Saturday, 13 April 2024 20:45

የእናቶች…የህጻናት…አፍላ ወጣቶች ጤና ጥራት…

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(0 votes)

   የስነ ተዋልዶ ጤናን በተመለከተ በተለያዩ ተቋማት የተለያዩ ስራዎች ይከና ወናሉ፡፡ባለፈው ሳምንት ለዚህ እትም እንግዳ የነበሩት ዶ/ር ኃ/ማርያም ሰኚ ቀደም ሲል በጅማ የነበሩ ሲሆን አሁን ለቦርድ ፕሬዝዳንትነት ሲመረጡ የት ሆነው ማህበሩን ሊመሩ ነው የሚል ጥያቄ ከአምዱ አዘጋጅ ቀርቦላቸው ነበር፡፡ እሳቸውም ሲመልሱ‹‹….በእርግጥ በጅማ ለረጅም ጊዜ ነበርኩ፡፡ ሕክምና የተማርኩት ጅማ ሲሆን የጽንስና ማህጸን ሕክምና እስፔሻሊስት ለመሆን አዲስ አበባ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ተምሬ በመመለስ በጅማ አገልግሎት ስሰጥ ቆይቻለሁ፡፡ በድምሩ ወደ አስራ ሰባት አመት በጅማ የቆየሁ ሲሆን ሁሉ ነገሬ ማለትም እውቀቴና ልምዴ ከጅማ የተገኘ ነው፡፡ ነገር ግን እንደ ውጭው አቆጣጠር ከ2016/ ጀምሮ አዲስ አበባ ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ጀምሮ በተለያዩ መስሪያ ቤቶች በማገልገል ላይ ነኝ ብለዋል፡፡


ዶ/ር ኃ/ማርያም አሁን ስለሚሰሩት ስራ ሲያብራሩ…መሰረቱን አሜሪካ ያደረገ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ውስጥ ተቀጥሬ የእናቶች፤የጨቅላ ህጻናት፤ህጻናትና ወጣቶች ጤናን ጥራትን ማሻሻል ላይ የሚሰራ ቡድን እየመራሁ በመስራት ላይ እገኛለሁ ብለዋል፡፡
ዶ/ር ኃ/ማርያም ዓላማውንም እንደሚከተለው ነበር የገለጹት፡፡ በጤና ጣብያ፤በመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል፤በሁለተኛ ደረጃ ሆስፒታልና በማስተማሪያ ሆስፒታሎች በተመረጡ ሰባት ክልሎች ያለውን የእናቶች፤የጨቅላ ህጻናት፤ህጻናትና አፍላ ወጣቶች የጤና ጥራትን ማሻሻል ነው፡፡ የጤና ጥራቱን ማሻሻል ሲበልም በጤና አገልግሎቱ መስጫው ዙሪያ ያለውን ብቻ የሚመለከት ሳይሆን ለመገልገል የሚመጣው ህብረተሰብም በምን ደረጃ ያለ ወይም በምን ጥራት ላይ የተመ ሰረተ የጤና አገልግሎት ይፈልጋል የሚለውንም ጎን ለጎን በመመልከት የሚሰራ ስራ ነው፡፡ ፕሮጀክቱ የሚሰራው በጤና ጣቢያና ከዚያም በላይ ባሉ የጤና ተቋማትና ሆስፒታሎች ሲሆን በመንግስት ሆስፒታሎች ብቻም አይደለም፡፡ የግል ጤና ተቋማትም ድጋፍ ይደረግላቸዋል፡፡


