Saturday, 23 December 2023 20:47

የናሳ የጠፈር ተመራማሪዉ ብርሃኑ ቡልቻ (ዶ/ር) የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን ጎበኙ።

Written by 
Rate this item
(0 votes)

በጉብኝቱ ወቅት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ኢንጅነር) ስለኢንስቲትዩቱ ሥራዎች ገለጻ አድርገዋል፡፡ በውይይቱ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂን ለማልማት በኢንስቲትዩቱ የሚሰሩ የምርምር ተግባራት ለሀገር የሚበጁ መሆናቸውን እንደተገነዘቡ ተመራማሪዉ ተናግረዋል።
ሳይንቲስቱ የሰዉሰራሽ አስተዉሎት ቴክኖሎጂ ለሰዉ ልጅ የሚያበረክተውን ሚና እንዲሁም በጠፈር ምርምር የቴክኖሎጂዉ አበርክቶ ጉልህ መሆኑን ገልፀዋል።
የሰዉሰራሽ አስተዉሎት ቴክኖሎጂ ቸግር ፈቺ የምርምር ዘርፍ በመሆኑ ወጣቶቸና በውጪ የሚኖሩ የዲያስፖራ አባላት በንቃት አንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል።
ብርሃኑ ቡልቻ (ዶ/ር) በጨረቃ ላይ ዉሃ መኖር አለመኖሩን የሚመረምር መሳሪያ የፈጠሩ የናሳ ተመራማሪ ናቸዉ።

Read 1419 times