Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 04 August 2012 11:38

የ”ትዋይላይት” ተዋናዮች ፍቅር መበላሸት ቁጣ ቀሰቀሰ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

የክርስቲን ስትዋርት እና ሮበርት ፓቲሰን የፍቅር ግንኙነት መበላሸቱ የ “ትዋይላይት” ፊልም አድናቂዎችን እንዳስቆጣ የተለያዩ ዘገባዎች አመለከቱ፡፡ ክርስቲን ከሩፕርት ሳንድረስ ጋር የያዘችው ድብቅ ፍቅር ከሳምንት በፊት መጋለጡ ነው ቁጣውን የቀሰቀሰው፡፡ ሩፕርት  ከ “ትዋይላይት” ፊልሞቿ በኋላ የሰራችበት “ስኖው ዋይት ኤንድ ዘ ሃንትስማን” የተባለ ፊልም ዲያሬክተር ነው፡፡ በትዋይላይት ፊልሞች ለአራት ዓመት   ከሰሩ በኋላ ሲያፈቅራት በኖረው ሮበርት ፓቲሰን ላይ የተፈፀመ ክህደት በሚል የፊልም  አድናቂዎች እያወገዙት ነው፡፡ ዲያሬክተር ሩፕርት ሳንድረስ ሁለት ልጆች ካፈራበት ትዳር ውጭ በመማገጡና የትዋይላይት ፊልም ተዋናዮችን የሞቀ ፍቅር በማደፍረሱ ከፍተኛ ወቀሳ ደርሶበታል፡፡  ቁጣው ከአራት ወር በኋላ በሚጠበቀው “ትዋይላይት ብሬኪንግ ዳውን” ክፍል 2  ገበያ ላይ ተፅእኖ እንዳይፈጥርም አስግቷል፡፡

ምስጥራዊ ግንኙነቱ የተጋለጠው ድብቁን ፍቅር የሚያሳይ ፎቶ ከፓፓራዚዎች  300ሺ ዶላር ከፍሎ ዩኤስ ዊኪሊ ለህትመት በማብቃቱ ነበር፡፡ክርስቲን ስትዋርት እና ሩፕርት ሳንድረስ   ለፒፕል መፅሄት በሰጡት መግለጫ፣ ይቅርታ ቢጠይቁም በሁኔታው አወዛጋቢነት የተነሳ ግንኙነታቸውን ለመቀጠል ይቸገራሉ ተብሏል፡፡ ሮበርት ፓቲሰን ለክርስቲን የጋብቻ ጥያቄ ለማቅረብ በተነሳበት ሰሞን  ዱብ እዳው መሰማቱን ፎክስ ኒውስ ገልጿል፡፡የ22 አመቷ ክርስቲን ስትዋርት እና የ26 አመቱ ሮበርት ፓቲሰን ፍቅራቸው ከደፈረሰ በኋላ ስድስት ሚሊዮን ዶላር ከሚገመተው የሎስአንጀለስ የጋራ መኖርያ ቪላቸው ለቅቀዋል፡፡ ሮበርት የተሰበረ ልቡን ለመጠገን ከሌላዋ ምርጥ ተዋናይት ሪዝ ዊዘርስፑን ጋር ግንኙነት መጀመሩን ከትናንት በስቲያ የወጡ ዘገባዎች አውስተዋል፡፡ሁለቱምተዋናዮችበ “ትዋይላይት” ፊልሞች አንድ ክፍል ስራቸው 12.5 ሚሊዮን ዶላር ይከፈላቸዋል፡፡

 

 

 

Read 1545 times Last modified on Saturday, 04 August 2012 11:44