Saturday, 17 June 2023 00:00

“ሳሌም” አዲስ ልቦለድ መፅሀፍ ለንባብ በቃ

Written by 
Rate this item
(4 votes)

 የደራሲ አንተነህ እሸቱ 6ኛ ሥራ የሆነው “ሳሌም” የተሰኘ ረዥም ልቦለድ መፅሀፍ ሰሞኑን ለንባብ በቃ። መፅሐፉ በዋናነት መቼቱን “ከፍታ” የተሰኘች ምናባዊ ከተማ ላይ መስርቶ ሳሌም የተባለችዋ ጋዜጠኛ በዚህች ከተማ ላይ ከአዲስ አበባ የሄዱ ዘመዶቿን ሽኩቻ የምትታዘብበትና ቤተሰቦቿ የሀገሪቱን ወቅታዊ ሁኔታ እንደሚወክሉ የምትታዘብበትን ታሪክ የሚያንጸባርቅ ነው ተብሏል፡፡ መፅሀፉ በ183 ገጾች ተቀነባብሮ በ290 ብር ለገበያ የቀረበ ሲሆን መታሰቢያነቱም ለታላቁ የስነ ፅሁፍ ምሁር ተባባሪ ፕሮፊሰር ዘሪሁን አስፋው መደረጉንም ደራሲው በመግቢያው ላይ አስፍሯል፡፡
ደራሲ አንተነህ እሸቱ ከዚህ ቀደም “ከግድግዳው ጀርባ”፣ “እኔ ሀብታም”፣ “ጥርስ የገባ”፣ “ቀሚስ የጋረደው” እና “ዳና ሥር” የተሰኙ መጽሐፍትን ለንባብ ማብቃቱ አይዘነጋም፡፡


Read 1316 times