Sunday, 03 September 2023 21:19

ሰው ሆንኩኝ… ከዛስ?

Written by  ኪሩቤል ሳሙኤል
Rate this item
(2 votes)

 እንዲሁ የሰው ልጆችን ሳያቸው ያሳዝኑኛል፡፡ሲራመዱ ሳያቸው፣ ሲስቁ፣ ሲዋሹ፣ ሲያልባቸው፣ ሲቆጡ፣ ሲያጠኑ፣ ሲያስቡ፣ ሲጎርሩ፣ ሲተኙ፣ ሲጓጉ፣ ሲመሩ፣ ሲያድኑ፣ ሲገሉ… እንዲሁ እንዲሁ ሲያደርጉ ሳያቸው ያሳዝኑኛል፡፡ ሁሉም ገፅ ላይ ተስፋ ይታየኛል፡፡ ሁልጊዜም ቢሆን ሊሞሉት ያልቻሉት የህይወት ጥያቄ እንዳለባቸው እያወቁ ነው፣ ጠዋት ከእንቅልፋቸው የሚነቁት፤ ከዚያ  መልፋት ከዚያ ተመልሶ መተኛት ነው ቀጣዩ ተግባራቸው፡፡ ግን ለመሆኑ ይህ ሁሉ ልፋት የት ድረስ? እዚህ ድረስ የለፋንበት፣ ያሰብንበትና የተሰቃየንበት ህይወት መጨረሻው ትርፉ ምንድነው?  
እስካሁን ድረስ ሚስጥራትን መመስጠርን፣ በቃላትና በቀለማት ቅኔ በተፈጥሮ የተተረከልንን ጥበብ ለግላችን አደረግን፤ ገፋ ሲልም ማስተማርን ተክነነው ተጉዘናል፤ መጨረሻው ምን እንዲሆን …ማን ጎሽ እንዲለን?
ከሞት በኋላ ህይወት አለ ብለን የምድር ላይ ስሜቶቻችንን በመግደል ሰነበትን፣ በማህበረሰባችን ውስጥ በጎ የሚባሉትን ስራዎች በሙሉ የአቅማችንን ያህል ሰራን፣ እንደ ሰዉ አግብተን ወለድን፣ ንብረት አፈራን…በከበቡን ሰዎች በሙላ ተዳኝተን እንዳንወድቅ ራሳችንን እየዋሸነውም ቢሆን፣ መልካም ሰው መስለን ለመታየት ብዙ የማንነት ትግሎች ውስጥ ገብተን ሰነበትን… አሸነፍን…ከዛስ?
ይሄ ብቻ ባይሆንም ሰው መስለን ለመታየት፣ በሰው መንገድ ለመጓዝ የምድርን መልክ የምንችለው ድረስ ተመተምን፡፡ ከዛስ?
ከየት ጀምረን የት ነው መጨረሻችን? በቅዱስ መፃሕፍት እንደተነገረን፣ ከሞትን በኋላ ዘላለም በጥፋታችን ልክ መቃጠል ወይስ ዘላለም አጎንብሰን ፈጣሪን ማመስገን ነው እጣፈንታችን፡፡ እኔ ግን እላለሁ… በዘላለም ዳርቻ በአንደኛው ቅፅበት ውስጥ የሚያነደውም እኛን ማንደዱ ይሰለቸዋል…ተመስጋኙም አካል ቢሆን ከሚገባው በላይ ሲመሰገን በቃኝ የሚል ይመስለኛል፡፡ ምናልባት ግን የሰማነውና ያመነው ባይሆን መጨረሻችን ምን የሚሆን ይመስላችኋል?
