Saturday, 14 October 2023 00:00

Hygiene….እንዴት ይጠበቃል?

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(0 votes)

Hygiene… በእጥበት የሚገኝ ንጽህናን፣
አንዳንድ መገልገያ መሳሪያዎችን በፈላ ውሀ በመቀቀል የሚገኝ ንጽህናን፤
አካባቢን በማጽዳት የሚገኝ ንጽህናን፤
ከአልባሳት…መኖሪያ አካባቢዎች…የስራ አካባቢዎች …የሚኖር ጽዳት፤
የአካል…የአመጋገብ…ወዘተ ንጽህናን የሚመለከት መሆኑን የቃላት መፍቺያ መዝገበ ቃላት ይናገራሉ፡፡
ሰዎች በእጅ አለ መታጠብ ምክንያት በንክኪ ሊመጣባቸው የሚችለውን የጤና ጉድለት በሚመለከት በቅርብ ጊዜ ተከስቶ በነበረው የወረርሽኝ በሽታ ማለትም በኮሮና ቫይረስ ጊዜ በአለም ዙሪያ በዘመቻ መልክ እውቀቱ እንዲንሰራፋ መደረጉ አይዘነጋም፡፡ ሌላው ተመሳሳይ የሆነው ነገር ሀይጂን ነው፡፡ እነዚህን ቁልፍ የጤና መሰረቶች በዚህ እትም ለንባብ ብለና ቸዋል፡፡ ለጉዳዩ ማብራሪያቸውን የሰጡን ዶ/ር ገላኒ ሌሊሳ የጽንስና ማህጸን ሐኪም ሲሆን በአሁኑ ጊዜም በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል የመካንነትና ሌሎች ተያያዥ የስነተዋልዶ ጤና ችግሮች ዙሪያ እስፔሻሊስት ለመሆን በማጥናት ላይ ናቸው፡፡
ዶ/ር ገላኔ እንዳብራሩት በአሁኑ ጊዜ ንጽህናን መጠበቅ ለጤና ያለውን ጠቀሜታ በሚመ ለከት ምንም የሚያነጋግር ነገር አይደለም፡፡ በግልጽ የሚታወቅና በዚያ ምክንያት ሊመጡ የሚችሉ የጤና ጉዳቶችም የታወቁ ናቸው ፡፡ እጅን መታጠብን በተመለከተ በሆስፒታሎችና በሌሎች ቦታዎችም ቢሆን እጅ ላይ ያሉ ለበሽታ ሊያጋልጡ የሚችሉ ተሀዋስያንን ለመቀነስ ቢቻል ደግሞ ለማጥፋት የሚደረግ ጥረት ነው፡፡ በአጠቃላይ ንጽህና ሲባል ደግሞ ከእጅም ባለፈ አካባቢንና ሰውነትን ሁሉንም ነገሮች የሚመለከት ስለሆነ ምክንያታዊ የሆነ ሁሉም ሰው የሚቀበለው ነው፡፡
የእጅ መታጠብን ወይንም የሀይጂንን ሁኔታ በተለይም በማዋለጃ አካባቢዎች ያለውን ሁኔታ የታዘበ አንድ ባለሙያ በ19ኛው ክፍለዘመን አስፈላጊነቱን ተመራምሮ ካገኘው እውነታ በመ ነሳት በሚያቀርብበት ጊዜ ምንም ተቀባይነትን አላገኘም ነበር፡፡ ሁኔታውም ወላድ ሴቶች በኢንፌክሽን የሚያዙበትና የከፋ አደጋ የሚከሰትበት አጋጣሚ የበዛ ስለነበር ለምንድነው ብሎ ጥናት ያደረገ ባለሙያ ነበር፡፡ በጊዜው ሴት አዋላጆች ያዋለዱአቸው እናቶች ብዙም የማይጎዱ ሲሆን ወንድ ሐኪሞች ያዋለዱአቸው ግን ለህመምና ለሞት ጭምር ይጋለጡ ነበር፡፡ ይህ ነገር መነሻው ምንድው ብሎ ከተለያዩ አቅጣጫዎች ከተመለከተ በሁዋላ መጨረሻው የእጅ መታጠብ ጉድለት መሆኑን በመረዳቱ ይፋ አድርጎት ነበር፡፡ ነገር ግን በጊዜው