የእናቶች፤የጨቅላ ህጻናት፤ህጻናትና ወጣቶች ጤናን ጥራትን ማሻሻል ስራ የሚሰራባቸው ክል ሎች ትግራይ፤ኦሮሚያ፤አማራ፤ሲዳማ፤ማእከላዊ ኢትዮጵያ፤ደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያና ደቡብ ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ በእነዚህ ክልሎች የሚሰራባቸው ወረዳዎች ከሰማንያ በላይ ሲሆኑ ከሶስት መቶ በላይ የጤና ጣቢያዎች፤ከሰባ በላይ ሆስፒታች እና ከሁለት መቶ በላይ የግል ተቋማት አሉ፡፡ ፕሮጀክቱ የአምስት አመት ሲሆን እንደውጭው አቆጣጠር አስከ 2028/ የሚያልቅ ስራ ነው የተነደፈው፡፡
የእናቶች፤የጨቅላ ህጻናት፤ህጻናትና ወጣቶች ጤና ጥራት የሚባለው ስራ የሚያተኩረው ጥራቱን የጠበቀ አገልግሎት በጤና ተቋም እንዲሰጥ ለማስቻል ሲሆን ትኩረት የሚደረገው ሁለት መሰረታዊ ነገሮች ላይ ነው፡፡ የመጀመሪያው  መሰረታዊ ስራዎችን ማስቀደም ነው፡፡ልክ ቤት ሲገነባ በመጀመሪያ መሰረት እንደሚጣል ሁሉ የጤና አገልግሎቱን ጥራት ለማስከበር ስራዎቹም የሚጀመሩት ከመሰረቱ ነው፡፡ በሁለተኛ ደረጃ የሚሰራው በተጣለው መሰረት ላይ ጥራቱን የጠበቀ አገልግሎት ማግኘት የሚያስችሉ ስራዎችን መስራት ነው፡፡


መሰረት ለሚባለው ነገር በአለም የጤና ድርጅት የተቀመጠው አምስት ወይንም ስድስት የሚሆኑ መመሪያዎች ተጠቃሾች ናቸው፡፡ በጤናው ሴክተር ብቃት ያለው አመራር መስጠት፤ ስልጠና መስጠት ፤ ብቁ የሆኑ እና ሩህሩህ፤ አዛኝ ፤በታካሚው ውስጥ እራሳቸውን አድርገው ሊያዩ የሚችሉ በቂ ቁጥር ያላቸው ባለሙያዎች መኖር፤ የፋይናንስ ጉዳይ፤ የጤና መረጃ ስርአትን የሚመለከት ነው፡፡ እነዚህ የተጠቀሱ ነጥቦች በአግባቡ ትኩረት እንዲደረግባቸው የጤና አገልግሎትን ጥራት የሚመለከተው ፕሮጀክት በሚያስፈልገው ደረጃ ተግባራዊ የሚያ ደርገው ነው፡፡
በሌላም በኩል የህክምና ተቋማት የመገልገያ መሳሪያዎች እጥረት ይታያል፡፡ ይህ እጥረትም በሁለት መንገድ የሚታይ ነው፡፡ አንደኛው መገልገያ መሳሪያዎቹ ጭራሹንም የሌሉባቸው ቦታዎች አሉ፡፡ ለእነዚያ ቦታዎች በተወሰነ መልኩ ተገዝቶ የሚሰጥበት ሁኔታ አለ፡፡ ሁለተኛ የምንለው እጥረት ደግሞ መገልገያ መሳሪያዎቹ ቢኖሩም በተለያዩ ብልሽቶች ምክንያት ካለስራ ይቆማሉ፡፡ እነዚህ መሳሪያዎች ወይ ግምጃ ቤት ውስጥ ተዘግቶባቸው አለዚያም በየኮሪደሩ ቆመው ይገኛሉ፡፡ ስለዚህ የፕሮጀክቱ ሌላው ስራው እነዚህን በብልሽት ምክንያት አገልግሎት ያቋረጡትን መሳሪያዎች በመጠገን ወደ ስራ እንዲመለሱ ማድረግ ነው፡፡ ጥገና ሲባል አንዳን ዶች በቀላል የሚጠገኑ ሲሆን አንዳንዶች ደግሞ የጎደለው እቃ የግድ ከውጭ እንዲመጣ የሚ ያስገድዱ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ይሄ ሁሉ ተሟልቶ ወደ ስራ እንዲገቡ ይደረጋል፡፡


