አዘጋጆቹ ልብ አንጠልጣይ ኤፒክ ነው ባሉት ፊልም ዳዊት ነፀረአብ፣ ኤፍሬም አደፍርስ፣ ኤልያስ ማዳ፣ ሳባ ጌታቸው እና ሌሎች ተውነዋል፡፡ ፊልሙን ያዘጋጀው ግርማ በቀለ ከምሲ ነው፡፡ በሌላም በኩል የድምፃዊት፣ ገጣሚና ተዋናይት ሩታ አርአያ “የኔታ” የተሰኘ ፊልም በደቡብ አፍሪካ ፖርት ኤልዛቤት ከተማ፣ ነሐሴ 12 ቀን 2004 ዓ.ም ከቀኑ በ10 ሰዓት በግራንድ ሆቴል እንደሚመረቅ ተገለፀ፡፡ በፊልሙ ላይ ከ16 በላይ ተዋናዮች የተሳተፉ ሲሆን ፍላይ ፒ.ዲ.ቤይ ቲቪ በተሰኘ ታዋቂ የፊልም ኩባንያ መሰራቱ ታውቋል፡፡ በዕውቅ እንግሊዛዊ የካሜራ ባለሙያ የተቀረፀ ነው የተባለውን ፊልም ሰርቶ ለማጠናቀቅ አንድ ዓመት ፈጅቷል፡፡ የፊልሙ ዳይሬክተርና ፕሮዲዩሰር ሩታ አርአያ ለዝግጅት ክፍላችን እንደገለፀችው፤ ፊልሙ በቅርቡ በሃገር ውስጥ ተመርቆ መታየት ይጀምራል፡፡ በ“ሔልዳን ፊልም ፕሮዳክሽን የተሰራው “ቪ አይ ፒ” አስቂኝ ምፀታዊ ፊልም ነገ ይመረቃል፡፡ ዶ/ር ናትናኤል ብርሃኑ እና ዘውዱ ዳርቻ ፕሮዲዩስ ያደረጉትን ፊልም ኤርምያስ ግርማ ጽፎት አየለ አበበ እና አብዱልከሪም ጀማል አዘጋጅተውታል፡፡ ሸዋፈራሁ ደሳለኝ፣ መኮንን ላዕከ፣ ድርብወርቅ ሰይፉ፣ ፍሬሕይወት ባህሩ፣ ሳሙዔል ተስፋዬ እና ሌሎች ተውነውበታል፡፡ የ100 ደቂቃ ፊልሙን ሠርቶ ለማጠናቀቅ 14 ወራት ፈጅቷል፡፡