ማንም ትክክል ነው ብሎ የተቀበለ አልነበረም፡፡ ከጥቂት አስርት አመታት በሁዋላ ግን ሁኔታው እንደገና አንሰራርቶ ሌሎች ባለሙያዎች በጉዳዩ ተነጋግረውና ሁኔታዎችን ታዝበው በደረሱበት የዳሰሳ ጥናት እውነትቱን ሲመሰክሩ በዚያን ጊዜ በጥናት የቀረበው ነገር እውነትነት ስላለው ትክክል መሆኑ ተረጋግጦ እጅን አለመታጠብ ከታማሚ ወደታ ማሚ፤ ከታካሚ ወደ አካሚ፤ከአካሚ ወደታካሚ ኢንፌክሽን እንዲተላለፍ የሚያደርግ በመሆኑ ትኩ ረት እንዲሰጠው ተደረገ፡፡ ቁልፍ የሆነው የኢንፌክሽን በሽታ የሚነሳው ከእጅ መታጠብ ብቻም ሳይሆን ከህምና መገልገያዎች ንጽህን፤ የተቋማት ንጽህና አለመጠበቅ ጭምር መሆኑ ስለተረጋገጠ በስፋት በመመሪያ በተደገፈ መልኩ ተግባራዊ መደረጉ የቀጠለ ምንም አነጋጋሪ ያልሆነ አስፈላጊ ነገር ነው፡፡  
የእጅ መታጠብና የሀይጂን ጉዳይ በአለም አቀፍ ደረጃ በአመት አንድ ጊዜ በተለያዩ ቀናት የሚከበር ሲሆን ነገር ግን ሁኔታውን ለማስታወስ፤ንቃተ ህሊናን ለማዳበር፤ጎልቶ እንዲታ ሰብ ለማድረግ እንጂ በአመት አንድ ጊዜ በሚደረግ ስብሰባ ፤ወይንም የግንዛቤ ማስጨበጫ በመነሳት ለአንድ ቀን የሚተገበር ሳይሆን በሁሉም ሰው ዘንድ በየእለቱ መተግር ያለበት ነው፡፡ ሀይጂን በአጠቃላይ የሁሉንም ነገር ጽዳት የሚመለከት ነው፡፡
ለምሳሌም፡-
ህጻን ሆነን ጀምሮ እንድንተገብረው የተማርነው የሰውነት፤የጸጉር፤የጥፍር፤የልብስ የመሳሰሉት ሁሉ ንጽህን መጠበቅ ሀይጂን በሚለው ውስጥ ይካተታል፡፡
ከላይ ከተገለጸው በተጨማሪ ሀይጂን ሲባል ከግለሰብ አካልና አልባሳት ወይንም መመገቢያ እቃዎች ውጭ የመኖሪያ አካባቢዎችን፤የስራ አካባቢዎችን፤የምናልፍ የምናገድምባቸውን መንገዶች፤ለስራ የምንገለገልባቸውን እቃዎች ሁሉ የሚመለከት ይሆናል፡፡
አንዳንድ ጊዜ ሰዎች ከግቢያቸው ውጪ ስለጽዳት ማሰብ ሲሳናቸው ይታያል፡፡ ከግቢ መልስ ወደ ውስጥ ብቻ ጽዳትን በመጠበቅ ሀይጂን ተሟልቷል ወይንም የጤና ሁኔታ ችግር አይደርስም ማለት አይቻልም፡፡ ስለዚህ ሀይጂንን ለመጠበቅ እዚህ ቀረሽ ሳይባል ከሰው ጋር ንክኪ ያላቸ ውን ሁሉንም ነገሮች እንደ ውሻ እና ድመት ያሉ የቤት እንስሳትም ቢኖሩ ማጽዳት ተገቢ ይሆናል፡፡
እጅ መታጠብ ሲባል ደግሞ በመጠኑ ለየት ያለ ነገር ነው፡፡
በእጃችን ሁሉንም ነገር እናደር ጋለን፡፡
በእጃችን ሰውነታችንን እንነካካለን፤
መጸዳጃ ቤት እንገባለን፤
በእጃችን ምግብ እናበስላለን፤
በእጃችን እንመገብበታለን፤
በእጃችን ሰዎችን እንነካለን፤
በእጃችን ልጆችን በመንከባከብ ደረጃ ሁሉንም እናደርጋለን፤
በእጃችን ….በቤታችን፤በመኖሪያችን ቤታችን…. በስራ ቦታችን ባጠቃላይም በምንንቀሳ ቀስባቸው አካባቢዎች ሁሉ ከሰዎች ጋር እንገናኛለን… እንነካካለን….ወዘተ፡፡
