Saturday, 16 December 2023 20:41

የትምሀርት ባለሙያው ዶ/ር አክሊሉ ሀብቴ ምስጋና ቀረበላቸው

Written by 
Rate this item
(0 votes)

እውቁ የትምህርት ባለሙያና የ95 ዓመት የእድሜ ባለፀጋው ዶ/ር አክሊሉ ሀብቴ ምስጋና ቀረበላቸው፡፡ የምስጋናና የእውቅና መርሃ ግብሩ
ባለፈው ማክሰኞ ታህሳስ 2 ቀን 2016 ዓ.ም ጦር ሀይሎች አካባቢ በሚገኘው “ሊባዊ ኢንተርናሽና” ት/ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥየተካሄደ ሲሆን የምስጋና መርሃ ግብሩበለባዊ አለም አቀፍ ት/ቤትና በተወዳጅ ሚዲያና ኮሚኒኬሽን አማካኝነት የተሰናዳ ነው፡፡
በእለቱ ልዩ ልዩ ኪነጥበባዊ መሰናዶዎች የቀረቡ ሲሆን ዶክተር አክሊሉ በስፍራው ተገኝተው ለለባዊ ት/ቤት መምህራንናተማሪዎች ልምዳቸውን በማካፈል እውቀትና ልምድ እንዲቀስሙ አድርገዋል፡፡ ዶ/ር አክሊሉ ሀብቴ በሀገራችን ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ ሲጀመር ከመጀመሪያዎቹ ምሩቃን
መካከል አንዱ ሲሆኑ ዩኒቨርስቲውንም በፕሬዚዳንትነትና በመምህርነት አገልግለዋል፡፡ ዶክተሩ በሀገራችን የትምህር ዘርፍ ላይ የጎላ ሚና ከማከናወናቸውም በተጨማሪ በአለም ባንክ ውስጥም በትምህርት ዘርፍ ላይ ያገለገሉና የቀዳማዊ ሀይስላሴ ዩኒቨርስቲን(የአሁኑን የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲን) ታሪክ በ600 ገፅ በመጽሀፍ በማሳተምና ታሪክ በመሰነድ ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል፡፡
 እኒህ የ95 ዓመት የእድሜ ባለፀጋ ለረጅም ዓመታት መኖሪያቸውን በሀገረ አሜሪካ ያደረጉ ሲሆን አልፎ አልፎ ወደ ሃገራቸው ኢትዮጵያ ብቅ እያሉ
ይመለሳሉም ተብሏል፡፡ የማክሰኞ እለቱ የምስጋናና የእውቅና መርሃ ግብርም ከአሜሪካ ተመልሰው ሀገራቸው በነበሩበትአጋጣሚ የተሰናዳና በአካል የታደሙበት ነውም ተብሏል፡፡ በእለቱ በርካታ እንግዶች የለባዊ እንተርናሽናል አካዳሚ ሀላፊዎች ተማሪዎችና መምህራን በታደሙበትዶ/ር አክሊሉ ሀብቴ ምስጋናና እውቅና ተሰጥቷቸው ተመስግነዋል፡፡

Read 1039 times