ለአዲሱ3D´ ሞባይል ታዲያ ..መነጽር ማድረግ ሊኖርብን ነው?.. የሚል ጥያቄ ሊነሳ ይችላል፡፡ ነገር ግን አዲሱ የኤልጂ ..ኦፕቲመስ 3D´ ሞባይል የሚፈለገውን እይታ ለማምጣት መነጽር አይጠይቅም፡፡
አዲሱ ሞባይል ያለ 3D´ መነጽር ነገሮችን ከሦስቱም አቅጣጫ ማየት የምንችልበትን ሁኔታ የሚፈጥርብን የምናይበትን አንግል አቀነባብሮ በማቅረብ ሲሆን በዚህ ስልክ ላይ በአንድ ጊዜ ምስሎችን በ |3D´ ማየት የሚችለው አንድ ሰው ብቻ ነው፡፡ ይህ ብቻ ሳይሆን በ3D´ ቪዲዮ ምስሎችን መቅረጽ የምንችልበት ባለ አምስት ሜጋ ፒክስል ካሜራም አለው፡፡ በዚህ መንገድ የቀረጽነውን ቪዲዮ ከ3D´ ቴሌቪዥን ጋር አገናኝተን ማየት የምንችል ሲሆን y|3D´ ፊልሞችንም ቀድተን ልንመለከትበት እንችላለን፡፡ 4.3 ኢንች ስክሪን ስፋት ያለው |3D´ ሞባይል ዋጋው 799 (13,600 ብር ገደማ) ዶላር እንደሆነ ታውቋል፡፡