Saturday, 16 December 2023 20:38

በ17ኛው የዓለም አትሌቲክስ ኮከቦች ሽልማት

Written by  ግሩም ሰይፉ
Rate this item
(0 votes)

 ~የዓለም ኮከቦች ብዛት ከ2 ወደ 6 አድጓል
           ~ማራቶንን በሴቶች ከ2 ሰዓት 10 ደቂቃዎች በታች መግባት ይቻላል?
           ~በዓመት ከ54 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ከ72 ሚሊዮን ዶላር በላይ ወጭ
           ~ትግስት 7ኛውን የዓለም ኮከብ አትሌት ሽልማት ወደ ኢትዮጵያ አምጥታለች


        በ2023 የአለም አትወጭበበስ ሽልማት አዳዲስ ነገሮች ተከስተዋል። የዓመቱ ኮከብ ሽልማቶች በአዲስ አሠራርና የሽልማት ዘርፎች ተሰጥተዋል። ባለፉት 16 የሽልማት ስነስርዓቶች የዓለም ኮከብ አትሌት ምርጫ ተካሂዶ የሚሸለሙት ከሁለቱም ፆታዎች አንድ አንድ አሸናፊዎች ነበሩ። ዘንድሮ ግን በዓለም አትሌቲክስ ማህበር አሰራሩ ተቀይሮ 3 ወንድና 3 ሴት አትሌቶች ለኮከብነት ሽልማቱ በቅተዋል። በ17ኛው የዓለም ኮ ከብ አ ትሌት ሽልማት 6 የዓለም ኮከብ አትሌቶች አሸናፊ ሆነው በ3 የተለያዩ ዘርፎች የተሸለሙበት ሆኗል። ከ2 ወደ 6 የዓለም ኮከብአትሌቶች የዓለም አትሌቲክስ ማህበር ፕሬዚዳንት ሴባስቲያን ኮው እንደገለፁት የኮከብ አትሌት ሽልማቶችን ብዛት ለመጨመር የተወሠነው ከአትሌቲክስ ባለድርሻ የቀረቡ አስተያየቶችን በመንተራስ ነው። በ2023 የአለም አትሌቲክስ ሽልማት አሸናፊዎች ምርጫ ፍትሃዊ እና ግልፅ የሆነ የድምጽ አሰጣጥ ሂደት የተከተለ እንደነበርም ፕሬዚዳንቱ አብራርተዋል። የአለም አትሌቲክስ ምክርቤት ፣ የዓለም አትሌቲክስ ማህበረሰብና ስፖርት አፍቃሪዎችበማህበራዊ ሚዲያና በኦፌሲያላዊ መንገድ ድምፅ ሰጥተዋል። ይህም የዓለም ኮከቦቹን ለመምረጥ ዋንኛው ግብአት መሆኑ ተገልጿል። ሽልማቶች በአዳዲስ ዘርፎች
መበርከታቸው በሁሉም የስፖርት አይነት ላይ መነቃቃት እንደሚፈጥር ታምኖበታል። በ2023 የውድድር ዘመን ላይ የዓለም አትሌቲክስ ማህበር በዓለምአቀፍ ውድድሮች ክንውኑ ከፍተኛ ደረጃ ያሳየበት ነ በር። በ የስፖርት መ ደቡ የዓለማችን ምርጥ አትሌቶች ዓመቱንሙሉ አስደናቂ ትጋት፣ ችሎታ እና ጽናት አሳይተዋል። ሪከርዶችን ከመስበር ባለፈ በልዮ የውጤት ክብረወሰንና ስኬታቸውበታላቅነት የሚመሠገኑ ሆነዋል። ለአዳዲስ ትውልዶች የብርታት ምንጭ የሚሆኑ ታሪኮች ተሰርተዋል ። ለሽልማት የበቁት 6 ኮከብ አትሌቶች በውድድር ዘመኑ 7 የዓለምሪከርዶችን ያስመዘገቡ፤ በዳይመንድ ሊግና ሌሎች ዓለም አቀፍ ውድድሮች ተደጋጋሚ ድል ያስመዘገቡ ፤ በትልልቅ ማራቶኖች ያሸነፉና በዓለም ሻምፒዮና ሜዳልያዎችንየተጎናፀፉ ናቸው። የዓለም አትሌቲክስ ማህበር በሞናኮ ባካሄደው ስነስርዓት በስፖርቱ አለም ላይ ትልቅ ተፅእኖ ያላቸውን ሁሉ ለ ማክበርና ለ መሸለም በ ቅቷል ።
