Saturday, 23 January 2021 10:57

የትግራይ ቴሌቪዥን ጋዜጠኛ በመቀሌ ተገደለ

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(0 votes)

የትግራይ ቴሌቪዥን የአማርኛ ክፍል ባልደረባ የነበረው ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ አርአያ ከጓደኛው ጋር ጥር 12 ቀን 2013 ዓ.ም በመቀሌ ከተማ መኪና ውስጥ ተገድለው መገኘታቸውን ተገለፀ፡፡
የጋዜጠኛውንና የጓደኛውን አስክሬን የቀይ መስቀል ሰራተኞች ማንሳታቸውንና ለቤተሰብ መስጠታቸውን የገለፁት ምንጮች፤ስለ ጋዜጠኛውና ጓደኛው ተገድሎ መገኘት የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር መረጃ አልሰጠም፡፡
“ስለ ጋዜጠኛው አሟሟት መረጃ እያሰባሰብን ነው፤ መረጃው እንደተጠናቀቀ ይፋ እናደርጋለን” ብለዋል - የጊዜያዊ አስተዳደሩ የደህንነት ሃላፊ ዋልታ ሀረጎት፡፡
ጋዜጠኛ ዳዊት የትግራይ ቲቪ በድጋሚ ስራ ከጀመረ በኋላ ለጋዜጠኞች የተደረገውን ጥሪ ተቀብሎ ስራ ጀምሮ እንደነበር ቢቢሲ ምንጮቹን ጠቅሶ በሰራው ዘገባ አመልክቷል፡፡
ጋዜጠኛው ለበርካታ ዓመታት በብሔራዊ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የሰራ ሲሆን ኢቲቪን ከለቀቀ በኋላም የራሱን በትግርኛ ቋንቋ የምትዘጋጅ መፅሔት ያዘጋጅ እንደነበርና ኋላም የትግራይ ቴሌቪዥንን እንደተቀላቀለ ለማወቅ ተችሏል፡፡ የጋዜጠኛውና ጓደኛው ስርአተ ቀብር ጥር 12 ቀን 2013 ዓ.ም በመቀሌ አቡነ አረጋዊ ቤተ ክርስቲያን መፈፀሙም ታውቋል፡፡

Read 914 times