Saturday, 10 February 2024 10:12

“ከዛሬ ጀምሮ ስምህ ተስፋ (HOPE) ይባላል..”

Written by 
Rate this item
(5 votes)

ከማኅበራዊ ድረገፅ

 ዋስይሁን ተስፋዬ)

ይህ ናይጄሪያዊ ህጻን  ተስፋ ይባላል .. ለባእድ አምልኮ እራሳቸውን ያስገዙት ቤተሰቦቹ ለሞት አሳልፈው ሊሰጡት ከቤት አውጥተው በጭካኔ በጎዳና ላይ ሲወረውሩት ምንም አልመሰላቸውም።  ምክንያቱም

ለነሱ ከዚህ ነብስ ከማያውቅ ምስኪን ህጻን ይልቅ .. የህጻኑን “ሟርተኛ”  እና “መአት አምጭ”  .. መሆን የተነበየላቸው  ጠንቋይ ያስፈራቸዋልና፣ አውጥተው ከጎዳና ጣሉት.። (በነገራችን ላይ በባእድ

አምልኮ ምክንያት ህጻናትን አውጥቶ መጣል በናይጄሪያ የተለመደ ነው)  በዚህ ምክንያት፤ የጭካኔ ውሳኔ ተወስኖበት  ከሞቀ ቤት ወጥቶ የተጣለው ይህ ህጻን  ቤተሰቦቹ እንዳሰቡት ቶሎ የሚሞት አልሆነም

...... ከእናቱ እቅፍ ተነጥቆ እራሱን ባገኘበት  አንዲት መንደር ውስጥ በትናንሽ እግሮቹ ከወዲያ ወዲህ እየባዘነ ያገኘውን ለቃቅሞ እየበላ .. በወደቀበት ተኝቶ እየተነሳ ከሩቅ የታሰበለትን በጎ ነገር ያወቀ

ይመስል ሞትን እንቢ ብሎ ....የሌሊቱ  ውርጭና የቀኑ  ሃሩር እየተፈራረቀበት፣ በጽናት ቢቆይም  8ኛው ወር ላይ ግን ለሞት እጁን የሰጠ መሰለ ..
እነዚያ ወዳላሰበበት የመሩት ሰዎች የሚወረውሩለትን ወደ አፉ እንዲያደርግ የሚረዱት እግሮቹ ረሃብ አዛላቸው ..እናም አንድ ሌሊት ከተኛበት ሜዳ ላይ መነሳት እንዳቃተው ቀረ .........በዚህ ቅጽበት

..Anja Ringgren በምትባል በጎ አድራጊ ተመስለው የፈጣሪ እጆች ወደሱ ቀረቡ፤ በሆላንዳዊትዋ በጎ አድራጎት ሰራተኛ ከወደቀበት ቦታ ተገኝቶ ሲነሳ የጎድን አጥንቶቹ የሚቆጠሩ፣ ከህይወት ይልቅ ለሞት

የቀረበ በፓራሳይት የተጎዳ በረሃብ የደቀቀ ... እጅግ አሳዛኝ ህጻን ነበር፡፡ ይህች መልካም ሴት ከወደቀበት አንስታ፣ አዲስ ህይወትና አዲስ ስም ሰጠችው፡፡እናም የሞት አፋፍ ላይ ላይ ወዳለው ምስኪን ህጻን

ተጠግታም...
“ከዛሬ ጀምሮ ስምህ ተስፋ (HOPE) ይባላል “ .. ስትል አንሾካሾከችለት፡፡
***
አሁን ያ ሁሉ አልፏል .. HOPE በአንድ ወቅት ከሞት ጋር ፊት ለፊት ተገናኝቶ የሚያውቅ አይመስልም .... በአካሉ በርትቶ ደስ የሚል ቆንጅዬ ልጅ ሆኖ፣ በበጎ አድራጊዋ Anja Ringgren

በሚመራው የበጎ አድራጎት ድርጅት ውስጥ ከሚያድጉ ህጻናት ጋር እየኖረ ነው፡፡....
ከተስፋ በተጨማሪ፤ በተመሳሳይ ሌሎች ህጻናትን ከወደቁበት አንስታ ያሳደገችው በጎ አድራጊዋ Anja Ringgren፤ እነዚህ በወላጆቻቸው ተገፍተው የተጣሉ ህጻናት ከየት እንደመጡ፣ ወላጆቻቸው እነማን

እንደሆኑ ሊያውቁ ይገባል ብላ ታምናለችና. .. በቅርቡ በህጻንነት እድሜው አውጥተው የጣሉትን የተስፋን ወላጆች አፈላልጋ ነበር። በአንድነት ተስማምተው ልጃቸውን የጣሉት ባልና ሚስት ትዳራቸው ፈርሶ

በመለያየታቸው ምክንያት እናትየውን ማግኘት ባይቻልም፣ ከአባቱ ጋር እንዲገናኝና አባቱ እሱ መሆኑን እንዲያውቅ  አድርጋው ነበር። HOPE አባቱን ካገኘና አብሮ ፎቶ ከተነሳ በኋላ፣ ከወደቀበት ወዳነሳችው አሳዳጊ

እናቱ ቤት ተመልሷል።
እዚህ ላይ ግን በጭካኔ አውጥቶ የጣለው አባት፣ ያለሀፍረት ልጁን ለማግኘት መፈለጉ ለብዙዎች አስገርሟል።
***
ቅን ልብና መልካም አስተሳሰብ ካለ ተአምር መስራት ይቻላል፡፡

Read 1517 times