Wednesday, 01 November 2023 00:00

የኢትዮጵያ ኤልክትሪካል መሃንዲሶች ማሀበር 25ኛ አመቱን በታላቅ ድምቀት ያከብራል

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ከ100 ሺ በላይ ጎብኝዎች የሚታደሙበት ሃይል ቁጠባ አረንጓዴ አፍሪካ የተሰኘ የኤሌክትሪሲቲ ኤግዚብሽን ሊካሄድ ነው።
3A ኤቨንትስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪካል መሃንዲሶች ማህበር ጋር በመተባበር  " ሃይል ቁጠባ አረንጓዴ አፍሪካ " በሚል መሪ ቃል 4ኛውን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪሲቲ ኤግዚብሽን ከየካቲት 13 እስከ የካቲት 16/2016 ዓ.ም ድረስ በታላቅ ድምቀት በሚልንየም አዳራሽ ለማካሄድ በዛሬው ዕለት በሰጡት መግለጫ አስታወቁ።
በተጨማሪም የኢትዮጵያ ኤልክትሪካል መሃንዲሶች ማሀበር 25ኛ አመቱን በታላቅ ድምቀት ያከብራል ተብሏል።
በኤግዚቢሽኑ ከ 300 በላይ የሚሆኑ በሃገር ውስጥ ያሉና ከውጭ የሚመጡ በኤሌክትሪሲቲ ዘርፍ
፣ላይ የተሰማሩ አምራቾች አስመጪዎችና አቅራቢዎች  ከ100,000 በላይ የሚሆኑ ጎብኚዎች የሚሳተፉ ሲሆን በዝግጅቱ ላይ የተለያዩ ሲምፖዚየሞች፣ ሴሚናሮች እና ጥናታዊ ፅሁፎች ይቀርቡበታል ተብሏል።
የ3A ኢቨንትስ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አብዱልፈታህ  አሊ እንደገለጹት በኤግዚቢሽኑ ላይ የሚሳተፉ ድርጅቶች ምርትና አገልግሎታቸውን የሚያስተዋውቁበት የሚያሳዩበት፣ በዘርፉ የካበተ ልምድ ያላቸውን መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን በማግኘት  የልምድ ልውውጥ ለማድረግ፤ ለቀጣይ ስራ አጋርነት ለመፍጠር እንደሚያስችል እና እንደሚረዳ ገልጸዋል።


Read 565 times