ዛሬ ስለ ሰው ልጅ ማውራት እፈልጋለሁ። መፍቀዱን ሳያውቅ ከምድር የተደወረውና ሳይፈቅድ ከምድር ስለሚለየው የሰው ልጅ ማውራት እሻለሁ፡፡ በምድር ላይ እያለ የገዢነቱንና የተገዢነቱን  ሚስጥር አብረን እንድንመረምረው ወደድኩ፡፡  አዕምሮውን የተጠቀመውንና በሰው አዕምሮ ተቃኝቶ ማንነቱን በማሰስ ስለሚደክመው የሰው ልጅ ልትናገር ነፍሴ ናፍቃለች፡፡  
ከHomo neanderthalensis፣ Homo neanderthalensis፣ Homo sapiens፣ Homo erectus፣ Homo heidelbergensis፣ Piltdown Man፣ Australopithecus africanus፣ Paranthropus robustus፣ Paranthropus boisei፣ Homo habilis፣  Homo rudolfensis፣ Australopithecus afarensis፣ Homo ergaster፣ Australopithecus bahreghazal፣ ustralopithecus anamensis፣ Ardipithecus ramidus፣ Homo antecessor፣ Australopithecus garhi፣ Kenyanthropus platyops፣ Orrorin tugenensis፣ Ardipithecus kadabba፣ Sahelanthropus tchadensis፣ Homo floresiensis፣ Ardipithicus ramidus፣ Australopithecus sediba፣ Homo neanderthalensis፣ Homo naledi፣ Australopithecus deyiremeda፣ Homo floresiensis ነው የመጣነው ብዬ አላሰለቻችሁም፡፡
እንጀምር፡፡
ይህ ሁለት እግሮችና ሁለት እጆች ተሸክሞ በየመንገዳችሁ የሚሄደው ሰው የተባለ ፍጥረት፣ እንዴት ያለ አስገራሚ ፍጥረት እንደሆነ፣ በተለያዩ እውቀቶች ውስጥ እያሳለጥን አብረን እንድንመለከተው ልሞክር፡፡ የሰው ልጅ ፍጥረቱ የአጥንትና የስጋ ጥርቅም ብቻ እንዳልሆነ፣ አለማት ላይ ከተከሰቱ አስደናቂ ክስተቶች በመነሳት ከስጋዊ ልዕልናው በላይ አድርገነው እንመልከተው፡፡ የእውነት እኛ የሰው ልጆች ማንም ስለራሳችን ከሚነግረን በላይ ውስጣችን ተቀብሮ ያለውን ጥበብ ብንረዳው፣ ምን ያህል የአማልዕክቶችን ማንነት በየግላችን ይዘን ተቀምጠን እንደሆነ መረዳት እንችል ነበር፡፡
በመጀመሪያ የሰው ልጅ ከደረቁ አለም ብቻም ሳይሆን፣ በማይታዩ አለማት ላይ እውቀትን ከሰማያትና ከምድር ጥልቀት ውስጥ ሲመረምር እናውቃለን፡፡ ፈልፍሎ ካገኛቸው እውቀቶቹ መካከል አንደኛው የሳይኪክ ብቃት (psychic power) ነው፡፡ ይህም በሌላ አገላለፅ ስናየው የዚህ እውቀት ባለቤት የሆነ ሰው፣ ከተለመደው የተፈጥሮ ስርዓት ውጭ በመሆን ነጻ ፍቃዱንና አዕምሮውን ብቻ በመጠቀም፣ ለአማልክቶች ብቻ የተሰጠ የሚመስለውን ተዓምራዊ ተግባራትን ማድረግ ይችላል ማለት ነው፡፡  ከነዚህ የእውቀት አዝመራ ውስጥ የሰው ልጅ  መዝምዞ እንዲህ ያሉትን ጥበቦች ተማረ አስተማረም (ካሉት በጥቂቱ …) …Clairvoyance (በገሀዱ አለም የማይታዩ አለማትን፣ እንስሳትንና  የሙት መናፍስትን የመመልከት