በተጨማሪም (Performance based financing) ስራን መሰረት ያደረገ የገንዘብ ድጋፍ የሚ ባል አለ፡፡ የአለም የጤና ድርጅት ካወጣቸው መሰረታዊ ነገሮች አንዱ ሲሆን የጤና ስርአቱን በጤና ኢንሹራንስ ለመጠበቅ መንግስትም ለጤናው ሴክተር በጀት ይመድባል፡፡ ከዚያ በተጨ ማሪ ግን አጋር ድርጅቶች የጤና ተቋማት ጥራቱን የጠበቀ አገልግሎት እንዲሰጡ ስራን መሰ ረት ያደረገ ስም ምነት በማድረግ ገንዘብ ይሰጣል፡፡ ይህንንም ድጋፍ 2/3ኛውንና ከዚያ በላይ የጤና ተቋማቱን ለማሻሻልም ይጠቀሙበታል፡፡ የህክምና መሳሪያዎች መግዛት፤ የመ ድሀኒት ክፍተት ያለበትን መሙላት፤ የህንጻ ጥገና ቢያስፈልግ ይጠገንበታል…ወዘተ የመሳ ሰሉት ስራዎች ይሰሩበታል፡፡ 1/3ኛ የሚሆነውን ደግሞ አገልግሎት የሚሰጡ ባለሙያዎቻቸ ውን ማትጊያ አድርገው ሊጠቀ ሙበት ይችላሉ፡፡ እውቀትን ለማጎልበት የሚረዱ ትምህርቶችን ማስተማር፤ማሰልጠን… ወዘተ…የመሳሰለው በዚህ ውስጥ ይካተታል፡፡  


ዶ/ር ኃ.ማርያም ሰኚ እንዳሉት የእናቶች፤የጨቅላ ህጻናት፤የህጻናትና የአፍላ ወጣቶች ጤናን ጥራት መከታተል ላይ የሚያተ ኩረው ይህ ግብረ ሰናይ ድርጅት በጤና ስርአቱ ላይ ሌላው የሚመለከተው ነገር የታካሚ ቅብብሎሽ ወይንም የ Referral ስራን የሚመለከት ነው፡፡ በዚህ አሰራርም በጤና ጣቢያና በሆስፒታሎች መካከል የሚደረገው የህመምተኛ ቅብብሎሽ በደንብ በተሟላ መንገድ መካሄድ ይጠበቅበታል፡፡
እስከአሁን ይሰራበት የነበረውን በወረቀት የታገዘ የመረጃ ቅብብሎሽ ወደ ዲጂታል ዘዴ መቀየ ርን ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ጋር እየተሰራ ሲሆን ይህም ተሞክሮ ውጤታማ የሚሆን ከሆነ በሀገር ደረጃ ለመጠቀም ያስችላል ተብሎ ይታሰባል፡፡
ሌላው በዚህ የታካሚ ቅብብሎሽ ስራ Referral ላይ እንደሀገር ችግር የሚታየው የአምቡላንስ አጠቃቀም ነው፡፡ አምቡላንሶቹ ብዙዎቹ መኪና አልጋ እና ኦክስጂን ነው ያላቸው፡፡ ግን መሆን ያለበት አንድ ታካሚ ከጤና ተቋም ወደ ጤና ተቋም በሚተላለፍበት ጊዜ በተቋማቱ መካከል የህክምና አገልግሎት እያገኙ መሄድ ነው ያለባቸው፡፡ ይህ ባለሙሆኑ ላኪው የጤና ተቋም የሚ ችለውን ያህል ሰርቶ ከአቅሙ በላይ በሚሆንበት ጊዜ ከፍ ወዳለ የጤና ተቋም ሲልክ በመሀከል ላይ የህክምና አገልግሎት ካልተሰጠ መንገድ ላይ ከፍተኛ ችግር ይፈጠራል፡፡ ብዙ ታካሚዎች መንገድ ላይ ሊያርፉ ይችላሉ፡፡ ምናልባትም በህይወት ቢተርፉ እንኩዋን ላይመለስ የሚችል ሕመም ሊገጥማቸው ይችላል፡፡ ስለዚህ አምቡላንሶች ምን አይነት እቃ፤መድሀኒት፤ ባለሙያ መያዝ አለባቸው የሚለው በሀገር ደረጃም የተቀመጠ አሰራር ስላለ ያንን ለማሟላት የጤና ጥራትን ለማሻሻል የተነደፈው ፕሮጀክት ይሰራል እንደ ዶ/ር ኃ/ማርያም ማብራሪያ፡፡


