Saturday, 13 April 2024 20:18

የአጼ ቴዎድሮስ የልጅ ልጅ ልጅ አዳዲስ ምስጢሮች

Written by 
Rate this item
(5 votes)

                  • ኢትዮጵያዊ መሆኑን ያወቀው ከ30 ዓመቱ በኋላ ነው
                  • የልዑል አለማየሁ አስከሬን በእንግሊዝ የለም ብሏል
                  • ልዑሉ በ18 ዓመቱ በለጋ ዕድሜው አልተቀጨም ባይ ነው





         ባለፈው ረቡዕ ወዳጄ ዘነበ ወላ ስልክ ደውሎ፣ የአጼ ቴዎድሮስ የልጅ፣ ልጅ ልጅ እዚህ እንደሚገኝና መጽሐፉን ማሳተምእንደሚፈልግና የሚዲያ ሰው ማነጋገር እንደሚሻ ነግሮኝ ስሙንና ስልኩን በቴሌግራም ላከልኝ፡፡ ”ስሜ ሲሰን አለማየሁ ቴዎድሮስይባላል፡፡ በአሜሪካን አገር ያደግሁኝ
ኢትዮጵያዊ ነኝ፡፡ ደራሲና የፊልም ፕሮዱዩሰር ስሆን፤ መጻሕፍቶቼ በኢትዮጵያ ገበያ ላይእንዲወጡልኝ እፈልጋለሁ” ይላል በቴሌግራም የደረሰኝ መልዕክት፡፡ ይህን ስም የሰማሁት ለመጀመሪያ ጊዜ ነው፡፡ አላውቀውም፡፡ ጉግል አደረግሁ፡፡ ጉግል ግን በደንብ ያውቀዋል፡፡ማንነቱን፣ ሥራዎቹን ወዘተ ዘረገፈልኝ፡፡ ጥቂት መረጃዎች ከሰበሰብኩ በኋላ ሰውየው ዘንድ ደወልኩለት፡፡ ለቃለ መጠይቅ ፈቃደኛ መሆኑንጠየቅሁት፡፡ አላቅማማም፡፡ ሲሰን አለማየሁ ቴዎድሮስ፤ የልዑል አለማየሁ ቴዎድሮስና የዳግማዊ አጼ ቴዎድሮስን ጨምሮ ከ7 ያላነሱመጻኅፍትን ለንባብ ያበቃ ታታሪ ብዕረኛ በመሆኑ ደራሲ ነው ብንል አልተሳሳትንም፡፡ ደራሲ ብቻ ግን አይደለም፡፡ ደራሲና ሁለገብ ብንለው ሳይቀል አይቀርም፡፡ ምክንያቱምየፊልም ፕሮዱዩሰር ነው፣ የታሪክ ልሂቅም ነው፡፡ በተጨማሪም ቪዲዮግራፈርና ግራፊክ ዲዛይነርም ነው፡፡ ይህ ሁሉ ታዲያ ቆፍጣናየአሜሪካ ወታደር መሆኑን ሳንረሳ ነው - አሁን ጡረታ ቢወጣም፡፡ የኢራቅ ግዳጁን ፈጽሞ ሲመለስ አባቱ አንድሪውቻርልስ ሊንዚ የነገሩትምስጢር የህይወቱን ዕጣ ፈንታ እንደቀየረው ይናገራል፡፡

 

አባቴ ለመጀመሪያም ለመጨረሻም ጊዜ የነገረኝ ይህ የቤተሰብ ምስጢር፤ አስቤውም አልሜውም የማላውቀው ነውይላል፡፡ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ታዲያ የተነገረውን ምስጢር ገላልጦ እውነቱን ለማወቅ ያልፈነቀለው ድንጋይ፣ ያልረገጠው የዓለም ዳርቻ የለም፤ ኢትዮጵያን ጨምሮ፡፡ እውነቱን
አወቀ ማለት ደግሞ ራሱን ማንነቱን አወቀ ማለት ነው፡፡ በዚህ ከአዲስ አድማስ ጋር ባደረገው ልዩ ቃለ ምልልስ፣ ሲሰን አለማየሁ፣ስለ ልዑል አለማየሁ ቴዎድሮስ ደረስኩበት ያለውን አዲስ እውነት ወይም ምስጢር ያጋራናል፡፡ የቤተሰቡን የዘር ሃረግ ለማግኘት የተጓዘበትን ርቀትናየደረሰበትንምያወጋናል፡፡
አሁን በቀጥታ ወደ ቃለ ምልልሱ፡-

