..አይኑማ.. በሚለው ዜማው የሚታወቀው ድምፃዊ እያዩ ማንያዘዋል ከ15 ዓመት በኋላ አዲስ አልበም አወጣ፡፡ ..አሞናል.. የሚለው አዲስ አልበም 10 ዘፈኖች ያሉት ሲሆን በካሴት እና በሲዲ ተዘጋጅቷል፡፡ግጥሙን አቤል መልካሙ ያዘጋጀው አዲስ አልበም ከሕዝብ ከተወሰዱ ዜማዎች በተጨማሪ አበበ ብርሃኔ እና እንዳለ አድምቄ ዜማውን የሰሩ ሲሆን አቀናባሪው ስንታየሁ ክብረት ነው፡፡ለበርካታ አመታት ከመድረክ ርቆ የነበረው ድምፃዊ እያዩ ..አቤል መልካሙ ለአምስት ዓመታት ከጐተጐተኝ በኋላ ተመልሻለሁ.. ሲል ለአዲስ አድማስ ተናግሯል፡፡