Sunday, 28 June 2020 00:00

ታሪክና ፖለቲካ ዳቦ አይሆነንም!

Written by 
Rate this item
(0 votes)

  ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ሰሞኑን በከተማዋ ትልቁ የተባለውን የሸገር ዳቦ ፋብሪካ ባስመረቁበት ወቅት ባደረጉት ንግግርና ባስተላለፉት መልዕክት፤ “በትላንት ውስጥ የሚኖር ህዝብ ነገን ለመመልከትና ወደ ብልጽግና ለመገስገስ ይቸግረዋል” የሚል ሃሳብ ያንፀባረቁ ይመስለኛል - ቃል በቃል ባይሆን፡፡
ሁሉም በየሙያ ዘርፉ ተግቶ በመሥራት ራሱንና አገሩን ውጤታማ ማድረግ እንዳለበትም ያሰመሩበት ጠ/ሚኒስትሩ፤ ሁሉም የትናንትናና የታሪክ ተንታኝ በሆነበት ሁኔታ ወደ ብልጽግና የሚደረገው ጉዞ አዳጋች እንደሚሆን አስረድተዋል፡፡ መፍትሔውስ? ትንተናውን ለታሪክ ባለሙያዎች በመተው ሁሉም በየራሱ የሙያና የሥራ ዘርፍ ተግቶ መስራት እንዳለበት ነው አስረግጠው የተናገሩት ለምን? ቢሉ… ታሪክና ፖለቲካ ዳቦና ኑሮ ሆነው አያውቁም፡፡ ለወጣቶች የሥራ ዕድል አይፈጥሩም፡፡ የአገርና የህዝብ ህይወት አይለውጡም፡፡ ይልቁንም የጭቅጭቅና ንትርክ ምንጭ ነው የሚሆኑት፡፡
በተጨማሪም ሰላምን ያደፈርሳሉ፤ የህብረተሰቡን ህይወት ያናጋሉ፡፡ የጥላቻ ሰበብ ይሆናሉ፡፡  ለጦቢያችን የሚያስፈልገን ግን ነገን አሻግሮ እየተመለከቱ፣ ከድህነት ለመላቀቅና የብልጽግና ጉዞን ለመጀመር ተግቶ መሥራት ነው፡፡ ታሪክን የሙጥኝ ማለት በትላንት ውስጥ መኖር ነው፤ አንዳንዴም ነገን ለመጋፈጥ ድፍረት ከማጣት ይመነጫል -ወደፊት ለመገስገስ የምንሻ ከሆነ ግን… ትላንት (ታሪክ) ውስጥ ከመኖር ልንወጣ ይገባል - ጠ/ሚኒስትሩ አጥብቀው እንደመከሩት!!

Read 1706 times