በዚሁ መሠረት የዳሽን ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ “ሜቄዶኒያ ሂዩማኒተሪያን አሶሾዬሽን” የሚያበረክተውን ማኅበራዊና ሰብአዊ አስተዋጽኦ በጥልቀት በማጤን ማኅበራዊ ኃላፊነትን በጋራ ለመወጣት በማሰብ የ200,000 ብር ድጋፍ በመስጠቱ ደስታ እንደተሰማው ገልጿል፡፡ የ“ሜቄዶኒያ ሂዩማኒተሪያን አሶሴሽን” መስራችና ሥራ አስኪያጅ አቶ ቢኒያም በለጠ ከጥቂት ሳምንታት በፊት ከአዲስ አድማስ ጋዜጣ ጋር በበጐ ተግባር እንቅስቃሴው ዙሪያ ቃለ ምልልስ ማድረጉ ይታወሳል፡፡ ድርጅታችሁ ረዳት ለሌላቸው አረጋውያንና የአዕምሮ ሕሙማን ለሚያደርገው ዕርዳታ ያለንን አድናቆት እንገልጻለን ያለው ዳሽን ባንክ፤ ለዚህ የተቀደሰ ሐሳብና ተነሳሽነት ድጋፍ ለመስጠት የጋራ ርብርብ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን እናምናለን ብሏል፡፡ ዳሽን ባንክ ረዳት የሌላቸውን አረጋውያንና የአዕምሮ ሕሙማን ከጐዳና እየሰበሰበ ለሚረዳው “ሜቄዶኒያ ሂዩማኒቴሪያን አሶሴሽን” የ200ሺ ብር ድጋፍ ማድረጉን አስታወቀ፡፡