አትሌቲክስ የኦሎምፒክ አብይ ስፖርት ሆኖ እንደሚቀጥልም ያመለከተበት ሆኗል። የአለም አትሌቲክስ ማህበር አሸናፊዎችየተመረጡት በገለልተኛና ግልጽ በሆነ የድምጽ አሰጣጥ ስርዓት መሆኑን ያስታወቀ ሲሆን በአትሌቲክስ መስክ የላቀ ብቃትን ለማድነቅ እና በስፖርቱ አለም ላይ ጉልህ
አስተዋፅኦ ላበረከቱ አትሌቶች ክብር ለመስጠት ስነስርዓቱን እነደሚያዘጋጀውም ገልጿል። በዓለም አትሌቲክስ ትጋትን፣ ጽናትን እና ስኬትን ያስመዘገቡትን ለማክበር እና እውቅና ለመስጠት አመቺ መድረክ ሆኖለታል። በ2023 እነማን ኮከቦች ሆኑ የዓለም ኮከብ አትሌቶች ምርጫው
ሲካሄድ በ3 የተለያዩ የሽልማት ዘርፎች የተደረገ ሲሆን፤ በሁለቱም ፆታዎች በትራክ፤ በጎዳና ሩጫ እና በሜዳ ላይ ስፖርቶችአሸናፊዎቹ ተመርጠዋል። በትራክ የዓለም ኮከብ አትሌት ሆነው የተሸለሙት አሜሪካዊው ኖህ ናይልስና ኬንያዊቷ ፌዝ ኪ ፕየገን ና ቸው። የ ዓለም ማ ራቶን
ሪከርድን በሁለቱም ፆታዎች በቺካጎ እና በበርሊን ማራቶኖች የሰበሩት የኬንያው ኬልቪን ኬፕቱምና የኢትዮጵያዋ ትግስት አሰፋ በጎዳና ላይ ሩጫ የዓለም ኮከብ አትሌት ተብለዋል። በሜዳ ላይ ስፖርቶች የዓለም ኮከብ አትሌት የተባሉት ደግሞ ስዊድናዊው የምርኩዝ ዘላይ ተወዳዳሪ ሞንዶ ዱፕላንቲስና ቬንዝዋላዊቷ ሥሉስ ዘላይ ዮልሚ ሮጃስ ናቸው። በዓመቱ አዲስ ወጣት አትሌት ሽልማት ላይ የኬንያዎቹ አትሌቶች ሲቀናቸው
የ3ሺ መሠናክል ተወዳዳሪ የሆነችው ፌዝ ቼሮቴየችና 800 ሜ ሯጩ ኢማኑኤል ዋን ዮኒ ናቸው። ለተሰንበት ግደይ በዓመቱ ምርጥ ስፖርታዊ ጨዋነት ለማሸነፍ ስትበቃ፤ የስዊዘርላንዱ ላውንተን ሚውሊ የዓመቱ ኮከብ አሠልጣኝ፤ የቶጎ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት የዓመቱ ኮከብ ሴትእንዲሁም ስ ዊድናዊ ፎ ቶግራፈር ማ ቲያ አዝቦት በምርጥ የአትሌቲክስ ፎቶግራፍ ተሸላሚዎች ሆነዋል። የአውስትራሊያ ፌዴሬሽን በዓመቱ ኮከብ አስተዳደር፤
የስድስቱ ትልልቅ ማራቶኖች አካሂያጅ አቦት ማራቶን ሜጀርስ Abbott Marathon Majors የፕሬዘደንሺያል አዋርድ በሽልማት ስነስርዓቱ ላይ አልተገኘችም። ዋና አሰልጣኟ ሆኖ የሚሰራውን ገመዶ ደደፎ ጠይቀነው አትሌት ትግስት በህክምና ላይ ስለምትገኝ ወደ ሞናኮመጎዝ አለመቻላቸውን ነው የገለፀው። የዓለም አትሌቲክስ ማህበር የሽልማት ዘርፉን በማስፋት የኮከብ አትሌት ሽልማቱን ለመስጠት መወሠኑን ከዓለማችን ምርጥ
የማራቶን አሰልጣኞች አንዱ የሆነው ገመዶ ደደፎ ተናግሯል። አሠልጣኝ ገመዶ ደደፎ በዴደሞና አትሌቲክስ ክለብ ማናጀር ሆነውከሚሠሩት ጂያኒ ጋር በመቀናጀት ከፍተኛ ውጤት በዓለም አትሌቲክስ ማስመዝገብችሏል። በዚህ ዓለምአቀፍ ክለብ ውስጥየዓለም ሻምፒዮኗ አማኔ በሬሶ፤ የቫለንሺያ
ማራቶን ያሸነፈችው ወርቅነሽ ደገፋና የኒውዮርክ ማራቶንን ያሸነፈው ታምራት ቶላ ይገኛሉ። ትግስት አሠፋ የዓለም ማራቶን ሪከርድን ያስመዘገበች ሠሞን መነጋገሪያ ከሆነችባቸው ጉዳዮች አንዱ ከ2 ሰዓት 10 ደቂቃዎች በታች መግባት ትችላለች የሚለው ነው። ቢቢሲ በጉዳዮዙርያ ባጠናቀረው ዘገባ ላይ “ የሚቻል ይመስለኛል።በእርግጥ ሪከርዴን መስበር እፈልጋለሁ። በጣም ተፎካካሪ ስለሆንኩኝ በተሻለ ስልጠናና ዝግጅት የማሻሽለው ነው ። በበርሊን ማራቶን ሳሸንፍ ብዙም ድካም አልተሠማኝም ነበር።በፈጠነ ሰዓት ለመግባት የምችልበት ጉልበት ነበረኝ።” ብላለች። በርካታ የአትሌቲክስ
