Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 11 August 2012 11:51

ሌዲ ጋጋ ወደ ትወና ገባች

Written by 
Rate this item
(3 votes)

 

አወዛጋቢዋ አቀንቃኝ ሌዲ ጋጋ ወደ ፊልም ትወና መግባቷ ተገለፀ፡፡ አርቲስቷ ሰሞኑን የሶስተኛ አልበሟን  መጠርያ  በክንዷ ላይ በመነቀስ ማስተዋወቋን የገለፀው ኤምቲቪ ኒውስ ነው፡፡
በ2013 መግቢያ ላይ ይወጣል የተባለው የሌዲ ጋጋ አዲስና ሶስተኛ አልበም   ‹አርትቶፕ› የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡ በ2008 እ.ኤ.አ ላይ የመጀመርያ አልበሟን “ዘ ፌም” ከዚያም በኋላ ተከታዩን አልበም “ቦርን ዚስ ዌይ” ባለፈው አመት ለገበያ ያበቃችው ሌዲ ጋጋ፤ የእነዚህን አልበም 30 ሚሊዮን ቅጂዎች እንዲሁም 60 ሚሊዮን ነጠላ ዜማዎች በመላው አለም መሸጧ ይታወቃል፡፡ይህ በእንዲህ እንዳለ በአነጋጋሪ የፋሽን ተከታይነቷና በመድረክ ላይ ቅብጠቷ የምትታወቀው ሌዲ ጋጋ፤ የመጀመርያ ትወናዋን በምታሳይበት ፊልም ላይ መስራት እንደጀመረች ታውቋል፡፡ ሮበርት ሮድሪጌዝ  ዲያሬክት የሚያደርገውን ‹ማቻቴ ኪልስ› የተባለ ፊልም የምትተውነው ሌዲ ጋጋ፤ አስደናቂ ችሎታ ማሳየቷ የሚጠበቅ መሆኑን ሮይተርስ አስታውቋል፡፡ በዚሁ የሌዲ ጋጋ የመጀመርያ ፊልም ላይ ኮሜዲያኑ ቻርሊ ሺንና ሜል ጊብሰን በተጋባዥነት ይተውናሉ፡፡

 

አወዛጋቢዋ አቀንቃኝ ሌዲ ጋጋ ወደ ፊልም ትወና መግባቷ ተገለፀ፡፡ አርቲስቷ ሰሞኑን የሶስተኛ አልበሟን  መጠርያ  በክንዷ ላይ በመነቀስ ማስተዋወቋን የገለፀው ኤምቲቪ ኒውስ ነው፡፡ በ2013 መግቢያ ላይ ይወጣል የተባለው የሌዲ ጋጋ አዲስና ሶስተኛ አልበም   ‹አርትቶፕ› የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡ በ2008 እ.ኤ.አ ላይ የመጀመርያ አልበሟን “ዘ ፌም” ከዚያም በኋላ ተከታዩን አልበም “ቦርን ዚስ ዌይ” ባለፈው አመት ለገበያ ያበቃችው ሌዲ ጋጋ፤ የእነዚህን አልበም 30 ሚሊዮን ቅጂዎች እንዲሁም 60 ሚሊዮን ነጠላ ዜማዎች በመላው አለም መሸጧ ይታወቃል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ በአነጋጋሪ የፋሽን ተከታይነቷና በመድረክ ላይ ቅብጠቷ የምትታወቀው ሌዲ ጋጋ፤ የመጀመርያ ትወናዋን በምታሳይበት ፊልም ላይ መስራት እንደጀመረች ታውቋል፡፡ ሮበርት ሮድሪጌዝ  ዲያሬክት የሚያደርገውን ‹ማቻቴ ኪልስ› የተባለ ፊልም የምትተውነው ሌዲ ጋጋ፤ አስደናቂ ችሎታ ማሳየቷ የሚጠበቅ መሆኑን ሮይተርስ አስታውቋል፡፡ በዚሁ የሌዲ ጋጋ የመጀመርያ ፊልም ላይ ኮሜዲያኑ ቻርሊ ሺንና ሜል ጊብሰን በተጋባዥነት ይተውናሉ፡፡

 

 

 

Read 2018 times