ስለዚህ እጃችን ካልታጠበ ከሌላው አካላችን በተለየ ወይንም በበለጠ ሁኔታ ጎጂ የሆኑ ተሀዋስያንን ስለሚያስተላልፍ ባላሰለሰ መልኩ መታጠብ መጽዳት ይገባዋል፡፡ የእጅ ሀይጂን በተለይም በጤና ተቋማት ውስጥ በጣም ወሳኝ ነገር ነው ብለዋል ዶ/ር ገላኔ ሌሊሳ፡፡
የእጅ መታጠብን በተለይም ከህክምና ባለሙያው ጋር አያይዘን ስንመለከተው አንድ ግር የሚያሰኝ ነገር ያለ ይመስላል፡፡ ይሄውም የህክምና ባለሙያው የእጅ ጉዋንት ሳያደርግ ታካሚውን አይነካም የሚል እሳቤ አለ፡፡ ስለዚህ ሐኪሙ እጁን ቢታጠብ ባይታጠብ ምን ለውጥ ያመጣል የሚል አንዳንድ አስተያየት ይሰጣል፡፡ ለዚህም ዶ/ር ገላኔ ሲመልሱ
‹‹… ምንም እንኩዋን የህክምና ባለሙያ ታካሚውን የሚያክመው ጉዋንት አድርጎ ነው ቢባልም ወይንም ከጉዋንት ውጭ ታካሚን አይነካም ቢባልም እጅን መታጠብን ግን ወሳኝ የሚያደርጉት ነገሮች አሉ፡፡
‹‹…ምንም እንኩዋን በተቀቀሉ እና ከተሀዋስያን በጸዱ የህክምና መሳሪያዎች አገልግሎት እንሰጣለን….እኛም የምንነካው እነዚህን የተቀቀሉ…የጸዱ መሳሪያዎች ነው ብንልም እጅን መታጠብን ግን የሚተካው ነገር የለም፡፡ ለምሳሌ…ወደቀዶ ጥገና ክፍል ስንገባ ከላይ የለበስውን ልብስ ቀይረን በደንብ የጸዳ እና ተሀዋሲ የሌለው የህክምና ልብስ ለብሰን ነው ወደ ታማሚው የምንገባው፡፡ ነገር ግን የእጅ መታጠብ በአካባቢው ያለውን መበከል በሙሉ ለማስወገድ እና በመነካካት የሚመጣውን ነገር ለመቀነስ ባጠቃላይም ስጋት እንዳይኖር ተብሎ ግላብ ከመደ ረጉ አስቀድሞ የሚደረግ ዝግጅት ነው፡፡
ከላይ ከተጠቀሰው ውጭ የህክምና ባለሙያ ከእጅ ጉዋንት ውጭ ከታካሚው ጋር ንክኪ የለውም የሚባለውም ነገር ሁልጊዜ ትክክል ነው የሚባል አይደለም፡፡ አንዳንድ ምርመ ራዎች በሚደረጉበት ጊዜ የእጅ ጉዋንት ላይደረግ ይችላል፡፡ ለምሳሌ በቀላሉ የደም ማነስ ምልክት በአይን ላይ አለ ወይንስ የለም….አፍ ላይ የድርቀት ምልክት አለ ወይንስ የለም….የመሳሰሉትን ምርመራዎች ለማድረግ ብዙ ጊዜ ጉዋንት ቢደረግ እንኩዋን የተቀቀለ ሳይሆን ዝም ብሎ ንጹህ ጉዋንት ሊደረግ ይችላል፡፡ ስለዚህ ሐኪም ምንጊዜም አንድ ታካ ሚን አይቶ ሌላኛው ሲተካ እጅን መታጠብ ተገቢ መሆኑን ያምናል፡፡ ደግሞም ያደርገ ዋልም፡፡
ወደ ጽንስና ማህጸን ታካሚዎችም ሆነ ወደ ማንኛውም ታካሚ ሁኔታ ስንመለከት ከህክምና ተቋሙ ተገቢውን አገልግሎት አግኝተው ወደ ቤታቸው ሲመለሱ ለራሳቸውም ሆነ ለልጆ ቻቸው ሊያደርጉ የሚገባቸውን ጥንቃቄ በሚመለከት የሚሰጣቸው ምክር መኖሩንም ዶ/ር ገላኔ ሌሊሳ ገልጸዋል፡፡
‹‹…..ሀይጂን ሁል ጊዜ በየትም ስፍራ እንዲኖር ማድረግ የሁሉም ሰው የሁልጊዜ ኃላፊነት መሆኑ ለአፍታም መረሳት የለበትም፡፡››

Read 386 times