Saturday, 30 June 2012 12:46

“የኢትዮጵያ ተስፋዎች” ፊልም ለሕዝብ ቀረበ

Written by  መልካሙ ተክሌ (melkamutekele@gmail.com)
Rate this item
(0 votes)

መጪውን የለንደን ኦሎምፒክ አስመልክቶ አዲስ አበባ በሚገኘው የእንግሊዝ ኤምባሲ ድጋፍ አድራጊነት የተሰራው “የኢትዮጵያ ተስፋዎች” (Hopes of Ethiopia) ፊልም ከትናንት ወዲያ ምሽት ለሕዝብ ቀረበ፡፡ በላፍቶ ሞል ያቀረበው የ10 ደቂቃ ፊልም ላይ የኢትዮጵያ የመጀመርያዋ ሴት የኦሎምፒክ ዋናተኛ ያኔት ስዩም፣ የ800 ሜትር ሯጭ መሃመድ አማን እና ፓራሊምፒያን ተስፋአለም ገብሩ ተሳትፈውበታል፡፡ ኦሎምፒክ ላይ ያጠነጠነውን ይሄው ፊልም ፊልም ባሳለፍነው ሳምንት በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ለተመልካች የቀረበ ሲሆን በፕላዝማ ቴሌቪዥን ለተማሪዎችና ለሌሎች የሕብረተሰቡ ክፍሎች እንደሚደርስም ለማወቅ ተችሏል፡፡ የብሪቲሽ ኤምባሲ መጪውን ኦሎምፒያድ አስመልክቶ በወር ሁለት ጊዜ በሸገር ኤፍኤም የሚቀርብ የሬዲዮ ዝግጅት አለው፡፡

 

 

Read 1044 times Last modified on Saturday, 30 June 2012 12:49