Monday, 28 January 2019 00:00

ምግብ አምራቾች፣ አቀናባሪዎችና አሻጊዎች በጋራ ኤግዚቢሽን ሊያካሂዱ ነው

Written by  መታሰቢያ ካሳዬ
Rate this item
(0 votes)

 በምግብ ማምረት፣ ማቀናባበርና ማሸግ ሥራዎች ላይ የተሰማሩ አካላት በጋራ የሚሳተፉበት ኤግዚቢሽን በሚሊኒየም አዳራሽ ሊካሄድ ነው፡፡
ከግንቦት 1 ቀን 2011 ዓ.ም እስከ ግንቦት 3 ቀን 2011 ዓ.ም በሚካሄደው በዚህ ኤግዚቢሽን፤ በግብርና ዘርፍ፣ በምግብና መጠጥ ማቀነባበርና የተቀነባበሩ ምርቶችን ማሸግ ሥራ ላይ የተሰማሩ ነጋዴዎች ይሳተፉበታል፡፡
በጀርመኑ ታዋቂ የንግድ ትርኢት አዘጋጅ ፌርትሬድና በፕራና ኢቨንትስ የጋራ ትብብር በሚዘጋጀው በዚህ 3ኛው የኢትዮጵያ የግብርና ምግብና መጠጥ ቴክኖሎጂ እና ተያያዥ የሆኑት የፕላስቲክ ህትመትና ፓኬጂንግ ዓለም አቀፍ የንግድ ትርኢት ላይ ጀርመን ኔዘርላንድ፣ ቱርክ፣ ቻይና፣ ፈረንሳይና ጣሊያን ይሳተፉበታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ለኢትዮጵያ ገበያ ፍላጐት የተዘጋጁ ቴክኖሎጂዎችና መፍትሔዎች ይገኙበታል የተባለውን ይህንኑ ኤግዚቢሽን አስመልክቶ አዘጋጆቹ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንደተናገሩት፤ ኢትዮጵያ ከምስራቅና ከመካከለኛው አፍሪካ ግንባር ቀደም የምግብ ገበያ አላት፡፡
የዓለም ንግድ ድርጅት ያወጣውን መረጃ ዋቢ አድርገው አዘጋጆች እንደገለፁት፤ ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ በ2017 ዓ.ም በአገር ውስጥ ያላት የምግብ ገበያ 4‚088 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ሲሆን ከውጪ የምታስገባው የምግብ ምርት ደግሞ 1‚889 ቢሊዮን ዶላር አስገኝቷል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም አገሪቱ ወደ ውጪ ከምትልካቸው የምግብ ምርቶች 2‚199 ቢሊዮን ዶላር ገቢ አግኝታለች፡፡  

Read 675 times