ከላይ የተጠቀሱትን የጤና ጥራትን ለመጠበቅ የሚያስችሉ ስራዎችን ለመስራት በየደረጃው የተዋቀሩ ስራውን የሚከታተሉ ኮሚቴዎች አሉ፡፡ ኮሚቴዎች በጤና ሚኒስቴር፤በክልል ጤና ቢሮዎች ፤በዞን ፤በወረዳ እንዲሁም በጤና ተቋማትም ውስጥ ይገኛሉ፡፡ ስለዚህ ኮሚተቴዎች ንም ለማጠናከር የሚሰራ ስራ አለ፡፡ የጤና ስርዓቱን የተሻለ ጥራት እንዲኖረው ከሚያደርገው መካከል መረጃን መሰረት ያደረገ ውሳኔ መስጠት መቻል አንዱ ነው፡፡ ስለዚህ መረጃን መሰረት ያደረገ ውሳኔ መስጠት ትክክለኛ ስራ ነው ብለን ስለምናምን የጤናውን ስርአት ጥራት ለመጠ በቅ በመንግስትም ይሁን በግል የጤና ተቋሞቻችን ድጋፍ በምናደርግባቸው አካባቢዎች ማህበረ ሰብንም ባሳተፈ መልኩ መረጃን በተገቢው ሰንዶ፤ተጠቅሞ ክፍተትን ለመሙላት ስራዎች ይሰራሉ፡፡


በስተመጨረሻም የእናቶች፤ጨቅላ ህጻናት፤ህጻናት፤አፍላ ወጣቶች የጤና ጥራትን ለመጠበቅ የተዘረጋው ፕሮጅክት ስራዎችን ለመስራት የሚመርጣቸው አካባቢዎችን በሚመለከት ዶ/ር ኃ/ማርያም የሚከተለውን ነበር ያሉት፡፡ …. እንደ ሀገር ህዝቦች የሚኖሩባቸው አካባቢዎች በሶስት ይከፈላሉ፡፡ ከተማ ፤ገጠር እና አርብቶ አደር በሚባል አካባቢ ህዝቡ ይኖራል፡፡ ፕሮጀ ክት ሲቀረጽ ደግሞ ገንዘብ የሚሰጠው ድርጅት፤ገንዘቡን ተቀብለው ስራ ላይ የሚያውሉ ድርጅ ቶች እና የመንግስት አካላት አሉ፡፡ እኛም በጤና ላይ እንደሚሰራ ድርጅት የጤና ሚኒስቴር በተዋረድም በየክልሉ …ወዘተ ያሉ የጤና ድርጅቶች አብረውን ይሰራሉ፡፡ስለዚህም ምን ይሰራ፤ የት ይሰራ የሚለው የሚወሰነው በጋራ በሚደረገው ምክክር ሲሆን በዋናነት የሚወስነው ግን የመንግስት አካል ነው  ብለዋል ዶ/ር ኃ/ማርያም ሰኚ የጽንስና ማህጸን ሕምና እስፔሻሊስትና የህብረተሰብ ጤና እስፔሻሊስት እንዲሁም የ ESOG ቦርድ ፕሬዝዳንት፡፡   

Read 298 times