ጥበብ) ፣ Clairaudience (የማይታዩ መናፍስትን ድምፅ የማድመጫ ጥበብ) ፣ Clairsentience (የአንድን ሰው የበፊትንና የሚመጣውን ስሜታቸውን የመረዳት እውቀት) ፣ Claircognizance( አንድ ነገር ከመከሰቱ በፊት ቀድሞ የመረዳት ጥበብ) ፣Astral Projection (ነፍስን ከአካል አውጥቶ የመጓዝ ጥበብ)፣ Automatic Writing (ከራስ እውቅና ውጭ በመሆን በሌሎች መንፈሳዊ አካላት በመታገዝ የመፃፍ ጥበብ)፣ Channeling (ከሙት መንፈስ ጋር የመገናኛ መንገድ) ፣ Divination (በውስጡ የ bibliomancy, cartomancy, palmistry, cleromancy, and I-Ching ጥበቦችን የያዘ ሲሆን tarot cards, crystal balls, pendulums, spirit boards በመጠቀም ወደፊት የሚመጣውን ነገር የመተንበያ ጥበብ)፣ Psychic Healing (ምንም አይነት ተጨማሪ መድሀኒቶችን ሳንጠቀም በገዛ ሰውነታችን ራሳችንን የምናክምበት መንገድ፤ ከመንገዶቹም መካከል Crystal healing፣ Acupuncture፣ Qigong፣, Reiki፣ Tai Chi እንደ ምሳሌ ይጠቀሳሉ)፣ Precognition (በህልም ውስጥ ሆኖ መጪውን የመተንበይ ጥበብ) ፣ Psychometry (ልብስ፣ ወንበር ወዘተ…ሊሆን ይችላል፤ ማንኛውንም እቃ በመንካት የዛን እቃ ባለቤት የማወቅ ጥበብ) ፣ Remote Viewing (ምንም አይነት መሳሪያ ሳንጠቀም ባለንበት ሆነን ከኛ እጅግ ርቀው ስላሉ ክስተቶች መረጃን የማግኘት ጥበብ)፣ Telekinesis (አዕምሮን ብቻ በመጠቀም እቃዎችን የማንቀሳቀሻ እውቀት)፣ Telepathy (ቃላት ሳንጠቀም አንድን ሀሳብ ወደ ሌላ ሰው የማስተላለፊያ እውቀት)  ናቸው፡፡
ለዚህ አምድ እንዲመጥን መሰረታዊ የሚባሉት የሳይኪክ እውቀቶች ላይ ትኩረት አድርጌ ገለፅኩላችሁ እንጂ ከዚህ በላይም ይሄዳል፡፡ አምላካዊ ማንነት የሚባለው እውቀት ጋር ከመድረሳችን በፊት ግን ጥቂት በእነዚህ የሳይኪክ ጥበቦች ላይ ትኩረት እናድርግ፡፡
የሳይኪክ ጥበብ ለአንዳንዱ ሰው በተፈጥሮ ከተወለደ ጀምሮ የሚሰጠው ሲሆን፤ ለሌሎች ግን አመታትን የሚፈጅ የአዕምሮን እውቀት በዝብዞ ከማንነት ጫፍ ላይ እንደሚያደርስ እንረዳለን፡፡ በተፈጥሮ የሚሰጠውን መንገድ ትተን በራስ ጥረት እንዴት አንድ ሰው ሳይኪክ መሆን ይቻለዋል የሚለውን ሀሳብ ጥቂት ቃርመን ካቆምንበት እንቀጥላለን፡፡
የጥንት አባቶቻችን በዚህ ጥበብ ላይ ያጠኑት ጥናት ላይ ትኩረት ስናደርግ የሚነግሩን አንድ ነገር እናገኛለን፡፡ እሱም አርምሞን (meditation) በመጠቀም የምናስበውን ሀሳብ በሙላ ወደ አካል መቀየር እንደምንችል ነግረው፣ ወደ ጥበባቸው ቀረብ እንድንል ያደርጉናል፡፡ በእንዴት አይነት የአርምሞ መንገድ ነው ሳይኪክ መሆን የሚቻለው ብለሽ ብትጠይቂያቸው፣ እነዚህን የአርምሞ መንገዶች ይጠቁሙሻል…. Kundalini yoga, Bhakti yoga, Asana yoga, Pranayama yoga, yama yoga, Niyama yoga….