        እስቲ ከትውልድህና አስተዳደግህ እንጀምር---የት ተወለድክ? የትስ አደግህ?
የተወለድኩት ሻን አንድሪው ሊንዚ ነው፤ ያደግሁት በከተማ ማህበረሰብ ውስጥ እንደ አፍሪካ-አሜሪካዊ፣ በሻምፓኝ፣ ኢሊኖይ ነው።የምኖርበት ሰፈር በዓመፅ፣ በአደንዛዥ ዕፅና በጠመንጃ የተሞላ ነበር። ፖሊስ የችግር ቦታ ሲል የፈረጀው ነው- አካባቢውን፡፡ ባለፉትዓመታት፣ ቤተሰቤንና የልጅነት ዘመን አብሮ አደጎቼን አጥቻለሁ፡፡ ኢትዮጵያዊ መሆኔን እስከ 30 ዓመት ዕድሜዬ ድረስ አላውቅም ነበር።በ1999 ዓ.ም የአሜሪካንን ጦርሰራዊትተቀላቀልኩ፡ በ2007 ዓ.ም የኢራቅ ግዳጄን ተወጥቼ ወደ አገር ቤት ተመለስኩ። በወቅቱ የአባቴ አንድሪው ቻርልስ ሊንዚ የጤና ሁኔታእያሽቆለቆለ ነበር፡፡ ያኔ ነው የቤተሰባችንን ምስጢሮች ለመጀመሪያ ጊዜ ገልጦ የነገረኝ፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ካሣ ከሚባል የንጉሥቤተሰብ እንደመጣን ገለጸልኝ፡፡ መጀመሪያ ላይ
ነገሩን አምኖ ለመቀበል አዳጋች ሆኖብኝ ነበር፤ ምክንያቱም ከዚያ በፊት ስለዚህ ጉዳይ ጨርሶአንስቶ አያውቅም፡፡ ከአንድ ወር በኋላ አባቴከዚህ አለም በሞት ተለየ።
አንተስ ይህን አዲስ መረጃ ከአባትህ ካገኘህበኋላ ምን አደረግህ?
አባቴ የመጨረሻዎቹ ቀናት ላይ ማንበብ የማልችለውን የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ መያዜን አውቆ ነበር፡፡ እናም ወደ ኢትዮጵያሄጄ ቤተሰባችንን ፈልጌ እንዳገኝ ትዕዛዝ ሰጠኝ፡፡ በ2012 ዓ.ም ከአሜሪካ ጦር ሠራዊት ጡረታ ወጣሁና ወደ ኢትዮጵያ ተጓዝኩ፡፡ ወደ ባህርዳርና ጎንደርም ተሻግሬ፣ አባቴ የጠቀሰውን ሃውልት ለማየት ቻልኩ፡፡ ያኔ ነው ካሣ የሚለው ስም ለካሳ ሀይሉ ጊዮርጊስ፤ ለባለ ዘውዱ ንጉስዳግማዊ አጼ ቴዎድሮስ መሆኑንየተረዳሁት፡፡
በ2017 ዓ.ም አንዲት ሴት በአማራ ቲቪቃለ መጠይቅ ተደረገላት። አበበች ካሳ መሸሻ ቴዎድሮስ ትባላለች። እቺን ሴት ከሁለት ወራትበኋላ አገኘኋት፡፡ እዚህ ኢትዮጵያ ያለ የቅርብ ወዳጄ አዲስ አበባ ሠርጉ ላይ እንድገኝ ጋብዞኝነበር፡፡ በዚያ አጋጣሚ እኔና እሷ የዲኤንኤምርመራ አደረግን፤ ውጤቱም ዘመዳሞችመሆናችንን አረጋገጠ፡፡ አባቴ የተወለደው አሜሪካ ነው፣ አባቱ ቻርለስ ሊንዚ ግን አሜሪካ አይደለምየተወለዱት፡፡ ቻርለስ ሊንዚ ተብለው የሚጠሩት አባታቸው ደግሞ ከንጉሥ ቴዎድሮስልጆች አንዱ ነበሩ።


