Saturday, 29 September 2018 14:43

“የኢትዮጵያ የጥፋት ምስጢር” በገበያ ላይ ዋለ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 በወጣቱ ደራሲ ዮናስ አለሙ የተጻፈውና የኢትዮጵያን ታሪክ በአዲስ አተያይ እንደሚያትት የተነገረለት “የኢትዮጵያ የጥፋት ምስጢር” መጽሐፍ በሳምንቱ መጀመሪያ ታትሞ በገበያ ላይ ውሏል፡፡
በተለያዩ ታሪካዊና ሃይማኖታዊ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ የሚያጠነጥኑ 15 ምዕራፎች ያሉትና በ478 ገጾች የተቀነበበው መጽሐፉ፤ የመሸጫ ዋጋው 250 ብር ሲሆን በቢኮሎ ማተሚያ ቤት ታትሞ ለንባብ መብቃቱም ታውቋል፡፡
በቅርቡ በባህር ዳርና በደብረ ማርቆስ ከተማ በይፋ የተመረቀው መጽሃፉ፤ አዲስ አበባ፣ ባህር ዳርና ሃዋሳን ጨምሮ በተለያዩ ክልሎች በሚገኙ መጽሐፍት መደብሮችና አዟሪዎች ዘንድ እየተሸጠ እንደሚገኝ ደራሲው በተለይ ለአዲስ አድማስ ገልጧል፡፡

Read 1413 times