እነዚህ የአርምሞ መንገዶች ላይ መንገድህ ከገጠመ አንደኛውን በር አልፈህ ወደሚቀጥለው ገብተሀል ማለት ነው፡፡ ምን ይሆን ደግሞ የሚቀጥለው በር የምትለኝ ከሆነ ….በቀጣይ ቻክራ የሚባሉትን፣ በሰውነትህ ውስጥ ተቀብረው ያሉትንና መንፈሳዊ ሀይልህን፣ ራስህ ከደበቅህበት አውጥተው የሚያሳዩህን… በቁጥር ሰባት የሆኑ የማንነትህን መንፈሳዊ ካርታ አሳይህና፣ በራስህ ላይ የዘጋኸውን በር ራስህው መክፈት ትጀምራለህ፡፡ ስለነሱ ጥቂት ልበልህ ….
ስለ Chakras (ቻክራዎች) ጥበብ ለመጀመሪያ ጊዜ ያስተዋወቁት ህንዶች ሲሆኑ፤ ዘመኑም ከ1500 እስከ 1000 ባለው ውስጥ እንደነበር ይገመታል፡፡ ቃሉም ለመጀመሪያ ጊዜ ተፅፎበት የተገኘው መፅሐፍ፤ the Vedas ተብሎ በሚታወቀው ጥንታዊው የህንዶች ቅዱስ መፅሀፍ ውስጥ ነው፡፡ በቀላሉ ቻክራ ማለት ቀጥታ ትርጉሙ ተሽከርካሪ ማለት ሲሆን፤ ሰባቱ ቻክራዎች የሚገኙትም በሰውነታችን ውስጥ ነው፡፡ ስማቸውም ይህን ይመስላል…
Root Chakra
Sacral Chakra
Solar plexus chakra
Heart chakra
Throat chakra
Third eye chakra (Ajna chakra)
Crown chakra
እንግዲህ እነዚህ ቻክራዎች ሲከፈቱ አዲስ አይንና አዲስ እውቀት ውስጥ መግባት እንጀምራለን ተብሎ ትምህርት ይሰጥበታል፡፡ ሶስተኛው አይናችን (Ajna chakra) ሲከፈት ከዚህ አለም ውጭ የሆኑ እውቀቶች ውስጥ መግባት እንጀምራለን፡፡ እዚህ ጋ አንድ ጊዜ ቆም እንበል፤ ምክንያቱም የምንጠልቀው የሀሳብ ውቅያኖስ እንዲህ እንደቀልድ ጀምረን የምንጨርሰው አይደለምና ነው፡፡  
የሰው ልጅ የእውነትም ወደ አምላካዊነቱ የሚገሰግስ መንፈሳዊ ፍጥረት ነው? የሚለውን ጥያቄ በመጠየቅ ጉዞዋችንን እንቀጥል፡፡
የሰው ልጆች አሁን እየኖርንበት ያለነውን ነባራዊው አለምና በእኛ ውስጥ ያለው የማሰብ ስፋት ተመጣጣኝ ነው ብዬ አላስብም፡፡ የሆነ እየተከናወነ ያለ ነገር እንዳለ ይሰማኛል። እስቲ ሚዲያዎችን ተመልከቱ… አብዛኞቹ የአለም ሚድያዎች የሚያተኩሩት የተወሰኑ ነገሮች ላይ ነው፤ በብዛትም የምንሰማው የአለምን ቀውስና የሰው ልጆችን የሞት ብዛት ነው፡፡ የተለያዩ የመዝናኛ ጣቢያዎችንም ብትመለከቱ የምታገኙት እውቀት ተስፋ የመቁረጥና የሌሎችን ሰዎች የአኗኗር መንገድ ተመልክቶ ከማድነቅ የዘለለ ምንም ትርጉም ያለው ነገር ሲሰጡን አይታይም፡፡ በእውቀት እኛን ከማጥለቅለቅ ይልቅ በወሲባዊ ገፅታዎች የአስተሳሰባችንን ልክ ለማዝቀጥ የመጡ ናቸው። ይህን ለምን ማድረግ ተፈለገ?