ልዑል አለማየሁ ቴዎድሮስን የተመለከተመጽሐፍ በአማርኛና በእንግሊዝኛ አሳትመሃል፡፡ አማዞን ላይ ለሽያጭ ቀርቦ ተመልክቼዋለሁ---
ትክክል ነው፡፡ በ2018 ዓ.ም በአንዱ ቀን፣ ልዑል አለማየሁ ቴዎድሮስን ለማክበር ወደእንግሊዝ ተጉዤ ነበር፡፡ ያኔ ነው ሚስጥሮቹንያገኘሁት፡፡ ለልዑል ዓለማየሁ በቦታው ላይ ምልክት ብቻ እንጂ የሬሳ ሳጥን መቃብር የለም።ሆኖም ሰ ዎች የ እኔንና የ ልዑል አ ለማየሁንበእጅጉ መመሳሰል ታል፡፡ እኔም ቅድመ- አያቴ የእውነትም ልዑል አለማየሁ ቴዎድሮስ እንደነበሩ ተረዳሁ፡፡ ልዑል አለማየሁ፤ እስከ 113ዓመት ዕድሜያቸው ድረስ በህይወት ኖረው፣
በ1974 ዓ.ም ሻምፓኝ፣ ኢሊኖይ ነው የሞቱት፡፡
አንተ ልዑል አለማየሁ ቅድመ አያቴ ነበሩ ስትል ማረጋገጫህ ምንድን ነው?
መጀመሪያ ላይ ልኡል አለማየሁ ቅድመ አያቴ መ ሆኑን አ ላውቅም ነ በር። ነ ገር ግ ን ከልኡል አለማየሁ ጋር እንደምንመሳሰልበየፎቶው ላይ አስተውያለሁ። ከአበበች ካሣ መሸሻ ቴዎድሮስ ጋር የተደረገ የDNA ምርመራማስረጃ አለኝ፤ ከ50% በላይ የዲኤንኤ መዛመድ እንዳለን ያሳያል። በቅርቡ የካፒቴን ትሪሻም ቻርልስ ስፒዲ ቤተሰብ ከኒውዚላንድ የልዑል አለማየሁን ናሙና ከመቃብር ቦታ ሳይሆንከቤተሰቡ አምጥቶልኝ ነበር። የፀጉር ናሙናዎች ዲኤንኤ ነው፡፡ እኔም ከቅድመ አያቴ ቻርልስ ፎቶና ልዑል አለማየሁ ጋር የፎቶ ልየታ ሰርቼ፣85% የተዛማችነት ውጤት ታይቷል፡፡ቅድመ አ ያቴ በ 1879 ዓ.ም ወደ ፍ ልስጤም መሄዱን ተረድቻለሁ፡፡ ስምየን አንበሳ ዘዮን የሚለውን ስሙን ለውጦታል። አንበሳ ዘዮንበእንግሊዝኛ የጽዮን አንበሳ ማለት ሲሆን፤ ሊንዚ ደግሞ የጽዮን አንበሳ ነው። እስከ 1919 ዓ.ምድረስ ቤተ ሺአን እና እየሩሳሌም ውስጥ ነበርየቆየው፡፡ ቻርልስ ከካፒቴን ትሪሻም ቻርልስስፒዲ ይባላል። ኢትዮጵያ እያለ ከወንድሙ መሸሻ ቴዎድሮስ ጋር ተገናኘ። ሚስት እንዲሁምሴት ልጅና ወንድ ልጅ ነበረው። ሚስቱ
በ1925 ዓ.ም ልጃቸው ቻርልስ የ2 ወር ልጅእያለ፣ኢትዮጵያ ውስጥ ህይወቷ አለፈ፡፡ እሱከልጁ ጋር ወደ አሜሪካ ሲመጣ ሴት ልጁ ግን ቀረች።
ከሰባት በላይ መጻሕፍትን አሳትመሃል፡፡ ወደ ጸሃፊነትና ፊልም ሙያ እንዴት ገባህ? ወታደር ቤትን ከመቀላቀሌ በፊት የሙዚቃ ኮንትራት (ውል) ለማግኘት የሚሻ የሂፕ ሆፕ ሪከርዲንግ አርቲስት ነበርኩ። መጀመሪያ ዘፈኖችን መጻፍ ጀመርኩ፤ በኋላ ወደ መጻሕፍትገባሁ፡፡ የበኩር መጽሐፌ በ2006 የታተመሲሆን፤ ከዚያ በኋላ ሰባት ተጨማሪ መጻሕፍትን መፃፍ ቀጠልኩ። ስለ ቤተሰቤ የዘር ሐረግምጽፌአለሁ፡፡ እናም ጉዞዬን በፊልም መ ቅረጽ
