ወላጅ መጽናኛ!
አንድ ዘመን ሄደ፣
አንድ ዘመን መጣ፣
በአንድ አመት አረጀሁ፣
በአንድ አመት ጐረመስኩ፣
በራሴ ሲያልፍብኝ፣
በልጄ እየደረስኩ፡፡
እምሻው ገ/ዮሐንስ
ሰው፣ ጊዜና ወርቅ!
በትውልድ እድገቱ
ኑሮውና ሞቱ
አድርጐ እንደ ጥላው
በእለትና ወራት
አመታት፣ ዘመናት
ቀምሮ እያሰላው
እንደ አፈር ቆንጥሮ
እንደ አፈር አንጥሮ
የሰው ልጅ ባይቀባው
የክብርን ቀለም፣
ከንቱ ውዳቂ እንጅ
በድን ለዘላለም
በሰው ካልተለካ
ጊዜ ወርቅ አይደለም፡፡
እምሻው ገ/ዮሐንስ
Published in
ማራኪ አንቀፅ