መልሱ ቀላል ነው፡፡ የሰው ልጆችን ለማደንዘዝ የሚደረግ ፕሮፓጋንዳዊ ስበት ነው፡፡ በአለማችን ላይ አሉ የተባሉት ኤሊቶች (1%)እኛን በአጀንዳቸው ውስጥ ሰትረው የማሰብ አቅማችንን እነሱ በሚፈልጉበት መንገድ መዘወር ነው የሚፈልጉት፡፡ እነሱ ያሻቸውን አየር እንድንተነፍስ፣ ባዘጋጁልን መንገድ እንድንራመድ፣ በፈቀዱልን ነፃነት ልክ እንድንደሰት ነው የሚፈልጉት….፡፡ አልተሳካላቸውም ማለት አልችልም፡፡ በአሁኑ ሰዓት ላይ ራሱን የሚያጠፋ፣ ካለበት ዲፕሬሽን ራሱን ለማዳን በአነቃቂ መድሀኒቶች ሰውነቱን ያሰቃየ፣ የምድር ላይ ጥረቱን ልፋቱን ከወዲያ አድርጎ ከጭንቀት ለመዳን ራሱን በየገዳማቱ የሚሰድ፣ የተማረው ትምህርትና እየኖረው ያለው ኑሮ ተምታቶበት ተስፋውንና ምኞቱን ቀዳዶ ጥሎ ተራ ሰው ለመሆን የሚጥር፣ በፖለቲከኞች የጦርነት ሱስ ተጠቂ ሆኖ ትላንቱንና ነገውን የተቀማ ….ብዙ አይነት ከማንነቱ እና ከሰዋዊ መገለጫው የተሸኘ የማህበረሰብ ክፍል በአለም ላይ ተበተኖ እንመለከታለን፡፡ ይህም የኤሊቶቹ ሀሳብ ነበር…ተራውም ህዝብ ተቀብሎ ያሳባቸውን ይሆንላቸዋል፡፡
ታዲያ ለምን ይሆን የሰው ልጅ ሁልጊዜ ራሱን በመፈለግ የሚባዝነው ብዬ ራሴን ስጠይቅ የማዳምጠው መልዕክት አንድ ነገር ብቻ ነው…ምክንያቱም ይህን ፍጥረት ከራሱ ጋር ከመተዋወቁ በፊት በምድር ላይ የሚኖርበትን መንገድ ገና ከእናቱ ማህፀን እንደወጣት ከራሱ ባልሆኑ እውቀቶች መሞላት ይጀምራል። እረፍት የለም፡፡ ገና ለአለም እንደነቃን የሚጠብቀን የቤተሰቦቻችን ህግጋቶች ናቸው፡፡ ቤተሰብ ራሱን የቻለ አንድ ተቋም ነውና፡፡ ቤተሰቦቹን ሸሸት ሲል ጓደኞችና አስተማሪዎች ከሚላቸው የማህበረሰብ ክፍል ጋር ይገናኛል፤ “ሰው ማለት እንዲህ አይነቱ ነው” እስኪባል ድረስ አብሯቸው እስከ እድሜው አጋማሽ ድረስ ይሄዳል፡፡ ራሴን አውቄያለሁ…በራሴ መንገድ ራሴን ልፈልግ ብሎም ሲነሳ በቅድሚያ በግሉ እውቀትን ስለመሰብሰብ ነው የሚያስበው…በዚህም ራሱ የመረጣቸውን የሚድያ ጣቢያዎችና መፅሀፍትን እየቃረመ ብቻውን እንደሆነ በማሰብ፣ ግለኝነቱን ማፋፋም ውስጥ ይገባል፡፡ ነገር ግን አሁንም ቢሆን ከሰው ሀሳብና አመለካከት ያስመለጠው ምንም ነገር የለም፡፡ በዚህ ሁሉ መሀል ይህ ሰው የኔ የሚለው ጊዜ እና የሀሳብ ቅርፅ ሳያበጅ ከተራው ጋር ተራ ሆኖ ይሞታል፡፡ በመጨረሻም፣ አፈሩን በልቶ ያጠራቀመውን ሀብትና ንብረት ትቶ በአፈር ሊበላ በታላቅ ፀጥታ ውስጥ ሆኖ ከጨለማው ይሰምጣል፡፡
