Tuesday, 23 April 2024 00:00

ዘመን ባንክ የሠራተኞቹን ዕውቀትና ክህሎት ለማሳደግ ከሊንክድኢን ለርኒንግ ጋር የአጋርነት ስምምነት ፈጸመ

Written by 
Rate this item
(2 votes)

ዘመን ባንክ የሠራተኞቹን ዕውቀትና ክህሎት ለማሳደግ፣ በዓለም  ትልቁ የኢንተርኔት የመማሪያ መድረክ ከሆነው ሊንክድኢን ሊርኒንግ ጋር የአጋርነት ስምምነት ተፈራረመ፡፡

የዘመን ባንክ የሰው ሀብት ምክትል ዋና ኦፊሰር አቶ ታከለ ዲበኩሉ ስለ ስምምነቱ ሲገልጹ፤ “ዘመን ባንክ ለሰራተኞቹ ቀጣይነት ያለው የመማርና የሙያ እድገት ባህልን ለማሳደግ ቁርጠኛ ነው። ከሊንክድኢን ለርኒንግ ጋር ያደረግነው ስምምነት፣ ይህንን ቁርጠኝነት የሚያጎላ ከመሆኑም በላይ ሠራተኞቻችን በፋይናንስ ዘርፉ የሚጠይቀውን ችሎታ፣ እውቀትና ክህሎት እንዲያሳድጉ የሚረዳ ነው፡፡" ብለዋል፡፡

የሊንክድኢን ታለንት ሶሉዩሽን ዋና ኃላፊ ማቲው ግሬይ በበኩላቸው፤ ”ከዘመን ባንክ ጋር ያደረግነው ስምምነት የሰራተኞቹን የክህሎትና የእውቀት ክፍተቶችን ለማሟላት እድሉን የሚሰጠን ከመሆኑም በላይ ሊንክድኢን ለርኒንግ በአፍሪካ ተመራጭ የክህሎት ልማት መድረክ ሆኖ  መቀጠሉን ስለሚያሳይ እጅግ ተደስተናል። የዘመን ባንክ የሰው ሃብት ስትራቴጂ በቀጣይ አመታት ይበልጥ እንዲጎለብትና ውጤታማ እንዲሆን አብረን እንሰራለን።" ብለዋል፡፡

የእነዚህ ኮርሶች ወጪ ሙሉ በሙሉ በዘመን ባንክ የተሸፈነ ሲሆን፤ የባንኩ ሠራተኞች ሥልጠናውን  በነፃ እንደሚያገኙ  ታውቋል፡፡

Read 717 times Last modified on Wednesday, 24 April 2024 15:18