Sunday, 14 June 2020 00:00

በአንድ ሳምንት ብቻ 1120 ሰዎች ሲያዙ 25 ሰዎች ሞተዋል

Written by  መታሰቢያ ካሳዬ
Rate this item
(6 votes)

      ባለፈው ሳምንት ውስጥ ብቻ ለ39ሺ492 ሰዎች የላብራቶሪ ምርመራ ተካሂዶ 1120 ሰዎች በኮረና ቫይረስ መያዛቸውን የጤና ሚኒስቴር መረጃ ጠቁሟል፡፡
የጤና ሚኒስቴር መረጃ እንደሚያመለክተው፤ ባለፈው አንድ ሳምንት ብቻ የተገኘው በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር፤ ባለፉት ሁለት ወራት  ውስጥ ከተገኙት ሰዎች ቁጥር በአምስት እጥፍ የሚበልጥ ነው። በትላንትናው ዕለት ለ5ሺ709 ሰዎች ምርመራ ተደርጎ፣ 245 ሰዎች ቫይረሱ የተገኘባቸው ሲሆን ይህም በአገሪቱ እስካሁን በአንድ ቀን ከተመዘገቡት ቁጥሮች ከፍተኛው ነው።
በአንድ ሳምንት ብቻ ለ39ሺ492 ሰዎች ምርመራው ተደርጎ 1ሺ120 የሚሆኑት በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን 25 ያህሉ ደግሞ በዚህ ቫይረስ ሳቢያ ሕይወታቸውን አጥተዋል። ከሟቾቹ መካከል የ15ቱ ውጤት የታወቀው በአስከሬን ምርመራ መሆኑም ተገልጿል።
በአሁኑ ወቅት በአስከሬን ምርመራ በቫይረሱ መያዛቸው የሚታወቅ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መሄዱም ታውቋል።


Read 10650 times