በእድሜዬ የታዘብኩት ነገር እንግዲህ ይሄ ነው፡፡ “አሁን ሰው ሆንክ” የሚለውን ፍጥረት ፍለጋ፣ የሰው ልጅ ጥረቱና ልፋቱ እንደዛ እንደሚሆን ተመለከትኩ፡፡ ሆኖም ሰው ከሆንን በኋላ ምንድነው የሚቀጥለው ጉዞዋችን? ብዬ እጠይቃለሁ፡፡ ቢሞሉትና ቢጠልቁት የማያልቀው የሰው ልጅ አዕምሮ እስካሁን ካየናቸው ተግባራቶቹ በላይ መሄድ እንደሚችል በጊዜ ስፋት ውስጥ ለመመልከት ሞክረናል፡፡ ምናልባት ዘመናዊነት ማለት ምን ማለት ነው የሚለው ሀሳብ፣ ለብቻው ግብረገባዊ ትርጉም ይዞ ሊያከራክረን ቢችልም፣ የሰው ልጅ እርስ በርስ መገዳደሉን ባያቆምም፣ በተቃራኒውም እያደገ ነውም ማለት እንችላለን፡፡ የሰው ልጅ የት ድረስ ነው ማደግ የሚችለው የሚለው የሁላችንም ጥያቄ ነው ሊሆን የሚገባው፡፡
የሳይኪክ እውቀትን በመጠቀም የማይታዩ አለማትን ማየት ከቻልን፣ አንድ ሰው ቃላት ሳያወጣ የሚያስበውን ሀሳብ በአዕምሮ ሞገዳችንና በሶስተኛው አይናችን ማድመጥና መመልከት ከቻልን፣ የመሬትን ስበት ለቀን በአየር ላይ ከተንሳፈፍን፣ በረቂቅ የመለኮት ጥበብ ውስጥ ሆነን ሊሞቱ ያሉ መሰሎቻችንን ማዳን የምንችል ከሆነ፣ በሞት የራቁንን ዘመዶቻችንን ማናገር ከቻልን…ከቻልን፡፡ እየቻልን ከታየን…ጥያቄን እንድጠይቅ ያደርገናል፡፡
በፊታችን ላይ ተለጥፈው ካሉት ሁለት አይኖች ውጭ የሆነ ሌላ አይን እንዳለን እንገነዘባለን፣ ከአፋችን ከሚወጡ ቃላቶች በላይ ሆነን የአየር ላይ ሞገድን ብቻ በመጠቀም በሰው ሀሳብ ውስጥ ሀሳብ መጨመር እንደማያቅተን እንደርስበታለን፣ የጥንቱን እውቀት ተጠቅመን አምላካዊ ባህሪይ ያለን ፍጥረቶች እንደሆንን እና በግላችን ማንም የማይደርስብን የራሳችን አምላክ እንደሆንን እንደርስበታለን፡፡
ራሳችንን ፈጥረናል? ለሚለው ጥያቄ አሁን ላይ መልስ ማግኘት ባልችልም፣ በተፈጠረው አለም ላይ ግን ህይወቴን የምሰራትና መልክ የማስይዛት እኔ ብቻ እንደሆንኩኝ እረዳለሁ፡፡ ብዙ ሰዎች አምላክ ነን ብለው አልፈዋል፡፡ ብዛት ያላቸውንም ተከታዮች በ cult ማዕቀፍ ውስጥ ከተው አሰግደዋል፡፡ ሰጋጁን ማህበረሰብ ተራው ህዝብ የምንለው ከሆነ አሰጋጁን ማን ልንለው ነው?
