Saturday, 13 April 2024 20:06

የዶንጋ ህዝብ በልዩ ወረዳ የመደራጀት መብቱን ተገፍፏል ተባለ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

የብሔረሰቡን ባህላዊ ልብስ ለመቀየር የሚደረገው ሙከራ እንዲቆም ፓርቲው ጠይቋል ከ20 በላይ የታሰሩ የብሔረሰቡ አባላት በአስቸኳይ
እንዲፈቱ ጠይቋል
       
         በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ውስጥ የሚገኘው የዶንጋ ህዝብ በልዩ ወረዳ የመደራጀት ህገ-መንግስታዊ መብቱን ተነጥቋል ሲልየዶንጋ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ አስታወቀ፡፡ ፓርቲው በሳምንቱ መጀመሪያ በሰጠው መግለጫ ነው፤ ይህን ያብራራው፡፡ የማዕከላዊ ኢትዮጵያክልልን ከመሰረቱ አስር ብሄረሰቦች አንዱ የዶንጋ ህዝብ ነው ያለው ፓርቲው፤ ሌሎቹ ብሄረሰቦች በልዩ ወረዳ የመደራጀትና ሌሎች መብቶቻቸው አንፃራዊ  በሚባል መልኩ ሲመለሱ የዶንጋ ህዝብ ወደ 20 የሚጠጉ መሰረታዊ የመብት ጥያቄዎች ግን አልተመለሱም ብሏል - ፓርቲው፡፡“ይባስ ብሎ የህዝቡ ነባር የባህል ልብስ ቀለምና ቅርፅ እንዲለወጥና ሌላ ቅርፅ እንዲይዝ ሙከራ እየተደረገ ነው” ያለው ፓርቲው፤ ይሄ የብሄረሰቡን ማንነት ባህልና እሴት የሚንድ እንቅስቃሴ በአስቸኳይ እንዲቆም ጠይቋል፡፡

ምንም እንኳ የዶንጋ ብሄረሰብ በልዩ ወረዳየመደራጀት ህገ መንግስታዊ መብት ቢኖረውም፤ ከህገ-መንግስትና ከብልፅግና እሳቤ ውጪ የሆኑ ህገ-ወጥ አመራሮች ከወረዳ እስከ ዞንና ክልል ድረስተሰግስገው ብሄረሰቡን አደጋ ላይ እየጣሉ በመሆኑ የህብረተሰቡን ችግርና መከራ የኢትዮጵያ ህዝብና ፌደራል መንግስት እንዲሰማና ችግሩ እንዲቀረፍፓርቲው ይህን መግለጫ ለማዘጋጀት መገደዱን የፓርቲው አመራሮች ገልፀዋል፡፡ የብሄረሰቡ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የወጣት ተወካዮችና የሀይማናት አባቶች በጋራ ተናግረዋል፡፡

በመሆኑም ፓርቲው የብሄረሰቡ የመብት ጥያቄዎች ሳይመለሱ ጊዜ እየተቆጠረ መሄዱ ብሄረሰቡን ዋጋ እያስከፈለና የተዛባ አመለካከት እንዲስፋፋእያደረገ በመሆኑ፣ የብሄረሰቡ ጥያቄዎች በአስቸኳይ እዲመለሱ፣ ሁለተኛ በ10 ብሄረሰቦች የተዋቀረውየማከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህገ መንግስት አንቀፅ47 መሰረት የክልሉ መንግስት መስራች ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች፣ እኩል መብትና ስልጣን አላቸው የሚል በመሆኑ ከመስራቾች ዘጠኙ በዞንናበወረዳየመደራጀትመብታቸውና እንዲሁም ሌሎች የልማትና የኢኮኖሚ ተጠቃሚነታቸው እንደተከበረላቸው ሁሉ የዶንጋ ህዝብም እነዚህን መብቶችና ጥቅሞች የማግኘት መብቱ እንዲከበርለት ጠይቋል፡፡


   ፓርቲው አክሎም፤ የዶንጋ ብሄረሰብ በአሁኑ ወቅት እየጠየቀ ያለው የልማትና የመዋቅር ጥያቄ እንጂ የአመራር ለውጥ ባለመሆኑ፣ የአመራር
ለውጥ ለዶንጋ ህዝብ ያመጣትው ፋይዳ ባለመኖሩም፣ ብሄረሰቡ የጠየቀው የልማትና የመዋቅር ለውጥተቀባይነት አግኝቶ በተግባር እንዲታይ በአቋም መግለጫው አብራርቶ፤ የዶንጋ ህዝብ ይህን ጥያቄ በተደጋጋሚ በሚጠይቁ ተወካዮቹ ላይ የእስር የማዋከብና የፓርቲውን ሀላፊዎችና ደጋፊዎችን ማስገደድ ስራ ላይ መጠመዱ የዴሞክራሲያዊ ስርዓት መገለጫ የሆነውን ጠያቂና ሞጋች ህበረተሰብመፍጠር በእጅጉ የሚቃረን በመሆኑ የዞኑና የወረዳው አመራሮች ከዚህ አሳፊሪ ድርጊት እንዲታቀቡ ጠይቆ፤ የታሰሩ ከሃያ በላይ የብሄረሰቡ አባላት በአስቸኳይእንዲፈቱ ጥሪ አቅርቧል፡፡ በሌላ በኩል የብሄረሰቡ ነባር ባህላዊ ልብስ እንዲለወጥና በሌላ እንዲተካ የሚደረገው ጥረት ለብሄረሰቡ ታስቦ ሳይሆን፤ሌላ የፖለቲካ አጀንዳ የያዘ መሆኑን ደርሼበታለሁ ያለው የዶንጋ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ፤ ይህ እንቅስቃሴ በዶንጋ ብሄረሰብ ተቀባይነት የሌለውመሆኑ ታውቆ በአስቸኳይ እንዲቆም በጋዜጣዊ መግለጫው ጠይቋል፡፡


Read 803 times