ጀመርኩ፡፡ ስለ ቤተሰቤ ታሪክ ለማወቅ ያደረግኋቸውን ጉዞዎች ለማድመቅ ዘጋቢ ፊልም ሰርቻለሁ። የጉዞዬ አካል፣ ኢትዮጵያበመላው አለም በአሜሪካ፣ በእስራኤል፣ በአውሮፓና በጥንቷ ባቢሎን ታላቅ ታሪክ እንዳላት መማር ነው።
የኢትዮጵያን ባህልና ታሪክ በሥራዎችህ ስታጋራ ያጋጠሙህ ተግዳሮቶች ወይም የተሳሳቱአመለካከቶች የሉም? እንዴት አስተናገድካቸው?
ልዑል አለማየሁ በ18 ዓመቱ ሞቷል ተብሎ ዓለም ሁሉ ስለተነገረው ብዙ ተግዳሮቶች ገጥመውኛል፡፡ የንጉሣዊው ቤተሰብ የልዑልአለማየሁን አስክሬን ለመላክ ፈቃደኛ ያልሆነው፣ ንግሥት ቪክቶሪያ ልኡሉ ሳይሞት የሞተ አስመስላ በመናገሯ ነበር፡፡ ለዚህ ደግሞምክንያቱ ንጉሥ ዮሐንስ ልዑል ዓለማየሁ
ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለስ የሚጠይቅ ሁለት ደብዳቤዎች ለንግሥት ቪክቶሪያ በመጻፋቸው የተነሳ ነው፡፡
አሁን ወደ ኢትዮጵያ የመጣህበት የተለየ ዓላማ ወይም ተልዕኮ ይኖርህ ይሆን?
ወደ ኢትዮጵያ ስመጣ ለዘጠነኛ ጊዜ ነው፡፡ ግቤ የኢትዮጵያ መታወቂያ አግኝቼ እዚህ አገር መኖርና መማር ነው፤ ምክንያቱም ወደ ኢትዮጵያ
መምጣት የቤት ዓይነት ስሜት ይፈጥርብኛል፡፡ ህዝቤን እወዳለሁ፤ ከኢትዮጵያውያን ጋር በመሆኔ የሰማዩን አባት አመሰግነዋለሁ፡፡ሌላው ግቤ ደግሞ በአማርኛም ሆነ በሌሎች የኢትዮጵያ ቋንቋዎች መናገር፣ ማንበብና መጻፍ መማር ነው። ወደ ቤት የሚመለስበትን መንገድለማግኘት የሚሞክር የጠፋ ልጅ ዓይነት ስሜት ይሰማኛል።
በመጨረሻ፣ በሥራዎችህ ምን አሻራ ትተህ ማለፍ ትፈልጋለህ?
የኢትዮጵያ ታሪክ አካል መሆን እፈልጋለሁ። ሁሉንም ሰው የሚጠቅም ታላቅ ነገር ማድረግ እንደምችል ተስፋ አደርጋለሁ። መጽሐፎቼኢትዮጵያ ውስጥ ቢታተሙ መታደል ነው፡፡ ታሪክን በፊልም ቀርጾ መስራትና ኢትዮጵያ በአለም ላይ ያሳደረችውን ተፅእኖ ማሳየትእፈልጋለሁ።

 

 

የቴሌግራም ቻናልችንን  በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
https://t.me/AdissAdmas

 

Read 5234 times Last modified on Sunday, 14 April 2024 20:05