Wednesday, 06 March 2024 10:29

የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ፕሮጀክት አፈፃፀም 95 በመቶ ደርሷል ተባለ

Written by 
Rate this item
(2 votes)

የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ፕሮጀክት አፈፃፀም 95 በመቶ መድረሱን የሕዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ገለጸ።

ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽ/ቤቱ  በዛሬው ዕለት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንደተነገረው፤ የሲቪል ሥራው 98 በመቶ እንዲሁም የኤሌክትሮሜካኒካል ሥራው 78 በመቶ ደርሷል፡፡

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታው አሁን ላይ 95 በመቶ የደረሰ ሲሆን፤ ሀይል የማመንጨት ምዕራፍ ላይም ይገኛል።

መላ የኢትዮጵያ ህዝብ ካለው ላይ በማዋጣት ግድቡን  ለዚህ እንዳደረሰው ያመለከተው ጽ/ቤቱ፤ በ13 አመታት ውስጥም ከ18.9 ቢሊዮን ብር በላይ ማሰባሰብ ተችሏል ብሏል።
 
ግድቡ አሁንም ከፍጻሜው እስኪደርስ ህዝቡ የሚያደርገውን ርብርብ እንዲያጠናከር ጽ/ቤቱ ጥሪ ቀርቧል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፤ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ  የኤሌክትሪክ ሀይል ማመንጫ ግድብ የመሰረት ድንጋይ የተቀመጠበትን 13ኛ ዓመት በተለያዩ ዝግጅቶች ለማክበር መዘጋጀቱን የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት አስታውቋል፡፡


   የቴሌግራም ቻናልችንን  በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
https://t.me/AdissAdmas

Read 682 times