ደራሲው መታሰቢያነቱን ለኢትዮጵያ ሰላምና ብልፅግና ሕይወታቸውን ሙሉ ለጣሩ ሰዎች ባደረገው መፅሐፍ የጀርባ ሽፋን ላይ አስተያየት ከሰጡ ግለሰቦች መካከል አርቲስት ስዩም ተፈራ መፅሐፉን “ልብ ሰቃይ፣ ፈጣንና የሥለላ ታሪኮች የተሰናሰሉበት” በማለት አስተያየቱን ሲሰጥ መፅሐፉን ማንበባቸውን የተናገሩት ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ “የመቻቻል ፖለቲካን አስፈላጊነት የገለፀ” ብለውታል፡፡ 270 ገፆች ያሉት መፅሐፉ ለሀገር ውስጥ በ39 ብር በውጭ ሀገራት በ19 ዶላር ለገበያ ቀርቧል፡፡ በሌላም በኩል “ሚስጢራዊ ማህተም” አዕምሮአዊ ልቦለድ መጽሐፍ ማክሰኞ ከቀኑ 10 ሰዓት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተመዛግብትና ቤተመፃሕፍት አዳራሽ ይመረቃል፡፡ 202 ገፆች ያሉትን መፅሐፍ ያዘጋጁት ገብረሥላሴ አፅብሃ (ባዜን) ናቸው፡፡ የመፅሐፉ ዋጋ 35 ብር ነው፡፡