አሁንም ስለራሳችን እንዳናውቅ እና ከፍታችን ድረስ እንዳንሄድ በጦርነት አረር አዕምሯችንን ወጥረው ይዘውታል፤ ልጆቻችንን በስነምግባር እንዳናሳድግ በየትምህርት ቤቱ አጀንዳቸውን ሰትረው ሽቅብ ሊወጣ ያለውን መንፈሳቸውን ቁልቁል እያንደረደሩ ወደ ውድቀታቸው እንዲቀርቡ ያደርጋሉ፣ ትውልድ ቢመላለስባት አዝዕርቷን የማትነፍገን ምድር ላይ እያለን፣ በኑሮ ውድነት ውስጥ ቀኖቻችንን ቀምተውን በኛ ጊዜ እነሱ ይኖራሉ…በኛ ልፋት እነሱ ይጠግባሉ፡፡ ሳቃችንን የሚስቁት እነሱ ናቸው፡፡ እንቅልፋችን ውስጥ ገብተው ቅዠት ይሆናሉ፣ ትዳራችን ውስጥ ገብተው ፍቅርን የማውደም ጥበብን ያስተምራሉ፡፡ እኛ የነዚህ ሰዎች የሀሳብ የሙዚቃ ኖታዎች ከሆንን እነሱን ማን እንበላቸው?
እመኑኝ የሰው ልጅን ጭንቅላት እነሱ በደረሱበት ጥበብ ሃክ እያደረጉት ነው፡፡ እኛ ራሳችንን ለማግኘት እድሜያችንን ስንቆጥር፣ እነሱ ሰው ላብራቶሪ ውስጥ መፍጠር ችለዋል። የምድር ላይ ጉብኝታችንን ልናሰፋ ደፋ ቀና በምንልበት ሰዓት ላይ እነሱ ምድርን ጥለው ሄደው አለማትን ይጎበኛሉ፣ እነሱ በሚሊየኖች የሚያገኙበትን ሚድያ ሰርተው በቀለምና በድምፅ የሚልኩልን ምስል ላይ አፍጥጠን፣ ያልገባንን መልስ ፍለጋ በጊዜያችን ላይ ህሊናችንን ስንገድል፣ እነሱ እያንዳንዷን ደቂቃ ስራቸው ላይ ናቸው፡፡ እኛ ምስኪን እውቀትና የተሻለ ኑሮ ፈላጊዎች ስንባል እነሱን ማን እንበላቸው?
ቅዱስ መፃሕፍቶችን እንመርምር፣ እንደ ቀልድ ያመነውን እምነት ቆፍጠን ብለን በትነን እንመልከተው፡፡ “ማሰብ ያሳስራል” ሳይሉን በፊት በፍጥነት እናስብ፡፡ ከውስጣችን ውስጥ ፈጣሪ የቀበረውንና ለኛ ግን የተሰወረብንን (የሰወሩብንን) ጥበብ አምጠን እንውለደው፡፡ ሁላችንም የሰው ልጆች በአንዲት አዕምሯችን ነው የምናስበው…ሁላችንም የሰው ልጆች ተመሳሳይ ጊዜ ነው ያለን፡፡ ሁላችንም የሰው ልጆች በአንድ ፈጣሪ ነው ታስበን የመጣነው…ማንም ሰው፤ ሰው ከመሆን ውጭ አማራጭ የለውም፡፡ ሆኖም ጉዞው በማያልቀው የዘላለም የሀሳብ ርዝማኔ ውስጥ ሆኜ እጠይቃለሁ። በስንት ትግል እኔ፣ ያሳደገኝ ማህበረሰብንም ሆነ ፈጣሪዬን አስደስቼ የምፈልገው አይነት ሰው ሆንኩኝ …. ከዛስ?


Read 1882 times