Saturday, 23 June 2012 08:34

በጃ ሉድ “ድግስ” ዳዊት መለሰ ይዘፍናል

Written by  መልካሙ ተክሌ (melkamutekele@gmail.com)
Rate this item
(0 votes)

የዛሬ ሁለት ሳምንት በላፍቶ ሞል በሚቀርበው የጃሉድ “ድግስ” ከመድረክ የራቀው ድምፃዊ ዳዊት መለሰ እንደሚዘፍን አዘጋጆቹ አስታወቁ፡፡ የሙዚቃ ድግሱ አዘጋጆች እንደገለፁት፤ “ያቺ ነገር” በሚል ርዕስ አዲስ የሬጌ ስልት አልበም ይዞ በመምጣት ተደማጭነት ያገኘው ጃ ሉድ፤ ከዚህ “ድግስ” በኋላ በውጭ ሀገራት በመዘዋወርም ኮንሰርቶችን ያቀርባል፡፡ ሰኔ 30 ቀን 2004 ዓ.ም ምሽት የሚቀርበውን የመዚቃ ድግስ አስመልክቶ አዘጋጆቹ “ኤቢሲ ሳውንድ” እና “ይሳቃል ኢንተርቴይመንት” በሰጡት መግለጫ፤ ጥራቱ የላቀ የድምፅና የብርሃን ግብአት እንጠቀማለን፣ ላይና ታች የሚያበራ ፋይበር ግላስ የሆነ መድረክ አለን፣ ለመጀመርያ ጊዜ ከኦዲዮ ዲጄ ወጥተን ቪዲዮ ዲጄ እንጠቀማለን፤ ላፍቶ ሞል ከአራት ሺህ እስከ አምስት ሺህ ሰው ይይዛል፤ ክረምት በመሆኑም የድንኳን መጠለያዎች ይኖሩናል” ብለዋል፡፡

ከጃ ሉድ ጋር ሥራውን የሚያቀርበው ድምፃዊ ዳዊት መለሰ፤ በመሃሪ ብራዘርስ የሙዚቃ ቡድን በመታጀብ ሁለት አዳዲስ እና ሌሎች ነባር ዘፈኖችን ያቀነቅናል ተብሏል፡፡ በመድረክ ዝግጅቶች አንዳንዴ ዘፋኞቹ በማስመሰል (mime) ይዘፍናሉ፣ ጉንፋንም ይዞን ነው የሚሉም አሉ፤ ያ እንዳይሆን ምን ያህል ዝግጁ ነህ ተብሎ ከአዲስ አድማስ የተጠየቀው ጃ ሉድ፤ “ይኼ እንዳይፈጠር ከኤቢሲ ጋር መስራት ከጀመርኩ ወዲህ ጉንፋን ስላለብኝ በየጊዜው ሐኪም ቤት ሄጄ እየታየሁ ነው” ብሏል፡፡የ”ድግስ” መግቢያ ዋጋው 300 ብር እና 500 ብር እንደሆነም ለማወቅ ተችሏል፡፡

 

Read 1145 times Last modified on Saturday, 23 June 2012 08:36