Saturday, 26 May 2012 12:58

የልጆች ሥነፅሁፍ ዝግጅት ተካሄደ

Written by  መልካሙ ተክሌ (melkamutekele@gmail.com)
Rate this item
(0 votes)

ዛጐል ቤተመፃህፍት ከእሸት ECYDO ጋር በመተባበር ያሰናዱት የሕፃናት የሥነፅሁፍ ዝግጅት ባለፈው ቅዳሜ ጧት በሩስያ ሳይንስ እና ባህል ማዕከል ፑሽኪን አዳራሽ ቀረበ፡፡ ደራሲ ኃይለመለኮት መዋዕል የልጆች እንካሰላንትያ ባቀረበበት ዝግጅት ገጣሚና ተዋናይ ሜሮን ጌትነት አርቲስትነትን ለልጆች በሚገባ ቋንቋ ገለፃ አድርጋለች፡፡ የዝግጅቱ የክብር እንግዳ በርካታ የልጆች መፃህፍት በማዘጋጀት የሚታወቀው ደራሲ ተሾመ ብርሃኑ ነው፡፡ ልጆች የራሳቸውን ትረካዎች፣ ግጥሞችና ድራማ አቅርበዋል፡፡

ለቤተ መፃህፍቱ አራተኛ የሆነው ዝግጅት ከ12 እስከ 17 አመት ያሉ ታዳጊዎች የተካተቱበት ነው፡፡ ስለ ዝግጅቱ ቀጣይነት ከዝግጅት ክፍላችን የተጠየቀው የቤተመፃህፍቱ ባለቤት እና ሥራ አስኪያጅ ደራሲ እንዳለጌታ ከበደ የቦታ እና የአቅም ችግር ባይኖርብን ዝግጅቱ በየወሩ ይሆን ነበር ብሎናል፡፡

 

 

 

Read 864 times Last modified on Saturday, 26 May 2012 12:59