሱሰኝነት" የሚለው ርዕስ የተመረጠ ሲሆን የመነሻ ሐሳብ በማቅረብ ውይይቱን የሚመራው የሙዚቃ ሃያሲ ሰርፀ ፍሬስብሀት ነው፡፡

ለ3ኛ ጊዜ በጐንደር ከተማ በተካሄደው "ኢትዮጵያን በጐንደር ብሔራዊ የባህል ፌስቲቫል ላይ በወጣቶች የቀረበው "ግጥም በዋሽንት በመሰንቆ" በቋሚነት እንዲካሄድ ተጠየቀ፡፡ ባለፈው ረቡዕ ማምሻውን በከተማዋ "ዕልልታ አዳራሽ" ተካሂዶ በነበረ ዝግጅት ወጣቶቹ በባህል የሙዚቃ መሣሪያዎች የታጀበ የግጥም፣ የመነባንብ እና የተውኔት ሥራዎቻቸውን አቅርበዋል፡፡
ዝግጅቱን የታደሙ ወላጆችና የኪነ -ጥበብ አድናቂዎች ዝግጅቱ በየጊዜው እንዲቀርብና
"ግጥም በዋሽንት በመሰንቆ" በቋሚነት እንዲካሄድ ተጠየቀ
በአዝማሪዎቿ የምትታወቀዋ ከተማ በገጣሚዎቿም እንድትታወቅ ጠይቀዋል፡፡ የከተማዋ አስተዳደር የባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ኃላፊዎች ዝግጅቱን ወርሀዊ ለማድረግ እገዛ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል፡፡
የከተማዋ ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊ አቶ ጌታሁን ስዩም ስለጉዳዩ ተጠይቀው ሲመልሱ፤ "ለወጣቶቹ ስልጠና ሰጥተን ያስጀመርነው እኛ ነን በየወሩ የስነ ጽሑፍ ምሽት ስላለንም ከእሱ ጋር በማቀናጀት እንዲቀጥል ማድረግ እንችላለን፡፡" ብለዋል፡፡

በረዳት ፕሮፌሰር ሙሉጌታ ጃዋሬ የተሰራው "ቺኮሎጂ" የተሰኘ ሳታየር ኮሜዲ ፊልም ነገ በግል ሲኒማ ቤቶች እንደሚመረቅ ተገለፀ፡፡
ጃዋሬ ፕሮዳክሽንስ ለአዲስ አድማስ በላከው መግለጫ፤ ፊልሙ በልዩ ጥናት ላይ ተመስርቶ እንደተሰራና ከግማሽ ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ እንደተደረገበት አስታውቋል፡፡ ከሰማንያ በላይ ነባርና አዳዲስ ተዋንያን ተሳትፈውበታል የተባለው "ቺኮሎጂ"፤ በቅርቡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲና በመላው አገሪቱ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በልዩ ስነስርዓት እንደሚመረቅና በሁሉም ሲኒማ ቤቶች በመደበኛ ፕሮግራም እንደሚቀርብ ተገልጿል፡፡

በጂም ራንኪን የተፃፈው "Jesus in Ethiopia" የተሰኘ መጽሐፍ በይኩኖ አምላክ ታምሩ "ኢየሱስ ክርስቶስ በኢትዮጵያ" በሚል ርዕስ ተተርጉሞ ሰሞኑን ለንባብ በቃ፡፡ መጽሐፉ ለ2ሺ ዓመታት የተደበቀው ምስጢር በሚል "የኢየሱስና የአብ ግንኙነት በጣና ቂርቆስ"፣ "ኢየሱስ ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ እንደነበረ ማረጋገጫ" እና "የሙሴ ጽላት ኢትዮጵያ ውስጥ እንደሚገኝ ፍንጭ የሚሰጡ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች"ን ይዳስሳል፡፡ በኤች ዋይ ኢንተርናሽናል ማተሚያ ድርጅት የታተመው መጽሐፉ፤ በ40.50 ለገበያ ቀርቧል፡

በእግር በፈረስ ፊልም ስራዎች" የተዘጋጀውና በደራሲና ዳይሬክተር አክሊሉ ገ/መድህን የተሰራው "በዚህ ሳምንት" የተሰኘ አስቂኝ የፍቅር ፊልም የፊታችን ረቡዕ በ11 ሰዓት በብሔራዊ ቴአትር እንደሚመረቅ ተገለፀ፡፡
ፊልሙ ጥር 19 ቀን 2005 ዓ.ም ደግሞ በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች በግል ሲኒማ ቤቶች ይመረቃል ተብሏል፡፡ ፊልሙን ሰርቶ ለማጠናቀቅ አንድ ዓመት ያህል ጊዜ እንደወሰደ የገለፁት አዘጋጆቹ፤ ከ610ሺ ብር በላይ ወጥቶበታል ብለዋል፡፡ ፊልሙ፤ በሳምንቱ መጀመሪያ ቀን ባጋጠመው የፍቅርና የሥራ መሰናክል ሙሉ ሳምንቱ ስለተቃወሰበት የስፖርት ጋዜጠኛና ስለሁለት አብሮ አደጐች እንደሚተርክ አዘጋጆቹ በላኩት መግለጫ ጠቁመዋል፡፡ 1 ሰዓት ከ33 ደቂቃ በሚፈጀው አስቂኝ የፍቅር ፊልም ላይ አክሊሉ ገ/መድህን፣ ህብረት ፈቃዱ፣ ፍቃዱ ከበደ ማሞ፣ አድማሱ ከበደ፣ ሚካኤል ታምሬ፣ አበበ ተምትም እና ሌሎችም ተሳትፈውበታል፡፡

በደራሲ ሚካኤል ይበይን እና ዳይሬክተር ኤልያስ ወርቅነህ የተሰራው "የኛ ቤተሰብ" የቤተሰብ ኮሜዲ ፊልም ባለፈው ረቡዕ በብሔራዊ ትያትር በልዩ ፕሮግራም ተመረቀ፡፡ ፊልሙ እሁድ እለት በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች የግል ሲኒማ ቤቶች እንደተመረቀም ለማወቅ ተችሏል፡፡ ጋላክሲ ፊልም ፕሮዳክሽን ለአዲስ አድማስ በላኩት መግለጫ፤ ፊልሙን ሰርቶ ለማጠናቀቅ አራት ወር እንደፈጀና ከ350ሺ ብር በላይ ወጪ እንደተደረገበት አስታውቋል፡፡
1 ሰዓት ከ30 ደቂቃ ርዝመት ባለው በዚህ ፊልም ላይ አበበ ወርቁ፣ ካሣሁን ፍስሃ (ማንዴላ)፣ ዳንኤል ገበየሁ፣ ወለላ አሰፋ እና ሌሎችም ወጣትና አንጋፋ ተዋንያኖች ተውነውበታል፡፡

Page 4 of 11