ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመከላከል የሚያስችል ግንዛቤ እንደሚፈጥር የተነገረለት በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ “ሰውነቷ” የተሰኘ ፊልም በትላንትናው ምሽት በሃያት ሪጀንሲ ሆቴል ተመርቋል፡፡
በምረቃ ሥነ ስርዓቱ ላይ የተገኙት የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፤ ህብረተሰቡ ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውርን እንዲከላከል መልዕክት ማስተላለፋቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡
ፊልሙን የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከዓለም የሥራ ድርጅት ጋር በመተባበር ያዘጋጀ ሲሆን ዓላማውም በህብረተሰቡ ውስጥ ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመከላከል የሚያስችል ግንዛቤ በጥበብ አማካኝነት ለማስረፅ ነው ተብሏል፡፡
Monday, 28 January 2019 00:00
“ሰውነቷ” በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ ፊልም ተመረቀ
Written by ናፍቆት ዮሴፍ
Published in
ኪነ-ጥበባዊ ዜና