ሊያ ከበደ በአምባሳደርነት ስለምትሰራለት የሊ ኦሪል ምርቶች ስትናገርም፤ “ማንነቴን የሚገልፁ” ስትል አወድሳለች፡፡ ከፌስቲቫሉ ጋር ተያይዞ ለኤድስ መድሃኒት ምርምር ማካሄጃ የገቢ ማሰባሰብ ፕሮግራም የተካሄደ ሲሆን 11 ሚሊዮን ዶላር በተገኘበት የእራት ግብዣ ላይ ሊያ ከበደ ከሆሊውድ ዝነኛ ተዋናዮች ጋር ተምነሽንሻለች፡፡
በቅርቡ በፈረንሳይ በተካሄደው የካኔስ ፊልም ፌስቲቫል ላይ በእንግድነት የተገኘችው ዓለም አቀፍዋ ሞዴል ሊያ ከበደ፤ፌስቲቫሉ የሚማርክ ምትሃት ነበረው ስትል አደነቀች፡፡ ሊያ በፊልም ፌስቲቫሉ ቀይ ምንጣፍ ላይ ከተምነሸነሹት የዓለም 1ኛ ደረጃ ዝነኞች (A-List) ተርታ መሰለፍ ችላለች ተብሏል፡፡ “ዘ ቬን” የተባለ መፅሄት፤ “በካኔስ ፊልም ፌስቲቫል እጅግ ያማረና ዘናጭ አለባበስ የነበራት ዓለም አቀፍ ሞዴል ሲል” ሊያን አድንቋታል፡፡ ይህ በዚህ እንዳለ ሲኒማ ፓራዲዞ የተባለው እውቅ የፊልም ኩባንያ ዲያሬክተር ጁሴፔ ቶራንቶሬ፤ ለሊያ የፊልም ትወና ግብዣ እንዳቀረበላት ታውቋል፡፡ ውዲ አለንን ከመሳሰሉ ታላላቅ የፊልም ባለሙያዎች ጋር መገናኘቷ እንዳስደሰታት የገለፀችው ሊያ፤ ለውበቷ መጠበቅያ ስለምትጠቀምባቸው ቅባቶችና ስለ ውበት አጠባበቋ ከዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ተጠይቃ፤ ልምድዋንና ተመክሮዋንና አጋርታለች ተብሏል፡፡