ባለሙያዎች የትግስት ሪከርድን ለማሻሻል ጊዜ እንደሚወስድ ተናግረዋል። የማራቶን ርቀቱን ከ2:14፤ ከ2:13 እና ከ2:12 በታች በመግባት የመጀመርያዋ አትሌት የሆነችው ትግስት የነበረውን የማራቶን ሪከርድ በ2 ደቂቃዎች 14 ሰከንዶች ማሻሻሏን ከ40 ዓመት በኋላ የታየ ድንቅ ብቃት ነው ብለው አድንቀውላታል። አሰልጣኝ ገመዶ ደደፎ በበኩሉ “ሴቶች አስደናቂ እድገት እያሳዩ ነው። ብዙ ጫና ነበረባቸው ፤ ምቹ ባልሆኑሁኔታዎች ውስጥ እየሮጡ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘግባሉ። ከወንዶች የተለየ ፅናትን የሚጠይቃቸው ቢ ሆንም ሴ ቶች በ ጣምጠንካራና ቁርጠኞች በመሆናቸው ከ2:10 በታችን በማራቶን ማሣካት እንደሚችሉ አስባለሁ” በማለት ለቢቢሲ በሰጠው አስተያየት ተናግሯል ።
  የአትሌቲክስ አገር ሞናኮና ልዑል አልበርት የሽልማት ስነስርዓቱ ሞናኮ በሚገኘው ቤተመንግስት ተካሂዷል። ሞናኮ የስፖርት አገር ተብላ ትታወቃለች። የዓለም አትሌቲክስ ማህበር ዋና ፅህፈት ቤት በዚያው ነው። ዋና ከተማዋ ሞናኮ በአትሌቲክስ ዳይመንድ ሊግና ሌሎች ዓለምአቀፍ ውድድሮች
መናኸርያነት የምትጠቀስ ስትሆን፤ የዓለም ታላላቅ አትሌቶች ይኖሩባታል ። በሞተር ስፖርት የግራንድ ፕሪ፤ በሜዳ ቴኒስ የሞንቴካርሎ ማስተርስ ፤ በብስክሌት ቱር ደፍራንስ፤ በእግር ኳስና ራግቢ ስፖርቶች ከፍተኛ እንቅስቃሴ ይደረጋል።የሞናኮው ልዑል አልበርት ጋልማርዲበሚለው ስማቸው ሞናኮን በመወከልበአራት የክረምት ኦሎምፒኮችተወዳድረዋል። አሁን በ66 ዓመታቸውላይ የሚገኙት ልዑል አልበርት ለስፖርትበተለይ ለአትሌቲክስ የበላይ ጠባቂ ሆነውከፍተኛ ድጋፍ የሚያደርጉ ናቸው። የዓለም አትሌቲክስ ገቢና ወጭ የዓለም አትሌቲክስ ማህበር ዕድሜ ያለው አባል አገራት ፌዴሬሽንን የሚያስተዳድር ዓለም አቀፍ የስስተቋም ነው። ዓመታዊው ገቢ በ2022 እኤአ ላይ ከ54 ሚሊዮን ዶላር በላይ የተመዘገበ ሲሆን ከ46ሚሊዮን ዶላር በላይ ተቀማጭ ገንዘብ ያስመዘገበ ነው። ከቴሌቪዥን የስርጭት መብትና ከስፖንሰርሺፕ ከ48.7 ሚሊዮንዶላር በላይ በየዓመቱ ይሰበስባል። በአንድ
የውድድር ዘመን ውስጥ ከትልልቆቹ የዓለም ሻምፒዮንሺፖች ባሻገር ከ200 በላይ አህጉራትን የሚያካልሉ የዳይመንድ ሊግናሌሎች ዓ ለም አ ትሌቲክስ ው ድድሮችን በበላይነት ያስተዳድራል። ዓለም አቀፍ ውድድሮችን በማዘጋጀት በየዓመቱ ከ72 ሚሊየን ዶላር በላይ ወጭ ያደርጋል።በሚቀጥሉት 10 ዓመታት ለማሳካትበነደፈው ስትራቴጂ መሠረት የዓለም አትሌቲክስ የሚዲያ ሽፋን ከ10 ቢሊዮን በላይ ተከታታይ እንዲኖረውና በሁሉምየማህበራዊ ሚዲያ አውታሮች እስከ 10 ሚሊዮን ቀላይ ተከታዮችን ለማፍራት አቅዷል።

Read 502 times